The Levitical Census
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና ከእያንዳንዱ ነገድ በተወከለ አንድ ሰው በ12 ስሞች ውስጥ አንብበናል ፤ እያንዳንዱ ስም ለእግዚአብሄር ያስፈልገዋል ፡፡ በዘኁ 1 በውትድርና ማገልገል የሚችሉ 20 አመትና ከዚያ በላይ የሆኑ 603,550 ወታደሮችን ለመቁጠር በሙሴና በአሮን እርዳታ እግዚአብሄር አነዚህን 12 ሰዎች ተጠቀመባቸው ፡፡ እስራኤላዊያን ለሆነ ነገር ተዘጋጁ - የእስራኤልን ህዝብ ለመከላከል ፡፡ በዘኁ 2 እንዴት ወደፊት እንደሚሄዱ ተነገራቸው ፤ መጀመሪያ የትኛው ነገድ እንደሚሄድ ከዚያም ማን እንደ ሚከተል ተነገራቸው ወ.ዘ.ተ ፡፡ ይህ የሚያመለክታችሁ እግዚአብሄር እንዴት የጠለቀ እንደሆነ ነው ፡፡ ዛሬ ዘኁ 3 እንዴት እንደሚያገለግሉ ሌዋዊያንን እንደ ሚያዝዛቸው እንመለከታለን ፡፡
ትምህርት
ዘኁልቁ(3፡ 1-4); የምናሳስባችሁ ሙሴ ስሞቹን አስቀመጠ በዚህም መጀመሪያ አሮን ተቀመጠ ምክንያቱም የዘኁልቁ መፅሀፍ ስለ ካህናት ነው ፤ ስለ ሙሴ አልነበረም ነገር ግን ስለ አሮንና ቤተሰቦቹ እና ሌዋዊያን ነበር ፡፡ አሮን አራት ወንድ ልጆች ነበሩት ፤ የአሮን ልጆች እንደ ካህን እንዲያገለግሉ የታዘዙ(የተለዩ) ነበሩ ፡፡ በኩሩ ናዳብና ወንድሙ አብዩዱ በእግዚአብሄር ያልተፈቀደ እሳት ባቀረቡ ጊዜ ሞቱ (ዘሌ 10፡ 1-3) ፤ ናዳብና አብዩዱ ልጆች አልነበሩአቸውም ስለዚህ የቤተሰብ መስመራቸው አበቃ ፡፡ አልአዛርና ኢታምር በአባታቸው በአሮን አቅጣጫ ስር እንደ ካህን አገለገሉ ይህ ማለት ናዳብና አብዩዱ የአሮንን ትዕዛዝ አልተከተሉም ፡፡ ዘኁ (20፡ 22-29) የሚለው አልአዛር አሮን በሞተ ጊዜ ታላቅ ካህን ሆነ ፡፡
ዘኁልቁ(3፡ 5-10); እግዚአብሄር ሙሴን ለሌዋዊያን ትዓዛዝ ሰጠው ፤ ሙሴ ለአሮን እና ለሁሉም ህብረተሰብ ተግባራትን በማድረግ እርዳታ እንዲያደርጉለት ሌዋዊያንን ለአሮን አቀረበ ፡፡ ሌዋዊያን ለሁሉም ለመገናኛ ድንካን እቃዎች እና ለመቅደሱ አገልግሎት በመሳተፍ በመጠንቀቅ የተሾሙ ነበሩ ፤ ሚናቸው ለማገልገል ነበር ፡፡ በእግዚአብሄር አቅጣጫ ሙሴ ሌዋዊያንን ለአሮንና ለልጆቹ እንዲያገለግሉና ለብቻቸው እንዲያግዙአቸው አስቀመጣቸው ፡፡ አሮንና ልጆቹ እንደ ካህን አገለገሉ ነገር ግን ማንኛውም ያልተፈቀደላቸው ሰዎች መቅደሱን ቀርበው የመጡ ይሞታሉ ፡፡
ዘኁልቁ(3፡ 11-13); እግዚአብሄር ሌዋዊያንን ከሁሉም እስራኤላዊያን እንደ በኩሩ እንደ ወሰዳቸው ተናገረ ፤ ከ2 ሚሊዮን ህዝብ ሌዋዊያን ለእግዚአብሄር ነበሩ ፡፡ እግዚአብሄር በግብፅ ሁሉንም በኩርን በገደለ ጊዜ እያንዳንዱን በኩር በእስራኤል ለራሱ ቀደሰ ወይም ለየ በዘጸ(13፡ 1-2) የእግዚአብሄርን ንግግር ለሙሴ ስንከልስ “ በእስራኤል ልጆች ዘንድ ከሰውም ከእንስሳም ማህፀንን የሚከፍት በኩር ሁሉ ለእኔ ቀድስልኝ የእኔ ነው ፡፡”
ዘኁልቁ(3፡ 14-16); እግዚአብሄር ሙሴን እያንዳንዱን ሌዋዊ አንድ ወር የሞላቸውን እና ከዛበላይ የሆነውን በቤተሰብ እና በጎሳ እንዲመዘግብ አዘዘው ፤ ስለዚህ ሙሴ እንደ ታዘዘው ቆጠረ ፡፡ ማሳታዎስ ያለባችሁ ሙሴ በዚህ ጊዜ እርዳታ አልነበረውም ፡፡
ዘኁልቁ(3፡ 17-20); ሌዊ ሰዎስት ወንድ ልጆች ነበሩት፡ ጌድሶን፣ ቀዓትና ሜራሪ ፡፡ ጌድሶን ሁለት ወንድ ልጆች ሎቤኒና ሰሜኢ ነበሩት ፡፡ ቀዓት አረት ወንድ ልጆች እንበረም፣ ይስዓር፣ ኬብሮንና ዑዝኤል ነበሩት ፡፡ ሜራሪ ሁለት ወንድ ልጆች ሞሆሊና ሙሲ ነበሩት ፡፡
ዘኁልቁ(3፡ 21-26); ሙሴ የጌድሶን ወንድ ልጆችን አንድ ወር ወይም በላይ ሆናቸውን ቆጠረ ፤ ጠቅላላ የጌድሶን ነገድ 7,500 ተቆጠረ ፤ እነዚህ ጎሳዎች ከመቅደሱ ኃላ በምዕራብ በኩል ይሰፍራሉ ፤ ኤሊሳፍ የዳኤል ወንድ ልጅ የጌድሶዋዊያን መሪ እንዲሆን ተሾመ ፡፡ የጌድሶዋዊያን ተግባራት ለድንካኑ ማደሪያ፣ ለድንካኑ፣ ለመደረቢያው፣ ወደ መገናኛው ድንካን ለመግቢያ መጋረጃ፣ ለአደባባዩ መጋረጃዎች እና ለገመዶች መጠንቀቅ ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(3፡ 27-32); እንበረምዋዊያን፣ ይስዓርዋዊያን፣ ኬብሮንዋዊያንና ዑዝኤልዋዊያን የቀዓትዋዊያን ጎሳዎች(ወገኖች) ነበሩ፤ ጠቅላላ የቀዓትዋዊያን ነገድ 8,600 ተቆጠረ ፡፡ ለመቅደሱ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኃላፊነት ነበራቸው ፤ በጣም ጠቃሚ ስራ ነበራቸው ምክንያቱም የተቀደሱ ነገሮችን ጥንቃቄ ይወስዱ ነበር ፡፡ቀዓትዋዊያን ከመገናኛ ድንካኑ ማደሪያ በስተደቡብ በኩል ይሰፍራሉ ፡፡
ዘኁልቁ(3፡ 33-37); የሜራሪ ወገኖች ሞሆላያዉያንና የሚሳያውያን ነበሩ ፤ ጠቅላላ የሜራሪ ነገድ 6,200 ተቆጠሩ ፤ ከመቅደሱ በስተሰሜን በኩል ይሰፍራሉ (ዘኁ 2፡ 25) ፡፡ ሜራሪያዊያን ከእንጨት ለተዋቀሩት ነገሮች፣ ለድጋፎቹ፣ ለመወርወሪያዎቹ፣ ለተራዳዎቹ፣ ለእግሮቹ እና ለሁሉም ለሚገናኙት እቃዎች ጥንቃቄ እንዲወስዱ ተመረጡ ፡፡ የአቢካኢል ወንድ ልጅ ሱሪኤል የሜራሪያዊያን መሪ ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(3፡ 38); ሙሴ፣ አሮንና ወንድ ልጆቹ ፀሀይ ወደ ምትወጣበት ከመገናኛው ድንካን ፊት ለፊት ከመቅደሱ በስተምስራቅ በኩል ይሰፍራሉ ፤ ለመቅደሱ ጥንቃቄን የመውሰድ ሀላፊነት ነበረባቸው ፡፡ ማንኛውም ያልተፈቀደለት ሰው ወደ መቅደሱ ከቀረበ ይሞታል ፡፡
ዘኁልቁ(3፡ 39)፡ የሌዋዊያን ወንዶች አንድ ወር የሞላቸው ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ጠቅላላ ቁጥር 22,000 ነበር ፡፡ በዘኁ 4 ቀጥሎ በማንበብ ሙሴ ቆይቶ “ እያንዳንዱን በመገናኛ ድንካኑ ላይ ለመስራት ብቁ የነበሩ ከ30 አመት እስከ 50 አመት ወንዶች ”(ዘኁ 4፡ 3፣ 23፣ 30፣ 35፣ 39፣ 43፣ 47) መቁጠሩን እንማራለን ፡፡ ወንድ 20 አመት ላይ ከደረሰ በኃላ ለማገልገል ዝግጁ እስኪሆኑ ድረስ አምስት አመት ይቆያል ፤ በመሰረቱ የመለማመጂያ ፕሮግራም ነበር ፡፡ ይህን ሁሉ ስራ ያደርግ የነበረው ማነው ? እነዚህን ሁሉ እንስሳቶች የሚገምተው ማን ነበር ? በዘኁ(8፡ 24) መሰረት “ የሌዋዊያን ህግ ይህ ነው ከ25 አመት ጀምሮ ከዚያም በላይ ያሉት በመገናኛው ድንካን ስራ ያገለግሉ ዘንድ ይገባል፡፡” ወንድ የሚበቃው 30 አመቱ ላይ ነበር ግን በ25 አመቱ ይጀምራል ፤ የካህናት ቤተሰብ ሁሉንም ተግባራትን ለመማር ለአምስት አመት ይለማመዳሉ ስለዚህ ማጥራት ይችላሉ ከዚያም ካህኑን ያግዛሉ ፡፡ ዘኁ (4፡ 36) ለማገልገል ከቀዓትዋዊያን ነገድ 2,750 ወንድ ብቁ እንደ ነበሩ ይናገራል ፤ ዘኁ(4፡ 40) ለማገልገል ከጌድሶዋዊያን ነገድ 2,630 ወንድ ብቁ እንደ ነበሩ ይናገራል ፤ ዘኁ (4፡ 44) ለማገልገል ከሜራሪያዊያን ነገድ 3,200 ወንድ ብቁ እንደ ነበሩ ይናገራል ፡፡
የኔልሰን ማብራሪያ ስለ ሌዋዊያን እነዚህን ምልከታዎች ሰጥቶአል፡
- ከሌሎቹ ነገዶች ለየብቻቸው ተቆጠሩ ፡፡
- ከወታደርነት ይልቅ በእግዚአብሄር አምልኮ ውስጥ ለአገልግሎት በግልፅ ተሾሙ ፡፡
- ህይወታቸውን የሚመሩበት ለመንገዳቸው የተወሰኑ ገደቦች ተሰጡዓቸው ፡፡
- የእግዚአብሄር የበኩር ስጦታን ይወክላሉ ፡፡
- በራሳቸው ከተማ ይኖራሉ ፡፡
- የመጨረሻ አላማቸው አሮንንና ልጆቹን ከዚያም እግዚአብሄርን ማገልገል ነበር ፡፡
ዘኁልቁ(3፡ 40-43)፡ እግዚአብሄር በመቀጠል ሙሴን እያንዳንዱ እስራኤላዊ አንድ ወር ወይም የሚበልጥ ወንድ እንዲቆጥርና የስማቸውን ዝርዝር እንዲያደርግ አዘዘው ፤ ከዚያም እግዚአብሄር ሌዋዊያንን ከእስራኤላዊያን መሀከል በእያንዳንዱ በኩር ቦታ ለራሱ አደረገ ፡፡ አንድ ወር እና በላይ የሆኑት የበኩር ወንዶች ጠቅላላ ቁጥር ባጠቃላይ 22,273 ፡፡
ዘኁልቁ(3፡ 44-48)፡ አሁን ሙሴ በሁሉም በእስራኤላዊያን በኩር ቦታ ሌዋዊያንን እንዲወስድ ተነገረው ፤ ጠቅላላ የእስራኤላዊያን በኩር(22,273) ሲቀነስ ጠቅላላ ሌዋዊያን(22,000) ማለትም የእስራኤላዊያን በኩር በ273 ቁጥር ይበልጣል ፡፡ እነዚህን 273 እስራኤላዊያን ለመዋጀት ለእያንዳንዳቸው አምስት ሸቅል በመሰብሰብ(273 ሰዎች ሲባዛ በ 5 ሸቅል) ከዚያም እንደ መዋጂያ ዋጋ ለአሮን እና ለልጆቹ ይሰጣል ፡፡
ዘኁልቁ(3፡ 49-51)፡ ሙሴ በመብለጥ በሌዋዊያን የተዋጁትን የተዋጁበትን ገንዘብ ሰበሰበ ፤ ሙሴ 1,365 ሸቅል ሰበሰበና ለአሮንና ለልጆቹ እግዚአብሄር እንዳዘዘ ገንዘቡን ሰጣቸው ፡፡
መዝጊያ
22,000 ሌዋዊያን በኩርን ይወክላሉ ፤ ለእግዚአብሄር መቅደሱን ለመክበብ ነበር ፡፡ ይህ የመጨረሻውን በኩር አለቱን እንዳስብ ያደርገኛል ፤ አለቱ ኢየሱስ ነው ፤ በተጨማሪም ኢየሱስ በኩር ነው ፡፡ ቆላ (1፡ 15) የሚለው “እርሱም የማይታየው አምላክ ምሳሌ ነው ፤ ከፍጥረት ሁሉ በፊት በኩር ነው ፡፡” ኢየሱስ ትንሽ በነበረ ጊዜ እንደ በኩር ለእግዚአብሄር ወደ ኢየሩሳሌም በመምጣት ቀረበ ፤ ሉቃ(2፡ 22-23) የተመዘገበው ድርጊት፡ “ እንደ ሙሴ ህግ የመንጻታቸው ወራት በተፈፀመ ጊዜ (በጌታ ህግ የእናቱን ማህፀን የሚከፍት ወንድ ሁሉ ለጌታ የተቀደሰ ይባላል ተብሎ እንደ ተፃፈ) በጌታ ፊት ሊያቆሙት ወደ ኢየሩሳሌም ወሰዱት ፡፡”
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 199.
ጥያቄዎች
-
የሞቱት የአሮን ሁለቱ ወንድ ልጆች ስም ማን ነበር ? ለምን ሞቱ (ዘሌ 10፡ 1-2; ዘኁ 3፡ 4) ? ይህ እንዴት የስህተት መስዋዕት/አምልኮ አይነት ነበር ? ዛሬ እንድናመልከው እግዚአብሄር እንዴት አዘዘን ? (ዮሐ4፡23-24)
-
የእስራኤልን ሁሉንም ትውልድ እግዚአብሄር እንደ “ ንጉስ ካህናት “ ጠቀሳቸው( ዘጸ 19፡ 5-6) ፡፡ ለመቅደሱ እንዲጠነቀቅ ማን አድርጎ ለብቻ ለያቸው ? የእነርሱ ጥቂት ሚናዎች ምንድን ነበሩ ?
-
የምትሳተፉበት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ላይኖሩ ይችላሉ እንደ ሌዊ ነገድ ፤ ስራውን ለመስራት አሁንም እግዚአብሄር በጥቂት የክርስቶስ አካል መጠቀም ይችላል ? እንዴት ሆኖ ? (መሳ 7፡ 7; 1ቆሮ 1፡ 25; 2ቆሮ 12፡ 9)
-
ሁሉም በኩር የእስራኤል ወንድ ልጆቹ አንድ ወር የሆናቸው ወይም የሚበልጡ የተቆጠሩት ለምን ነበር ? ለዘኁ(3፡ 14) የሌዋዊያን ተተኪዎች እነማን ነበሩ ? ለሁሉም ፍጥረት እንደ በኩር ይህ እንዴት ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ? (ቆላ 1፡ 15)
-
በዘኁ 3 በትምህርት ወይም በማጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 3:5-7
“The LORD spoke to Moses: ‘Bring the tribe of Levi near and present them to Aaron the priest to assist him. They are to perform duties for him and the entire community before the tent of meeting by attending to the service of the tabernacle.’”
የሌዋዉያን ነገድ
ቆጠራ
ኦሪት ዘኁልቁ 3
የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እግዚአብሔር ለእስራኤላዉያን በሙሉ ትዕዛዝን እና የሥራ ድርሻን ከሰጠ በኋላ በ22,000 ሌዋዉያን ላይ አትኩሮቱን አደረገ። የሌዋዉያን ሥራ፥ በመገናኛዉ ድንኳን በመገኘት አሮንና ልጆቹን መርዳት ነዉ። በተለየ መንገድ የታዘዙትም የማሳዋብ ሥራ እንዲሰሩ ነበር። ምን ዓይነት ሥራ ነዉ!
ብዙ ጊዜ፥ ነገሮችን የማስዋብ ሚና፥ የወደቀ፣ ከቦታዉ የተዛነፈ እና የቆሸሸ ነገር እስከሚገኝ ድረስ በዓይን የሚገባ አይደለም። ከዚያም ከመድረኩ በስተጀርባ የሚያሰናዱ እና የሚንከባከቡ የሰዎች ቡድን ምን ያክል እንደሚያስፈልግ ትገነዘባለህ። ይህ ዓለም እንደ እነዚህ ዓይነት ሥራዎችን እንደ አስፈላጊ እና ክብር እንደሚገባቸዉ ላይቆጥር ይችላል። ነገር ግን እንደ የክርስቶስ ተከታይ፥ ልክ ኢየሱስ ሊያገለግን እንደመጣ አንተም እንዲሁ ልታገለግል ተጠርተሃል። ጌታን እና ለህይወትህ ያለዉን ዓላማ እየተከተልህ ከሆነ፥ መፀዳጃ ቤት መፈግፈግ እንኳ ቢሆን ከዚያ የተሻለ ስፍራ የለም!
"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የሌዊን ነገድ አቅርበህ ያገለግሉት ዘንድ በካህኑ በአሮን ፊት አቁማቸው። የማደሪያውንም ሥራ ይሠሩ ዘንድ፥ እርሱንና ማኅበሩን ሁሉ ለማገልገል የሚያስፈልገውን ነገር በመገናኛው ድንኳን ፊት ይጠብቁ።"
ኦሪት ዘኁልቁ 3:5-7
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የዮሐንስ ወንጌል 12:26፦ "የሚያገለግለኝ ቢኖር ይከተለኝ፥ እኔም ባለሁበት አገልጋዬ ደግሞ በዚያ ይሆናል፤ የሚያገለግለኝም ቢኖር አብ ያከብረዋል።"
- ወደ ሮሜ ሰዎች 12:4-7፦ "በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን። እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፤ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ ይትጋ፤"
- ወደ ገላትያ 5:13፦ "ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ ነገር ግን በፍቅር እርስ በርሳችሁ እንደ ባሪያዎች ሁኑ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 74
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።