The Kinsman Redeemer
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Kinsman Redeemer Ruth 3-4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ብዙ ትምህርቶችን እያደረግን እንደሆነ ይመስላል ትክክሉ ግን በሩት መፅሀፍ ሁለት ክፍል ብቻ መሆኑ ነው ፡፡ ትናትና ምዕራፍ አንድን እና ሁለትን ሸፍነናል ፤ ዛሬ ስለ ቡዔዝ እና ሩት ግንኙነት እናወራለን ፡፡ በሩት መፅሀፍ ለኢየሱስ ሀረጋችን የወንድ ዘመድ ተቤዢ ነው ፡፡ ስለ ሞዓብ ቤተ ልሄምን ትተዉ ከሄዱ በኃላ ኑኃሚን እና ሩት እንደ መበለት እየተመለሱ ነበር ፤ እግዚአብሄር ይህን ሁኔታ ለኑኃሚን እና ሩት ዋጀዉ ፡፡ እግዚአብሄር እንዴት በማድረግ ነበር የሚዋጃቸው ? በአንድ ተቤዢ ዘመድ በኩል ዋጃቸው ፡፡
ትምህርት
ሩት (3፡ 1-2)፡ ኑኃሚን ስለ ሩት በማሰብ ለእርሷ ደህንነት ለማግኘት ፈለገች ፤ ሩት እንክብካቤ ስለ ማግኘቷ እርግጠኛ መሆን ፈለገች ፤ ኑኃሚንም “ ቡዔዝ ዘመዳችን አይደለምን “ በማለት ሩት በቡዔዝ ማሳ ላይ እየሰራች እንደ ነበር አስታወሰቻት ፡፡ ኑኃሚን ቡዔዝ በመዉቂያዉ አዉድማ እንደ ሚሆን ታዉቃለች ምክንያቱም ከህዝቡ የወጣ ስለ ነበር ፤ በዚህም ምክንያት ሁሉም ሰዉ ቡዔዝ ወደ መዉቂያ አዉድማዉ በምሽት እንደ ሄደ አወቁ ፡፡
ሩት (3፡ 3-5)፡ ኑኃሚን ሩትን እንዴት ቡዔዝን መቅረብ እንዳለባት መመሪያ ሰጠቻት ፤ ሩትን ራሷን እንድትታጠብ እና ምርጡን ልብሷን እንድትለብስ አዘዘቻት ፡፡ ስለ ዚህ ስዕል የምወደዉ ዋይርስቤ “ ከእግዚአብሄር ጋር የጠለቀ ግንኙነት ለማድረግ የእግዚአብሄር ሰዎች ማድረግ ያለባቸዉን እርምጃዎች ብሎ የተራቸዉን “ ማየታችንን ነው ፡፡ እነዚህ አምስት ደረጃዎች ለወንድ ዘመድ ተቤዢ ለመዘጋጀት የሚጠቅሙ ነበሩ ፤ ለእኛ ለወንድ ተቤዢአችን ለመሲሁ እንዴት እንደ ምንዘጋጅ ነዉ ፡፡
- መታጠብ (ኢሳ 1፡ 16) ፤ ይህ ንግግር ቀላል ቢሆንም የዝግጅት አካል ነበር (2ቆሮ 7፡ 1-2) ፡፡
- ራሳችሁን መቀባት (1ዮሐ 2፡ 20፣ 27) ፤ ከእግዚአብሄር መንፈስ ቅባት አለን ፡፡
- ልብሶችን መቀየር (ኢሳ 61፡ 3፣ ሉቃ 15፡ 22) ፤ የሰርግ ድግስን መልክ እና የትክክለኛ ልብሶች መኖርን ይስላል ፤ ለእኛ የቅድስና ካባ ነው ፡፡
- በመከሩ ጌታ እግር ፊት ራሳችንን እንዴት ማቅረብ እንዳለብን መማር ፤ ይህ በእግሩ ስር በመቀመጥ ሙሉ በሙሉ አሳልፎ የመሰጠት አስተሳሰብ ነው ፡፡
- ለመታዘዝ ቃል መግባት ፡፡ ኑኃሚን ስለ ነገረቻት ሩት ሁሉንም እንዴት እንደምታደርግ አዉቃለች ፤ ይህ 2ጢሞቲዎስ የሚያንሱትን ሽማግሌዎች ይመክሯቸዋል (ያስተምሯቸዋል) የሚለዉ አስተሳሰብ ያለዉ ነው፡፡
ሩት (3፡ 6-7)፡ ሩት ኑኃሚን እንድታደርግ የነገረቻትን ሁሉንም ነገር አደረገች (ቁጥር 6) ፤ በመጠጣቱ ቡዔዝ እንዴ ጥሩ ሙድ ላይ እንደ ነበር ሩት በድብቅ በመሄድ እግሮቹን በመግለጥ በዚያ ጋደም አለች (ቁጥር 7) ፡፡ የዚህን ፅሁፍ አንዳንድ ልማዳዊ ባህሪያቶችን ዉስጥ ልጓዝ ፤ ዋይርስቤ “ በአንድ ሰዉ ላይ የለበሰዉን መልበስ ማለት ያን ሰዉ ለራስ መፈለግ (1ነገ 19፡ 19፣ ሕዝ 16፡ 8) በተለይም ለጋብቻ ማለት እንደ ሆነ “ ይገልፃል ፤ ይህ ድርጊት በግልፅ የሚናገረው “ ላገባህ እፈልጋለሁ “ የሚል ነው ፡፡ ቡዔዝ ከሩት የሚበልጥ ትዉልድ ነበር ነገር ግን ባህሉን በማክበር ሁሉንም ሁኔታዎች በሚገባ በማክበር አስተናገደች ፡፡
ሩት (3፡ 8-9)፡ እኩለ ሌሊትም ላይ በመደንገጥ እግሩም ጋር ሩትን ለማግኘት ነቃ ፤ ሩትም ለቡዔዝ “ የቤተሰብ ዋጂ ነህ አለችዉ “ (ሩት 2፡ 12) ፤ የወንድ ዘመድ ዋጂ (ዋርሲያ) ተግባራት የነበሩት፡
አንድ የቤተሰብ አባል ተገዶ እንዲሸጥ የተደረገዉን ንብረት በቤተሰቡ ዉስጥ ለመጠበቅ መልሶ የመግዛት ፡፡
ለሟች ወንድሙ የሞተዉን ሚስት በማግባት ከእርሷ ልጅ በመዉለድ ወራሽ መስጠት ፡፡
ለባሪያነት ተሸጦ የነበረን ማንኛዉም የቤተሰብን አባል መልሶ መግዛት ፡፡
ተገድሎ ለነበረዉ ማንኛዉም የቤተሰብ አባል መበቀል ፡፡
እግዚአብሄር ለሁሉም ሰዉ የሚጠነቀቅ የመጨረሻ ተቤዢ ነው (ኢሳ 60፡ 16) ፡፡
ሩት (3፡ 10-11)፡ ቡዔዝ ሩትን ባረካት እንዳትፈራም በማበረታታት የጠየቀችዉን ሁሉ እንደ ሚያደርግላት አረጋገጠላት ፡፡ የቤተሰብ ተቤዢ ለመሆን ፍቃደኛ ሆኖ የነበረበት ምክንያት የሩት የጨዋነት(መልካም) ባህሪይ ነበር (ምሳ 31፡ 10) ፡፡
ሩት (3፡ 12-13)፡ ቡዔዝ እርሱ የቤተሰብ ዋርስያ ከነበር መጀመሪያ ሊቀረብ የሚገባ ሌላ የቤተሰብ ዋርስያ እንደ ነበር አመለከተ ፤ ቡዔዝ የድርጊቱ እቅድ ነበረው ፡፡ ሩትንም ያን ምሽት ከእርሱ ጋር ቆይታ በማለዳ ቤት እንዲትሄድ ነገራት ፤ ሩትንም ሌላ የቤተሰብ አባል ሊዋጃት የሚፈልግ እንዳለ ያያል ፡፡
ሩት (3፡ 14-15)፡ ሩትም እግሩ ጋር ጋደም አለች ፤ በማለዳም ከፀሀይ በፊት ነቃች ፡፡ ቡዔዝም በጋቢዋ ላይ ስድስት መስፈሪያ ገብስ በመስፈር ቤት ላካት ፤ ቡዔዝ በእርሷ ላይ ለጋስነቱን አፈሰሰ ፡፡
ሩት (3፡ 16-17)፡ ሩት ከምሽቱ በፊት ዝርዝሩን ልትሰጣት ወደ ኑኃሚን ተመለሰች ፤ ሩትም ሁሉንም ነገር በመስጠት ቡዔዝ ከእርሷ ጋር ልኮት የነበረዉን ገብስ ሰጠቻት ፡፡
ሩት (3፡ 18)፡ ኑኃሚን ሩትን ቡዔዝ በቀኑ መጨረሻ ላይ ማድረግ የሚፈልገዉ ነገር እንዳለ ነገረቻት ፡፡
ሩት (4፡ 1)፡ የቅርብ ወንድ ተቤዢዉ ምድሪቱን ፈለገ ነገር ግን ሩትን ለማግባት አልፈለገም ፤ ተቤዢዋ ለሚሆነዉ የቀረበዉን መለሰ ፡፡
ሩት (4፡ 13)፡ ቡዔዝ ሩትን ወሰዳት ሚስቱም ሆነች ፤ ልጅም ፀነሰች ቆይታም አንድ ወንድ ልጅ ወለደች ፡፡
መደምደሚያ
ሞዓባዊያኗ ሩት ሙሉ ለሙሉ ተዋጀች ! ተቤዢዉ ሰዉዬ የቤተሰቡን አባል ሞትን በመዉሰድ ሁሉንም ሁኔታ ተቤዠዉ ፡፡ በተቤዢዉ ሰዉዬ ምክንያት የክርስቶስ ዘር ግንድ ኖረን ፡፡ የሩት ወንድ ልጅ ኢዩቤድ ነበር ፤ ኢዩቤድ የኢሴይ አባት ነበር ኢሴይ ደግሞ የዳዊት አባት ነበር ፡፡ ሁሉም ነገር ሩት ኑኃሚን “ ወደ ምትሄችበት ሁሉ እሄዳለሁ…አምላክሽ አምላኬ ይሆናል “ ወዳለቻት ይመልሳል ፡፡
ይህ ተቤዢ ሰዉዬ ቡዔዝ እንዴት ከክርስቶስ ጋር ይገናኛል ? የተቤዢ ሰዉዬ መስፈርቶች የነበሩት፡
የደም ዝምድና (ዘሌ 25፡ 25፣ ዘዳ 25፡ 5-7) ፤ በክርስቶስ ይህ እንዴት ተፈፅሟል ? ቤዛነቱ (መቤዠቱ) እንደ ወንድ ልጆቹ እና ሴት ልጆቹ ከክርስቶስ በተቀበለን(በሞግዚነታችን) በኩል መጣ (ገላ 4፡ 3-5) ፡፡
የግድ የሆነ ምንጭ (1ቆሮ 6፡ 20) ፤ በእኛ ቦታ መስቀል ላይ በሞተዉ በክርስቶስ ዋጋ ተገዝተናል ፤ ተቤዢዉ ሰዉዬ ሀብትን ገዛ ክርስቶስ ግን ነፃነታችንን ገዛልን ፡፡
ፍቃደኛ መሆን አለበት (ዘዳ 25፡ 7-9፣ 1ዮሐ 3፡ 16) ፤ ኢየሱስ ህይወቱን ለመስጠት ፍቃደኛ ስለሆነ እናንተ እና እኔ የተቤዠን መሆን እንችላለን ፡፡
1ጴጥ (1፡ 18-19) ለተቤዢ ሰዉ ቁልፍ ጥቅሳችን ነው ፤ ከህይወት ባዶ መንገዳችን ተዋጅተናል ፡፡ ክርስቶስ የሚቤዠን ዘመዳችን ነው !
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Ruth (Colorado Springs, David C. Cook, 2003), p. 191.
Wiersbe, pp. 191-193.
Wiersbe, p. 194.
Alexander Maclaren, “Kinsman-Redeemer,” Expositions of Holy Scripture, available online at https://biblehub.com/library/maclaren/expositions_of_holy_scripture_h/the_kinsman-re-deemer.htm.
ጥያቄዎች
-
ኑኃሚን ሩትን በእግሩ ላይ ጋደም እንድትል ለምን ሩትን እንዳዘዘቻት ምን ታስባላችሁ ?
-
በሩት (3፡ 14) ቡዔዝ “ ሴት ወደ አዉድማዉ እንደ መጣች ማንም እንዳያዉቅ “ ለምን እንዳለ ምን ታስባላችሁ ?
-
ሩት (4፡ 7) ላይ የተጠቀሰው አንድ ሰዉ ጫማዉን አዉልቆ ለሌላ እንዲሰጠዉ ልማድ የነበረው ለምን ነበር (ዘዳ 25፡ 8-10) ?
-
በሩት መፅሀፍ የሩት ተቤዢ ዘመድ ማን ነበር (ሩት 3፡ 12-13) ? ያ ማለት ምን ማለት ነው ? የእኛ ተቤዢ ዘመድ ማን ነው ? (መዝ 82፡ 4)
-
በሩት (3-4) በትምህርት ወይም ጥናት ዉስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Ruth 4:13-14
“Boaz took Ruth and she became his wife. When he was intimate with her, the Lord enabled her to conceive, and she gave birth to a son. Then the women said to Naomi, ‘Praise the Lord, who has not left you without a family redeemer today. May his name become well known in Israel.’”
ሩት በእርሻ ውስጥ ስትቃርም ከቆየች በኃላ ኑኃሚን ቦዔዝ የሩትን ህይወት የሚቤዥ ዘመድ መሆኑን ተረድታ ስለነበር ሩት ለወደፊት ህይወቷ ዕረፍትን ትፈልግ ዘንድ ነገረቻት ፡፡ በ……ህግ መሰረት የሚቤዥ ዘመድ ማለት ሰውን ወይም ንብረትን የሚያድን ወይም የሚቤዥ ማለት ነው ፡፡ ቦዔዝ እርዳታ ከሚያሰፈልጋት ከሩት ጎን የመቆም መብት ወይም ደግሞ ሀላፊነት ያለው ወንድ ዘመድ ነው ፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ቦዔዝ አድናቆትንና አክብሮትን ለሩት አሳይቷል ፡፡ ቦዔዝና ሩትም በተጋቡ ጊዜ ኢዮቤድን ወለዱ ፡፡ በእግዚአብሔር ቸርነት ኢዮቤድ የዳዊት አያት ሆነ ፡፡ ዳዊት የእስራኤል ታላቅ ንጉስ ብቻ አልነበረም ይልቁንም የአድስ ኪዳን አዳኝህ የኢየሱስ ከርሰቶስ የዘር ግንድም ነበር እንጅ ፡፡
ይህ የቦዔዝና ሩት ምሳሌ እግዚአበሔር ላንተ አንዴተ የሚቤዠ ወይም አዳኝ ዘመድን በልጁ በከርስቶስ ኢየሱስ በኩል እንዴት እንዳዘጋጀልህ ለማሰታወስ ይረዳል ፡፡ ኢየሱስ የሚያስፈልግህን በማሟላት ይታደግሀል ፡፡ ኢየሱሰ አማኝ ወንድሞች አንዳቸው የሌላውን ፍላጎት እነድያሟሉ ያዛል ልክ የቦዔዘ እርዳታ የሩትን ፈላጎት እንዳሟላው ሁሉ ፡፡ ኢየሱስ የሁሉንም አማኝ ህይወት በመስቀል ላይ ባፈሰሰው ደሙ ገስቶታል ከፍ ያለ ዋጋ ከፍሎ ፡፡ ኢየሱሰ በቸርነቱ ላንተ መልካምነትን ተሰፋንና ደስታን በቤዛነት ወስጥ አድርጎልሀል አንተ ልታገኘው የማይቻልህን ማለት ነው ፡፡ ቤዛነት ማለት ኢየሱስ አንተን በጸጋ ሲወድህ ማለት ነው ፤ ቤዛነት ማለት እግዙአብሔር ለራሱ ህዝብ ያለው የመጨረሻ ግብ ነው ፡፡
“ ቦዔዝም ሩትን ወሰደ ሚስትመ ሆነችው ደረሰባትም እግዚአብሔርም ፅንስ ሰጣት ወንድ ልጅም ወለደች ሴቶችም ኑኃሚንን ዛሬ ወርሳ ያላሳጣሽእግዚአብሔር ይባረክ ስሙም በእስራኤል ይጠራ ፡፡ “
ሩት 4፡13-14
ተጨማሪ ጥቅስ
- ሩት 4፡17 –“ ሴቶችም ጎረቤቶችዋ ለኑኃሚን ወንድ ልጀ ተወለደላት እያሉ ስም አወጡለት ስሙንም ኢዮቤድ ብለው ጠሩት ፡፡ እርሱም የዳዊት አባት የእሴይ አባት ነው ፡፡ ”
ገላትያ 4፡4-5 –“ ነገር ግን የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ከህግም በታች የተወለደውን ልጁን ላከ እንደ ልጆች እንሆን ዘንድ ከሀግ በታች ያሉትን ይወጀ ዘንድ ፡፡ “
ኤፌሶን 1፡7-8 –“ በወድ ልጁም አንደ ፀጋው ባለ ጠግነት መጠን በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት ነው ፡፡ ጸጋውንም በጥበብና በአእምሮ ሁሉ አበዛልን ፡፡ “
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።