Offerings from the Leaders
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በጠቅላላው ሳምንት ውስጥ ዘሌዋውያን በመጨረሽ እና ዘኁልቁን በመጀመር ይህ አድርጋችሁታል ፤ እግዚአብሄር በስሞችና በቁጥሮች እቅድ አለው ፡፡ በዘኁ 6 ስለ ናዝራዊ ስለት አውርተናል ፤ በዘኁ 1 በእያንዳንዱ ነገድ 20 አመትና ከዚያ በላይ የሆናቸውን ወንዶች በመጀመሪያው በእስራኤል ጦር እንዲዋጋ እንዲዘጋጁ ቁጥራቸውን እንዲቆጥሩ እግዚአብሄር 12 ሰዎች አስነሳ ፡፡ እግዚአብሄር የቀዓትዋዊያንን፣ የጌድሶዋዊያንና ሜራሪያዊያን እና ካህናቱ ሙሴና አሮን በመቅደሱ የእግዚአብሄርን መገኘት እንዲለምዱ እስራኤል ለመፍቀድ ይህን የሌዊን ነገድ ተመለከተ ፡፡
ትምህርት
ዘኁልቁ(7፡ 1-3)፡ ሙሴ የመቅደሱን ተከላ በጨረሰ ጊዜ መቅደሱንና ሁሉንም እቃዎቹን ከመሰዊያው እና ከእቃዎቹ ጋር ቀባም ቀደሰም ፡፡ ወደ ዘጸ(40፡ 17) ተመልሰን ስናጣቅስ በደንብ ዝርዝር ይሰጠናል፡ “ እንዲህም ሆነ በሁለተኛው አመት በፊተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን ማደሪያው ተተከለ ፡፡” በዚህ ጊዜ የእስራኤል መሪዎች የዘሮቻቸው ቤቶች ሹመኞች መስዋዕት አቀረቡ ፤ ምዝገባውን የሚቆጣጠሩ የጎሳ መሪዎች ነበሩ (ቁጥር 1-2) ፡፡ 6 የተሸፈኑ ሰረገላዎች እና 12 በሬዎች አንድ ሰረገላ ከሁለት መሪዎች እና አንድ በሬ ከእያንዳዳቸው አመጡ በመቅደሱም ፊት በስተ ምስራቅ በኩል አቀረቡአቸው ፡፡
ዘኁልቁ(7፡ 4-6)፡ በእግዚአብሄር ትዕዛዝ ለመገናኛ ድንካኑ ስራ ለመጠቀም ሙሴ እነዚህን መስዋዕት ተቀበለ ፤ የመገናኛ ድንካኑ ለማገልገል እንደ ፍላጎታቸው መሰረት ለሌዋዊያን አሰራጫቸው ፡፡
ዘኁልቁ(7፡ 7-9)፡ ሙሴ ጌድሶናዊያንን ሁለት ሰረገላ እና አራት በሬዎች ሰጣቸው ፡፡ ጌድሶናዊያንን ጨርቆስን እና መሸፈኛዎችን አጎአጎአዙ ፤ ይህን እቃ ለመሸከም የተሸፈኑ ሰረገላዎች እና በሬዎች ያስፈልጉአቸዋል ፡፡ ሙሴ ሜራሪያዊያን 4 ሰረገላዎችና 8 በሬዎች ሰጣቸው ፤ ሁሉንም የመዋቅር ስራ አጎአጎአዙ ፤ ምናልባትም በጣም የበዛ እቃ ያጎአጉዛሉ ስለዚህ ብዙ ሰረገላዎች እና በሬዎች አስፈለጉአቸው ፡፡ ሙሴ ለቀዓትዋዊያን ምንም አልሰጣቸውም ፤ ንዋይ ቅድሳትን ጥንቃቄ አደረጉ በዚህም በተካሻቸውም የሚሸከሙ ነበሩ ፡፡ እግዚአብሄር የመቅደሱን ጥንቃቄ እንዲወስዱ ሌዋዊያንን የሚያስፈልጋቸውን ሰጣቸው ፡፡
ዘኁልቁ(7፡ 10-11)፡ መሪዎቹ ለመሰዊያው በተቀባበት ጊዜ የመታሰቢያነት ስጦታ አቀረቡ ፤ የመሰዊያውን ለመታሰቢያነት ከእያንዳንዱ ነገድ እያንዳንዱ ቀን አንድ መሪ መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡ 12 የጎሳ መሪዎች ስለነበሩ የመስዋዕት ማቅረቢያ ቀኖች 12 ነበሩ ፡፡
ዘኁልቁ(7፡ 12-17)፡ በመጀመሪያው ቀን ከይሁዳ ነገድ የአሚናዳብ ልጅ ነአሶን መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡ በዘኁ(2፡ 3) በመቅደሱ ዙሪያ ቦታ በመጀመሪያ የተመረጠው የይሁዳ ነገድ ነበር ፡፡ ነአሶን ሰዎስት ሙሉ አንድ አራተኛ ፓውንድ የሚመዝን አንድ የብር ሳህን እና አንድ ሙሉ ሰዎስት አራተኛ የሚመዝን ጎድጎአዳ ሳህን አመጣ ለእህል መስዋዕት ሁለቱንም በዘይት በተለወሰ ልም ዱቄት የተሞላ ነበር (ቁጥር 13) ፡፡ አራት ትንሽ መጠን የሚመዝን አንድ የወርቅ ሳህን በእጣን የተሞላ አመጣ (ቁጥር 14) ፤ ለሚቃጠል መስዋዕት አንድ ወይፈን፣ አንድ በግ እና አንድ አመት የሞላው አንድ ወንድ ጠቦት(ቁጥር 15) ፤ ለኃጢዓት መስዋዕት አንድ ወንድ ፍየል (ቁጥር 16) ፤ ከዚያም ለደህንነት መስዋዕት ሁለት በሬዎች፣ አምስት ወጠጤ በግ፣ አምስት ወንድ የሚራቡ ፍየሎች እና አንድ አመት የሞላቸው አምስት ወንድ ጠቦቶች አመጣ(ቁጥር 17) ፡፡ በጠቅላላ ነአሶስ 21 እንስሳቶችን አመጣ ፡፡
ከጎሳ መሪዎች ይህ የመጀመሪያ ቀን መስዋዕት ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(7፡ 18-83)፡ የቀሩት 11 የጎሳ መሪዎች በእነዚህ ቀናት ተመሳሳይ መስዋዕት አቀረቡ ፤ ሙሴ በዘኁ 2 በመቅደሱ ዙሪያ 12 ነገዶች ማስቀመጡን እንደገለፀው ይህ ተመሳሳይ ለውጥ(አካሄድ) ነበር ፡፡
- ቀን 2፡ የይሳኮራዊያን መሪ ናትናኤል መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡
- ቀን 3፡ የዛብሎናዊያን መሪ ኤልያብ መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡
- ቀን 4፡ የሮቤላዊያን መሪ ኤሊሱር መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡
- ቀን 5፡ የስምዖናዊያን መሪ ስለሚኤል መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡
- ቀን 6፡ የጋድአዊያን መሪ ኤሊሳፍ መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡
- ቀን 7፡ የኤፍሬማዊያን መሪ ኤሊሳማ መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡
- ቀን 8፡ የምናሴያዊያን መሪ ገማልኤል መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡
- ቀን 9፡ የብናሚያዊያን መሪ አቢዳን መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡
- ቀን 10፡ የዳናዊያን መሪ አኪኤዘር መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡
- ቀን 11፡ የአሴራዊያን መሪ ፋግኤል መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡
- ቀን 12፡ የንፍታሌማዊያን መሪ አኪሬ መስዋዕቱን አቀረበ ፡፡
ስሞቻቸው በሚያስደንቅ ጠቃሚዎች ነበሩ ምክንያቱም እግዚአብሄር የሁሉንም እስራኤላዊያን ስሞች እንደሚያውቅ ያሳያቸዋል ፤ በተመሳሳይ መንገድ ዛሬም እግዚአብሄር የሁሉንም አማኝ ስም ያውቃል ፡፡ የእነዚህን መፅሀፍ ጥቅሶችን እገዛ ተመልከቱ፡
ዮሐ(10፡ 3)፡ “ ለእርሱ በረኛው ይከፍትለታል ፤ በጎቹም ድምፁን ይሰሙታል የራሱንም በጎች በየስማቸው ጠርቶ ይወስዳቸዋል ፡፡” እግዚአብሄር ስማችሁን እንደሚያውቀው አምናለሁ ፡፡
ሉቃ(10፡ 20)፡ “ ነገር ግን መናፍስት ስለተገዙላችሁ በዚህ ደስ አይበላችሁ ስማችሁ ግን በሰማያት ስለተፃፈ ደስ ይበላችሁ ፡፡ “ ስማችን በሰማያዊ መዝገብ ተመዝግቦአል ፡፡
ፊል(4፡ 3)፡ “ አንተም ደግሞ በስራዬ አብረህ የተጠመድህ እውነተኛ ሆይ እንድታግዛቸው እለምንሀለሁ ፤ ስሞቻቸው በሕይወት መፅሀፍ ከተጻፉት ከቀሌምንጦስና ደግሞ ከእኔ ጋር አብረው አብረው ከሰሩት ከሌሎች ጋር በወንጌል ከእኔ ጋር አብረው ተጋድለዋልና ፡፡” በህይወት መፅሀፍ ስማችን ተፅፎአል ፡፡
1ቆሮ(10፡ 4)፡ “ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ አለት ጠጥተዋልና ያም አለት ክርስቶስ ነበር ፡፡ “ ወደ ህይወት መፅሀፍ ያስገባን ያ አለት ነው ፡፡
በ 2ሳሙ 23 ዳዊት የጠንካራ ሰዎቹን ስም ዘርዝሮአል ምክንያቱም እያንዳንዳቸው ለእሱ ጠቃሚዎች ነበሩ ፡፡
በሮሜ 16 ሐዋሪያው ጳውሎስ በአገርግሎቱ የረዱትን የ26 ሰዎችን ስም መዝግቦአል ፡፡
እያንዳንዱ ሰው ለእግዚአብሄርና ለስራው ጠቃሚ ነው ፡፡ የሆኑን ሰዎች ስም ካላስተዋሳችሁ ጠይቁአቸው ፤ ስሞች ጠቃሚ ናቸው ስለሆነም የሆኑ ሰዎችን በስማቸው ስትጠሩአቸው ዋጋ እናዳላቸው እንዲሰማቸው ያደርጋቸዋል ፡፡
ዘኁልቁ(7፡ 84-88)፡ ሁሉንም 12 ቀናቶች በወሰዳችሁ ጊዜ የመታሰቢያ ስጦታው ከእስራኤል መሪዎች የተመጣጠነ ነበር፡
12 የብር ሳህኖች - እያንዳንዳቸው 3 ሙሉ አንድ ሰዎስተኛ ፓዉንድ ይመዝናሉ ፡፡
12 የብር ጎድጎአዳ ስህኖች - እያንዳንዳቸው 1 ሙሉ 3 አራተኛ ፓውንድ ይመዝናሉ ፡፡
12 የወርቅ ሳህኖች - እያንዳንዳቸው 4 28 ግራም ይመዝናሉ ፡፡
የብር እቃዎቹ ጠቅላላ 60 ፓውንድ ይመዝኑ ነበር፣ በመቅደሱ መለኪያ ሽቅል ተመዘኑ ፡፡
የወርቅ ሳህኖቹ ጠቅላላ ክብደት 3 ፓውንድ ነበር ፡፡
ለሚቃጠል መስዋዕት ሁሉም ከብቶች ከእህል መስዋዕታቸው ጋር በጠቅላላው12 በሬዎች፣ 12 ወጠጤዎች እና አንድ አመት የሞላቸው 12 ወንድ ጠቦቶች ነቸው ፡፡
ለኃጢዓት መስዋዕት 12 ወንድ ፍየሎች ፡፡
ለደህንነት መስዋዕት ሁሉም ከብቶች በጠቅላላው 24 በሬዎች፣ 60 ወጠጤዎች፣ 60 የሚራቡ ወንድ ፍየሎች እና አንድ አመት የሞላቸው 60 ወንድ ጠቦቶች ፤ ይህ ለመሰዊያው ከተቀባ ቦኃላ የመታሰቢያ ስጦታ ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(7፡ 89)፡ ሙሴ ከእግዚአብሄር ጋር ለማውራት ወደ መገናኛው ድንካን በገባ ጊዜ ከሁለቱ ኪሩቤል መሀከል በምስክርነቱ ታቦት ላይ ከነበረው ከስርየት መቀመጫው ላይ ለእርሱ የሚናገረውን ድምፅ ሰማ ፤ ይህ ሙሴ የፈፀመውን እግዚአብሄር ያፀደቀበት ነበር ፡፡
መዝጊያ
ማር(12፡ 42-44) የሚለው “ አንዲትም ድሀ መበለት መጥታ አንድ ሳንቲም የሚያህሉ ሁለት ናስ ጣለች ፡፡ ደቀ መዛሙርቱንም ጠርቶ እውነት እላችኃለሁ በመዝገብ ውስጥ ከሚጥሉት ሁሉ ይልቅ ይህቺ ድሀ መበለት አብልጣ ጣለች ፡፡ “
እግዚአብሄርን የምትሰጡትን በፍፁም መተው አትችሉም ፡፡ 2ቆሮ(9፡ 7) የተናገረው “ እግዚአብሄር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም ፡፡” አዚህ ቦታ ላይ እግዚአብሄር እንዳደረሳቸው ያዩና በጣም ደስተኛ የነበሩ ለጋስ ሰዎችን አይቻለሁ ፡፡በዘኁ 7 “ እሺ እግዚአብሄር ያንተ ነው” ብለው የተናገሩ ለጋስ ህዝብ አይቻለሁ ፡፡
ጥያቄዎች
-
በዘኁ (7፡ 2-3) 12 ነገዶች የመጀመሪያ ስጦታቸዉን አመጡ፡ በሬዎች እና ሰረገላዎች ፤ እነዚህ ወደ ሌዋዊያን ክፍል ተሰራጩ ፡፡ ለምንድን አንዳንድ ሌዋዊያን ከሌሎች የሚበልጥ ተቀበሉት ? ቀዓትዋዊያን ምንም ነገር ለምን አልተቀበሉም (ዘኁ 7፡ 9) ? ይህ እንዴት የእግዚአብሄር ስጦታ ስዕል ነው ?
-
የስጦታ 12 ቀናቶች ምንድን ነበሩ ? እያንዳንዱ ነገድ ተመሳሳይ ስጦታ ለምን እንደሰጡ ምን ታስባላችሁ ? የእነዚህ መስዋዕቶች አላማቸው ምንድን ነበር ?
-
በዘኁ 7 የእስራኤላዊያን ለጋስነት ስጦታ እና በሐዋ (4፡ 32-35) እና በማር(12፡ 42-44) ስጦታ መሀከል ምንድን ተመሳሳይነት ማዉጣት እንችላለን ? ያን በተመለከ እግዚአብሄር ደስተኛ ሰጪዋችን ይወዳል(2ቆሮ 9፡ 7) በእግዚአብሄር በተጠየቀ ጊዜ ሁል ጊዜ በፍቃደኝነትና በለጋስነት እንሰጣለን ?
-
እግዚአብሄር የሚሰጡትና እና በትክክል ያቀርቡት የነበረው የእያንዳንዱን ሰው ስም ማወቁ ለምን ነበር ጥቅሙ ? የሐ (10፡ 3) የሚያወራው መልካም እረኛ በጎቹን በስማቸው ይጠራቸዋል ፤ እግዚአብሄር ስማችሁን በማዎቁ እንዴት እንዲሰማችሁ ያደርጋል ? ከሌሎች ጋር ይህን እውነት እንዴት ማጋራት ትችላላችሁ ?
-
ሙሴ ከእግዚአብሄር ጋር ተገናኘ ከስርየት መቀመጫው ላይ ድምፁን ሰማ (ዘኁ 7፡ 89) ፤ ከእግዚአብሄር መስማት እንዴት ለእኛ ያስፈልጋል ? በጣም በግልፅ ድምፁን የምንሰማባቸው ጥቂጥ መንገዶች ምንድን ናቸው ?
-
በዘኁ 7 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 7:4-5
“The LORD said to Moses, ‘Accept these from them to be used in the work of the tent of meeting, and give this offering to the Levites, to each division according to their service.’”
መስዋዕት(ቁርባን) ከመሪዎች
ኦሪት ዘኁልቁ 7 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
ሙሴ የመገናኛ ድንኳኑን አስተካክሎ ከጨረሰ በኃላ ከማስዋቢያዉ፣ መስዋዕት ከሚቀርብበት ስፍራ እና ከቤተ-መቅደስ እቃዎች ጋራ ዘይት በመቀባት ቀድሶታል። ከዚህም በኃላ የእስራኤል አለቆች በመገናኛዉ ድንኳን ፊት ለፊት ቁርባናቸዉን አቀረቡ። እግዚአብሔር ሙሴን ይህንን ቁርባን እንዲቀበል አዘዘዉ። ከዚያም ይህ ቁርባን ለተለየ ዓላማ እንዲዉል ትዕዛዝን ሰጠዉ። በመጨረሻም ሙሴ ቁርባኑን ለተለዩ ሰዎች ሰጠዉ።
እግዚአብሔር አምላክ ስለ ቁርባን አቀባብል ስርዓት ምሳሌ የሆነ ነገር አሳየ። ከእርሱ ስጦታን በምንቀበልበት ጊዜ ልናስበዉ የሚገባ ትልቅ ምሳሌነት ነዉ። እግዚአብሔር አምልክ አንድ ነገር እንዲሰጥህ ካደረገ ተቀበለዉ። እንዴት መጠቀም እንዳለብህ እንድታዉቅ፥ ለምን እንደሰጠህ የልቦናህን አይኖች ከፍተህ ተመልከት! እናም ለሌላ ሰዉ አሳልፈህ መስጠት ያለብህ ነገር ካለ ደግም ሳታወላዉል አድርገዉ! አስታዉስ፥ ፍፁምና በጎ በረከት ሁሉ ከጌታ ዘንድ ናቸዉ! ዛሬ፥ ስለእግዚአብሔር መልካምነት አመስግን!
"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለመገናኛው ድንኳን ማገልገል ይሆን ዘንድ ከእነርሱ ተቀብለህ ለሌዋውያን ለእያንዳንዱ እንደ አገልግሎታቸው ስጣቸው።"
ኦሪት ዘኁልቁ 7:4-5
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 84:11፦ "እግዚአብሔር አምላክ ምሕረትንና እውነትን ስለ ወደደ፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም።"
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9:8-9፦ "በተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።"
- የያዕቆብ መልዕክት 1:17፦ "በጎ ስጦታ ሁሉ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው፥ መለወጥም በእርሱ ዘንድ ከሌለ በመዞርም የተደረገ ጥላ በእርሱ ዘንድ ከሌለ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 77
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።