Struggling to Rely on God
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 7-8 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የ 1-ሳሙኤል ምዕራፍ 7-8 ፍሬ ነገር ወይም በ1-ሳሙኤል መሀከል ላይ መሸጋገሪያ ሀሳብ ናቸው ፤ በእነዚህ ሁለቱ ምዕራፎች ብዙ ነገሮች ይካሄዳሉ ፡፡
ትምህርት
1-ሳሙኤል (7፡ 1-4)፡ ታቦቱ ልጁ አልዓዛር በሚጠብቀዉ በአሚናዳብ ቤት ለ 20 አመታት ቆየ (ቁጥር 1-2) ፤ የኪዳኑ ታቦት በምትኖሩበት ቤት ሲቀመጥ አስባችሁታል ? በዚህ አንድ ጥቅስ 20 አመታትን አግኝተናል ፤ አስታዉሉ የድንኳኑ ማደሪያ ወይም የመቅደስ መጠቀስ የለም ፡፡ ኤሊና ልጆቹ ስለሞቱ ጠቅላላ የክህነት አገልግሎት በትርምስ ነበር ፡፡ ሳሙኤልም እንኳን አልተጠቀሰም ፤ በዚህ በ20 አመታት ጊዜ ዉስጥ እንደ ነቢይ ህዝቡን ነገድ በነገድ እና ከተማ በከተማ እያስተማረ ተንቀሳቅሷል ፤ እንደ ነቢይም ከዳን (በእስራኤል ከብዙዉ ሰሜናዊ ቦታ) እስከ ቤርሳቤህ (ደቡባዊ ብዙ ስፍራ) የታወቀ ነበር (1ሳሙ 3፡ 20) ፡፡ “ የእስራኤልም ቤት ሁሉ አዝኖ እግዚአብሄርን ተከተለ “ (ቁጥር 2) ፡፡
ጊዜዉ ወደ ከተማዋ መነቃቃትን ባደረገ ጊዜ በማህበሩ ዉስጥ ሰዎስት ነገሮችን ያገኛሉ(ይመለከታሉ)፡ አንድነት (ቁጥር 2)፣ ርሀብ (ቁጥር 2) እና ትህትና (ቁጥር 3-4) ፤ “ ሁሉም የእስራኤል ቤት “ አንድነትን ያሳያል ፤ እግዚአብሄርን በመፈለጋቸዉ እስራኤል ለረጅም ጊዜ አድርጎት የማያዉቀዉን ርሀብ በርሃባቸዉ አሳዩ ፡፡ በሳሙኤል ትዕዛዝ መሰረት በሙሉ ልባቸዉ እግዚአብሄርን እንዲፈልጉት የሌሎች አማልክቶችን በማስወገድ ትህትናቸዉን አሳዩ (ቁጥር 3-4) ፡፡ በትዕዛዙ ዉስጥ በቅዱስ ንስሀ በእግዚአብሄር ፊት ለመምጣት የሚያስፈልጉ ነገሮችን ሳሙኤል ዘርዝሯል ፡
- ዉሳኔአቸዉ ከልብ የመነጨ መሆን አለበት - “ ወደ እግዚአብሄር በሙሉ ልባቸዉ መመለስ ነበረባቸው “ ፤ ንስሀቻዉ አስቸጋሪ ይሆናባቸዋል ምክንያቱም በከበበዉ ልምድ ፊት ስለሚበር ፡፡
- ዉሳኔአቸዉ ተጨባጭ መሆን አለበት - በቤታቸዉ እና በልባቸዉ የነበረዉን “ የሌሎች አማልክቶችን እና አስታሮቶችን ማባረረ ነበረባቸው “ ፤ አስታሮቶች የመራባት እና የወሲባዊ አምልኮት የነበረው የባዖል ህብረቶች ነበሩ ፡፡ አነዚህ አማልዕክቶች በጣዖት ቅርፅ የተወከሉ ከነበሩ ድርጊታቸዉ በአካላዊ ለማስወገድ እና ጣዖቶችን ለማጥፋት ድርጊታቸዉ የጠነከረ መሆን አለበት ፡፡
- ዉሳኔአቸዉ እግዚአብሄርን ብቻ ለማምለክ መሆን አለበት - “ ያህዌን ማምለክ ይችላሉ ሳይሆን “ “ያህዌን ብቻ ማምለክ አለባቸዉ “ ፡፡
1-ሳሙኤል (7፡ 5-6)፡ ነቢዩ ሳሙኤል በምጽጳ መላዉን የእስራኤልን ቤት መድረስ ፈለገ (ቁጥር 5) ፡፡ ምጽጳ ማለት “ መመልከቻ ስፍራ “ ወይም ከፍ ያለ ሜዳ ማለት ነው ፡፡ ምሁራን የምፅጳን ትክክለኛ ስፍራ እርግጠዮች አይደሉም፡፡ ሁሉም ህዝብ ከመገናኛ ድንኳኑ ማደሪያ ወይም ከመቅደሱ ዉጪ በአንድ መጡ ፤ በሰሜን ሰዎች እና በደቡብ ሰዎች መካከል አሁንም ዉጥረት ነበር ፤ ለምሳሌ የሰሜን ነገዶች የይሁዳን ነገድ አይወዱትም ምክንያቱም ይሁዳ ከሌሎች እንደ ተሸለ ተደርጎ ተቆጥሮ ስለነበር በመረዳታቸዉ ቀንተዉ ነበር ፤ ይሁን እንጂ ዉጥረቱም እያለ ሳሙኤል ሁሉንም ነገዶች በአንድ ላይ ማምጣት ይችል ነበር ፡፡ ይህ ደቡብ እና ሰሜን መከፋፈል ለቀጣዮቹ 500 አመታት በመተኮስ ለመፈንዳት እንደ ቀጠለ እንዳትረሱ ፡፡
በቁጥር 6 ሳሙኤል ዉሃ ቀድተዉ በእግዚአብሄር ፊት በማፍሰስ የዉሃ መሰዋዕት እንዲያደርጉ መራቸው ፤ በርጌን ይህ የእስራኤል ንስሃ “ የእግዚአብሄር ሞገስ ለህይወታቸው ከሚጠቅመዉ ዉሃ ይልቅ በጣም እንደ ሚጠቅማቸዉ “ እንደ ነበር ያቀርባል ፤ የእስራኤል ሰዎች በመፆም ኃጢዓታቸዉን ለእግዚአብሄር ተናዘዙ ፤ “ ሳሙኤልም በእስራኤል ልጆች ላይ በምጽጳ ፈረደ “ (ቁጥር 6) ፡፡ ይህ ሳሙኤል እንደ ነቢይ ብቻ ሳይሆን እንደ ዳኛም የተገበረበት የመጀመሪያ ጊዜ ነበር ፡፡ ሳሙኤል የሌዊ ነገድ እስከሆነ ድረስ ህጋዊ(ትክክለኛ) ካህን ነበር ፤ ሳሙኤል በመሳፍንት ዘመን እና በነገስታት ዘመን መካከል ድልድይ ሆነ ፡፡ ሳሙኤል የመሳፍንቶች የመጨረሻ በመሆን በመሪነት ማዕከል ስር ወደ ሁሉም እስራኤል ተላከ ፤ በተጨማሪም ሳሙኤል ንጉስ አስተካካይም ነበር ማለትም በእኛ አረዳድ የተቀባን ማለት ነው በእዉነቱ ሳሙኤል ንሳዊያን ቀቢ ነበር ፡፡ ሳሙኤል የመሲሁ ጥላዎች መልክ ነው፡ ካህን፣ ነቢይ፣ ንጉስ እና የንጉሳዊያን ቀቢን ፡፡ በመናዘዛቸዉ እና በንስሀቸዉ ምክንያት ሳሙኤል ፀለየ ፤ ይህ ጠላት ያልወደደዉ ታላቅ የማነቃቂያ ክስተት ነበር ከዚያም በፍልስጤማዉያን በኩል በእስራኤል ላይ ተንቀሳቀሰ ፡፡
1-ሳሙኤል (7፡ 7-11)፡ ፍልስጤማዉያን ምፅጳ ላይ መሰባሰባቸዉን ሰሙ እስራኤልም ወደ ጦርነት ለመሄድ እየተዘጋጁ እንደ ነበር አሰቡ ፤ ከዚህ በፊት ተመዝግቦ የማያዉቅ ጦር ታላቅ የፍልስጤማዉያን ጦር መለመሉ (ቁጥር 7) ፡፡ የእስራኤል መላዉ ህዝብ ሚስቶችን እና ልጆችን ጨምሮ ምፅጳ ላይ እየገሰገሰ የነበረዉን ግዙፉን የፍልስጤማዉያንን ጦር ኃይማኖታዊ ስብሰባ ካደረጉበት ከፍ ካለዉ ሜዳ ላይ ተመለከቱ ፤ እስራኤላዊያን መሳሪያ እና የጦር ልብስ አልነበራቸዉም ፡፡ ማርከዉት በነበር ጊዜ ፍልስጤማዉያን ከልምዳቸዉ የታቦቱን ኃይል ያዉቃሉ (1ሳሙ 4) ፤ ታቦቱ ከእስራኤል ጋር እንዳልነበር ባስተዋሉ ጊዜ ተጠቃሚ እንደ ነበሩ ተሰማቸው (ቁጥር 7) ፡፡
አዲስ የሆነ ነገር እየሆነ ነበር ፤ እስራኤል ተሰብስቦ የነበረዉ ለመንፈሳዊ ዉጊያ ላይ እንጂ በአካላዊ ጦርነት አልነበረም ቁልፉም ያ ነበር ! ጣላትን ለመቀበል አስራኤል በተሸለ የተዘጋጀ አልነበረም ፡፡ ከክርስቲያን አለት ቡድን እንደ ግጥም ጴጥራ በመደነቅ የተናገረው “ በጉልበታቸሁ እንደ አንድ ሰዉ መዋጋት “ ፡፡ ወደ እግዚአብሄር ይፀልይላቸዉ ዘንድ ሳሙኤልን ጠየቁት (ቁጥር 8) ፤ ቀድሞ አድርገዉት በነበረዉ በታቦቱ ከእግዚአብሄር ጋር በመታረቅ ፋንታ እስራኤል በአማላጅነት ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ ፡፡ የሚያስቅ ወረራ የሚመስል ጣልቃ ገብነት ተዓምራት ለመጠየቅ ደፈሩ ፤ ሳሙኤል ለእግዚአብሄር የሚቃጠል መስዋዕት አቀረበ እግዚአብሄርም መለሰለት (ቁጥር 9) ፡፡ ጊዜዉ አጭር ስለ ነበር ሳሙኤል ከንግግር ዉጪ ተገበረ ፤ ሁሉን እንሰሳትም እንኳን እንደ ሚቃጠል መስዋዕት አቀረበ ፤ በሚሰዋበት ክስተት ላይ እግዚአብሄር በነጎድጓድ ድምፅ ፍልስጤማዉያንን አስፈራ (ቁጥር 10) ፤ ወዲያዉኑ ፍልስጤማዉያን ወደ ታላቅ ትርምስ እና ሁከት ገቡ ፡፡ በመጨረሻም እስራኤል የእግዚአብሄር የመለዓክ ጦር ለእነርሱ እየተዋጉ እንደ ሆነ በመረዳት በቤትካር በታች የፍልስጤማዉያንን ጦር አሳደዷቸዉ (ቁጥር 11)፡፡
1-ሳሙኤል (7፡ 12-18)፡ ለእግዚአብሄር በመታደሳቸው ከፍልስጤማዉያን ጦር በእግዚአብሄር ዳኑ ሳሙኤልም እግዚአብሄር ላደረገላቸዉ እንደ መታሰቢያ የመታሰቢያ ድንጋይ አኖረ ፤ ቦታዉንም አቤንኤዘር ወይም የተስፋ ድንጋይ ብሎ ሰየመዉ (ቁጥር 12) ፤ ይህ በተለያዬ ቦታ ቀድመዉ እስራኤላዊያ የተሸነፉበት ስፍራ ተመሳሳይ ስም ነው ፡፡ በዚህም ፍልስጤማዉያን ፍልስጤማዉያን ፈሩ ደግመዉም እስራኤልን አልወረሩም (ቁጥር 13) ፡፡ ሳሙኤል ለ40 አመት እስራኤል ላይ ፈረደ (ቁጥር 15-17) ፤ ስለ ታቦቱስ ምን አለ(የትስ ገባ) ? ምናልባትም ሳሙኤል ሆን ብሎ እስራኤላዊያንን ከእምነት ምልክት በይበልጥ በእምነት መዋቅር(ጥልቅ ነገር) ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ለማስተማር ታቦቱን በቂርያትይዓሪ ተወዉ ፡፡
1-ሳሙኤል (8፡ 1-5)፡ ሳሙኤል ሲሸመግል ሁለቱን ወንድ ልጆቹን እንደ ፈራጅ ሾማቸው (ቁጥር 1) ፤ ይሁን እንጂ በእግዚአብሄር መንገድ አልተጓዙም (ቁጥር 2-3) ፤ የእስራኤል ሽማግሌዎች ሳሙኤልን እርሱ በሞተ ጊዜ ልጆቹ በሳሙኤል ቦታ መምራት እንደ ማይችሉ ነገሩት ፡፡ ሽማግሌዎች ለእግዚአብሄር ሳይሆን ለምድራዊ ንጉስ አንድነት እና ርሀብ ነበራቸው ፤ ሳሙኤል ሊያደርግ በነበረዉ ነገር ሲነግሩት ትህትና አልነበራቸውም (ቁጥር 4-5) ፡፡ ምዕራፍ 8 ኪይዝ ላኖን፡ “ በእዉነቶች አትወዛገቡ ፤ ይህ ዲሞክራሲይ ስህተት ሲሆን የሚገልጥ ነው ፤ ምንም እንኳን ሰዎቹ ቆይተዉ ደግመዉ ቢቆሽሹም እግዚአብሄር ወደ ደህና ቀይሮ በመስራት እንደ ሚያግዝ ገልጧል “ ፡፡ ሽማግሌዎቹ ንጉስ ስለ ፈለጉ የምድራዊ መሪዎችን ይመስላሉ ክርክራቸዉም የሳሙኤል ልጆች አይመጥኑም የሚል ነበር ፡፡
1-ሳሙኤል (8፡ 6-9)፡ ሳሙኤል ይህ ለእግዚአብሄር እና ለራሱ ማዋረድ ነበር ፤ ጥያቄአቸዉ ለራሳቸዉ ያተኮረ ቢሆንም ሳሙኤል ወደ እግዚአብሄር ፀለዬ ፤ እግዚአብሄር ወደ እነርሱ እንዲያደምጥ ነገረዉ ምክንያቱም “ በእነርሱ ላይ እንዳልነገስ እኔን እንጂ አንተን አልናቁምና “ (ቁጥር 6-7) ፡፡ ይህ የህዝቡ ፍላጎት ከ 300 አመት ቀድሞ በሙሴ ተተንብዮ ነበር (ዘዳ 17፡ 14-20) እንዲሁም እግዚአብሄር ለአብርሃም(ዘፍ 17፡ 7-16) እና ለያዕቆብ (ዘፍ 35፡ 11) ለሁለቱም የነገስታቶች አባት እንደሚሆኑ ተስፋ ሰጥቷቸዉ ነበር ፡፡ እግዚብሄር ሳሙኤልን ወደ ህዝቡ ድምፅ በማድመጥ በኃይል በማስጠንቀቅ የንጉስ ድርጊትንና ተግባራትን እንዲያዉቁ እንዲያደርጋቸዉ ነገረው (ቁጥር 9) ፡፡
1-ሳሙኤል (8፡ 10-18)፡ ሳሙኤል የእግዚአብሄርን ቃል ለህዝቡ ደገመላቸው ፤ ንጉስ ምን መሆን እንዳለበት አልነገራቸዉም ይልቁንም ሳሙኤል ንጉስ ምን መምሰል እንዳለበት እግዚአብሄር ያለዉን ነገራቸው (ቁጥር 10-18)፡፡ እግዚአብሄር የተናገረዉ ሁሉም ነገር በነገስታት አስተዳደር በሰሜን እና በደቡብ እስራኤል በሁለቱም ወደ እዉነት ይመጣል ፤ ነገር ግን ህዝቡ ሳሙኤለን ለመስማት እምቢ አሉ (ቁጥር 19-20) ፡፡ እግዚአብሄር ሳሙኤልን ንጉስ እንዲሾም ነገረው (ቁጥር 22) ፡፡
መደምደሚያ
እምቢ ማለታቸዉ እያለ እግዚአብሄር ወደ ፍሬ የሚያመጣዉ እቅድ ነበረው ፡፡
Robert Bergen, New American Bible Commentary: 1, 2 Samuel, v. 7 (Nashville: Broadman & Holman Publishers, 1996), p. 107.
Keith Lannon, available online at https://lannononsamuel.wordpress.com/category/1-samuel-8-verses-1-22/.
ጥያቄዎች
-
የእግዚአብሄርን ታቦት እስራኤላዊያን በቂርያትይሪ ለምን ለ20 አመት እንደ ተዉት ምን ታስባላችሁ ? እስራኤላዊያን ወደ እግዚአብሄር በመመለስ ጣዖቶቻቸዉን እንዲያስወግዱ ምክንያቱ ምን ነበር ? (1ሳሙ 7፡ 3-4)
-
አቤኔኤዘር የሚለዉ ስም ምን ማለት ነው ? ሳሙኤል አንድ ድናጋይ በማስቀምጥ ይህን(አቤኔኤዜር) ብሎ ለምን ጠራው ? በመፅሀፍ ሌላ የት ላይ እግዚአብሄር እንደ አለት ወይም በድንጋይ ተወከለ ? (ዘፍ 49፡ 24፣ ዘዳ 32፡ 4፣ 1ሳሙ 2፡ 2፣ መዝ 118፡ 22፣ ኢሳ 44፡ 8፣ ሐዋ 4፡ 11፣ 1ቆሮ 10፡ 4፣ 1ጴጥ 2፡ 4)
-
እስራኤላዊያን ንጉስ እንዲሾምላቸዉ ለመጠየቅ ምን ምክንያት አደረጉ (1ሳሙ 8፡ 4-5) ? ቀድሞዉኑ ንጉስ ነበራቸዉ (1ሳሙ 8፡ 7) ? በዘዳ (17፡ 14-16) እግዚአብሄር ሙሴን ምን ነገረው ?
-
እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን እየጠቁ ስለ ነበረዉ የንጉስን ልምድ እና መብት እንዴት አስጠነቀቃቸው ? (1 ሳሙ 8፡ 11-18)
-
የእስራኤላዊያን ምላሽ ለማስጠንቀቂያው ምን ነበር (1 ሳሙ 8፡ 19-20) ? ዉጊያቸዉን ሲዋጋላቸዉ የነበረዉ ማን ነበር (ዘጸ 14፡ 13-14፣ ዘዳ 1፡ 30፣ 3፡ 22፣ ኢያ 23፡ 3) ? ይህን እዉነት ለምን እንደረሱት ምን ታስባላችሁ ? በአሁኑ ጊዜ የእግዚአብሄር ሰዎች ተመሳሳይ ነገር ያደርጋሉ ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
በ 1 ሳሙኤል (7-8) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Samuel 8:6–7
“When they said, ‘Give us a king to judge us,’ Samuel considered their demand sinful, so he prayed to the LORD. But the LORD told him, ‘Listen to the people and everything they say to you. They have not rejected you; they have rejected Me as their king.’”
ሳሙኤልም ዕድሜውን ሁሉ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር ፡፡ ሆኖም ግን ሸማግሌዎች ወደ ሳሙኤል መተው የመሳፍንት ስርዓት እንደበቃቸው ፤ ሰማያዊው ንጉሳቸው እግዚአብሔርም እንዳልተመቻቸውና ይልቁንም ምድራቸውን ይገዛ ዘንድ ምድራዊ ንጉስን እንደሚፈልጉ ነገሩት ፡፡ ሳሙኤልም ጥያቄቸውን ሰማ ኀጥያት መሆኑንም አወቀ ፡፡ ከዝያም ወደ እግዚአብሔር ፀለየ እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን እንጅ እንተን አልናቁምና “ በሚሉህ ነገር ሁሉ የህዝቡን ቃል ስማ “ አለው ፡፡
በጣም ከባድ ነው ሰዎች አለማዊ በሆነ መንግድ ሲጓዙ ማየት ፡፡ ከእነርሱ ጋር እውነትን ትካፈል ይሆናል ነገር ግን እነርሱ አያደምጡህም ፡፡ እነርሱ የሚፈልጉት ሌሎች ያላቸው እንድኖራቸው ነው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እነርሱ ጠንከር ባለ መንገድ ሊማሩ ሊገነዘቡ ይገባቸዋል ፡፡ ከባድ ሊሆን ይችላል ለመቆምና ለማስተዋል ፡፡ አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር ሰዎች የሚያስቡትን የሚፈልጉትን መልስ እንድያገኙ ያስችላቸዋል ፡፡ ይህን እውነት አስታወስ እግዚአብሔር ዓላማ እንዳለው ዓላማውም እንደሚያሸንፍ ፡፡ ሰዎች እግዚአብሔርን እንድከተሉ ማስገደድ አትችልም ነገር ግን ኢየሱስ እንደወደዳቸው እንተም እንድትወዳቸው ተጠርተሀል ፡፡ በእርሱ ለሚታመኑት ለእነርሱ ነገርን ሁሉ ለበጎ የሚያደርግላቸውን እግዚአብሔርን አመስግን ፡፡
“ የሚፈርድልንም ንጉሥ ስጠን ባሉት ጊዜ ነገሩ ሳሙኤልን አስከፋው ሳሙኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ ፡፡ እግዚአብሔርም ሳሙኤልን አለው በእነርሱ ላይ እንዳልነግሥ እኔን እንጅ አንተን አልናቁምና በሚሉህ ነገር ሁሉ የሕዝቡን ቃል ስማ ፡፡
-1 ሳሙኤል 8፡6-7
ተጨማሪ ጥቅስ
- መዘሙር 80፡11-12 –“ ሕዝቤ ግን ቃሌን አልሰሙኝም እስራኤልም አላዳመጠኝም ፡፡ እንደ ልባቸው ስራ ተውኋቸው በልባቸውም አሳብ ሄዱ ፡፡
ምሳሌ 1፡29-31 –“ እውቀትን ጠልተዋልና እግዚአብሔርንም መፍራት አልመረጡምና ምክሬን አልፈቀዱምና ዘለፋዬንም ሁሉ ንቀዋልና ስለዚህ የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ ከራሳቸው ምክር ይጠግባሉ ፡፡ “
ሮሞ 8፡28 –“ እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንድደረግ እናውቃለን ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።