Historical Books 1 Samuel

Seeing the Big Picture

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 226 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

መቼም ቢሆን በብሉይ ኪዳን ብንሆን 1ቆሮ (10፡ 11) በአይምሮአችህ ይሆናል፡ “ ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸዉ እኛንም የዘመናት መጨረሻ የደረሰብንን ሊገስፀን ተጻፈ “ ፡፡ በሪቫይቭ ት/ቤት በእያንዳንዱ 66 የመፅሀፍ ቅዱስ መፅሀፍት ላይ ኢየሱስ እንዴት እንደ ቀረበ ለማየት እንመለከታለን ፤ በእዉነት ያመንኩ የሚያደርገኝ አንድ ነገር በትንሹ ከመፅሀፍ ወደ ኃላ ፈቀቅ ማለት የሚያስፈልግ ነዉ ስለሆነም “ ትልቅ ስዕል “ ማየት እችላለሁ ፡፡ ወደ ምዕራፍ 3 ከመጓዛችን የ 1ሳሙኤልን ትልቅ ስዕል ማሰስ እፈልጋለሁ ፡፡

የሳሙኤል የዉልደት ተዓምራት እግዚአብሄር በዚያን ጊዜ እያደረገ ስለነበረዉ እንዴት ይናገራል ? ከምዕራፍ 1-2 የእግዚአብሄር ቤት ከስርዓት ዉጪ ወጥቶ እንደ ነበር ተምረናል ፤ ታላቁ ካህን ኤሊ ሽማግሌ እና የማያይ ነበር ፤ ወንድ ልጆቹ የክህነት ስራዉን ትክክለኛ ወራሾቹም መጥፎዎች ነበሩ ፡፡ የሚታሰብባቸዉ ጥያቄዎች፡ እግዚአብሄር ምንድን ያደርጋል ? እግዚአብሄር ምንድን ማድረግ ይችላል ? “ አዲስ ስርዓት “ ለማምጣት እግዚአብሄር ሀናን እና ሕልቃናን ተጠቀመባቸዉ ፤ ሀና ልጅ ትፈልጋለች እግዚአብሄር ደግሞ ነቢይ አስፈለገው ፤ የሀና ክርክር ከእግዚአብሄር እቅዱ ወደ ፍሬ ያመጣዋል ፡፡ ሀና በራሷ የጊዜ ወቅት ዉስጥ እርግዝናን አግኝታ ከነበር የሳሙኤል መወለድ ተዓምራት ነበረን ? ይህ ለእግዚአብሄር ጊዜ እና እንቅስቃሴ ትኩረት መስጠት እንደ ሚያስፈልገን ያሳያል ምክንያቱም እግዚአብሄር ዛሬም ተመሳሳይ ነገር እንደ ሚያደርግ አምናለሁ ፡፡ በእኛ ጊዜ እግዚአብሄር ባልመለሰልን ጊዜ እንበሳጫለን ነገር ግን እግዚአብሄር እንዲሰራ የፈለገዉን በመረዳት በኩል ወደ ስምምነት እንድንመጣ እግዚአብሄር ትልቅ ስዕል አለዉ ፡፡

ትምህርት

1-ሳሙኤል (3፡ 1-3)፡ ሳሙኤል ጢት መጥባት ካቆመ በኋላ ለኤሊ ተሰጠ ፤ ሳሙኤል በኤሊ ቁጥጥር ስር እግዚአብሄርን አገለገለ ፡፡ “ በዚያም ዘመን የእግዚአብሄር ቃል ብርቅ ነበር ራዕይ አይገለጥም ነበር “ (ቁጥር 1) ፤ የንጉስ ያዕቆብ ክፍል “ በዚያም ዘመን የእግዚአብሄር ቃል ዉድ ነበር የሚታይም ራዕይ አልነበረም “ ይላል ፡፡ ኤሊ እና ሳሙኤል በመቅደሱም የምሽቱን መብራት ያበራሉ በመተኛትም እስከ ንጋት ማለዳ ድረስ ያርፋሉ (ቁጥር 3) ፡፡

1-ሳሙኤል (3፡ 4-14)፡ ሁለቱም እንደ ተኙ ሳሙኤል የእግዚአብሄርን ድምፅ ሰማ ፤ የኤሊ ድምፅ እንደ ነበር በማሰብ ሳሙኤል ሰዎስት ጊዜ ወዳለበት ሄደ (ቁጥር 5-6፣ 8) ፡፡ ይህ እግዚአብሄር ለልጆች መናገር እንደ ሚችል ያሳስበናል ፡፡ በመጨረሻም ኤሊ ለሳሙኤል እግዚአብሄር እየተናገረዉ እንደ ነበር ገባዉ መመሪያም ሰጠው (ቁጥር 8) ፤ ኤሊም ሳሙኤልን “ ጌታሆይ ባሪያህ ይሰማል ተናገር “ (ቁጥር 9)ብሎ እንዲመልስ አዘዘዉ ፡፡ እግዚአብሄር ሳሙኤልን ልጆቹን አዉቀዉ ኃጢዓትን ከማድግ እና የድንኳኑን ማደሪያ ከማቆሸሽ ስላላስቆማቸዉ በኤሊ ላይ እንደሚፈርድበት ነገረው (ቁጥር 12-14) ፤ ይህ ቃል እግዚአብሄር ለኤሊ በአንድ ሰዉ በኩል ቀድሞ ልኮለት ነበር (1ሳሙ 2፡ 27) ፡፡ እግዚአብሄር ለእስራኤል በሚሆነው ሊገባን በማይችለዉ ፍላጎቱን የሚያደርግበት መንገድ አለዉ፡፡

1-ሳሙኤል (3፡ 15-18)፡ በማለዳም ሳሙኤል እንደ ተለመደዉ ለመሆን ሞከረ ነገር ግን ኤሊ እግዚአብሄር ነግሮት የነበረዉን ለማወቅ ፈለገ ፤ ሳሙኤል ኤሊን የሚመጣዉን የእግዚአብሄርን ፍርድ በነገረዉ ጊዜ ሳሙኤል በትክክል እግዚአብሄርን እንደሰማ ኤሊ አረጋገጠለት (1ሳሙ 2፡ 27-36) ፡፡ ኤሊ የእግዚአብሄርን ፍቃድ ለመናገር እና የሰማ ለመሆን ያወቀ እንደ ነበር አምናለሁ ፤ ይሁን እንጂ እስካሁን መናገር አልቻለም በቤተሰቡ ሆነ ተከስቶ በነበረው ምክንያት እና ከእግዚአብሄር ቀድሞ ሰሞቶት ስለ ነበር ፡፡

ለኤሊ በጥቂቱም ቢሆን አዝናለሁ ፤ በዚህ ጊዜ በአገልጋይ ቤት ዉስጥ ተወልዳችሁ በነበር ጊዜ ልታደርጉዓቸዉ ይገቡ የነበሩ ጥቂት ነገሮች ነበሯችሁ ፡፡ የኤሊ ወንድ ልጆች በክህነት አገልግሎቱ ሊከተሉት ያስፈልጋቸዉ ነበር ነገር ግን መጥፎ ነገሮችን በማድረግ ሙሉ ለሙሉ በኃጢዓት እየኖሩ ነበር ፡፡ ኤሊ ስህተት እያደረጉ እንደ ነበር ያዉቃል ነገር ግን ራሱን በአስቸጋሪ ስፍራ አገኘዉ ፤ ኤሊ ለሳሙኤል “ እርሱ እግዚአብሄር ነው ፤ ደስ ያሳኘዉን ያድርግ “ (ቁጥር 18) በማለት መለሰለት ፡፡ በእኔ የግል አስተያየት ኤሊ በጥቂቱም ቢሆን የእግዚአብሄር መልዕክት በድንኳኑ ማደሪያ የነበረበትን ኃላፊነት እንደሚያስቀርለት ተስፋ እያደረገ እንደ ነበር አስባለሁ ፡፡ ሽማግሌ እና የማያይ ነበር ስለዚህ ሁሉንም ለማድረግ እንዴት ይሾማል(ይቀመጣል) ? በመፅሀፍ ቅዱስ እነዚህ ታሪኮች ጣልቃ ገብነት እንደሚኖር እና እግዚአብሄር በራሱ ጊዜ ጣልቃ እንደ ሚገባ ያሳያሉ ፡፡ ኤሊ በወራሾቹ ማፈር እና ተስፋ መቁረጥ ሊሰማዉ ስለቻለ የእርሱን ቦታ ለሚወስድ ወራሽ እንደ ማይሰጥ አሰበ ነገር ግን እግዚአብሄር ወራሽ ሰጠ ፤ ይህ ወደ “ ትልቅ ስዕል “ እግዚአብሄር ያደረገዉን ለማየት በጣም ወደ ኃላ ያመጣናል ነገሮችን ለራሳችን መንከባከብ በምንችልበት ጊዜም እንኳን ፡፡ እግዚአብሄር ጣልቃ የገባበትን ማየት እንድንችል በደንብ ወደኋላ መመለስ እንድንችል እፈልጋለሁ ፡፡

በእግዚአብሄር ጠብቆት በነበረዉ ስፍራ ላይ የተቀመጠዉ ይህ ልጅ ነበር ፤ ከካህኑ ወንድ ልጆች በተቃራኒ ለታላቁ ካህን ተገኘ ፡፡ ኤሊ ሳሙኤል ከእግዚአብሄር በመስማቱ እና በእግዚአብሄር እይታ በመሆኑ በነበረዉ እዉቀት ኤሊ ያረፈ ይመስላል ፤ ሮሜ (12፡ 1) የሚለዉ “ እንግዲህ ወንድሞች ሆይ ሰዉነታችሁን እግዚአብሄርን ደስ የሚያሰኝ እና ሕያዉ ቅዱስም መስዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሄር ርህራሄ እለምናችኋለሁ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው “ ፤ በድንኳኑ ማደሪያ ሳሙኤል እያደረገ ለነበረዉ ይህ የአዲስ ኪዳን መልክ ነዉ ፡፡

1-ሳሙኤል (4፡ 1-11)፡ በምዕራፍ 4 እስራኤል ከፍልስጤም ጋር ለመዋጋት ሄደ ተሸነፈም (ቁጥር 1-2) ፤ የእስራኤል ሰዎች ለምን እግዚአብሄር እንዲሸነፉ እንደ ፈቀደ አልተረዱም ስለዚህም ከተጨማሪ በፍልስጤም ከመሸነፍ እንደ ሚያድናቸዉ በማሰብ የኪዳኑን ታቦት ከሴሎ አመጡት (ቁጥር 3-5) ፡፡ እግዚአብሄር በእግዚአብሄር የኪዳን ታቦት ሳጥን ዉስጥ እንደ ነበር አሰቡ ፡፡ ፍልስጤማዉያን ከእስራኤላዊያን ሰፈር ታላቅ ጩኸት ሰሙ አምላካቸዉም እንደ ደረሰ ተገነዘቡ (ቁጥር 6-9) ፤ ፍልስጤማዉያን ፈሩ ነገር ግን ከእስራኤል ጦር ጋር ተዋጉ (ቁጥር 10) ፡፡ ታቦቱም ተማረከ እግዚአብሄርም እንዳለዉ ሁለቱም የኤሊ ልጆች ሞቱ (ቁጥር 11) ፡፡

1-ሳሙኤል (4፡ 12-18)፡ አንድ መልዕክተኛ ከጦርነቱ ወደ ሴሎ ለኤሊ ተቦቱ መማረኩን እና የኤሊ ልጆች መሞታቸዉን ለመናገር ሮጠ (ቁጥር 12-17) ፤ ኤሊ ታቦቱ መወሰዱን በሰማ ጊዜ ከወንበር ወድቆ አንገቱ ተሰብሮ ሞተ (ቁጥር 18) ፤ በጥልቅ አዥኖ የነበረዉ በታቦቱ መማረክ እንጂ በልጆቹ መሞት አልነበረም ፡፡

1-ሳሙኤል (4፡ 19-22)፡ የፊንሐስ እርጉዝ ሚስት ባሏ እና ኤሊ እንደ ተገደሉ እንዲሁም ታቦቱ እንደ ተማረከ በሰማች ጊዜ በጉልበቷ ተንበረከከች (ቁጥር 19) ፡፡ እያጣጣረች አንድ ወንድ ልጅ እንደ ወለደች ተነገራት ስሙም ኢካቦድ ሲሆን ትርጉሙም “ ክብር ከእስራኤል ለቀቀ “ ማለት ነው (ቁጥር 20-22) ፤ አሁን ከእግዚአብሄር መገኘት ዉጪ ያሉ ህዝቦች ነበሩ ፡፡

መዝጊያ

በመጨረሻዉ ዘመን ለምንኖር ለእኛ ዛሬ ከዚህ ፅሁፍ “ ትልቁ ስዕል “ ምንድን ነው ? በጨለማ ቀን በምንኖር ጊዜ እግዚአብሄር ለእግዚአብሄር መንግስት ነፃ የሚያወጣ እና ወደ ቅባት ስፍራ የሚያመጣቸዉ ወኔ ያለዉ ሰዉ ማስነሳት እንደ ሚችል አምናለሁ ፡፡ እግዚአብሄር የእግዚአብሄርን ድምፅ ማስተዋል በሚችሉ በወጣት እንዲሁም በሽማግሌ ሊናገር ይችላል ፤ እግዚአብሄር ለእርሱ ራሳቸዉን ከማያስገዙት ጋር ላደረገዉ ኪዳን መጨረሻ ሊያመጣለት ይችላል ፡፡ እግዚአብሄር ወደ አደገኛ ሁኔታ ለሚያስገባ ስርዓት የሚያስፈልገዉን ማስተካከያ ሊያመጣ ይችላል ፡፡

በሚመጡት ምዕራፎች ምንም እንኳን ታቦቱ የተወሰደ ቢሆንም እግዚአብሄር አሁንም ለመልካም ነገሮችን መስራት እንደሚችል እናያለን (ሮሜ 8፡ 28) ፡፡ ሙግቴ (ፈተናዬ) ፡ እግዚአብሄር ለእኔ የሚናገራቸዉን ለትምህርቴና ለኑሮዬ የተፃፉልኝን መመልከት ነው ፤ ከአንት እቅድ ጋር ወደ ስምምነት እንድመጣ እግዚአብሄር ዛሬ እንዳደርግልህ የምትፈልገዉ ምንድን ነው ?

ጥያቄዎች

  1. በሕይወታችሁ እግዚአብሄር እየጠራችሁ እስከ ትንሽ ጊዜ ድምፁን ያለያችሁበት ጊዜ ነበራችሁ ?
  2. በአሁኑ ጊዜ ኤሊ ማድረግ እንዳቃተው ልጆቻችንን ባለማስተካከላችን የረጅም ጊዜ ዉጤት ምን ሊገጥመን ይችላል ? (1 ሳሙ 3፡ 13)
  3. ኤሊ ፍርድ ወደ ቤተሰቡ እየመጣ እንደ ነበር ያዉቃል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  4. 1 ሳሙ ( 4፡ 3) እንደ ሚጠቅሰው የኪዳኑ ታቦት በመገኘታቸዉ በመኖሩ ምክንያት እስራኤላዊያን ከጠላቶቻቸዉ ነፃ እንደ ሚወጡ ለምን እንዳሰቡ ምን ታስባላችሁ ? በመጀመሪያ ቦታ ታቦቱን መዉሰዳቸዉ ለእነርሱ ስህተት ነበር ? (ዘሌ 16፡ 2)
  5. በ 1ሳሙ (4፡ 13) ስለ እግዚአብሄር ታቦት የኤሊ ልብ ለምን እንደ ተንቀጠቀጠ ምን ታስባላችሁ ?
  6. በ 1 ሳሙኤል (3-4) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ)?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Samuel 3:10

“The LORD came, stood there, and called as before, ‘Samuel, Samuel!’ Samuel responded, ‘Speak, for Your servant is listening.’”

ሀና ለእግዚአብሔር ለመስጠት በተሳለችው መሰረት የሀናና የህልቃና ልጅ ሳመኤል ካህኑ ዔሊ ባለበት አደገ ፡፡ ሳሙኤልም በእግዚአብሔር መቅደስ ተኝቶ ሳለ እግዚአብሔር ጠራው ፡፡ ሆኖም ግን ሳሙኤል ጥቂት ጊዜ ፈጅቶበት ነበር የጠራው እግዚአብሔር እንጅ ዔሊ እንዳልሆነ ለመረዳት ፡፡ በመጨረሻም ከዔሊ ምክር በኃላ ሳሙኤል “ ተናገር ባርያህ ይሰማልና “ ብሎ ለእግዚአብሔር መለሰ ፡፡

ታላቁ እረኛህ እግዚአብሔር በእርሱ የሚምኑትን ይናገራል ፡፡ በጎቹም ድምፁን ያውቃሉ ፡፡ የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት የምትችልበት ቦታ ላይ ነህ ያለኸው ? አሁን አስር ደቂቃ ውሰድና በእግዚአብሔር ፊት እረፍ ከዝያም “ ተናገር ባርያህ ይሰማልና “ በለው ፡፡ ዝግጁ መሆን አለብህ ጆሮችህን ለመክፈትና ድምፅ ለመስማት ፡፡ በጊዜው ልትረዳው ከማትችለው የበለጠ በደንብ የሚታይ ነገር እንድያሳይህ ጠይቀው ፡፡ ከእግዚአብሔር በሰማህ ጊዜም ያለህን ነገር አድርግ ፡፡ እግዚአብሔር ለሳሙኤል ለዔሊ ይናገር ዘንድ ጠንካራ መልዕክትን ሰጠው ሳሙኤልም ታዘዘ ፡፡ የእግዚአብሄርን ድምፅ ከመስማት አታቋርጥ ምናልባት እርሱ ባንተ ሌሎችን ይናገር ይሆናል ፡፡

“ እግዚአብሔር መጥቶ ቆመ እንደ ቀድሞውም ሳሙኤል ሳሙኤል ብሎ ጠራው ፡፡ ሳሙኤልም ባሪያህ ይሰማልና ተናገር አለው ፡፡ ”

1ኛ ሳሙኤል 3፡10

ተጨማሪ ጥቅስ

  • ዮሐንስ 10፡27 –“ በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል ፡፡ “

1ኛ ቆሮንቶስ 10፡11 –“ ይህም ሁሉ እንደ ምሳሌ ሆነባቸው እኛንም የዘመናት መጨረሻ ሰየደረሰብንን ሊገስጸን ተፃፈ ፡፡ “

ራዕይ 3፡20 –“ እነሆ በደጅ ቆሜ አንኳኳለሁ ማንም ድምፄን ቢሳማ ደጁንም ቢከፍትልኝ ወደ እርሱ እገባለሁ ከእርሱም ጋር እራት እበላለሁ እርሱም ከእኔ ይበላል ፡፡ “