Historical Books 1 Samuel

The Anointing of King Saul

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 9-10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 229 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በ 1-ሳሙኤል 7 ሳሙኤል እስራኤላዊያንን ወደ መነቃቃት ጊዜ በመምራት ወደ እግዚአብሄር መለሳቸው ፤ ነገር ግን በምዕራፍ 8 ህዝቡ ሳሙኤልን ባለመቀበል ሳሙኤልን ንጉስ እንዲሰጣቸዉ ጠየቁት ፡፡ ሳሙኤል በእነርሱ ላይ ንጉስ ኖሮአቸው በመሄዳቸው በተግባራቸዉ እና በድርጊታቸዉ ደስተኛ እንደ ማይሆኑ ህዝቡን አስጠነቀቸው ፡፡ ምዕራፍ 9 ከማንኛዉም በእስራኤል ካለ ሰዉ በቁመቱ የሚበልጥ ወጣቱን ሰዉ ሳዖልን ያስተዋውቃል (ቁጥር 2) ፡፡ የጠፉትን አህዮች እንዲፈልግ ተልኮ ነበር ነገር ግን ስለ እርሱ አባቲ ሊጨነቅ ስለሚችል በአባቱ ፊት ቤት ተመለሰ (ቁጥር 5) ፤ በከተማዋ ምንድን ማድረግ እንዳለበት ስለ ሚነግረዉ አንድ ሰዉ እንዲመለከት(እንዲሄድ) ተነገረው (ቁጥር 6) ፤ እግዚአብሄርም ሳሙኤልን ወደ ሳዖልን በመመልከት እንደ ንጉስ እንዲቀባዉ ነገረው (ቁጥር 15-16) ፡፡ ምንድን እንደሚሆን ሳዖል በተነገረዉ ጊዜ ከሚያንሰዉ ነገድ እንደሆነ አመለከተ ነገር ግን ይህ ለሳሙኤል ከቢኒያም ነገድ ስለ ነበር ማረጋገጫ ነበር (ቁጥር 19-21) ፡፡ አህዮቹን በመፈለግ አባቱን በመታዘዝ ሂደት ዉስጥ ሳዖል ጥሪዉን እንደ ንጉስ አገኘው (ቁጥር 22-27) ፤ ሳዖል በጥሪዉ ሲጓዝ ሳሙኤል እንዳደረገው ይጓዛል ማለት ነው ፤ ይህ ለ1ሳሙኤል 10 መነሻና የመጀመሪያዉ የእስራኤል ንጉስ መሾም ነው ፡፡

ትምህርት

በምዕራፍ 10 ዉስጥ ስድስት ቁልፍ ሀሳቦችን እናያለን ፡፡

መጀመሪያዉ የግል ጥሪ ተሰጠ (ቁጥር 1) ፡፡ ይህ በእስራኤል ወይም ከነገዶቹ በማንኛዉም ፊት አልነበረም ፤ ቅባቱ በሳዖል ህይወት የእግዚአብሄር መገኘት፣ የእግዚአብሄር ጥሪ በህይወቱ እና መንፈስ ቅዱስ በህይወቱ መጓዝ የመጀመሩ ምልክት ነበር (ዘጸ 29፡ 7፣ 40፡ 14-15) ፡፡ በብሉይ ኪዳን በዉስጥ መንፈስ ቅዱስ አያድርም ነገር ግን በሰዎች ላይ ይመጣል ፤ ቅባቱ እኛን በፍፁም አይተወንም ( 1ዮሐ 2፡ 20, 27) ፡፡

ሁለተኛዉ ማረጋገጫ ይጠበቃል (ቁጥር 2-8) ፡፡ ሳዖል በጼልጻህ በራሄል መቃብር ከነበሩት ሁለት ሰዎች(ቁጥር 2)፣ ከቤቴል ከሆኑት ሰዎስት ሰዎች (ቁጥር 3) እና ከእግዚአብሄር ተራራ ከነቢያት ጉባኤ በዜማ (በቅኔ) (ቁጥር 5) ማረጋገጫ ይሰማል ፡፡ ከቤቴል የሆኑት ሰዎች በካህናት የሚበላ እንደ መስዋዕት የተገባ ከእነርሱ ጋር ዳቦ ይኖራቸዋል (ዘኁ 18፡ 8) ፤ የነቢያቱ ጉባኤ ምናልባትም የወደፊቱን ክስተት ይተነብያሉ ፤ የእግዚአብሄርም መንፈስ በእርሱ ላይ በመጣበት ጊዜ ሳዖልም ተነበዬ ወደ ሌላም ሰዉ የተቀየረ ሆነ ፡፡ በ 1ሳሙ (16፡ 13-14) በተቀባ ጊዜ የእግዚአብሄር መንፈስ በዳዊት ላይ መጣበት ፡፡ እንደ ሚተነብይ ሳዖል ተነገረው ፤ 1ቆሮ (14፡ 1) የሚለው “ ፍቅርን ተከታተሉ መንፈሳዊ ስጦታንም ይልቁንም ትንቢት መናገርን በብርቱ ፈልጉ “ ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ትንቢት በኃይለኛዉ ኑሮን መቀየር ይችላል ፤ ምንም ቢፈጠር እንዳያስብ ሳዖል ተነገረው የሚፈልገዉን ሁሉንም ነገር ያደርጋል ምክንያቱም እግዚአብሄር ከእርሱ ጋር ስለ ነበር (ቁጥር 7) ፤ ከዚያም ወደ ገሊላ በመሄድ በዚያ ሳሙኤልን ጠበቀ (ቁጥር 8) ፤ በማረጋገጫ ሳዖል እንዲሄድ ከተነገረዉ በኋላ እንዲጠብቅ መነገሩ አስደናቂ ነው ? በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ዉስጥ ካልተጠነቀቅን እንድንጠብቅ በተነገረን ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ቀድመን እናገኘዋለን ፡፡ አ.ዋ.ቶዘር “ በአሁኑ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ከቤተ ክርስቲያን ሲለይ 95 ፐርሰንት እያደረግን በምንሄድበት ምናም ልዩነቱን እንደ ማያዉቀዉ ተናግሯል “ ፡፡ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ ለሙሉ የምትሞተዉ መንፈስ ቅዱስ በዚያ እንደ ሌለ ማወቅ አለባችሁ !

ሰዎስተኛዉ ኃይልን ይጠብቃል (ቁጥር 9-16) ፡፡ ሁሉም ምልክቶች ከሆኑ በኋላ በዚያዉ ቀን የእግዚአብሄር መንፈስ ሳዖልን ተቆጣጠረዉ ትንቢትም ተናገረ ፤ የሚያዉቁት ሰዎች በሆነዉ ነገር እና ከነቢያት መካከል እንዴት እንደሆነ ተደነቁ (ቁጥር 9-12) ፡፡ ሳዖል በኃይል ተሞላ ፤ ኃይል በጥሪዉ ለመጓዝ የሚሰጥ አቅም ነው ፡፡ የሳዖል አጎት የትሄዶ እንደ ነበር ጠየቀዉ (ቁጥር 14) ፤ ሳዖልም አህዮች ፍለጋ ከዚያም ሳሙኤልን ለማየት እንደሄደ መለሰለት ነገር ግን ሳሙኤል ለእርሱ የነገረዉን ለአጎቱ አልነገረዉም (ቁጥር 15-16) ፡፡

አራተኛው በህዝብ ፊት ጥሪ ተሰጠ (ቁጥር 17-24) ፡፡ ሳሙኤል የሳዖልን መጠራት እንዲሰሙ ህዝቡን ሰበሰበ ሳዖልም ይህ እንዲሆን ፈቀደ ምክንያቱም በቅንነት ስለ ቅባቱ ነበር (ቁጥር 17) ፤ ሳሙኤል እግዚአብሄር ንጉሳቸዉ እንደ ሚሆን የእግዚአብሄርን ቃል ሰጣቸዉ ነገር ግን ይህን ስላልተቀበሉት ንጉስ የተመረጠላቸዉ ይሆናል (ቁጥር 18-19)፡፡ ነገዶች ወደፊት ተጠርተዉ የምርጫ ሂደቱ ተጀመረ ፤ ሳዖል የተመረጠ ንጉስ ነበር ነገር ግን በዚያ አልነበረም ምክንያቱም በእቃ ዉስጥ ተሸሽጎ ስለ ነበር (ቁጥር 20-22) ፡፡

አምስተኛዉ ድጋፍ ይጠብቃል (ቁጥር 25-26) ፡፡ በተጠራችሁ ጊዜ የሚያስፈልጋችሁን ድጋፍ ታገኛላችሁ ፤ እንደ ደጋፊ ከእርሱ ጋር እንዲሄዱ ልባቸዉን እግዚአብሄር ነክቷቸዉ የነበሩ ኃያላን ሰዎች ለሳዖል ተሰጡት (ቁጥር 26) ፡፡

ስድስተኛዉ ተቃዉሞ ይጠብቃል (ቁጥር 27) ፡፡ ምናምንቴ ሰዎች ሳዖልን ናቁትም ተቃወሙትም ነገር ግን ሳዖል ምንም አላለም (ቁጥር 27) ፡፡

መደምደሚያ

ሳዖል የተቀባ፣ በግሉ የተጠራ እና በሂደት ማረጋገጫ የተቀበለ ነበር ፤ የእስራኤል የመጀመሪያዉ ንጉስ እንዲሆን ኃይል የተሰጠዉ ነበር ፤ ሳዖል በኃያላን ሰዎች የተከበበ ነገር ግን በምናምንቴ ሰዎች ተቃዉሞ የደረሰበት ነበር ፡፡ በእርግጠኝነት ይህ በኢሳያስ 61 እና በሉቃስ 4 ቅባት እና ድጋፍ የተቀበለዉን ነገር ግን ኃይለኛ ተቃዉሞ የገጠመዉን የክርስቶስ ህይወትን ይመስላል ፡፡

ጥያቄዎች

  1. የቄስ ልጅን ሳዖል “ እንደ ተመረጠ መልካም ልጅ እና ከእስራኤልም ልጆች ከእነርሱ ይልቅ መልካም የሆነ ሰዉ እንዳለነበረ “ ይገልፀዋል ፤ እነዚህ ዝርዝሮች ለምን እንደ ተመዘገቡ ምን ታስባላችሁ ? ያን ከኢሳ (53፡ 2) አነፃፅሩ ፤ ከአለማዊ እይታ በእነዚህ ገለፃዎች መሰረት እንደ ንጉሳቸዉ ብዙ ሰዎች የትኛዉን ይመርጣሉ ?
  2. 1 ሳሙ (9፡ 16) እግዚአብሄር ሳዖልን በእስራኤል ላይ እንደ ልዑል( ሌሎች ትርጉሞች፡ አስተዳዳሪ፣ መሪ፣ አዛዥ፣ ዋና) እንዲቀባዉ ነገረው ፤ “ እንደ ንጉስ ቀባዉ “ ለምን አላለዉም ?
  3. በ1ሳሙ (9፡ 20) የሳዖል ምላሽ ለሳሙኤል ሀሳብ ከቢኒያም ነገድ እንደ ነበር በመናገር ነበር ፡፡ መሳፍንት 20 እና 21 ላይ ተመልሳችሁ ተመልከቱ ፤ ሳዖል እንዴት ስለ ነገዱ ተሰማው ?
  4. ሳሙኤል በዘይት የሳዖልን ራስ በመቀባት በእግዚአብሄር ርስት ላይ አስተዳዳሪ እንዲሆን አወጀው ፤ ለንጉሱ የእስራኤልን ፍላጎት እግዚአብሄር እንዴት አየዉ ? (1 ሳሙ 10፡ 17-19)
  5. በ 1ሳሙ (10፡ 22) እግዚአብሄር ሳዖል እራሱን በእቃ መካከል ተደብቆ እንደ ነበር ለህዝቡ ገለጠላቸው ፤ በጥሪአቸዉ ከመጓዝ ይልቅ በራሳቸዉ እቃዉስጥ የተደበቁ ሰዎችን ታዉቃላችሁ ?
  6. 1 ሳሙኤል 10 መጨረሻ ላይ ምናምንቴ ሰዎች “ ይህ ሰዉ እንዴት ያድነናል ? አሉ ሳዖልንም በመናቅ ምንም አይነት ስጦታ አላመጡለትም ፤ ይህ ሀሳብ እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን ካዩበት እና ከተቀበሉበት መንገድ ጋር ተመሳሳይ ይመስላል ?
  7. በ 1ሳሙኤል(9-10) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Samuel 9:16

“At this time tomorrow, I will send you a man from the land of Benjamin. Anoint him ruler over My people Israel. He will save them from the hand of the Philistines because I have seen the affliction of My people, for their cry has come to Me.”

ሳኦል የተባለ ከብንየም ወገን የሆነ ያልታሰበ እንደገናም የሚማርክ ወጣት በእስራኤል ላይ እንደሚነግስ እግዚአብሔርም ለሳሙኤል ገለጠለት ፡፡ ሳሙኤልም ለዚህ ልዩ ጥሪ ሳኦልን በዘይት ቀባው ፡፡ እግዚአብሔርም በሳኦል ላይ የእግዚአብሔር መንፈስ እንድወርድበትና እንድቆጣጠረው በማድረግ ምርጫውን አረጋገጠ ሳኦልም ከነበያቱ ጋር አብሮ ትንቢትን ተናገረ ፡፡ ኋላም ሳኦል ለህዝቡ ንጉስ ሁኖ በቀረበ ጊዜ በትህትና ተራመደ ፤እግዚአብሔርንም አሳቡ ይፈጸም ዘንድ ጊዜው መሆኑን እንድገልጥ አስቻለ ፡፡

እንደ ክርስቶስ ተከታይ በህይወትህ ላይ ቅባት አለ ፡፡ የተቀባ የሚለው ቃል ሌላ ትርጉም “የተመረጠ” ማለት ነው ፡፡ አሁን አንተ የተመረጥክ ነህ ለልዩ ዓለማ ማለትም የእግዚአብሔርን መንግስት ለማስፋት ፡፡ ይህም ማለት የእግዚአብሔርን አሳብ ትፈጽም ዘንድ ሀይል ተሰቶሀል ፤ አደራ አለብህ ደግሞም ተሾመሀል ፡፡ ቅባት ለክርስትያን ሰባኪዎች ወይም ደግሞ መሪዎች ብቻ የተሰጠ አይደለም ለሁሉም አማኞች የተሰጠ እንጅ ምክንያቱም የእግዚአብሔር መንፈስ በውስጣችን ስለሚኖር ፡፡ ከክርስቶስ ጋር መኖርህ ምንም አይነት እንቆቅልሽ ይፍጠር ፤ በትህትና ውስጥ በቅባትህ ስልጣን ተራመድ ፡፡ አንተ ተመርጠሀል ፡፡ ምንም ይሁን የእግዚአብሔርን ቃል ማስተማር ፤ ድርጅት ማስተዳደር ወይም ደግሞ ፋብሪካ ውስጥ መስራት ፤ አንተን መንፈስ ቅዱስ የእርሱን መንግስት እንድታሰፋ ሾሞሀል ፡፡ ስለዚህ ትልቅ እውነት እግዚአብሔር ይመስገን ፡፡

“ ነገ በዚህች ሰዓት ከብንያም አገር አንድ ሰው እሰድድልሀለሁ ልቅሶአቸው ወደ እኔ የደረሰ ሕዝቤን ተመልክቻለሁና ለሕዝቤ ለእስራኤል አለቃ ይሆን ዘንድ ትቀባዋለህ ከፍልስጤማውያንም እጅ ሕዝቤን ያድናል ፡፡ “

-1 ሳሙኤል 9፡16

ተጨማሪ ጥቅስ

  • 1 ሳሙኤል 10፡16 –“ ሳኦልም አጎቱን አህዮች እንደ ተገኙ ገለጠልን አለው ነገር ግን ሳሙኤል የነገረውን የመንግስትን ነገር አላወራለትም ፡፡ “

2 ቆሮንቶስ 1፡22-23 –“ ደግሞም ያተመን የመንፈሱንም መያዣ በልባችን የሰጠን እርሱ ነው ፡፡ እኔ ግን ልራራላችሁ ስል እንደ ገና ወደ ቀሮንቶስ እንዳልማጣሁ በነፍሴ ላይ እግዚአብሔርን ምስክር እጠራለሁ ፡፡ “

1 ዮሐንስ 2፡27 –“ እናንተስ ከእርሱ የተቀበላችሁት ቅባት በእናንተ ይኖራል ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልጋችሁም ነገረ ግን የእርሱ ቅባት ስለ ሁሉ እንደሚያስተምራችሁ እውነተኛም እንደ ሆነ ውሸትም እንዳልሆነ እናንትንም እንዳስተማራችሁ በእርሱ ኑሩ ፡፡ “