The Census of Israel
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Rock Numbers 1-2 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዘኁልቁ መፅሀፍ ጥናታችን ላይ እንካን ደህና መጣችሁ - ስለ እድሎች እና የዘኁልቁን እድሎች 36 ምዕራፎችን እናወራለን ፡፡ በእርእስ ፃሀፊዎቹ አስደናቂ ፈጣሪ አልነበሩም ምክንያቱም ስለ ዘኁልቁ ያወራሉ ፤ ይህ ሁሉ ወደ አንድ ነገር ወደ መሲሁ ያመለክታል ፡፡
- በዘፍጥረት ዘሩ ወደ መሲሁ ያመለክታል ፡፡
- በዘጸዓት ከግብፅ ወደ ነፃነት እስራኤላዊያንን የሳባቸው ነፃ አዉጪው እውነት መሲሁ ነበር ፡፡
- በዘሌዋውያን ነፃ እንድንሆን የፈቀደልን የክርስቶስ ደም አስተሰሪያችን ነበር ፡፡
አሁን በዚህ በዘኁልቁ ነን እናም የእኛ አንድ ቃል አለት ነው፡፡ በ 1ቆሮ (10፡ 1-4) ጳዉሎስ የፃፈውን እንመልከት “ወንድሞች ሆይ ይህን ታውቁ ዘንድ እወዳለሁ ፡፡ አባቶቻችን ሁሉ ከደመና በታች ነበሩ ሁሉም በባህር መካከል ተሻገሩ ሁሉም ሙሴን ይተባበሩ ዘንድ በደመናና በባህር ተጠመቁ ፤ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መብል በሉ ሁሉም ያን መንፈሳዊ መጠጥ ጠጡ ፤ ይከተላቸውም ከነበረው ከመንፈሳዊ አለት ጠጥተዋልና ያም አለት ክርስቶስ ነበር ፡፡”
በዘኁልቁ ከአንዱ ትውልድ ወደ ቀጣይ ትውልድ ሄዱ ፡፡ በበርሃ ነበሩ ከዚያም የተካፈሉበት አለትም ክርስቶስ ነበር ፤ ኢየሱስ መሰረታቸው ነበር ፤ ኢየሱስ መነሻቸው ነበር ፡፡
ትምህርት
ዘኁልቁ(1፡ 1)፡ ፀሀፊው ሙሴ ነበር ፡፡ ከዘኁልቁ 20 በኦሪት መጨረሻ ውስጥ( የዘዳግም መጨረሻ ) አንድ አመት ይሸፍናል ይህም የሙሴን ቀሪ ህይወት ይዞአል ፤ ከግብፅ ከተነሱ በኃላ እስራኤላዊያን በበርሃ ቢያንስ እዚህ በሲና ተራራ ላይ 11 ወራት ይሆናቸዋል (ዘጸ 19፡ 1) ፡፡
ዘኁልቁ(1፡ 2)፡ ዋይሰርቤ የተናገረው “ በጦርነት የሚያገለግሉ ያሉ ወንዶችን ቆጠራ እንዲወስድ “ ሙሴ ትዕዛዝ ተሰጠው ፡፡ እያንዳንዱ ወንድ በማህበረሰቡ ውስጥ በነገድ በጎሳ በቤተሰብ ይቆጠራሉ ፤ በዘሌ(30፡ 11-12) እግዚአብሄር ሙሴን “ አንተ የእስራኤልን ልጆች ቁጥር ተቀብለህ በቆጠርሀቸው ጊዜ መቅሰፍት እንዳይሆንባችሁ በቆጠርሀቸው ጊዜ ከእነርሱ ሰው ሁሉ እንደ ቁጥራቸው መጠን የነፍሱን ቤዛ ለእግዚአብሄር ይስጥ ” ብሎ ተናገረው፡፡ ዘጸ(38፡ 25-26) የተቆጠረው ብር ተመዝግቦአል በተጨማሪም 603,550 ወንድ ተቆጥሮአል ፤ በዘኁ 1 እንደ ምናነበው ይህን ቁጥር በአይምሮአችሁ ያዙ፡፡
ዘኁልቁ(1፡ 3-4)፡ 20 አመት እና የሚበልጡ በጦርነት ማገልገል የሚችሉ ወንዶች ብቻ ተቆጠሩ ፤ አላማው ወንድ ለጦርነት እንዲዘጋጁ ነበር ፡፡ ሙሴ ይህን ቆጠራ ብቻውን አልጨረሰውም ፡፡
ዘኁልቁ(1፡ 5-15)፡ ሙሴን እንዲረዱት ከእያንዳንዱ ነገድ አንድ ሰው ተሰየመ፡
ከሮቤል ነገድ ኤሊሱር (የያዕቆብ በኩር እና የልያ ወንድ ልጅ)፡፡
ከስምዖን ነገድ ሰለሚኤል ፡፡
ከይሁዳ ነገድ ነአሶን ( በሩት 4፡ 20 መሰረት ከዳዊት ቤተሰብ ግንድ) ፡፡
ከይሳኮር ነገድ ናትናኤል፡፡
ከዛብሎን ነገድ ኤልያብ፡፡
ከኤፍሬም ነገድ ኤሊሳም (የዮሴፍ ወንድ ልጅ)፡፡
ከምናሴ ነገድ ገማልኤል (የዮሴፍ ወንድ ልጅ)፡፡
ከብንያም ነገድ አቢዳን፡፡
ከዳን ነገድ አኪኤዘር ፡፡
ከአሴር ነገድ ፋጉኤል ፡፡
ከጋድ ነገድ ኤሊሳፍ ፡፡
ከንፍታሌም ነገድ አኪሬ ፡፡
ዘኁልቁ(1፡ 16-19)፡ እነዚህ ሰዎች የነገዶቻቸው መሪዎች ነበሩ - የእስራኤል ጎሳዎች መሪ ፤ ልክ እንደ ኢየሱስ 12 ደቀመዝሙር ነበሩ ፡፡ ሙሴና አሮን በስማቸው በተሰየሙት በእነዚህ ሰዎች ላይ በሁለተኛው ወር በመጀመሪያው ቀን በአንድ ላይ ሁሉም ማህበረሰብ ተጠሩ ፡፡ በጎሳቸው እና በቤተሰባቸው መሰረት 20 አመት እና ከዚያ በላይ አንድ በአንድ በስማቸው ተዘረዘሩ ፤ እግዚአብሄር እንዳዘዛቸው አደረጉ ፡፡
ዘኁልቁ(1፡ 20-43); ሙሴ 20 አመት እና ከዚያ በላይ የሆኑትን የእስራኤላዊያን ወንዶችን በጦርነት ማገልገል የሚችሉትን መዘገበ ፡፡
የሮቤል ነገድ 46,500 ወንድ
የስምዖን ነገድ 59,300 ወንድ
የጋድ ነገድ 45,650 ወንድ
የይሁዳ ነገድ 74,600 ወንድ
የይሳኮር ነገድ 54,400 ወንድ
የዛብሎን ነገድ 57,400 ወንድ
የኤፍሬም ነገድ 40,500 ወንድ
የምናሴ ነገድ 32,200 ወንድ
የብንያም ነገድ 35,400 ወንድ
የዳን ነገድ 62,700 ወንድ
የአሴር ነገድ 41,500 ወንድ
የንፍታሌም ነገድ 53,400 ወንድ
ባለ ጥቂት አባላት ነገድ ምናሴ(32,200) ነበር ባለ ብዙ አባላት ነገድ ደግሞ ይሁዳ(74,600) ነበር ፡፡ እነዚህን የተቆጠሩትን ሰዎች እና የቀረውን ይህን መረጃ ቀላል እውነት አንመለከትም ፡፡
ዘኁልቁ(1፡ 44-46); እነዚህ በሙሴ፣ በአሮን እና እያንዳንዳቸው ቤተሰባቸውን በወከሉ በእስራኤል 12 መሪዎች የተቆጠሩ ሰዎች ነበሩ ፡፡ ሁሉም 20 አመት እና ከዚያ በላይ ወንድ በእስራኤል ተዋጊ(ጦር0 ውስጥ ማገልገል ሚችሉ ነበሩ ፡፡ ጠቅላላ ቁጥራቸው 603,550 ያክላል ፤ ወደ ዘጸ(38፡ 25-26) በመመለስ አወዳድሩት ፡፡
ዘኁልቁ(1፡ 47-51); እግዚአብሄር ሙሴን ሌዋዊያንን እንዳይዘግብ ወይም እንዳይቆጥር ነገር ግን በመቅደሱ ላይ በውስጥ እቃውና በውስጡ ባለው ሁሉም ነገር ላይ እንዲሾማቸው አዘዘዉ ፡፡ ለመቅደሱና ከመቅደሱ ጋር የሚገናኘውን ነገር ሁሉ በማጎአጎአዝ እና በመጠንቀቅ ሸክም ነበረባቸው ፤ መቼም ቢሆን እስራኤላዊያን መኖሪያ ከሰሩ ሌዋዊያን በመቅደሱ ዙሪያ ይሰፍሩ ነበር ፤ መቼም ቢሆን እስራኤላዊያን ከተጎአዙ ሌዋዊያን መቅደሱን እና እቃዎቹን የማንቀሳቀስ ኃላፊነት ነበረባቸው ፡፡ ከእነዚህ እቃዎች ከእነርሱ ውጪ ማንም ከነካ ይሞታል ፡፡ እያንዳንዳቸው ቡድን የራሳቸው ሚና የነበራቸው ካህናት ከዚያም ሌዋዊያን ነበሩ ፤ በመቅደስ ዙሪያ ላሉ ሁሉም ነገር ሌዋዊያን ጥንቃቄ ሲያደርጉ ካህናቱ መስዋዕትን ያደርጋሉ ፡፡ ሌዋዊያን ከኃላ የሚቀመጡና እግዚአብሄርን በዚህ መልኩ የሚያገለግሉ ነበሩ ፤ በጦር ሜዳ የሚዋጋ የጦር ድርሻ የላቸውም ፤ ሌዋዊያ ስንቅ ሰራተኞች ነበሩ ፡፡
ዘኁልቁ(1፡ 52-54); እስራኤላዊያን በየቤተሰባቸው ነገድ ፅሁፍ ስር ተሰብስበው ሰፈሩ ፤ ሌዋዊያን በምስክርነቱ መቅደስ ዙሪያ ተቀመጡ ስለዚህ በእስራኤላዊያን ላይ ቁጣ አይወድቅም ፡፡ እስራኤላዊያን ሙሴን እንዳዘዘዉ ሁሉንም ነገር አደረጉ ፡፡
መዝጊያ
ይህ እንዴት ለእኛ ይተገበራል ? ሁላችንም የራሳችን መስመር አለን ፡፡ ለመፈፀም ሁላችንም የራሳችን ሚና አለን ስለዚህ እግዚአብሄር ክብር ያገኛል ፤ ሁሉም አካል በአንድ ሲመጣ እግዚአብሄር የሚከብር ነው ፡፡ በኤፌ(4፡ 11-13) መሰረት እነዚህ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ነገዶች ናቸው “ ሁላችን የእግዚአብሄርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደ ሚገኝ አንድነት ሙሉ ሰውም ወደ መሆን የክርስቶስም ሙላት ወደ ሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመስራትና ለክርስቶስ አካል ህንፃ ፍፁማን ይሆኑ ዘንድ ፡፡”
እግዚአብሄር ባስቀመጠልን ትክክል መንገድ በተጎአዝን ጊዜ እግዚአብሄር ክብር ያገኛል ፤ ለእግዚአብሄር ክብር እንዲያገኝ እያንዳንዱ ሰው እንዴት በትዕዛዝ ጥቅሙን ይህን ቃለ ምልልስ እንቀጥላለን ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 313.
ጥያቄዎች
-
ለዘኁልቁ ጭብጡ አለት ነው ፡፡ በ 1ቆሮ(10፡ 1-4) ኢየሱስን እንዴት ታዩታላችሁ ?
-
በዘኁ (1፡ 1) በሲና ምድረዳ በመገናኛው ድንካን እግዚአብሄር ለሙሴ ተናገረው ፤ በምንም ሁኔታ ወይም አጋጣሚ ውስጥ ብትሆኑ(በምድረ በዳ የሚመስል ሁኔታ እንካን ቢሆን) ችግር የለውም እግዚአብሄር ሊናገራችሁ ይፈልጋል ይህ ያበረታታችኃል ?
-
በመጀመሪያዎቹ ጥቂት የዘኁልቁ ጥቅሶች እግዚአብሄር ሙሴ እንዲያደርግለት ምንድን ጠየቀው ? እነዚህ የያዕቆብ(የእስራኤል) ሁሉም ወንድ ልጆች ነበሩ ፡፡ ለምን ነበር ?(ዘኁ 1፡ 47-51)
-
ዘኁ 2 በመቅደሱ ዙሪያ ነገዶቹን አደራጀ ፤ እንደ ክለሳ ቅዱስተ ቅዱሱ ቦታ በምንድ ይወክላል ? እዚያ ምንድን ነበር የቀጠለው ? (ዘጸ 25፡ 21-22; ዕብ 6፡ 19-20)
-
በመቅደሱ ዙሪያ በምድሩ እንዲሰፍሩ እግዚአብሄር የእያንዳንዳቸውን ነገድ መሪዎችን ሾመ ፡፡ ወደ አድስ መድረሻ በሚጎአዙ በምንድን ቅደም ተከተል ነገዶቹ ተቀመጡ ? ይህን ለማድረግ የእግዚአብሄር አላማ ምንድን ነበር ? አሁን ለእናንተ የእግዚአብሄርን አላማ ማየት ትችላላችሁ ? (ምሳ 19፡ 21; ፊል 2፡ 12-13) ለምን ወይስ ለምን አይደለም ?
-
በዘኁ 1-2 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Numbers 1:2
“Take a census of the entire Israelite community by their clans and their ancestral houses, counting the names of every male one by one.”
የእስራኤል ህዝብ ቆጠራ
ኦሪት ዘኁልቁ 1-2 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እግዚአብሐር፦ ሙሴን እና አሮንን ስማቸዉን አንድ በአንድ በመቁጠር፥ ማህበረሰቡን በሙሉ እንዲቆጥሩ ትዕዛዝን ሰጣቸዉ። እግዚአብሔር አምላክ ስነ-ስርዓትን ወደ እስራኤል እያመጣ እና ሰራዊቱንም መገንባት እየጀመረ ነበር። የእያንዳንዱ የዘር ሀረግ ቤት ስም ዝርዝር በምትመለከቱበት ጊዜ፥ ቁጥሮቹን እና ስሞቹን በአንክሮት ተመልከቱ። ምንም ኮምፑይተር፣ እስኪርቢቶ እና ወረቀት በሌለበት በአንድ ጊዜ ይህንን ሁሉ ህዝብ መቁጠር ምን ማለት እንደሆነ አስባችሁታል? ቢሆንም እግዚአብሔር እያንዳንዱ ዘር እና ስም እንዲቆጠር ትዕዛዝን ሰጥቷል። ክንዋኔዉ ለጊዜዉ እና ለእግዚአብሔር የሚገባ ጥረት ነዉ!
ልክ እንደዚሁ እግዚአብሔር አምላክ ስምህን ያዉቀዋል። ለአንተ ጥልቅ የሆነ እቅድ አለዉ! የየትኛዉም ማህበረሰብ አባል ብትሆን፥ የምትጫወተዉ ሚና እና ለእግዚአብሔር አካል ሙላት ፋይዳ አለህ። ለእርሱ ክብር እንድታመጣለት እየጠበቀህ ነዉ!
"የእስራኤልን ልጆች ማኅበር ሁሉ ድምር፥ በየወገናቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ በየስማቸው ቍጥር፥ ወንዱን በየራሱ፥ ውሰዱ።"
ኦሪት ዘኁልቁ 1:2
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ትንቢተ ኢሳይያስ 43:1፦ "አሁንም ያዕቆብ ሆይ፥ የፈጠረህ፥ እስራኤልም ሆይ፥ የሠራህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ተቤዥቼሃለሁና አትፍራ፤ በስምህም ጠርቼሃለሁ፥ አንተ የእኔ ነህ።"
- የዮሐንስ ወንጌል 10:14-15፦ "መልካም እረኛ እኔ ነኝ፥ አብም እንደሚያውቀኝ እኔም አብን እንደማውቀው የራሴን በጎች አውቃለሁ የራሴም በጎች ያውቁኛል፤ ነፍሴንም ስለ በጎች አኖራለሁ።"
- ወደ ኤፌሶን 4:11-13፦ "እርሱም አንዳንዶቹ ሐዋርያት፥ ሌሎቹም ነቢያት፥ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፥ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ፤ ሁላችን የእግዚአብሔርን ልጅ በማመንና በማወቅ ወደሚገኝ አንድነት፥ ሙሉ ሰውም ወደ መሆን፥ የክርስቶስም ሙላቱ ወደሚሆን ወደ ሙላቱ ልክ እስክንደርስ ድረስ፥ ቅዱሳን አገልግሎትን ለመሥራትና ለክርስቶስ አካል ሕንጻ ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 73
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።