The Pentateuch Leviticus

Dedicating Persons and Things

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 27 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 72 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዘሌዋውያን መጨረሻ ክፍል እንካን ደህና መጡ ! ከ 72 ክፍሎች በኃላ ይህ ጠንካራው ይሆናል ፤ ይህ ክፍል ስለ ስለት(ስጦታ) ነው ፡፡ ስለ ስጦታ ባሰብን ጊዜ የሰርግን ስጦታ እናስባለን ፡፡ ዘሌ 26 እግዚአብሄር “ትዕዛዜን ከጠበቃችሁ የተትረፈረፈ ምግብ እሰጣችኃለሁ፣ መገኘቴን እና በምድራችሁም ሰላምን ነገር ግን እነዚህን ነገሮች የማታደርጉ ከሆናችሁ ጭንቀት፣ በሽታ፣ ጦርነትና እና ጠላትነጥን አመጣባችኃለሁ “ ብሉ የተናገረውን ብቻ አጥንተናል ፡፡ አሁን ሙሴ ስጦታ ማድረግን ያደርሳል ፤ ስጦታ በህግ የምደርግ ነገር የለውም ፤ አር. ኬ. ሀሪሰን የተናገረው “ ስጦታ ለእግዚአብሄር ሰው ወይም ንብረት በተለየ ስለት ግንኙነት ከህግ መደበኛነት ውጪ የቆመ ፍላጎት ነው” ፤ ስጦታዎች የሆነ ሰው ከእግዚአብሄር ጋር ያደረገውን የተለየ ስምምነት ይወክላሉ ፡፡

ኮንስታብል እነዚህን የስጦታ ገለፃዎች ሰጥቶአል፡

  1. በጠቅላላው ስጦታዎችን እንድናደርግ አልታዘዝንም ፡፡
  2. ስጦታዎች የሰዎች የተፈጥሮ ፍላጎቶች ናቸው ምክንያቱም እግዚአብሄርን ወደው ወይም ከእርሱ የሆነ ነገር ፈልገው በራሳቸው የሚያደርጉአቸው ናቸዉ ፡፡
  3. እግዚአብሄር ህዝቦቹ ስጦታዎችን(ስለቶችን) እንዲያደርጉለት ይጠብቃል ፡፡
  4. እግዚአብሄር በእዉነት ስጦታቸውን(ስለቶችን) እንዲጠብቁ(እንዲፈፅሙ) ይጠብቃል ፡፡

ሙሴ ለእግዚአብሄር ስዕለት ለሚያደርጉ እስራኤላዊያን ጥቂጥ ኃይለኛ መመሪያዎችን ፅፎአል ፤ ስለትን የመጠበቅ ጥቅም በመፅሀፍ ውስጥ የተረጋገጠ ነው ፤ ምሳ(20፡ 25) የሚለው “ ሰው በችኮላ ለእግዚአብሄር የተቀደሰ ነው ብሎ ቢሳል ከተሳለም በኃላ ቢፀፀት ወጥመድ ነው ፡፡” ለእግዚአብሄር በግድየለሽነት ስለት ከማድረጋችሁ በፊት ለነገሩ ትንሽ ሀሳብ ስጡት ፡፡ መክ (5፡ 4-5) የሚለው “ ሰነፎች ደስ አያሰኙትምና ለእግዚአብሄር ስዕለት በተሳልህ ጊዜ ትፈፅመው ዘንድ አትዘግይ የተሳልኸውንም ፈፅመው ፡፡ ተስለህ የማትፈፅም ብትሆን ባትሳል ይሻልሀል ፡፡” ለእግዚአብሄር ስለት ባደረጋችሁ ጊዜ እንደምትፈፅሙት እርግጠኛ መሆን ይኖርባችኃል ፡፡

በተጨማሪም ኢየሱስ እርሱን ለመከተል የምናደርገው ስለትን በጥንቃቄ መመልከት ያለውን ጠቀሜታ አድርሶአል ፤ በሉቃ( 14፡ 26-31) ኢየሱስ የተናገረው፡ “ ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱን እና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እህቶቹንም-አዎ የራሱን ሕይወት እንካን ሳይቀር ባይጠላ- ደቀመዝሙሬ ሊሆን አይችልም ፡፡ ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኃላዬ የማይመጣ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም ፡፡ ከእናንተ ግንብ ሊሰራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ከሳራውን የማይቆጥር ማነው ? ያለዚያ መሰረቱን ቢመሰርት ሊደመድመውም ቢያቅተው ያዩት ሁሉ ፡፡ ይህ ሰው ሊሰራ ጀምሮ ሊደመድመው አቃተው ብለው ሊዘብቱበት ይጀምራሉ ፡፡ ወይም ሌላው ንጉስ በጦርነት ሊጋጠመው የሚሄድ ከሁለት እልፍ ጋር የሚመጣበትን በአንድ እልፍ ሊገናኝ የሚችል እንደ ሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ የማያስብ ንጉስ ማነው ?

ስለት ካደረጋችሁ የኑሮ ሁኔታችሁን፣ ቃላችሁን እና ድርጊታችሁን ወደ ስለቱ መመለስ ይሻላል ፤ እራሳችሁን ከእግዚአብሄር ኃላ መከተልን ባደረጋችሁ ጊዜ ዋጋውን ትቆጥራላችሁ ፤ ሙሴ ቦኃላ የነበረው ያን ነው ፤ ኢየሱስ ቦኃላ የሆነው ያን ነው ፡፡

ትምህርት

ዘሌዋውያን(27፡ 1-4); ለእግዚአብሄር ልዩ የሆነ ስለት ለሚያደርጉ እስራኤላዊያን እግዚአብሄር ሙሴን የተለየ ትዕዛዝ ሰጠው ፤ ለእግዚአብሄር የተለዩ ሰዎችን የተለየ ስለት ማድረግ ለካህናቱ በተለየው ሰው እድሜና ፆታ መሰረት የተለያየ መጠን ያለው ክፍያ ይጠይቃል ፡፡ ከ20-60 አመት እድሜ መጠን ዋጋቸው ለወንዶች 50 ሸቅል ብር እና ለሴቶች 30 ሸቅል ብር ነበር ፡፡

ዘሌዋውያን(27፡ 5-6); እድሜአቸው ከአምስት እስከ 10 የሆኑት ለወንዶች 20 ሸቅል እና ለሴቶች 10 ሸቅል ነበር ፤ ሰዉየው ከአንድ ወር እስከ አምስት አመት ከነበረ ዋጋው ለወንድ 5 ሸቅል እና ለሴት 3 ሸቅል ነበር ፡፡ ቤተሰቦቹ ለልጁ በእግዚአብሄር ፊት ይህን ስለት ያደርጋሉ ፤ ቆይቶ በመፅሀፍ በሀና ህይወት ላይ ይህ ተገልጦ እናየዋለን ፤ በ 1ሳሙ (1፡ 8-11) ሕልቃና ሀና ስታለቅስና አልበላም ስትል አያት ምክንያቱም በመካንነታ ተጨንቃ ነበር ፤ ሀና ለመፀለይ እና በእግዚአብሄር ፊት ለመጥረግ ወደ መቅደስ ሄደች ለመነችም “ አቤቱ የሰራዊት ጌታ ሆይ የባሪያህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ እኔንም ባትረሳ ለባሪያህም ወንድ ልጁ ብትሰጥ ዕድሜውን ሁሉ ለእግዚአብሄር እሰጠዋለሁ ምላጭም በራሱ ላይ አይደርስም ብላ ስዕለት ተሳለች “ (ቁጥር 11) ፡፡ ሀና ለእግዚአብሄር ስለት አደረገች ሳሙኤልም ከተወለደ ቦኃላ ፈፀመችው ፡፡

ዘሌዋውያን(27፡ 7-8); ሰውየው 60 አመት እና ትልቅ ከሆነ ዋጋው ለወንዶች 15 ሸቅል እና ለሴቶች 10 ሸቅል ነበር፤ ግምቱን ለመክፈል በጣም ድሀ የሆኑት ስለቱን ያደረገው መክፈል በሚችለዉ መሰረት ዋጋውን እንዲያስቀምጥላቸው ሰውየውን ለካህኑ ያቀርባሉ ፡፡

ዘሌዋውያን(27፡ 9-13); ቀጣይ እግዚአብሄር በስለቶቻቸው ስለ እንስሳቶች መስዋዕት አወራ ፤ እንደ ስለት አካል ከቀረበ እንስሳዉ ቅዱስ መሆን አለበት ስለዚህ ለቀረበው እንስሳ ጥሩም ይሁን መጥፎ ሰውየው መቀየር ወይም ቅያሬ ማድረግ አይችልም ፡፡ ስለቱ በርኩስ እንስሳ ከተደረገ እና እንደ መስዋዕት ተቀባይነት ከሌለው ካህኑ ዋጋውን ይገምታል ፤ ባለቤቱ እንስሳውን መዋጀት ከፈለገ በዋጋው ላይ ሩቡን ይጨምራል ፡፡

ዘሌዋውያን(27፡ 14-25); እነዚህ ቁጥሮች በንብረት ላይ የተደረገን ስለት ይደርሳሉ ፤ አንድ ሰው ቤቱን ለእግዚአብሄር ከተሳለ ካህኑ ዋጋውን ይገምተዋል ፤ ቤቱን ለመዋጀት ሰውየው ጠቅላላ ዋጋውን ሩብ ጨምሮ ይከፍላል ፤ አንድ ሰው ለእግዚአብሄር የማሳውን ማንኛውንም አካል ከተሳለ ለእያንዳንዱ አምስት መስፈሪያ የገብስ ዘር ለመዝራት የሚያስፈልገው ዋጋው የተገመተው 50 ሸቅል ነበር ፡፡ ማሳው የተሳለው(የተቀደሰው) በኢዩቤልዩ አመት ከሆነ ዋጋው እንዳለ ይሆናል ፤ ከኢዩቤልዩ አመት በኃላ ከሆነ የተቀደሰው ካህኑ እስከ ቀጣዩ ኢዩቤልዩ አመት ድረስ በቀሩት አመታት ቁጥር መሰረት ይወስነዋል ፡፡ ማሳውን የቀደሰው ሰውዬ መመለስ ቢፈልግ ዋጋውን ሩብ ጨምሮ ይከፍላል ከዚያም ባለቤትነቱ ወደ ቀደሰው ሰዉዬ ይመለሳል ፡፡

ዘሌዋውያን(27፡ 26-29); የማይዋጅ ነገር ነበር ፤ ማንም የከብቶቻቸውን በኩራት መዋጀት አይችሉም ምክንያቱም ቀድሞውኑም የእግዚአብሄር ስለሆነ ፡፡ ሩኩስ እንስሳ ከሆነ በዋጋው ላይ ሩብ በመጨመር መልሶ መግዛት ይችላሉ ፡፡ አንድ ሰው ለእግዚአብሄር የሰጠውን ሰዉም ይሁን፣ እንስሳም ወይም መሬት ይሁን መሸጥ ወይም መዋጀት አይችልም ፤ ሰው ለእግዚአብሄር የተሳለውን መልሶ መውሰድ አይችልም ፤ ካደረገው ይሞታል ፡፡

ዘሌዋውያን(27፡ 30-34); የሁሉም ነገር አስራት ከምድር፣ ፍሬ ከአፈር ወይም የዛፎች ፍሬ የእግዚአብሄር ነው ፤ አንድ ሰው ማንኛውም አስራቱን መዋጀት ከፈለገ በዋጋው ላይ ሩቡን ይጨምራል ፡፡ የእረኛው መንጋ እያንዳንዱ አስረኛው እንስሳ ለእግዚአብሄር ቅዱስ ነበር ፤ እነዚህ ሁሉ ትዕዛዞች እግዚአብሄር ሙሴን በሲና ተራራ ላይ ሰጠው ፡፡

ዋይርስቤ የተናገረው አይሁዶች የሚያቀርቡአቸው ሰዎስት አይነት አስራቶች ነበሩ፡

ለሌዋዊያን/ለካህናቱ የሚቀርብ አስራት (ዘኁ 18፡ 21-32) ፡፡

“ ለመቅደሱ የሚያመጡት እና በእግዚአብሄር ፊት የሚበላ “ አስራት (ዘዳ 14፡ 22-27) ፡፡

“ ለድሀ በእያንዳንዱ ሰዎስት አመት የሚሰጥ አስራት” (ዘዳ 14፡ 28-29) ፡፡

አስራት ለእግዚአብሄር የሚደረግ ገንዘብ ነበር ነገር ግን ስለት ሁል ጊዜ ያ ማለት አይደለም ፡፡

መዝጊያ

እግዚአብሄር ለእርሱ የገባነውን ቃላችንን እንድንጠብቅ ይጠብቃል ፤ ከእርሱ ጋር ባለን ስምምነት ታማኞች መሆን ያስፈልገናል ፡፡ ከእስራኤላዊያን አንለይም ፤ ሁላችን መዋጀት ያስፈልገናል ነገር ግን የመጣው በታላቁ ሊቀ ካህን በራሱ በኩል ብቻ ነው ፤ ጴጥሮስ እንደ ተናገረው “ ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ “(1ጴጥ 1፡ 18-19)፡፡

በዘሌዋውያን መፅሀፍ ውስጥ በጠቅላላው ያወራነው በክርስቶስ ደም በኩል ስለሆነው መዋጀት ነው ፤ ለእኛ ክርስቶስ ያደረገልንን ምንያክል እንደተረዳችሁት አላውቅም ፤ ኢየሱስ የተናገረው “ እኔ አስተሰሪያችሁ ነኝ ፤ ያለ እንከን የሆንኩ በጋችሁ ነኝ ፡፡” ዘሌዋውያን ብዙ የሚደረጉ እና ብዙ የማይደረጉ ያሉት መፅሀፍ ነው ነገር ግን ስለ ተስፋ ያለውን ወድጀዋለሁ ፡፡ ይህ ተስፋ በክርስቶስ ደም በኩል መጣ ሁላችንም ለመዋጀት ያስፈልገናል ፡፡

  1. R. K. Harrison, Tyndale Old Testament Commentary: Leviticus (Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 1980), p. 235; quoted in Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Leviticus, p. 219; available online athttps://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/leviticus.pdf.

  2. Constable, p. 218.

  3. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 305.

ጥያቄዎች

  1. ስለት ምንድን ነው ? በህይወታችሁ ያደረጋችኃቸው የስለቶች ምሳሌዎች ምንድን ናቸው ?
  2. ስለት በሚደረግ ጊዜ ለካህኑ የሚደረገው ክፍያ ምንድን ነበር (ዘሌ 27፡ 2-8) ? ስለቶችን ለሚያደርጉ እግዚአብሄር የክፍያ ዘዴ ለምን እንዳቐቐመ ምንድን ታስባላችሁ ?
  3. መክ(5፡ 3-7) አንብቡ ፤ ይህ እናንተን እግዚአብሄር እንዴት ስጦታዎችን እንደሚያይ እንድትረዱ እንዴት ይረዳችኃል ? ለእግዚአብሄር ስዕለት በማድረግ እና አንዴ ለሰው በማድረግ መሀከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው ?
  4. በዘሌ 27 ቁጥር(13, 15, 19 , 27-28, 31) የሆነን ነገር “መዋጀት” ማለት ምን ማለት ነው ? የሆነን ነገር ለመዋጀት ምንድን ዋጋ ይከፈል ነበር ? በ 1ጴጥ (1፡ 18-19) ከክርስቶስ ጋር ይህን እንዴት ይነፃፀራል ?
  5. ኢየሱስን የመከተል ውሳኔአችሁን እንደ ስለት ታዩታላችሁ ? ኢየሱስን ልንከተለው በተሳልን ጊዜ እግዚአብሄር ከእኛ ምንድን ይጠብቃል ? (ሉቃ 14፡ 25-33)
  6. በዘሌ 27 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Leviticus 27:9

“If the vow involves one of the animals that may be brought as an offering to the LORD, any of these he gives to the LORD will be holy.”

ሰዋችንና ነገሮችን መቀደስ

ኦሪት ዘሌዋዉያን 27 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

ኦሪት ዘሌዋዉያን ወደ መደምደሚያዉ በሚቃረብበት ጊዜ፥ ለእስራኤላዉያን የመጨረሻ የሚሆኑ ትዕዛዛት እግዚዓብሔር ለሙሴ ሰጠዉ። በተለይ እንዴት ለእግዚአብሔር መሃላ እንደሚገባ እና መሃላዎችን መዋጀት እንደሚቻል ተነጋግረዋል። በዋናነት ደግሞ በተወሰነ የብር መጠን መሃላዉን ማፍረስ እንደሚቻል ተነጋግረዋል።

እንደ አማኝ ክርስቶስን መከተል ዋጋ ያስከፍላል። ክርስቶስ ኢየሱስ፥ ደቀ-መዝሙሩ መሆን ከፈለክ መስቀልህን ተሸክመህ እርሱን መከተል እንዳለብህ ተናግሯል። ኢየሱስ፥ ዋጋቸዉን የማይተምኑ እና የዚህን ዓለም ነገር አጥብቀዉ የሚይዙ፥ ደቀ-መዛሙርቴ ሊሆኑ አይችሉም ብሏል። ነገር ግን፥ በዚህ ሁሉ ዉስጥ የሚያስፈነድቀዉ እዉነት፥ ክርስቶስ ለአንተ ህይወቱን መስጠቱ ነዉ። ኢየሱስ ዉድ በሆነዉ ደሙ ለኃጥያተኞች ስርየት ለመሆነ መጥቷል። እናም ከክርስቶስ ጋራ የሆነ ህይወት፥ በተለይም ሁሉንም ነገር ለእርሱ አሳልፈህ ስትሰጥና ስትከተልዉ፥ ነፃ እና ምሉዕ ነዉ!

"ለእግዚአብሔርም መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው እንስሳ ቢሆን፥ ሰው ከእነዚህ ለእግዚአብሔር የሚሰጠው ሁሉ ቅዱስ ይሆናል።"

ኦሪት ዘሌዋዉያን 27:9

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የሉቃስ ወንጌል 14:27፦ "ማንም መስቀሉን ተሸክሞ በኋላዬ የማይመጣ፥ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።"

የሉቃስ ወንጌል 14:33፦ "እንግዲህ እንደዚሁ ማንም ከእናንተ ያለውን ሁሉ የማይተው ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም።"

1ኛ ጴጥሮስ መልዕክት 1:18-19፦ "ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 72