The Second Passover & Guidance by Cloud
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 8-9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በተለያየ መንገድ እግዚአብሄር እኛን መናገር ቀጠለ ፡፡
ትምህርት
ዘኁልቁ(8፡ 1-26)፡ እነዚህ አሮን መብራቶቹን፣ የመብራቶቹ መቀመጫ ስራ እና በቅዱሱ ስፍራ ብርሃኑን መጠበቅ እንዴት ማመቻቸት እንዳለበት ትዕዛዞች ነበሩ ፡፡ የሌዋዊያንን በኩር ለመታሰቢያ እና ለመለየት(ለመቀደስ) ትዕዛዞች ተሰጥተው ነበር ፤ በተጨማሪም ለሌዋዊያን እንደ ካህናት ለማገልገል የእድሜ ወሰኖችን ያስቀመጠ ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(9፡ 1-3)፡ ሁለተኛው ፋሲካ፡ ከግብፅ ከተነሱ በኃላ ይህ የሁለተኛው አመት መጀመሪያ ነበር ፤ በግብፅ የሞት መንፈስ እንዳለፋቸው ለማስታዎስ የእስራኤላዊያን ሁለተኝ ጊዜአቸው ነበር (ዘጸ 12፡ 1-32) ፡፡ በትውልዶች መውስጥ ይከብሩት ነበር ፡፡ የሚያስደስት ክስተት ነበር ፡፡ የተመረጠው ጊዜ በመጀመሪያው ወር በአስራ አራተኛው ቀን(በአልቦካ ቂጣ ቀን) ፀሀይ በምትገባበት ጊዜ ላይ ነበር ፡፡ ዮሐንስ ማክአርቱር ድንግዝግዝን እንደ “ በቀጣዩ ቀን መጀመሪያ እና በቀኑ መሀከል ያለው ጊዜ “ብሎ ለይቶታል ፡፡ ምሽት(የፀሀይ መጥለቅ) የቀኑ ስራ የሚያልቅበት የተረጋጋ ጊዜ ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(9፡ 4-5)፡ እግዚአብሄር ሙሴን ያዘዘውን ሁሉንም እስራኤላዊያን አደረጉ ፡፡ በቆሻሻ ህይወት በሌለበት ቦታ በሲና በርሃ ግብዣ ነበራቸው ፤ ፋሳኪና ለማክበር ትውልዱ ቀጠለ ፡፡ ሁልጊዜ ፋሲካ ወደ ሚመጣው መሲህ ያመለክታል ፤ በእርግጥ ማቴ(26፡ 17) “ በቂጣው በዓል በመጀመሪያ ቀን ደቀ መዛሙርቱ ወደ ኢየሱስ ቀርበው ፡፡ ፋሲካን ትበላ ዘንድ ወዴት ልናሰናዳልህ ትወዳለህ አሉት ፡፡”
ኢየሱስ ፋሲካን አከበረ ፤ መጥምቁ ዮሐንስ መንገዱን አዘጋጀ (ዮሐ 1፡ 29) ፡፡ በአገልግሎቱ መጀመሪያ ላይ ኢየሱስ የአይሁድን ፋሲካ አክብሮአል (ዮሐ 2፡ 13) ፤ በህይወቱም መጨረሻም ላይ ኢየሱስ ፋሲካን አከበረ (ሉቃ 22፡ 15) ፡፡ 1ቆሮ 5፡ 7 በሚመስል በአጠቃላይ ተሰጠ ፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ የፋሲካ በግ ነው ፤ ለኃጢዓታችን እንደ ማስተሰሪያ(ተተኪ፣ ማመካኛ፣ ሞት) ደሙን አፈሰሰ ፡፡ ክርስቶስ ሞተ በዚህም ፋሲካ ሆነ ስለዚህ ህይወት ሊኖረን ቻለ ፡፡ በእያንዳንዱ አመት ፋሲካን ማክበርን እንዲጠብቁ እስራኤል ታዝዞ ነበር ምክንያቱም ለእኛ “ፋሲካ” ክርስቶስ መጣ ፤ እዚህ ጋር እግዚአብሄር የተፈጥሮ ሽግግር እንዲሆን ፈለገ ፡፡
ዘኁልቁ(9፡ 6-8)፡ ጥቂት ሰው በሰው ሬሳ ምክንያት ፋሲካን ማክበር አልቻሉም ፤ በብዓሉ ላይ መካትት ይቻል እንሆን በዚያ ሁኔታ ያሉ በትክክለኛ የልብ አሳብ ወደ ሙሴ ሄደው ጠየቁት ፡፡ በትህትና ከጥያቄአቸው ጋር ሙሴ ወደ እግዚአብሄር ሄደ ፤ ሙሴ በራሱ ውሳኔ ለማድረግ አልሞከረም ፡፡ በመሪነት በራሳችን ኑሮ ውስጥ ውሳኔ ከማድረጋችን በፊት ሁልጊዜ በመጀመሪያ ወደ እግዚአብሄር ፊት ሄደን ቢሆን ምን ያክል የተሸለ ይሆን ነበር ?
ዘኁልቁ(9፡ 9-12)፡ እግዚአብሄር በሩቅ ጉዞ ወይም በሬሳ የረከሰ ከሆነ ቀጥሎ ፋሲካን እንዲያከብሩ ነገር ግን ከህዝቡጋር እንዳልሆነ ሙሴን መለሰለት ፡፡ የታዘዙትን ሁሉንም ትዕዛዝ ይጠብቃሉ ፤ በሁለተኛው ወር (በመጀመሪያው አይደለም) በአስራ አራተኛው ቀን ፀሀይ ስትጠልቅ ያከብራሉ ፤ ካልቦካ ቂጣ ጋር እና ከሚመር ቅጠል ጋር ጦቦቱን ይበላሉ እስከ ጥዋት ድረስ ምንም መትረፍ አይኖርበትም ፤ በመጨረሻም የጠቦቱን አጥንት አይሰብሩም ፡፡
የጠቦቱን ምንም አጥንት እንዳይሰበር የሚለው ትዕዛዝ የመሲሁን መምጣት ያሳያል፡
- 1ቆሮ (5፡ 7)፡ ጳውሎስ ኢየሱስ ፋሲካችን እንደሆነ አውርቶአል ፡፡
- ዮሐ (1፡ 29)፡ ኢየሱስ ጠቦት እንደሆነ እናውቃለን ፡፡
- ዘጸ (12፡ 46)፡ አስራኤል የመስዋዕቱን በግ ምንም አጥንት አይሰብርም ነበር ፡፡
- መዝ (34፡ 20)፡ “ እግዚአብሄር አጥንቶቻቸውን ሁሉ ይጠብቃል ከእነርሱም አንድ አይሰበርም ፡፡”
- ዮሐ (19፡ 31-36)፡ የኢየሱስ አካል ጥንቃቄ፡
- ቁጥር 31፡ አይሁዶች በችኮላ በሰንበት ፊት ስጋዎችን ይወስዱ ነበር እናም የሰዎቹን የጭን አጥንት ከመውሰዳቸው በፊት እንዲሰብሩት ጲላጦስን ጠየቁት ፡፡
- ቁጥር 32፡ ሁለቱ ሰዎች በኢየሱስ በሁለቱም በኩል የነበሩት በህይወት ነበሩ ፤ ጭናቸው ተሰብሮ ነበር ፡፡
- ቁጥር 33፡ ኢየሱስ ሞቶ ነበር ስለዚህ በእግሩ ላይ ምንም ቦታ ላይ ስብራት አላዩም ፤ ኢየሱስ የፋሲካው በግ የተሰበረ አጥንት አልነበረውም ፡፡
- ቁጥር (34-35)፡ የኢየሱስን ጎን የወጋው ወታደር እንደሞተ ተናገረ ፤ ሁሉም ያዩት እንደሞተ አወቁ ፡፡
- ቁጥር 36፡ እና “ ከእርሱ አጥንት አይሰበርም የሚል የመፅሀፍ ቃል እንዲፈፀም ነው ፡፡”
ሙሴ ይህን ፅፎአል ፤ መዝሙረኛው ይህን ፅፎአል ፤ ዮሐንስ ይህን ፅፎአል ፡፡ ሁሉም ወደ እውነቱ ትክክለኛው የፋሲካ በግ የኢየሱስን ሚና በማሳየት እንደ ፋሲካ በግ አመለከቱ ፡፡ ለዚያ ነው እስራኤል በእያንዳንዱ አመት እንዲያከብር የታዘዘው ስለዚህ አይረሱትም ፡፡
ዘኁልቁ(9፡ 13-14)፡ አንድ ሰው ብቁ ከነበረ ፋሲካን ያከብር ነበር ፤ የተመረጠ ካላከበረ የሚጠፋ ይሆናል እናም የኃጢዓቱንም ዉጤት የሸከማል ፡፡ እንግዶች ከእስራኤላዊያን ጋር መሳተፍ ይችላሉ ተመሳሳይ ስርዓትና ትዕዛዝ ያድርጉ ፡፡
ዘኁልቁ(9፡ 15-23)፡ መቅደሱ ተተከለ ከዚያም ቀን ጀምሮ የምስክርነቱን ድንካን ደመናው ሸፈነው ፤ ደመናው በማታ እንደ ሚታይ እሳት ይሆናል ፤ ያለማቐረጥ በዚህ መንገድ አስታወሳቸው ፡፡ መቼም ቢሆን ዳመናው ሲነሳ እስራኤላዊያን ከመኖሪያቸው ይነሳሉ ከዚያም እስከሚቆም ድረስ ደመናውን ይከተላሉ ፡፡
በመቅደሱ ላይ ደመናው እሰከቆየ ድረስ ይሰፍራሉ ነገር ግን በተንቀሳቀሰ ጊዜ እግዚአብሄር እንዳዘዛቸው ይጎአዛሉ ፤ አንድ ምሽትም ይሁን፣ ሁለት ቀናትም ይሁን፣ አንድ ወር ወይም ከዚያ በላይ ቢሆንም ለሙሴ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት በእግዚአብሄር ትዕዛዝ ይሰፍራሉ ፣ ደመናው በተንቀሳቀሰ ጊዜ ይንቀሳቀሳሉ፣ ደመናው ከቆመ ደግሞ ይቆማሉ ፡፡
መዝጊያ
ደግሞ ደግሞ እግዚአብሄር እምነትን መሰረተ ፤ እነዚህ ጥቂቶቹ ምሳሌዎች ናቸው፡
ዘጸ (13፡ 21-22)፡ በቀን በደመና አምድ እና በሌሊት በእሳት አምድ በመገኘት እግዚአብሄር ከእስራኤላዊያን ጋር እምነትን(መተማመንን) መስርቶ ነበር ፡፡
ዘጸ (16፡ 1)፡ እምነት ከአንዱ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ የተመሰረተ ነበር ፤ እስራኤላዊያን ደግመው ደግመው እንደገና ተረድተውት፣ አይተውት እና የእግዚአብሄርን መገኘት ኖረውበት ነበር ፡፡
ዘጸ (33፡ 9)፡ ሙሴ ልክ እንደ እስራኤላዊያን ሳይሆን ደግሞ ደግሞ ለእርሱ በተናገረው በእግዚአብሄር ላይ የተደገፈ ነበር፣ እግዚአብሄር ተገልጦለታል ፡፡ ሁል ጊዜ የትም ብንሄድ ከእኛ ጋር ይሆናል ፡፡
መዝ (18፡ 9)፡ እግዚአብሄር በደመና መገለጡ የእግዚአብሄር መገኘት ወደ ምንሄድበት ሁሉ እንዳለ የሚያስደንቅ ምልክት ነው ፡፡
ማቴ (17፡ 5)፡ በአድስ ኪዳን እንካን በደመና በመሲሁ በኩል ለመልዕክቱ ህዝቡን ሲያዘግጁ የእግዚአብሄርን ንግግር ህዝቡ ለምደውታል ፡፡
ማቴ (24፡ 30)፡ ለእኛም ምልክት በደመና ይሆንልናል ! በዘኁ 9 እስራኤላዊያን የእግዚአብሄርን መገኘት ደመና በመከተል ቀን እና ማታ እንዲኖሩ ተነገሩ ፡፡ አሁን የሰው ልጅ “በደመና !” ሲመጣ እያየን ነው ፡፡
ይህ ሁላ ወደ ክርስቶስ መመለስ ያመለክታሉ ፤ ኢየሱስ በደመና እንደሄደ በደመና ተመልሶ ይመጣል (ሐዋ 1፡ 9-11)! ለመሲሁ ልንዘጋጅ እና ልንጠብቀው ያስፈልገናል (ራዕ 1፡ 7) ፡፡ ሁሉም አይኖች በህይወት የሚኖሩትም የሞቱትም ሁለቱም ያዩታል ፡፡ ሁሉም አይን….. ጥንዶች ወይም የተመረጠው ቡድን ብቻ አይደለም ነገር ግን ሁሉም አይን ! ለመመለሱ ልንከታተለው እና ልንጠብቀው ይገባናል ፡፡ የያዝናቸውን ነገሮች ያሉንን (መኪናዎች፣ ቤቶች፣ ቤተሰቦች ወ.ዘ.ተ) እናጣቸዋለን ፤ ለመሄድ መዘጋጀት ይጠበቅብናል ፡፡ ከእግዚአብሄር መንፈስ ለመስማት ዝግጁ መሆን እና ሁልጊዜ የመከታተል እሳቤ ሊኖረን ይገባል (ማቴ 24፡ 42) ፡፡
በዘኁ 9 እንዳሉት እንደ የሹዋ(ኢየሱስ) ተከታይ በመንፈስ ተሞልተን ዝግጁ መሆን ያስፈልገናል ደመናው በተጎአዘ ጊዜ የሚጎአዝ አለብን ፡፡ አምላካችን መቼ ተመልሶ እንደሚመጣ ስለማናውቅ ጠባቂ ሰው መሆን ያስፈልገናል ! መገኘቱን ለመከተል ዝግጁ እንሁን ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 174.
ጥያቄዎች
-
በዘኁ (9፡ 12) የጠቦቶቹን ምንም አጥንት አትሰበረው የሚለው ትዕዛዝ እንዴት ለክርስቶስ ጥላ ነው ? (ዘጸ12፡ 46; መዝ 34፡ 20; ዮሐ 19፡ 36)
-
በ 1ቆሮ (10፡ 1) “ ከደመና ስር ” ሆኑ ምን ማለት ነው ? (ዘኁ 9፡ 15-23)
-
እስራኤላዊያን እያንዳንዱ እርምጃቸውን እንዲመራቸው በደመና መልክ የእግዚአብሄርን ምሪት ይጠብቁ ነበር (ዘኁ 9፡ 15-23) ፤ እግዚአብሄር እርምጃዎቻችሁን ሲመራ በምን መንገድ(መንገዶች) ትረዱታላችሁ ? (መዝ 37፡ 23; ምሳ 16፡ 9)
-
በዘኁ 8-9 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 9:6-10a
“So they came to Moses and Aaron that same day and said to Moses, ‘We have become unclean because of a dead body, but why should we be kept from presenting the LORD’s offering with the other Israelites at the appointed time?’ Moses answered them, ‘Wait until I find out what the LORD commands concerning you.’ Then the Lord said to Moses, ‘Tell the Israelites...’”
ኦሪት ዘኁልቁ 8-9 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እስራኤላዉያን የመጀመሪያዉን ፋሲካ በግብፅ ምድር ካከበሩ በኃላ ሁለተኛዉን ፋሲካ በአመቱ ለማክበር ተዘጋጁ። ቅዱስ ጉባኤዉን እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸዉ መመሪያዎችን ከሰሙ በኃላ፥ የተወሰኑ ሰዎች ወደ ሙሴ ጥያቄዎችን ይዘዉ መጡ። ሙሴም እንዲያብራራላቸዉ ሲጠይቁት፥ እንዲህ ብሎ መለሰ፥ "እግዚአብሔር ስለ እናንተ የሚያዝዘውን እስክሰማ ድረስ ቈዩ።" ሙሴ በራሱ መንገድ ሊመልስላቸዉ ወይንም እግዚአብሔር እንዲህ ሊመልስ ይችላል ብሎ ሊነግራቸዉ ይችል ነበር። በዚያ ፈንታ ግን ሙሴ፥ ቆም አለና፥ እንዲጠብቁ ነገራቸዉ። ያን ጊዜ፥ ሙሴ ለእነዚህ ሰዎች እግዚአብሔር አምላክ መልስ እንደሚሰጣቸዉ በማመን እርግጠኛ ሆኖ ጠየቀ።
ዉሳኔ ለመወሰን የምትቸኩሉት ምን ያህል ጊዜ ነዉ? ወይም የጌታን ምክር ሳትፈልጉ እና ሳታዳምጡ፥ በህይወታችሁ ዉስጥ ላሉ ሰዎች መልስ የምትሰጡት ምን ያክል ጊዜ አለ? ሙሴ፥ በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታ ዉስጥ ስንሆን ከሁሉም አስቀድመን ጌታን መፈልግ እንጂ፥ ምክር እና መልስ ለመስጠት መቸኮል እንደሌለብን የሚያሳይ ጥሩ አብነት ነዉ። እንደ አማኛ ሁልጊዜ ሊመክርህ ቅርብ የሆነ፥ በውስጥህ የሚኖር መንፈስ ቅዱስ አለህ። ይህንን ዛሬ በራስህ ህይወት ተመላለስበት! ጌታም በመንገዶችህ ሁሉ እንዴት እንደሚመራህ ተመልከት!
"በሞተ ሰው ሬሳ የረከሱ ሰዎችም ነበሩ፥ ስለዚህም በዚያ ቀን ፋሲካን ያደርጉ ዘንድ አልቻሉም። በዚያም ቀን ወደ ሙሴና ወደ አሮን ቀረቡ። እነዚያም ሰዎች፦ በሞተ ሰው ሬሳ ረክሰናል፤ በእስራኤል ልጆች መካከል በጊዜው ቍርባን ለእግዚአብሔር እንዳናቀርብ ስለ ምን እንከለከላለን? አሉት። ሙሴም፦ እግዚአብሔር ስለ እናንተ የሚያዝዘውን እስክሰማ ድረስ ቈዩ አላቸው። እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ከእናንተ ወይም ከትውልዶቻችሁ ዘንድ ሰው በሬሳ ቢረክስ፥ ወይም ሩቅ መንገድ ቢሄድ፥ እርሱ ደግሞ ለእግዚአብሔር ፋሲካን ያድርግ።"
ኦሪት ዘኁልቁ 9:6-10
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 32:8፦ "አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።"
የዮሐንስ ወንጌል 14:26፦ "አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ እርሱ ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።"
የያዕቆብ መልዕክት 1:5፦ "ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 78
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።