Historical Books 1 Samuel

Hannah's Vow to God

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Anointed One 1 Samuel 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 225 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ይህ የ1ሳሙኤል የመጀመሪያው የብሉይ ኪዳን ደግሞ አራተኛዉ የታሪክ መፅሀፍ ክፍል ነው ፡፡ ኢያሱን፣ መሳፍንትን፣ ሩትን አጥንተናል አሁን ደግሞ 1ሳሙኤልን ፡፡ በብሉይ ኪዳን የሳሙኤል መፅሀፍ 1ሳሙኤል እና 2ሳሙኤል በመባል ወደ ሁለት ክፍል የተከፈለ ነው ፤ በመነሻዉ ረቂቅ ፅሁፍ አንድ ሙሉ ፅኁፍ ነበር ፡፡ በ1 እና 2ሳሙኤል ሰዎስት ዋና ገፀ ባህሪያት አሉ፡ እያንዳንዳቸዉ በመቀባት ወደ መሲሁ የሚያመለክቱ ሳሙኤል፣ ሳዖል እና ዳዊት ናቸው ፡፡ ለ1ሳሙኤል መፅሀፍ ሀረጋችን የተቀባዉ ነው ፡፡

የእርሱን ስም የተሸከሙትን 1እና 2 ሳሙኤልን ሁለቱንም ነቢዩ ሳሙኤል መፃፉን ማሰብ እንወዳለን ፤ ይሁን እንጂ የሳሙኤል ሞት በ1ሳሙኤል የተመዘገበ ነው ፤ በዚህም ፀሀፊዉ አይታወቅም ለማለት ትክክል ያደርገዋል 1ዜና (29፡ 29) ፀሀፊዎቹ ናታንን እና ጋድን እንዳካተተ ይገልፃል ፡፡ 1ሳሙኤል የ135 አመታት ጊዜን ሸፍኗል ፤ እግዚአብሄር ካህናትን ከመጠቀም ወደ መሳፍንት ከዚያም ወደ ነቢያት ጊዜ በመጨረሻም ወደ ነገስታት ጊዜ ሲጓዝ በመሳፍንት ምስቅልቅል እና በሩት መካከል የሽግግር መፅሀፍ ነው ፡፡ ይህ ጊዜ ከመጣ በኋላ የእስራኤል ወደ ሁለት መንግስት መከፈል ሆነ - እስራኤል ወደ ሰሜን እና ይሁዳ ወደ ደቡብ ፡፡ በ1ሳሙኤል በመጀመሪያዉ ምዕራፍ እስራኤል የተበላሹ ካህናት፣ የረከሰ ቤተ መቅደስ እና የድንጋይ ታቦት ነበሯት ፤ ይህ አደገኛ ሁኔታ በተቀቡት በኩል የተገለበጠ ይሆናል ፡፡

በ1 እና በ2 ሳሙኤል አራት ዋና ፍሬ ነገሮች አሉ፡

  • የዳዊት ኪዳን (1ሳሙ 2፡ 10፣ 2ሳሙ 22፡ 51) - የተቀቡት ነገስታቶች ወደ ተቀባዉ መሲህ ይመራሉ ፡፡
  • የእግዚአብሄር ልዓላዊነት - እግዚአብሄር ሙሉ በቁጥጥሩ ነበር ፡፡
  • የመንፈስ ቅዱስ ስራ (1ሳሙ 10፡ 10፣ 16፡ 13) - መንፈሱ ለተሸሙበት መለኮታዊ ተግባራት ሰዎችን ኃልን ይሰጣል ፡፡
  • የግል እና የባሄራዊ(የቡድን) ኃጢዓት ችግር - የሚያካትታቸዉ ምሳሌዎች፡ ኤሊ እና ልጆቹ ለኪዳኑ ታቦት አምልኮት ባለመኖሩ እና የዳዊት ኃጢዓት ፡፡

ትምህርት

1-ሳሙኤል (1፡ 1-3)፡ ሕልቃና የሚለዉ ስም “ እግዚአብሄር ፈጥሮታል “ ማለት ነው ፡፡ ሕልቃና ሁለት ሚስቶች ነበሩት - ልጅ ያልነበራት እና ልጆች የነበራት ፍናና (ቁጥር 1-2) ፤ ሀና የመጀመሪያዉ ሚስቱ ስለ ነበረች መጀመሪያ የተጠቀሰችዉ ለዚያ ነዉ ብለዉ ብዙ ስነ መለኮታዊያን ጫን ይላሉ ፤ ይሁን እንጂ ሀና ልጅ ስላልነበራት ሕልቃና ለሁለተኛ ጊዜ አገባ ፡፡ የሀና ስም ትርጉሙ “ ፀጋ “ ማለት ሲሆን በእርሷ ላይ እግዚአብሄር የተትረፈረፈ ፀጋዉን ሲያፈስባት የስሙን ትክክለኛነት እናያለን ፡፡ በየአመቱ ሕልቃና በሲሎ ወዳለዉ የድንኳኑ ማደሪያ እግዚአብሄር ለማምለክ እና መስዋዕት ለማቅረብ ጉዞ ያደርጋል (ኢያ 18፡ 1) ፤ የኤሊ ወንድ ልጆች አፍኒንና ፊንሐስ በዚያ እንደ ካህን ያገለግላሉ (ቁጥር 3) ፡፡

1-ሳሙኤል (1፡ 4-8)፡ ሕልቃና የፍናና እና የልጆቹን ድርሻ ስጋ ለመስዋዕት ሰጠ (ቁጥር 4) ነገር ግን ለሀና እንዴት በይበልጥ እንደሚወዳት እንደ ምልክት እጥፍ ድርሻ ሰጣት (ቁጥር 5) ፡፡ የእርሱም ድርጊት እግዚአብሄር ልጅ እንዲኖራት ያልፈቀደላትን ሀናን በየዓመቱ ለምታበሳጫት ፍናና የማስቀናት ምክንያት አለው (ቁጥር 6) ፤ ጣዉንቲቷም ሀናን በኃይል ታበሳጫታለች በማልቀስም ምንም ነገር ለመብላት እምቢ ትላለች (ቁጥር 7) ፡፡ ሕልቃና ሀና ለምን በጣም እንደ ምታዝን ጠየቃት ልጅም ባይኖራት እንኳን የእርሱ ፍቅር ነበራት (ቁጥር 8) ፡፡

1-ሳሙኤል (1፡ 9-28)፡ ካህኑ ኤሊ ባለበት ሀና ስትፀለይም በማልቀስ ለእግዚአብሄር ፀለየች (ቁጥር 9-10) ፤ ሀና እግዚአብሄርን መካንነቷን እንዲያስብ በመጠየቅ ልጅ እንዲኖራት እንዲፈቅድላት ለመነችዉ ፡፡ ልጇም ለእግዚአብሄር አገልጋይ በመሆን ህይወቱን እንደ ሚያሳልፍ እና ፀጉሩን በፍፁም እንደ ማትቆርጥ ቃል በመግባት(የናዝራዊነት መሀላ) ተሳለች (ቁጥር 11) ፡፡ ሀና በፀሎቷ፡

የእግዚአብሄርን ስራ አስታወሰች (ቁጥር 11) - ሀና ወደ እግዚአብሄር ፀለየች ምክንያቱም እግዚአብሄር ምን እንደ ሆነ እና በቀድም ምን አድርጎ እንደ ነበር ስላስታወሰች ፡፡ እግዚአብሄር ጣልቃ የመግባት ኃይል እንደ ነበረዉ አዉቃለች ፤ ስለ ኢያሪኮ እና ጌዴዎን ታዉቃለች ፤ እግዚአብሄር ድሮ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ስለቻለ መካንነቷንም ማስወገድ እንደ ሚችል ሀና አዉቃለች ፡፡ “ ሁሉን ያዘጋጀ አምላክ “ በማለት ወይም እንደ እግዚአብሄር ጦር አዛዥ አደረሰችዉ (ኢያ 5፡ 14) ፡፡

ልቧን ለእርሱ አፈሰሰች ( ቁጥር 12-16) - የሀና ከንፈር እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም ድምፅ አልተናገረችም ፤ የአደባባይ ፀሎት ድምፁ የሚሰማ ነበር ስለሆነም ኤሊ ሀና ሰክራ ነበር በማለት ተደነቀ (ቁጥር 13) ፤ ኤሊም ወይንሽን አስወግጂ በማለት ሰደባት (ቁጥር 14) ፡፡ ሀና እንዳልሰከረች ነገር ግን ልቧ በመሰበሩ ህመሟን ለእግዚአብሄር እያፈሰሰች እንደ ነበር ገለፀች (ቁጥር 15) ፤ ለእግዚአብሄር ህመማችንን ማፍሰስ መልካም ነው (መዝ 62፡ 8፣ 142፡ 1-3፣ ማቴ 11፡ 28፣ ፊል 4፡ 6፣ 1ጴጥ 5፡ 7) ፡፡

የእርሱን ሰላም ተቀበለች ( ቁጥር 17-18) - ኤሊ በሰላም እንድትሄድ ነግሯት ለጥያቄዋ ባርኮቱንም ጨመረላት (ቁጥር 17) ፤ ሀና በሄደች ጊዜ ከዚያም በኋላ አዘንተኛ አልመሰለችም (ቁጥር 18)(ዮሐ 14፡ 27፣ ቆላ 3፡ 15) ፡፡

የእርሱን ጊዜ አመነች (ቁጥር 19-20) - በሰላሟ ሀና የእግዚአብሄር ጊዜ መታመን ትችል ነበር ፤ “ ከጥቂት ጊዜ በኃላ “ ወይም አንዳንድ ሽግግሮች እንደ ሚሉት “ በጊዜዉ “ ሀና በመፀነስ “ ከእግዚአብሄር ለምኘዋለሁና “(ቁጥር 20) የሚል የስም ትርጉም ያለዉን ሳሙኤልን ወለደች ፡፡ የእግዚአብሄርን ሰላም በተቀበልን ጊዜ እንድናደርገዉ በነገረን መጓዝ እንችላለን ፡፡

በድሉ አመለከችዉ (ቁጥር 21-28) - ሕልቃና ስለ ሳሙዔል መሰጠት እግዚአብሄርን ለማምለክ ወደ ሴሎ ቤተሰቡን ወሰደ ፤ ሀና እና ልጁ ቀርተዉ ተቀመጡ ምክንያቱም ልጁ ጡት እስካላቆመ ድረስ ወደ እግዚአብሄር ለመመለስ ጊዜዉ አልመጣም ነበርና ፤ ሳሙኤል ጡት ማጥባት እንዳቆመ ሀና ከሚያስፈልጉ መስዋዕቶች ጋር ወደ ሴሎ ወሰደችዉ፡ ከአንድ ሰዎስት አመት ወይፈን ጋር፣ ከአንድ የኢፍ መስፈሪ ዱቄት እና ከአንድ አቁማዳ የወይን ጠጅ ጋር (ዘኁ 15፡ 8-10) ፡፡ የሀና መስዋዕቶች ከሚያስፈልገዉ በላይ ነበር (መዝ 95፡ 2-3፣ 100፡ 4-5)

መደምደሚያ

በእግዚአብሄር ጊዜ ላይ በምንታመን ጊዜ በእርሱ ድል እግዚአብሄርን ማምለክ እንችላለን ፤ ሁሉም በ1ሳሙ (2፡ 1-10) ወደ ሀና የምስጋን የአምልኮ ፀሎት ይመራሉ ፡፡ የ 1ሳሙኤል ምዕራፍ 2 ሳሙኤል በኤሊ ጥበቃ ስር እንዴት እንዳደገ እና የኤሊ ወንድ ልጆች የረከሱ እንደ ነበሩ መዝግቧል ፡፡ እግዚአብሄር የተበላሸዉን የክህነት ቤተሰብን ማስወገድ ሲጀምር ሳሙኤል የሚባል አንድ ወጣት ወንድ ልጅ እያሳደገ ነበር ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 1999), p. 343.

  2. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), pp. 300–301.

ጥያቄዎች

  1. በ 1ሳሙ (1፡ 1-8) ልጅ ያልነበራትን በማካተት ሁለት ሚስቶች ነበሩ ፤ በብሉይ ኪዳን ላይ ተመሳሳይ ነገር ከዚህ ዉጭ የት ላይ አለ ? (ዘፍጥረት 29)
  2. ካህኑ ኤሊ ሀናን ለምን ጠጥታ እንደ ነበር አሰባት ? (1ሳሙ 1፡ 13-14)
  3. በ 1ሳሙ (1፡ 18) ሀና ንደቷን በማቆም ምግብ በላች ፤ እንድትቀየር የተፈጠረዉ ምንድን ነዉ ብላችሁ ታስባላችሁ ? እግዚአብሄር ሰምቷችሁ የፀሎታችሁ ዋስት በመሆን ከጥርጣሬአችሁ በላይ በመሆን ታዋቂ የሆነ ፀልያችኋል ? በምን አይነት መንገድ ?
  4. በ 1ሳሙ (1፡ 11) ሀና ለእግዚአብሄር ምን አይነት ስለት አደረገች ? ስለቷን ጠብቃለች (1 ሳሙ 1፡ 24) ? እንደ ቤተሰብ ለእርሷ ያን ስለት መጠበቅ ማለት ምን ማለት ? (1ሳሙ 2፡ 2፡ 11)
  5. በ 1ሳሙ (2፡ 20-21) ኤሊ ለሀና በእያንዳንዱ አመት ፀለየላት ፤ ፀሎቱ ምን ነበር ? እግዚአብሄር ፈፅሞታል?
  6. ካህኑ ኤሊ በመቅደስ የሚያገለግሉ በእግዚአብሄር ላይ ኃጢዓት የሰሩ ሁለት ልጆች ነበሩት ፤ በ 1ሳሙ (2፡ 27) እግዚአብሄር ኤሊን አንድ መልዕክት ሊሰጠዉ አንድ ሰዉ ላከ ፤ መልዕክቱ ምን ነበር ? እርሱና ልጆቹ ምን መሆን ነበረባቸዉ ?
  7. በ 1 ሳሙኤል (1-2) በትምህርት ወይም በጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin 1 Samuel 1:15–16

“‘No, my lord,’ Hannah replied. ‘I am a woman with a broken heart. I haven’t had any wine or beer; I’ve been pouring out my heart before the LORD. Don’t think of me as a wicked woman; I’ve been praying from the depth of my anguish and resentment.’”

ከአርማቴም መሴፋ የሆነ ሕልቃና የተባለ ኤፍሬማዊ ሰው ነበረ እርሱም ፍናና እና ሀና የተባሉ ሁለት ሚሰቶች ነበሩት ፡፡ ፍናና ልጆች ነበሩአት ሀና ግን ልጅ አልነበራትም ፡፡ ሀና መካን ብትሆንም እንኳ ህልቃና ይወድዳት ነበር ፡፡ሆኖም ሀና ልጅ ትፈልግ ነበር ፡፡ እርስዋም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ወስጥ ካህን ወደ ነበረው ወደ ዔሊ ሄደች ፡፡ እርስዋም በተሰበረ ልብ ወደ አግዚአብሔር ቀረበች ከውስጥ ከነፍስዋም ፀለየች ከእግዚአበሔርም ልጅን ለመነች ፡፡ በእግዚአብሔር ጊዜም ሀና የለመነቸውን ተቀበለች ፡፡

የሆነ ነገር ፈልገህ ታውቃለህ ማለትም ልብህን በጣም የሰበረውን ያሳዘነውን ነገር ? ራስህንስ በእግዚአብሔር ፊት ነፍስህን ስታፈስ አግኝተኸው ታውቃለህ ? ሀና ይህንን የልብ ስብራትና ጠንካራ የሆነ ፍላጎትን ትመስልልናለች ፡፡ በተሰበርክ ባዘንክ ጊዜ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ አስታውስ ፤ አስታውስ ከእምነት የሆኑ የእርሱን ስራዎች ፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገው አንተ ነፍስህን ለአርሱ እንድታፈሰ ነው ፡፡ እርሱ ሚፈልገው ጥየቄህን ለእርሱ እንድታሳውቀው ነው ፡፡ እግዚአብሔር እንድረዳህ ለምን እናም የእርሱን ሰላም ተቀበል ፡፡ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ እርሱንም አምልክ ፡፡

“ሐናም ጌታዬ ሆይ አይደለም አኔስ ልብዋ ያዘነባት ሴት ነኝ ጠጅና ሌላ የሚያሰክር ነገር አልጠጣሁም ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ነፍሴን አፈሰስሁ ኀዘኔና ጭንቀቴ ስለ በዛ እስከ አሁን ድረስ ተናግሬአለሁና ባሪያሀን እንደ ምናምንቴ ሴት አትቁጠረኝ ብላ መለሰችለት ፡፡ “

1 ሳሙኤል 1፡15-16

ተጨማሪ ጥቅስ

  • መዝሙር 61 (62) ፡8 –“ የሕዝብ ማኅበር ሁላችሁ በእርሱ ታመኑ ልባችሁንም በፊቱ አፍስሱ እግዚአብሔር ረዳታችን ነው ፡፡ “

ዮሐንስ 14፡27 –“ ሳላምን አተውላችኋለሁ ሰላሜን እሰጣችኋለሁ እኔ የምሰጣችሁ ዓለም እንደሚሰጥ አይደለም ፡፡ ልባችሁ አይታወክ አይፍራም ፡፡ “

ፊልጽስዮስ 4፡6 –“ በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጅ በአንዳች አትጨነቁ ፡፡ “