The Pentateuch Numbers

The Nazirite Vow

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 5-6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 76 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የእኛ አላማ እነዚህን ክፍሎች መውሰድ እንድንችል እና ለሌላ አካል ለመናገር ነው ፡፡ ዘፍጥረት በመውሰድ ለሌላ አካል መናገር “ ዘሩን ክርስቶስን ታውቁታላችሁ በዘፍጥረት ውስጥ አለ ?” ወይም “በዘኁልቁ ክርስቶስ አለት እንደሆነ ታውቃላችሁ ?” ለዘኁልቁ አለት እንዴት ነው ቃል የሚሆነው ? በ 1 ቆሮ (10፡ 3-4) ጳውሎስ የተናገረው “ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ አለት ጠጥተዋልና ያም አለት ክርስቶስ ነበር ፡፡”

ትምህርት

ዘኁልቁ 5 በተለየ የሚገልፀው እስራኤላዊያን እንዴት ከእርኩስ ሰዎች ጋር እንደሚግባቡ ነው ፤ ቁጥር (2-3) የሚናገረው ማንም በመኖሪያቸው የቆዳ በሽታ፣ ፈሳሽ የነበረበት ወይም በሬሳ የረከሰ ከመኖሪያቸው ዉጪ ይላካል፡፡ ከዚያም ዘኁ 5 መጨረሻው ላይ እስራኤላዊያን እንዴት የዝሙት ሁኔታዎችን እንደሚፈቱ ተነገራቸው ፡፡ ዘኁልቁ ለኑሮአችን ትክክል ይናገራል ፤ ለዛሬ መተግበር ይቻላል ፡፡ ዘኁ 6 ስለ ስለት ነው ፤ ሀሪሰን የተናገረው “ ስለት ሰው ወይም ንብረት በተቀደሰ ግንኙነት ከተገቢው የህግ ፍላጎት ዉጪ የቆመ ለእግዚአብሄር ይቀመጣል ፡፡“ ስለት የአስሩ ትዕዛዛት ወይም የ613 የአይሁድ ህጎች አካል አልነበረም ፡፡ ዌንሀም የተናገረው ስለት ማድረግ ትዕዛዝ አልነበረም ነገር ግን እግዚአብሄርን በሚወድ እን ከእግዚአብሄር የሆነ ነገር በሚፈልግ ሰው ልቦች ውስጥ የተፈጥሮ ፍላጎት ነበር፡፡

ዘኁልቁ(6፡ 1-8)፡ እግዚአብሄር ሙሴን የተለየ ስለት ለእግዚአብሄር ናዝራዊነት ስለት ለሚያደርጉ ለወንድ እና ለሴት ትዕዛዝ ሰጠው ፤ ናዝራዊ ማለት “ መለየት” ማለት ነው ፡፡ የሆነ አካል የተለየ ስለት ካደረገ ራሳቸውን ከእየዕለት እንቅስቃሴ ይለዩ ነበር ፤ የሆነ ሰው ናዝራዊነት ስለት ካደረገ ከወይን፣ ከቢራ፣ ከወይን ጁስ፣ ከወይኖች እና ከዘቢቦች መታቀብ ይጠበቅበታል ፡፡ ናዝራዊ ከነበረ ከወይን ፍሬ የሚመጣውን ማንኛውንም ነገር መብላት አይችልም ዘሩን ወይም ቆዳውን እንካን አይችልም ፡፡ በመቀደሻ ጊዜው ፀጉሩን መቆረጥ አይችልም በተጨማሪም በሞተ አካል አጠገብ መሄድ የተከለከለ ነበር ፡፡ ለናዝራዊነት ስለት መስፈርቶች ለታላቁ ካህን ከነበሩት ጋር ተመሳሳይ ነበር ፤ ሁለቱም ናዝራዊ እና ታላቅ ካህን ከልማድ እራሳቸውን ለብቻቸው እንዲለዩ ተጠሩ ፡፡ ዘሌ(10፡ 9) የታላቁን ካህን ያደርሳል “እንዳትሞቱ ወደ መገናኛው ድንካን ስትገቡ አንተና ልጆችህ የወይን ጠጅና የሚያሰክር ነገር ሁሉ አትጠጡ ፤ ይህም ለልጅ ልጆቻችሁ የዘላለም ስርዓት ይሆናል ፡፡” ለታላቁ ካህን ፀጉራቸውን እንዳይቆረጡ የት እንደተናገረ እስካሁን አላየሁም ፤ ዘሌ(21፡ 11-12) መላጣ ካህናት ከሞተ ሰዎች አጠገብ የሚሄድ ወይም ራሳቸውን ርኩስ ያደርጋሉ ፡፡ ዛሬ የ40 ቀን ፆም ከናዝራዊነት ስለት ጋር በማነፃፀር ውስጥ እንሄዳለን ፤ ከእግዚአብሄር ጋር የጠለቀ ግንኙነት ለመለማመድ በኃይለኛ(በፅኑው) መሄድ የሆነ ነገር አለው ፡፡

ዘኁልቁ(6፡ 7-12)፡ በመለየት ጊዜው ራሱን ማርከስ አይችልም የቤተሰብ አባል እንካ ቢሞት(ቁጥር 7-8) ፤ የኃይለኛው ጊዜ በመሀል እግዚአብሄር ስለቱን ለመቀበል የእግዚአብሄር ሰውን ያነሳዋል ፡፡ መሳ(13፡ 1-5) የሚገልፀው የእግዚአብሄር መልዓክ ለማኑሄ እና ለሚስቱ ስለሚወልዱት ወንድ ልጅ ሊነግራቸው ተገለጠላቸው ፤ “ እነሆ አንቺ መካን ነሽ ልጅም አልወለድሽም ፤ ነገር ግን ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ፡፡ አሁንም ተጠንቀቂ የወይን ጠጅን የሚያሰክርም ነገር አትጠጪ ርኩስም ነገር አትብዪ ፡፡ እነሆ ትፀንሻለሽ ወንድ ልጅም ትወልጃለሽ ልጁም ከእናቱ ማህፀን ጀምሮ ለእግዚአብሄር የተለየ ናዝራዊ ይሆናል በራሱም ላይ ምላጭ አይድረስበት ፤ እርሱም እስራኤልን ከፍልስጤማዊያን እጅ ማዳን ይጀምራል “(መሳ 13፡ 3-5) ፡፡

ሳምሶን እግዚአብሄር ለናዝራዊ ስለት እንዲሆን የጠራው ሰው ነበር ፡፡

ናዝራዊ ራሱን ከማንኛውም ሌላ ሰው ራሱን ይለያል ነገር ግን በትእቢት መንገድ አይደለም ከዚያም ራሱን ለእግዚአብሄር ይሰጣል ፡፡ የሆነ ሰው በድንገት አጠገቡ ከሞተ ናዝራዊው በድንገተኝነት ይረክሳል ስለሆነም በሰባተኛው ቀን ራሱን ይላጫል ፤ በስምንንተኛው ቀን መገናኛው ድንካን ጋር ለካህኑ ሁለት ዋኖስ ወይም እርግቦች ያመጣል ፤ ካህኑ አንዱአን እንደ ኃጢዓት መስዋዕት እና ሌለኛውን እንደ ሚቃጠል መስዋዕት ያቀርባል ፡፡ ይህ ለናዝራዊ (ማሳሰቢያ ርኩስ ሰው ናዝራዊ ስያሜ አልነበረም) በሞተ አካል መገኘት ውስጥ ለሆነ ስርየትን ያደርጋል ፡፡ በዚያ ተመሳሳይ ቀን ናዝራዊ እንደገና ራሱን ይቀድሳል ከዚያም ለእግዚአብሄር የመቀደሻ ጊዜውን መልሶ ያቀርባል ፤ በመቀጠልም አንድ አመት የሞላው ጠቦት እንደ ካሳ መስዋዕት ያመጣል ፡፡ የበፊቱ የመቀደሻ ጊዜ አይቆጠርም ፤ ሁሉንም አንደገና መጀመር አለበት (ዘኁ 6፡ 12) ፡፡

ዘኁልቁ(6፡ 13-21)፡ ከዚያም ለእግዚአብሄር መስዋዕት ለማቅረብ ናዝራዊው ወደ መገናኛው ድንካን መግቢያ ይመጣል፡ እንከን የሌለበት የአንድ አመት ወንድ ጠቦት እንደ ሚቃጠል መስዋዕት፣ እንከን የሌለባት የአንድ አመት ሴት ጠቦት እንደ ኃጢዓት መስዋዕት፣ እንከን የሌለበት በግ እንደ ደህንነት መስዋዕት፣ ከእህል መስዋዕት ጋር ፣ የመጠጥ መስዋዕት፣ አንድ ሌማት ያልቦካ ቂጣ እና በዘይት የተለወሰ ያልቦካ ስስ ቂጣ (ቁጥር 14-15) ፡፡ ካህኑ እነዚህን ለእግዚአብሄር ያቀርባል ከዚያም የናዝራዊን የኃጢዓት መስዋዕትና የሚቃጠል መስዋዕት ይሰዋለታል (ቁጥር 16) ፡፡ ካህኑ እንደ ደህንነት መስዋዕት በግ፣ በጋራ በሌማት ዳቦ፣ የእህል መስዋዕት እና የመጠጥ መስዋዕረት ያቀርባል (ቁጥር 17) ፡፡ ናዝራዊው ወደ መገናኛው ድንካን መግቢያ ላይ ራሱን ይላጫል ከዚያም እንደ ህብረት መስዋዕት ፀጉሩን በእሳቱ ላይ ያስቀምጠዋል (ቁጥር 18) ፡፡ ካህኑ የተቀቀለውን የበጉን ወርች፣ አንድ ያልቦካ ቂጣ እና አንድ ያልቦካ ስስ ቂጣ ይወስዳል ከዚያም ፀጉሩን ከተላጨ ቦኃላ በናዝራዊው እጅ ውስጥ ያስቀምጠዋለወ (ቁጥር 19) ፤ ካህኑ በእግዚአብሄር ፊት እንደ ውዝዋዝ መስዋዕት ይወዘውዘዋል ፤ ለካህኑ የመስዋዕቱን ፍርምባ እና የስጦታውን ጭን በመጨመር ቅዱስ ድርሻው ነበር (ቁጥር 20) ፡፡ ሰለቱን በመፈፀም ናዝራዊው አሁን ወይን መጠጣት ይችላል (ቁጥር 20) ፡፡ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁሉም ሰው በናዝራዊ ስለት በኩል መሄድ እንዳለባቸው አስባለሁ ፡፡ የናዝራዊ ስለት ለእኔ በምንድን ይመስለዋል ?

የመፅሀፍ ቅዱስ ሌሎች ሰዎች በናዝራዊ ስለት በኩል የሄዱ፡

መጥምቁ ዮሐንስ፡ ሉቃ(1፡ 13-17) በጠቅላላ ህይወቱ ናዝራዊ እንዲሆን ለመጥምቁ ዮሐንስ የእግዚአብሄርን እቅድ ይገልፃል ፤ “ መልአኩም እንዲህ አለው ዘካሪያስ ሆይ ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ ሚስትህ ኤልሳቤጥም ወንድ ልጅ ትወልድልሀለች ስሙንም ዮሐንስ ትለዋለህ ፡፡ ደስታና ተድላም ይሆንልሀል በመወለዱም ብዙዎች ደስ ይላቸዋል ፡፡ በጌታ ፊት ታላቅ ይሆናልና የወይን ጠጅና የሚያሰክር መጠጥ አይጠጣም ፤ ገናም በእናቱ ማህፀን ሳለ መንፈስ ቅዱስ ይሞላበታል ፤ ከእስራኤልም ልጆች ብዙዎችን ወደ ጌታ ወደ አምላካቸው ይመልሳል ፡፡ እርሱም የተዘጋጁትን ሕዝብ ለጌታ እንዲያሰናዳ የአባቶችን ልብ ወደ ልጆች የማይታዘዙትንም ወደ ጸድቃን ጥበብ ይመልስ ዘንድ በኤልያስ መንፈስና ኃይል በፊቱ ይሄዳሉ ፡፡”

ጳውሎስ፡ ሐዋ(18፡ 18) ጳውሎስ የናዝራዊነት ስለት እንዳደረገ ይገልፃል ፤ “ ከዚህም ቦኃላ ጳውሎስ እጅግ ቀን ተቀምጦ ወንድሞቹንም ተሰናብቶ በመርከብ ወደ ሶሪያ ሄደ ፤ ስለትም ነበረበትና ራሱን በክንክራኦስ ተላጨ ፤ ጵርስቅላና አቂላም ከእርሱ ጋር ነበሩ ፡፡”

ለእግዚአብሄር ስለት ማድረግ እና መጠበቅ ያለውን ጥቅም የሚገልፁ ሌላ ጥቅሶች፡

  • ምሳ(20፡ 25)፡ “ ሰው በችኮላ ፡፡ለእግዚአብሄር የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል ከተሳለም ቦኃላ ቢፀፀት ወጥመድ ነው ፡፡”
  • ሉቃ(14፡ 28) የሚለው ስለት ከማድረጋችን በፊት ዋጋውን መቁጠር አለብን፡ “ ከእናንተ ግንብ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ከሳራውን የማይቆጥር መነው ?
  • መክ(5፡ 4-5) የሚለው ያደረግነውን ስለት መፈፀም አለብን፡ “ ሰነፎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሄር ስእለት በተሳልህ ጊዜ ትፈፅመው ዘንድ አትዘግይ ፤ የተሳልኸውን ፈጽመው ፡፡ ተስለህ የማትፈጽም ብትሆን ባትሳል ይሻልሀል ፡፡”
  • ዮና(2፡ 10)፡ “ እኔ ግን በምስጋና ቃል እሰዋልሀለሁ ፤ የተሳልሁትንም እከፍላለሁ ፡፡ ደኅንነት ከእግዚአብሄር ዘንድ ነው ፡፡”
  • መዝ(22፡ 25) የተናገረው ስለት ካደረግን ልናከብረው ይገባል ምክንያቱም እግዚአብሄርን ስለምንፈራ፡ “ በታላቅ ጉባኤ ምስጋናዬ ከአንተ ዘንድ ነው ፡፡ እርሱን በሚፈሩት ፊት ስእለቴን እሰጣለሁ ፡፡ “
  • 1ቆሮ(9፡ 19-23) ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነት እንዲኖረው ጳውሎስ የተመለከተውን አደረገ ስለዚህ ሎሌችም ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነት እንደሚኖራቸው ይገልፃል ፡፡

መዝጊያ

ከስለቱ ሃላ ያለው ልብ በጊዜው እግዚአብሄርን በብዙ የመልመድ ፍላጎት ነው ስለዚህ ሌሎችም ወንጌልን መለማመድ ይችላሉ ፡፡ ሰዎች ስለት ባደረጉ ጊዜ ስለቱነን ለሚቀበለው እና ለእግዚአብሄር መንግስት ጥቅሞች አሉት ፤ የናዝራዊነት ስለት ጥቅሙን ለተረዳው ለማንኛውም የስለቱ ዋጋ( በተጨባጭነት ስለ ወይን ወይም ስለ ፀጉር መቆረጥ አይደለም) የቤት ኑሮ ነው ፡፡ በተለየ ለመስራት የምትፈልጉት ምንም ነገር ካለ ለእግዚአብሄር በማውራት አሳዩት የጠለቀ፣ የቀረበ ግንኙነት ከእርሱ ጋር ይኖራችኃል ስለዚህ ከእርሱ በግልፅ መስማት ትችላላችሁ ከዚህም የተነሳ ሌሎች ከወንጌል በትልቁ መጠቀም ይችላሉ ፡፡

  1. R. K. Harrison, Tyndale Old Testament Commentary: Leviticus (Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1980), p. 235; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Leviticus, p. 219; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/leviticus.pdf

  2. Gordon J. Wenham, New International Commentary on the Old Testament: The Book of Leviticus (Grand Rapids: Wm. B. Eerdmans Publishing Co., 1979), p. 337.

ጥያቄዎች

  1. በዘኁ 5፡ 2-3 እግዚአብሄር ሙሴን ሁሉንም ለምፃም፣ በአካሉ ላይ ፈሳሽ ያለበት ማንኛውንም ወይም በሞተ የረከሰን ማንኛውንም ከሰፈር ውጭ እንዲያስቀምጥ አዘዘው ፡፡ ይህን ለምን እንዳዘዘው ምን ታስባላችሁ ?
  2. በዘኁ(5፡ 15) የቅናት መስዋዕት ምን ማድረግን ይይዛል ? ይህ ለካህኑ ለምንድን ነበር የሚቀርበው ? የዚህ መስዋዕት ዉጤቱ ምንድን ነበር ? (ዘኁ 5፡ 27-28)
  3. አንድ የናዝረዊነት ስለት ባደረገ ጊዜ ወይን፣ ሆምጣጤ፣ ጠንካራ መጠጥ፣ የወይን ፍሬዎች ወይም የወይን ጁስ አለመውሰዳቸው ምንድን ነበር አላማው ? (መሳ 13፡ 5-7)
  4. በዘመናዊ ጊዜ የናዝራዊነት አይነት የሆነው ማን እንደሆነ ታስባላችሁ ? ወንዶች/ሴቶች ? ኢየሱስ ናዝራዊ መሆን እንደሚችል ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አይችልም ?
  5. ናዝራዊ መሆን የስለቶች ስለት ነው ፡፡ ለእግዚአብሄር ወይም ለሆነ ሰው እስካሁን ስዕለት አድርጋችሁ ታውቃላችሁ ? ያን ስለት መፈፀም ችላችሁ ነበር ? ለምን ወይስ ለምን አልፈፀማችሁም ?
  6. በዘኁ (6፡ 24-26) ማለትም ለእናንተ የክነት በረከት ምንድን ነው ? ቁጥር 27 ልክ እንደ ዘፍ (12፡ 3) ይናገራል ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  7. በዘኁ (5-6) በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Numbers 6:22-27

“The LORD spoke to Moses: ‘Tell Aaron and his sons how you are to bless the Israelites. Say to them: May Yahweh bless you and protect you; may Yahweh make His face shine on you and be gracious to you; may Yahweh look with favor on you and give you peace. In this way they will pronounce My name over the Israelites, and I will bless them.’”

የናዝራዊነት ስለት

ኦሪት ዘኁልቁ 5-6

የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

መሃላዎችን እና የንፅህና ህጎችን በተመለከተ ትዕዛዛት ከተሰጡ በኃላ፥ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር አቁሞ ረጅም ትንፋሽ የወሰደ ይመስላል። እግዚአብሔር አሁንም እንደገና፥ ለሙሴ፥ አሮንና ልጆቹ እስራኤላዉያንን እንዴት መባረክ እንዳለባቸዉ የሚያትት ህግጋትን ስጣቸዉ። ይህ የአሮን ቡራኬ፥ ከክፉ ነገር ጥበቃን፣ ሞገስን፣ ነፃ መዉጣትን፣ ተስፋን እና ሌሎች ብዙ ነገሮችን ያመጣል።

ከሌሎች ሰዎች ጋራ ምን አይነት ህብረት ሊኖረን እንደሚገባ እግዚአብሔር ጥሩ አብነት ይሆናል። በእያንዳንዱ ዝርዝር ነገር እና መዋቅር ዉስጥ እንኳ፥ አንዳንዴ ቆም በልና አጠገብህ ያሉ ሰዎች ስሜት ያላቸዉ መሆኑን ተገንዘብ። አንዳንዴ የህይወት ዉጣ ዉረድ ዉስጥ ተጠምደን ሰዎችን መባረክ እንዳለብን ቸል እንላለን። ዛሬ በየትኛዉም ስፍራ ብትሆን ለደቂቃ ቆም በልና አንድ ሰዉ በኢየሱስ ፍቅር ባርክ!

"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለአሮንና ለልጆቹ ንገራቸው፦ የእስራኤልን ልጆች ስትባርኩአቸው እንዲህ በሉአቸው፦ እግዚአብሔር ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ያብራልህ፥ ይራራልህም፤ እግዚአብሔር ፊቱን ወደ አንተ ያንሣ፥ ሰላምንም ይስጥህ። እንዲሁ ስሜን በእስራኤል ልጆች ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እባርካቸዋለሁ።"

ኦሪት ዘኁልቁ 6:22-27

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የዮሐንስ ወንጌል 1:16፦ "እኛ ሁላችን ከሙላቱ ተቀብለን በጸጋ ላይ ጸጋ ተሰጥቶናልና ሕግ በሙሴ ተሰጥቶ ነበርና፤"
  • 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9:11፦ "በእኛ በኩል ለእግዚአብሔር የምስጋና ምክንያት የሚሆነውን ልግስና ሁሉ እንድታሳዩ በሁሉ ነገር ባለ ጠጎች ትሆናላችሁ።"
  • ወደ ፊልጵስዩስ 2:4፦ "እያንዳንዱ ለራሱ የሚጠቅመውን አይመልከት፥ ለባልንጀራው ደግሞ እንጂ።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 76