The Pentateuch Numbers

Duties of the Kohathites, Gershonites and Merarites

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 4 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 75 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ተመልሰን ዘኁ 1 እንመልከት ፡፡ 12 ነገዶች እስራኤላዊያን ለምንድን ተቆጠሩ ? በውትድርና ለማገልገል ብቁ የሆኑትን ከ20 አመት በላይ የሆናቸውን ወንዶች መለየት ነበረባቸው ፡፡ ዛሬ በእስራኤል ጦር ሁለቱም ወንድም ሴትም ያገለግላሉ ነገር ግን በእስራኤል በዚያን ጊዜ ወንድ ብቻ አገለገለ ፡፡ ጠቅላላ ቆጠራው 603,550 ፡፡ ሌዋዊያን ከውትድርናው ነፃ ወጡ ፤ ቦታቸው በመቅደሱ ዙሪያ እና ከአሮንና ከልጆቹ ጎን መስራት ነበር ፡፡ ዘኁ 2 እያንዳንዱ ነገድ በመቅደሱ ዙሪያ የት እንደሚሰፍሩ ይናገራል ፤ ዘኁ 3 እንዴት አሮንና ካህኑ ከሌዋዊያን እንደ ሚለዩ ይገልፃል ፡፡ ሌዋዊያን የሁል ቀን ስራ ያደርጋሉ ምክንያቱም የእግዚአብሄር የበኩር ሰዎች ነበሩ ፡፡ ሁሉን ነገር ለአሮን፣ ለአልዓዛርንና ለኢታምር ያዘጋጃሉ ፤ ስለዚህ ለ40 አመታት አደረጉት !

የሜንዲን ስዕልን እወደዋለሁ፡ አለቱ፣ ደመናው፣ እግሮቹ፣ የእስራኤል አገር አበባ ፤ ይህ አለቱን ክርስቶስን ይወክላል፡፡ 1ቆሮ (10፡ 4) በበርሃ የኢየሱስን ሚናዎች ይገልፃል “ይከተላቸው ከነበረው ከመንፈሳዊ አለት ጠጥተዋልና ያም አለት ክርስቶስ ነበር ፡፡” ይህ የአለቱ ስዕል እንዲኖራችሁ እፈልጋለሁ ፡፡ ሁል ጊዜ እስራኤላዊያን እርምጃዎቻቸውን የሚያስቀምጡበት ያ አለት ክርስቶስ በበርሃ ደገፋቸው(ረዳቸው) ፡፡ ዛሬ በዘኁ 4 በብዙ ስለ ሌዋዊያን ሚና እናወራለን ፡፡

ትምህርት

ዘኁልቁ(4፡ 1-3)፡ በዚህ ጊዜ ሙሴ ምንም እንካን አሮን በሰዎስት አመት ቢበልጠውም መጀመሪያ ሰየመ ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን በመገናኛው ድንካን ላይ መስራት የሚችሉ እድሜአቸው ከ30 እስከ 50 አመት የሆናቸውን ቀዓትዋዊያንን እንዲቆጥር ነገረው ፤ ይህ በዘኁ( 3፡ 15) ከነበረው ቆጠራ ያም እያንዳንዱ ወንድ አንድ ወርና ከዚያ በላይ ከተቆጠሩበት ይለያል ፡፡ ዘኁ (8፡ 24) የሚናገረው “ የሌዋዊያን ህግ ይህ ነው ፤ ከ25 አመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት በመገናኛው ድንካን ስራ ያገለግሉ ዘንድ ይገባሉ ፡፡” በተጨማሪም የ 1ዜና(6፡ 2-3) ፀሀፊ የሌዋዊያንን ትውልድ አስቀምጦአል፡ “ የቀዓትም ልጆች ፤ እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮንና ኡዝኤል ፤ የእንበረምም ልጆች አሮን፣ ሙሴና ማሪያም ፡፡” አሮንና ሙሴ ከሌዋዊያን ነገድ ነበሩ ፡፡

ዘኁልቁ(4፡ 4-6)፡ መቼም ቢሆን የእስራኤላዊያን መኖሪያ ሲንቀሳቀስ ቀዓትዋዊያን በጣም ለቅዱስ ነገሮች ተጠያቂ(ኃላፊዎች) ነበሩ ፤ አልዓዛር የቀዓትዋዊያን ተቖጣጣሪ ነበር ፡፡ መጀመሪያ አሮንና ልጆቹ በመሸፈኝ መጋረጃ የምስክርነቱን ታቦት ይሸፍናሉ ከዚያም ከአቆስጣ ቆዳ ከተሰራ መሸፈኛ ይሸፍኑታል ከዚያም በመቀጠል በላዩ ላይ ሰማያዊ የሆነ መጎናፀፊያ ይዘረጋሉ ከዚያም ቐሚዎቹን በቦታቸው ያስቀምጣሉ ፡፡

ዘኁልቁ(4፡ 7-10)፡ በገበታው መገኛው ላይ ሰማያዊ ልብስ ይዘረጋሉ ከዚያም ሳህኖቹን፣ ጽዋዎቹን፣ ወጭቶችንና ጭልፋዎችን ለሚጠጣው መስዋዕትና ለህብስቱ መስዋዕት ያስቀምጣሉ ፤ በእነዚህም ላይ ቀይ ልብስ ይዘረጋሉ ከአስቆጣ ቆዳ ከተሰራ መሸፈኛ ይሸፍኑታል ከዚያምቐሚዎቹን በቦታቸው ላይ ያስቀምጣሉ ፡፡ ይህ እኛን በዘጸዓት ካሉት ትዕዛዞች ውስጥ በሰማያዊና በቀይ መቅደሱን መስራታቸውን ያስታውሰናል ፤ ቆይቶ ወደ ወይነጠጅ እንገባለን፡፡ ካህናቱ እንደ መቅደሱ ተመሳሳይ ቀለም ይለብሳሉ ፡፡ በሰማያዊ ልብስ የሚያበራውን መቅረዝ ቀንድሎችን፣ መኮስተሪያዎችን፣ የእሳት ማስቀመጫዎችንና የዘይቱን እቃዎች ይሸፍናሉ ከዚያም በመቀጠል እያንዳንዱን ነገር ከአስቆጣ ቆዳ ከተሰራው መሽፈኛ ላይ ያስቀምጡታል ከዚያም ቐሚዎቹን በቦታቸው ያስቀምጣሉ፡፡

ዘኁልቁ(4፡ 11-14)፡ መሰዊያውንና እቃዎቹን በሰማያዊ ልብስ ከሸፈኑ በኃላ በአስቆጣ ቆዳ ይጠቀልሉታል ከዚያም በሚሸከመው መዋቅር ላይ ያስቀምጡአቸዋል ፡፡ ከነሀስ መሰዊያው ላይ አመዱን ያስወግዳሉ፣ በላውም ላይ ሀምራዊ ልብስ ይዘረጋሉ፣ ሁሉንም እቃዎች ያስቀምጡበታል ከዚያም በመቀጠል በአስቆጣ ቆዳ ይሸፍኑታል ቐሚዎቹንም በቦታቸው በማስገባት ያስቀምጡአቸዋል ፡፡ እነዚህ ሁሉም ትዕዛዝ በጣም ጠቃሚዎች ነበሩ ፡፡ እያንዳንዳቸው የመገናኛ ድንካኑን በማጎአጎአዝ የሚጫዎቱት ጠቃሚ ሚና ነበራቸው ፡፡

ዘኁልቁ(4፡ 15-20)፡ አሮንና ልጆቹ ሁሉንም ቅዱስ ነገር ከሸፈኑ በኃላ ቀዓትዋዊያን ይሸከሙአቸዋል ፤ ነገር ግን ቀዓትዋዊያን ማንኛውንም ቅዱሱን ነገር ከነኩ ይሞታሉ ! ይህ በእውነትም በ 2ሳሙ(6፡ 6-7) ሆኖአል “ ወደ ናኮንም አውድማ በደረሱ ጊዜ በሬዎቹ ይፋንኑ ነበርና ዖዝ እጁን ዘርግቶ የእግዚአብሄርን ታቦት ያዘ ፡፡ የእግዚአብሄርም ቁጣ በዖዝ ላይ ነደደ እግዚአብሄርም ስለድፍረቱ በዚያው ቀሰፈው ፤ በእግዚአብሄርም ታቦት አጠገብ በዚያው ሞተ ፡፡” የካህኑ የአሮን ልጅ አልዓዛር በመብራቱ ዘይት ላይ፣ በጣፋጩ ዕጣን ላይ፣ የየቀን የእህል መስዋዕት ላይ እና የቅባቱ ዘይት ላይ ሹመት ነበረው ፤ ምክንያቱም አልዓዛር የጠቅላላ መቅደሱና በውስጡ ላሉት ሁሉም ነገር ተቆጣጣሪ ነበር፣ የቀዓትዋዊያንም ተቆጣጣሪ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ለሙሴና ለአሮን “የቀዓትን ወገኖች ነገድ ከሌዋዊያን መካከል አታጥፉአቸው ፡፡“ አሮንና ልጆቹ ይህን ዝግጅት ያደርጋሉ ከዚያም በመቀጠል እያንዳንዱን ሰዉ ስራውን እና የጉዞ ተግባሩን ይሾማሉ ፡፡ ቀዓትዋዊያን ቅዱስ ነገሮች ላይ መመልከት አይችሉም ይሞታሉ ፡፡

ዘኁልቁ(4፡ 21-28)፡ ከዚያም እግዚአብሄር ሙሴን ጌድሶዋያንን በቤተሰባቸውና በወገናቸው በመገናኛ ድንካኑ መስራት የሚችሉ እያንዳንዳቸው ሰዎች እድሜአቸው ከ30 እስከ 50 አመት የተመዘገቡ ቆጠራቸውን እንዲወስድ ተናገረው ፡፡ ይህ የጌድሶዋያን ወገን የመቅደሱን መጋረጃዎች፣ የመገናኛውን ድንካን ከመሸፈኛዎቹ ጋር እና ከአስቆጣ ቆዳ ከተሰራ ውጨኛው መሸፈኛ፣ ወደ መገናኛው ድንካን ለመግቢያ መጋረጃውን፣ የአደባባዩ መጋረጃዎችን፣ መቅደሱንና መሰዊያውን የሚከብበውን አደባባዩ በር ላይ ለመግቢያው ያለውን መጋረጃ ከገመዶች ጋር እና ሁሉንም እቃዎች በአገልግሎቱ የሚጠቀምባቸውን በማጎአጎአዝ እንዲያገለግሉ ተሸሙ ፡፡ ለእነዚህ ነገሮች ሀላፊ ነበሩ በአሮንና በልጆቹ ትዕዛዝም ሁሉንም ነገር አደረጉ ፡፡ በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አቅጣጫ ስር ነበሩ ፡፡ ጌድሶዋዊያን መሸፈኛዎችን ይመርጡ ነበር ፤ በዉጪ ላለው ለሁሉም ነገር ሀላፊነት ነበረባቸው ፡፡

ዘኁልቁ(4፡ 29-33)፡ በመቀጠል እግዚአብሄር ሙሴን ሜራሪያዊያንን በቤተሰባቸውና በወገናቸው በመገናኛ ድንካኑ መስራት የሚችሉትን እያንዳንዳቸው ሰዎች እድሜአቸው ከ30 እስከ 50 አመት የተመዘገቡ ቆጠራቸውን እንዲወስድ ተናገረው ፡፡ ሜራሪያዊያን ለመገናኛ ድንካኑ መዋቅሮች፣ የመቅደሱ ደጋፊዎችን፣ መወርወሪያዎቹን፣ ምሰሶዎች እና እግሮች እንዲሁም በተጨማሪ የአደባባዩ ዙሪያ ምሰሶዎች ከእግሮቻቸው ጋር፣ ድንካን ችካሎች፣ ገመዶቹ፣ ሁሉም እቃዎቻቸው እና ሁሉም ነገር ለጥቅማቸው የሚገናኙትን ለመሸከም ስራዎች ተሾሙ ፡፡ ለመዋቅር ስራ ሀላፊዎች ነበሩ ፤ ሜራሪያዊያን በካህኑ በአሮን ልጅ በኢታምር አቅጣጫ ስር ነበሩ ፡፡

እነዚህ የሰዎስቱ ወገኖች የቤት መሰረት ነበር፡ ቀዓትዋዊያን ከመቅደሱ በስተደቡብ በኩል ነበሩ፤ ጌድሶዋዊያን ከመቅደሱ በስተ ምዕራብ በኩል ነበሩ፤ ሜራሪያዊያን ከመቅደሱ በስተ ሰሜን በኩል ነበሩ ፡፡

ዘኁልቁ(4፡ 34-37)፡ ሙሴና አሮን ለቅዱስ ነገሮች ጥንቃቄ በመውሰድ በመገናኛ ድንካኑ ስራ ላይ ለማገልገል ከ30 እስከ 50 አመት ቀዓትዋዊያንን 2,750 ሰው መዘገቡ ፡፡ ከ25 እስከ 30 አመት እንዴት ከቅደሱ ነገሮች ጋር እንደሚገናኙ ያስቡ ነበር ፡፡ ዘኁ(3፡ 28) ሁሉም ቀዓትዋዊያን ሰው ተመዝግቦአል፡ “ ወንዶች ሁሉ እንደ ቁጥራቸው ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ 8,600 ነበሩ ፤ መቅደሱንም ይጠብቁ ነበር ፡፡”

ዘኁልቁ(4፡ 38-41)፡ ሙሴና አሮን በመገናኛው ድንካን ላይ ለማገልገል ከ30 እስከ 50 አመት እድሜ ጌድሶዋዊያንን 2,630 ሰው መዘገቡ ፡፡ ዘኁ(3፡ 22) ሁሉም ጌድሶዋዊያን ሰው ተመዝግቦአል፡ “ ከእነርሱም የተቆጠሩት የወንዶች ሁሉ ቁጥር ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያ በላይ የተቆጠሩት 7,500 ነበሩ ፡፡”

ዘኁልቁ(4፡ 42-49)፡ ሙሴና አሮን በመገናኛው ድንካን ላይ ለማገልገል ከ30 እስከ 50 አመት እድሜ ሜራሪያዊያንን 3,200 ሰው መዘገቡ ፡፡ ዘኁ(3፡ 34) ሁሉም ሜራሪያዊያን ሰው ተመዝግቦአል፡ “ ከእነርሱም ወንዶች ሁሉ እንደ ቁጥራቸው ከአንድ ወር ጀምሮ ከዚያም በላይ የተቆጠሩት 6,200 ነበሩ ፡፡” በጠቅላላው ከ30 እስከ 50 አመት እድሜ ሰው 8,580 የመጎአጎአዝ ተግባራትን እንዲያደርጉ ተመረጡ ፡፡

መዝጊያ

በ 2ጢሞ(2፡ 2) ጳውሎስ ጢሞቲዎስን ነገረው፡ “ ብዙ ሰዎች የመሰከሩለትን ከእኔም የሰማኸውን ሌሎችን ደግሞ ሊያስተምሩ ለሚችሉ ለታመኑ ሰዎች አደራ ስጥ ፡፡” ስለ እምነታችን ሌሎችን የምናስተምር ነን ፡፡

ሜራሪያዊያንን በማይ ጊዜ ከ3,200 በላይ መሰልጠን የቻሉ 3,200 ሰዎችን አያለሁ ፡፡ የደቀመዝሙር ሂደቱን አያለሁ፡፡ ስራውን ለማግኘት ብዙ ሰዎችን አያለሁ ፡፡ በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ጠንቃቆች የማንሆን ከሆነ ብቁ የሆንን እኛ ብቻ እንደምንሆን እና ብዙ ህዝብ እንደ ማናለማምድ አስባለሁ ፤ የእኛ ስራ ፍሬአማ እና ብዙ መሆን ነው ይህም ማለት በአገልግሎታችን ቦታ ላይ እንደሆነ በእውነት አስባለሁ ፡፡ ይህ የሆነን ሰው ለአምስት አመት የማሰልጠን አስደናቂ ምሳሌ ነው ፤ ኢየሱስ ይህን ከ12 ሰዎች ጋር አድርጎታል ከዚያም ከእነዚያም ሰዎች አንዱ ባያገኘውም ፡፡

በሐዋ 19 ሐዋሪያው ጳዉሎስን ተመልከቱ ፡፡ 12 ሰዎች ውስጥ በየቀኑ ለሁለት አመት አፈሰሰባቸው ፡፡ ሁሉም እስያ የእግዚአብሄርን ቃል ሰምቶአል ፡፡ ከጌድሶዋዊያን፣ ቀዓትዋዊያንና ሜራሪያዊያን ውጪ በፍፁም ወጥታችሁ መሮጥ የለባችሁም ምክንያቱም ቅጣት ሁል ጊዜ ፀባይተኛ ያደርጋል ፡፡ የትም ቦት ስታገለግሉ ተግባራዊ ጥያቄ፡ “ሁል ጊዜ ራሳችሁን ለመተካት ትመለከታላችሁ ?” ኢየሱስ ከ12 ጋር አድርጎታል ፤ ጳዉሎስ ከ12 ጋር አድርጎታል ፡፡ ብዙ ሲሰለጥኑ ብዙ የእግዚአብሄር መገኘትን መለማመድ ይቻላሉ ፡፡ በጣም ቀላል ማስተማር የምትችሉትን ደቀመዝሙር ሄዳችሁ ፈልጉ ስለዚህ ሌላ አካል ማስተማር ይጀምራሉ ፡፡

ጥያቄዎች

  1. ሰዎስቱን የሌዊ ገኖች ጥቀሱ ፤ በእያንዳንዳቸው ወገን ምን ያክል ነበሩ ? (ዘኁ 4፡ 34-45)
  2. አሮን እና ልጆቹ የመቅደሱን እቃዎች በወሰዱ ጊዜ ሁሉንም ነገር በአስቆጣ ቆዳ ለምን ሸፈኑ ?
  3. በቁጥር 18-20 ቀዓትዋዊያን ይኖራሉም ንዋይ ቅዱሳቱን እቃዎች በገቡ እና በቀረቡ ጊዜ እንዳይሞቱ እግዚአብሄር እንዲያደርጉ ምንድን አዘዛቸው ?
  4. ዘኁ (4፡ 20) ሲናገር ቀዓትዋዊያን እንዳይሞቱ በፍፁም የተቀደሰውን ነገር መመልከት ወይም መንካት የለባቸውም ፡፡ ያ ለምን እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ?
  5. በዘኁ 4 በትምህርት ወይም በማጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ(አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Numbers 4:48-49

“Their registered men numbered 8,580. At the LORD’S command they were registered under the direction of Moses, each one according to his work and transportation duty, and his assignment was as the Lord commanded Moses.”

የቀዓትዋዊያን፣ የጌድሶዋዊያን እና የሜራሪያዋን ተግባራት

ኦሪት ዘኁልቁ 4 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

እግዚአብሔር የቀዓት፣ የጌድሶንና የሜራሪን ልጆችን የማጓጓዝ ሥራ ላይ መደባቸዉ። በተለየ መልኩ የመገናኛዉ ድንኳን እንዲጠናቀቅ የሚያስፈልገዉ የማጓጓዝ ሂደት ኃላፊነት የተሰጠዉ ለእነሱ ነበር። እግዚአብሔር አምላክ ዝርዝር የማጓጓዣ ኃላፊነቶችን ካስቀመጠ በኃላ የህይወት እያንዳንዱ ጉዳይ ላይ እንደሚገባ ማስታወሻ ነበረ። ከአሁን ቀደም እግዚአብሔር፥ በእስራኤላዉያን እና በሙሴ ፊት በደመና እና በእሳት አምድ እየመራቸዉ እንደሚሄድ ተናግሯል። ስለዚህም እስራኤላዉያን እንደሚሄዱ ያዉቁ ነበር። ከዚያም እንዴት የመገናኛዉን ድንኳን መገንባት እንዳለባቸዉ ዝርዝር ትዕዛዝ ሰጣቸዉ። እግዚአብሔር እንደሚሰሩት ካዘዛቸዉ እና እንደሚሄዱ ይሁንታ ከሰጣቸዉ የመጓጓዣዉ ዝርዝር መሰጠቱ ተገቢ ነዉ!

አስታዉስ፦ እግዚአብሔር ለሆነ ነገር ከጠራህ፥ በረቂቅ ለተሰሩ ዝርዝሮች ሁሉ እርሱ ዓላማ አለዉ። እግዚአብሔር ሊመክርህ እና የምትሄድበትን መንገድ ሊያሳይህ ቃል ይገባልሃል! ይህ እረፍትን አይሰጥህምን? እግዚአብሔር ዓላማ አለዉ!

"ከእነርሱ የተቈጠሩት ስምንት ሺህ እምስት መቶ ሰማንያ ነበሩ። እንደ እግዚአብሔር ትእዛዝ እያንዳንዳቸው በየአገልግሎታቸውና በየሸክማቸው በሙሴ እጅ ተቈጠሩ፤ እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ እንዲሁ በእርሱ ተቈጠሩ።"

ኦሪት ዘኁልቁ 4:48-49

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ኦሪት ዘፀዓት 13:21፦ "በቀንና በሌሊትም ይሄዱ ዘንድ፥ መንገድ ሊያሳያቸው ቀን በደመና ዓምድ፥ ሊያበራላቸውም ሌሊት በእሳት ዓምድ እግዚአብሔር በፊታቸው ሄደ።"
  • ኦሪት ዘፀዓት 35:10-11፦ "በእናንተም ዘንድ ያሉ በልባቸው ጥበበኞች ሁሉ መጥተው እግዚአብሔር ያዘዘውን ሁሉ ያድርጉ። ማደሪያውን፥ ድንኳኑንም መደረቢያውንም፥ መያዣዎቹንም፥ ሳንቆቹንም፥ መወርወሪያዎቹንም፥ ምሰሶቹንም፥ እግሮቹንም፤"
  • መዝሙረ ዳዊት 32:8፦ "አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ፤ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 75