Ascribe God His Glory
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
1ሳሙኤል 3-4 እወደዋለሁ ፤ የእግዚአብሄር ድምፅ በስማችሁ ሲጠራችሁ መስማት እንዴት የሚያስደንቅ ነው ? በተለዩ ግለሰቦች ላይ የእግዚአብሄር ቅባት ሂደት እንመለከታለን በመጀመሪያ ሳሙኤል ላይ ከዚያ ደግሞ ሳዖል እና ዳዊት ላይ ፤ እነዚህ ሁሉም ወደ ዋናዉ(መጨረሻዉ) የተቀባዉ ኢየሱስ ክርስቶስ ያመለክታሉ ፤ የተቀባ የሚለው ይህ ለ 1ሳሙኤል መፅሀፍ ሀረጋችን ይሆናል ፡፡ በ1ሳሙኤል የሀና ፀሎት በሳሙኤል መወለድ ሲፈፀም አይተናል ፤ በ1ሳሙኤል 2 ሀና በትንቢታዊነት ፀለየች ሳሙኤልም እግዚአብሄርን እንዲያገለግል በመቅደሱ ተቀመጠ ፤ በ1ሳሙኤል 3 ሳሙኤል የእግዚአብሄርን ድምፅ ለመስማት ተማረ ፡፡ በ1ሳሙኤል 4 እስራኤላዊያን ከፍልስጤማዊያን ለመዋጋት ሄዱ፣ የኪዳኑንም ታቦት ተወሰደ የእግዚአብሄርም ፍርድ በኤሊ ላይ ተፈፀመ ፤ ምዕራፉ ስሙ “ ክብሩ ከእግዚአብሄር ለቀቀ “ የሚል ትርጉም ባለዉ በኢካቦድ መወለድ አለቀ ፡፡ በምዕራፍ 5 ፍልስጤማዉያን የማረኩትን ታቦት ከከተማ ወደ ከተማ አንቀሳቀሱት - ከአቤንኤዘርም ወደ አዛጦን ወደ ጌት ወደ አስቀሎና አንቀሳቀሱት ፤ በእያንዳንዱ ከተማ ሰዎቹ የእግዚአብሄር እጅ በእነርሱ ላይ እንደ ከበደች ተሰማቸው ፤ ታቦቱም ከእነርሱ እንዲሄድላቸዉ ጮኹ ፡፡ ምዕራፉም “ ያልሞቱትም ሰዎች በእባጭ ተመቱ ፤ የከተማይቱም ዋይታ እስከ ሰማይ ወጣ “ በሚል ገለፃ ያበቃል (ቁጥር 12) ፡፡
ትምህርት
1-ሳሙኤል (6፡ 1-6)፡ ከሰባት ወር በኋላ ፍልስጤማዉያን ካህናቶቹን እና ማዋርተኞቹን በመሰብሰብ የኪዳኑን ታቦት እንዴት ወደ እስራኤል እንደ ሚመልሱት ተማከሩ (ቁጥር 1-2) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ “ ምዋርተኞቹ ወደ ፊት ያለዉን መተንበይ የሚችሉ እንደ ሆኑና የሚበርሩ ወፎችን ምልክት ወይም የተሰዋን እንሰሳት ጉበት በመመልከት የአምላኮቻቸዉን ፍቃድ መወሰን እንደ ሚችሉ የሚናገሩ እንደሆኑ “ ይገልፃል ፡፡ ካህናቶቹ እና ሙዋርተኞቹ መፈወስ ከፈለጉ ለዳረጉት ወይም ለጥፋታቸዉ ካሳ ከታቦቱን ሳይሰዱ እንዳይልኩ ነገሯቸው (ቁጥር 3) ፤ ፍልስጤማዊያን ምን አይነት መስዋዕት ለካሳ ማቅረብ እንዳለባቸው ጠየቁ (ቁጥር 4፣ ዘሌ 5፡ 14-19) ፤ ካህናቶቹም እያንዳንዳቸዉ የፍልስጤም መሪዎች ገጥሟቸዉ የነበረውን ለመወከል አምስት የወርቅ እንቦጮች እና አምስት የወርቅ አይጦች እንዲያደርጉ መለሱላቸው (ቁጥር 4-5) ፡፡ ሌሎች ህዘቦችን እና ሌሎች ኃይማኖት ወደ እግዚአብሄር መጪህ ሲጀምሩ በምናይ ጊዜ ወደ መጨረሻ እንደ ሚመራ እናዉቃለን ፡፡ መፅሀፍ ፍልስጤማዉያን በመጨረሻዉ ጊዜ የሚሆነዉን እንዳደረጉ ይናገራል (ኢሳ 45፡ 23፣ ሮሜ 14፡ 11፣ ፊል 2፡ 9-11፣ ራዕ 5፡ 13) ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ ፍልስጤማዉያን የእግዚአብሄር ኃይል በእነርሱ ላይ ያንን መቅሰፍት እንዳ መጣባቸው እንዳወቁ ይገልፃል ፤ ካህናቱም ፈርዖን በእስራኤል አምላክ ላይ ልቡን ባደነደነ ጊዜ በግብፅ ላይ መቅሰፍቱ የከፋ እንደ ሆነ ፍልስጤማዉያንን አሳሰቧቸው (ቁጥር 6) ፡፡
1-ሳሙኤል (6፡ 7-12)፡ ፍልስጤማዉያን አድስ አንድ ሰረገላ በመስራት ቀንበር ተጭኖባቸዉ የማያዉቁ ሁለት የሚያጠቡ ላሞችን እንዲወስዱ ተጨማሪ ትዕዛዝ ተሰጣቸው (ቁጥር 7) ፤ እምቦሶቹም ከእናቶቻቸዉ በመወሰድ በረት ተቀመጡ ፡፡ ከዚያም ሰረገላዉን በማሰር ላሞቹን በማስተሳሰር ወደ እስራኤል ይላካሉ (ቁጥር 8) ፤ ላሞቹ ወደ እስራኤል (ቤትሳሚስ) ከሄዱ ለመቅሰፍታቸዉ ምክንያት የነበረዉ የእስራኤል አምላክ ነበር ፤ ነገር ግን ላሞቹ በተለየ መንገድ ከሄዱ መቅሰፍቱ የመጣብን በአጋጣሚ ነበር (ቁጥር 9) ፡፡ ቤትሳሚስ የግጦች ምድር የሌዋዊያን ከተማ ነበረች (ኢያ 21፡ 16) ስለሆነም በዚያ የነበሩ ካህናት ታቦቱን ሊንከባከቡት ይችላሉ ፡፡ ፍልስጤማዊያን እንደ ተነገራቸዉ አደረጉ ላሞቹም ወደ ግራም ወደ ቀኝም ሳይሉ ቀጥታ ወደ ቤትሳሚስ ሄዱ (ቁጥር 10-12) ፡፡
እግዚአብሄር እንድታደርጉለት የሚፈልገዉን በትክክል እያወቃችሁ ነገር ግን ለመስጠት እና ለማድረግ በጣም እለኸኞች በመሆን ይህንን ፅሁፍ ካጠኑት ሰዎች ምን ያክሉ በደንብ ተከትለዋል ? ምናልባት እግዚአብሄር የሆነ ነገር እንድታደርጉ እንደ ጠራችሁ እዉቅና ለመስጠት እና ራሳችሁን በትህትና ለማስገዛት እምቢ ብላችሁ ይሆናል ፡፡ ጠንቃቆች ካልሆንን በፍልስጤማዉያን ሰፈር ልንሆን እንችላለን እግዚአብሄርን ለማዳመጥ እና የሚፈልገዉን ለማድረግ እምቢ እያልን ማለት ነው ፤ ነገር ግን በትህትና በእግዚአብሄር ፊት በምንመጣ ጊዜ ከሰባት ወር በኋላም እንኳን ሁኔታዉን ይቅር በማለት ለቀጣዩ ያዘጋጀናል (መዝ 139፡ 9-10) ፡፡
ላሞቹ እየሄዱ “ እየቀነሱ(ቀስ እያሉ) “ ከኃላቸዉም ለቀሩት ጥጆች እያለቀሱ ነበር ፤ ይህ እግዚአብሄርን ለማገልገል ያለዉን ጥሪያቸዉን እና የሚወዱትን ቤተሰባቸዉን ለማጣጣም ሲሞክሩ ሁሉም ወደ አገልግሎት የተጠሩ የሚገጥማቸዉ የዉጥረት መልክ ነው ፡፡
1-ሳሙኤል 6፡ 13-18)፡ የቤትሳሚስ ሰዎች ታቦቱ መቅረቡን ባዩ ጊዜ በማሳዎች ላይ የስንዴ እህልን እየሰበሰቡ ነበር ፤ የእግዚአብሄርን መገኘት በማየታቸዉ ከመጥን በላይ ተደሰቱ (ቁጥር 13) ፡፡ ሰረገላዉም በአንድ ትልቅ አለት አጠገብ ቆመ ፤ የቤትሳሚስ ሰዎች የሰረገላዉን እንጨት በመፍለጥ ላሞቹን ለእግዚአብሄር እንደ ሚቃጠል መስዋዕት ሰዉዓቸው (ቁጥር 14) ፡፡ ሰዎቹ የሚቃጠል መስዋዕቱን ማድረግ እንደ ቀጠሉ ሌዋዊያን ታቦቱን እና የወርቅ መስዋቱን በትልቁ አለት ላይ አስቀመጡ (ቁጥር 15) ፤ የፍልስጤም መሪዎች የሆነዉን ካዩ በኋላ ወደ አስቀሎና ተመለሱ (ቁጥር 16) ፡፡ ቁጥር 17-18 ምንድን እንደሆነ ያጠቃልላል ፡፡
1-ሳሙኤል (6፡ 19-21)፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሄር የቤትሳሚስን ሰዎች ወደ ታቦቱ ዉስጥ ስለ ተመለከቱ ገደላቸው (ቁጥር 19) ፤ ምናልባትም ይሄ የሆነው ለታቦቱ ክብር ስላላሳዩ ወይም ደግሞ ታቦቱ በመመለሱ እየፈነደቁ ስለ ነበር ይሆናል ፡፡ እግዚአብሄር መከበር፣ ዉዳሴ እናአክብሮታዊ ፍርሀት ይፈልጋል ፡፡ እግዚአብሄር በዚያ ከነበሩ 50,000 ሰዎች 70 ሰዎችን ገደለ ( ቁጥር 19) ፤ የእግዚአብሄር መልዕክት ከቀደሙት ስህተቶች እንዳይደገም ነበር - የእግዚአብሄርን መገኘት አለማቅለል ማለት ነው ፡፡ የቤትሳሚስ ሰዎች “ በዚህ በቅዱስ አምላክ በእግዚአብሄር ፊት መቆም ማን ይችላል ? ከእኛስ ወጥቶ ወደ ማን ይሄዳል ? በማለት ጠየቁ “ (ቁጥር 20) ከዚያም ለቂርያትይዓሪም ሰዎች ታቦቱን መጥተዉ እንዲያገኙት መልዕክተኞችን ላኩ (ቁጥር 21) ፡፡ ቂርያትይዓሪም ከእስራኤል 10 ማይል ርቀት ላይ የምትገኝ ነበረች ታቦቱም ንጉስ ዳዊት ወደ ኢየሩሳሌም እስኪወስደዉ ድረስ በዚያ ቆየ (2ሳሙ 6፡ 1-9) ፡፡
መደምደሚያ
ሁላችንም እግዚአብሄር የሚገባዉን ክብር በመስጠት ለመቀጠል ማስብ አለብን ፤ 1ዜና (16፡ 28-30) የሚለው “ የአሕዛብ ወገኖች ለእግዚአብሄር አምጡ ክብርንና ኃይልን ለእግዚአብሄር አምጡ ፡፡ ለስሙ የሚገባ ክብርን ለእግዚአብሄር አምጡ ፤ ቁርባንን ይዛችሁ በፊቱ ግቡ ፤ በቅድስናዉ ስፍራ ለእግዚአብሄር ስገዱ ፡፡ ምድር ሁሉ በፊቱ ትነዋወጥ ፤ ዓለሙም እንዳይናወጥ ጸንትአል “ ፡፡
2Nelson’s Commentary, p. 354
3Nelson’s Commentary, p. 354
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 354.
ጥያቄዎች
-
ፍልስጤማዊያን “ የእግዚአብሄር እጅ በእነርሱ ላይ በከበደችባቸዉ “ ጊዜ ታቦቱን ለእስራኤል ከመመለስ ይልቅ ወደ ሌሎች ከተሞች ለምን እንደ ሰደዱት ምን ታስባላችሁ ? (1 ሳሙ 5፡ 6)
-
በ 1ሳሙ (6፡ 6) ፍልስጤማዉያን መቅሰፍት እየደረሰባቸዉ ለሰባት ወር ልባቸዉን ማደንደን ለምን ቀጠሉ? (ዕብ 3፡ 15-16)
-
በታቦቱ ባደረጉት መሰረት ወደ እነርሱ በተመለሰ ጊዜ በእዉነት እስራኤላዊያን የእግዚአብሄርን ቃል ያልተረዱት ይመስላል ? (1 ሳሙ 6፡ 18-19)
-
እንደ እግዚአብሄር ህግ ታቦቱ የት መወሰድ አለበት ? (ዘጸ 40፡ 1-3)
-
በ 1 ሳሙኤል (5-6) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin 1 Samuel 5:11
"The Ekronites called all the Philistine rulers together. They said, ‘Send the ark of Israel’s God away. It must return to its place so it won’t kill us and our people!’ For the fear of death pervaded the city; God’s hand was oppressing them.”
ፍልስጤማውያን የእግዚአብሔርን ታቦት ከወሰዱ በኃላ የእግዚአብሔር እጅ በእነርሱ ላይ ከበደች ፡፡ እነርሱም ታቦቱን ወደ አሽዶድ ከዝያ ወደ ጋዛ እንደገናም ወደ አቃሮን ወሰዱት የእግዚአብሔርም ቁጣ ተከተላቸው ፡፡ የእግዚአብሔርም አጅ በፍልስጤማውያን ላይ ከብዳ ነበርና አስቀሎናውያን እነርሱ በእግዚአብሄር ሀሳብ ውስጥ እንዳልነበሩ ስለተረዱ የፍልስጤማውያንን አለቆች ጠርተው “ የእስራኤል አምላክ ታቦት ስደዱ እኛንና ህዝባችንን እንዳገድል ወደ ስፍራው ይመለስ ፡፡ “ አሉ ፡፡ እነርሱም የእግዚአብሔርን ታቦት ወደ ሚፈልገውና ወደ ራሱ ስፍራ መመለስን ፈለጉ ፡፡
ሁሉም ነገሮች ጥሩ ያልሆኑበት ጊዜ አሳልፈህ ታውቃለህ ? ምናልባትም ሁከት ወይም ህመም ገጥሞህ ይህንንም ለማስተካከል ያለህን አቅም ሁሉ ጨርሰህ ይሆናል ፡፡ በመጨረሻም አንድ ነገር እንደቀረህ ትረዳለህ እርሱም ነገሩን ለእግዚአብሔር መስጠትና የእርሱን መንገድ መከተል ነው ፡፡ ያ ነው በፍልስጤሞች ዘንድ የሆነው ነገር ፡፡ ምናልባትም ዛሬ አንተም ያለኸው እንደዚህ ይሆናል የተሳሳተ ምርጫ መርጠህ በዝያም መንገድ እየሄድክ ነገሮችን ለማስተካከል እየጣርክ ይሆናል ፡፡ ዛሬ መሮጥህን አቁም ራስህን ለእርሱ ስጥ ልብህን ደግሞ ወደ እግዚአብሔር አንሳ ከዝያም ተሸክመኸው የነበረውን ቀንበር ትረዳለህ ፡፡ ስላጠፋኸው ነገር ተናዘዝ ልታስተካክለው የምትፈልገው ነገርም ካለ አስተካክለው ፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድ ፍፁም ሰላም ይገኛል ፡፡ አንተ ደግሞ ይህን ሰላም ስትናፍቀው ነበር ስለዚህ ተመለስ ወደ እግዚአብሔር ፍቅር ግባ ወደ እርሱም እቅፍ ሩጥ ፡፡ ፍቅሩ በላይህ ላይ እንድፈስስ ፍቀድ ፡፡
“ በከተማይቱ ሁሉ የሞት ድንጋጤ ነበርና የእግዚአብሔርም እጅ በዚያ እጅግ ከብዳ ነበረችና ልከው የፍልስጥኤማውያንን አለቆች ሁሉ ሰብስበው የእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱ እኛንና ህዝባችንን እንዳይገድል ወደ ስፍራው ይመለስ አሉ ፡፡
1ኛ ሳሙኤል 5፡11
ተጨማሪ ጥቅስ
- ኢሳያስ 26፡3 –“ በአንተ ላይ ታምናለችና በአንተ ለምትደገፍ ነፍስ ፈጽመህ በሰላም ትጠብቃታለህ ፡፡ “
ኢዮኤል 2፡13 –“ ልባችሁን እንጅ ልብሳችሁን አትቅደዱ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ ቁጣው የዘገየ ምህረቱም የበዛ ለክፋትም የተፀፀተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ ፡፡ “
ማቴዎስ 7፡13-14 –“ በጠበበው ደጅ ግቡ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ወደ ሕይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።