Covenant Blessings & Discipline
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 26 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዛሬ ዘሌ 26 እናጠናለን ፤ እንደ አስታዋሽ ሙሴ ዘሌዋውያንን ፃፈ ፡፡ በዘፍጥረት የእኛ አንድ ቃል ዘር ነበር እናም ወደ መሲሁ እንዴት እንዳመለከተ አይተናል ፤ በዘጸዓት የእኛ አንድ ቃል ነፃ አዉጪ ነበር እናም ኢየሱስን እንደ ነፃ አውጪ ህዝቡን ከግብፅ ሲያወጣ አይተናል ፤ በዘሌዋውያን የእኛ አንድ ቃል አስተሰሪይ ነው ፤ ይህ ቃል አስተሰሪይ ማለት ተተኪ፣ ማመካኛ ወይም መሞት ማለት ነው ፤ ኢየሱስ በእኛ ጥፋት እና ኃጢዓት ተወሰደ ከዚያም ስለ እኛ ሞተ ፡፡
ትምህርት
ዘሌዋውያን(26፡ 1); እግዚአብሄር እስራኤልን ጣዖቶችን ወይም የተቀረፁ ምስሎችን ከማምለክ እና ከመስራት እንዲርቁ አስጠነቀቃቸው -“ እኔ አምላካችሁ እግዚአብሄር ነኝና ፡፡” ሙሴያው ኪዳን የሚቀየር ነበር ፤ ይህ ማለት ኪዳኑን ለመጠበቅ ለእግዚአብሄር ሰዎች የሆነ ነገር ያደርጉ ነበር ማለት ነው ፡፡ የኔልሰን ማብራሪያ እንደ ጠቀሰው ጡሩ መሪዎች ህዝባቸው ምን እንደሚያደርግ ወይም እንደማያደርግ እንዲሁም እነዚያ የሚገመቱትን በመጠበቅ ወይም ባለመጠበቅ ያለውን ውጤት በግልፅ በመግለፅ እንዳወቁ እርግጠኞች ይሆናሉ ፡፡ በዘሌ 26 የእግዚአብሄርን ኪዳን ለመፈፀም ሙሴ እስራኤላዊያን እንዲሰሩት የሚፈለገውን እና ከማድረግ እንዲቆጠቡ የሚፈለገውን መሰረተ፤ በተጨማሪም የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ካልፈፀሙ የሚያመጣውንም ውጤት ግልፅ አደረገላቸው ፡፡ ዋይርስቤ እስራኤላዊያን ለምን የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ማክበር እንደሚጠበቅባቸው አራት ምክንያቶች አቅርቦአል፡ 1)” እግዚአብሄር ስለሆነ ነው”; 2) “ምክንያቱም እግዚአብሄር ስላደረገላቸው ነው”; 3) “እግዚአብሄር የሚኖርበት ስለነበር ነው”; 4) “እግዚአብሄር ቃል ገብቶላቸው ስለነበረው ፡፡”
ዘሌዋውያን(26፡ 2); “ ሰንበታቴን ጠብቁ መቅደሴንም ፍሩ ፤ እኔ እግዚአብሄር ነኝ ፡፡” እግዚአብሄር ከስድስት ቀን ፈጠራ በኃላ አረፈ (ዘፍ 2፡ 2) ሰባተኛውንም ቀን እንደ ቅዱስ አወጀው (ዘፍ 2፡ 3) ፤ እግዚአብሄር በተጨማሪ ለእስራኤላዊያን እንደ እረፍት ቀን ሰንበትን መሰረተላቸው (ዘጸ 20፡ 8-10) ፡፡ በዚህ ምክንያት የሆነ ነገር ይመለካላ ማለት ይከበራል ማለት ነው ፤ እግዚአብሄር በመቅደሱ(በመገናኛ ድንካኑ ውስጥ) ስለሚኖር እስራኤላዊያን በመገኘቱ መሆን ይችላሉ ፡፡
ዘሌዋውያን(26፡ 3-5); ሙሴ የእግዚአብሄርን አካሄድ አስቀመጠ፡ “ በስርዓቴ ብትሄዱ ትዕዛዝቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉትም “ ፤ እስራኤላዊያን አማኝ ከሆኑ እግዚአብሄር ዝናብን በትክክለኛው ጊዜ እንደሚሰጣቸው ቃል ገባላቸው ስለዚህ ምድሪቱ ብዙ የምግብ አቅርቦታ ታፈራለች ፡፡ በእርግጥ ወይን እስከሚሰበሰብ ጊዜ ምድሪቱ ብዙ የሚወቃ ስንዴ መስጠት ትቀጥላለች ይህም እንደገና እስከሚዘራ ጊዜ እስኪመጣ ድረስ ይቀጥላል ፡፡ እግዚአብሄር በምድሪቱ በፀጥታ እየኖሩ የሚበሉት የተትረፈረፈ ምግብ ቃል ገባላቸው ፤ ይሁን እንጂ በዓላትን በማክበር ያለማቐረጥ እንዲዘንብ ለማድረግ ሞክረዋል ፡፡
ዘሌዋውያን(26፡ 6-8); እግዚአብሄር ለእስራኤል ተጨማሪ ቃል ኪዳን አደረገ፡ በምድሪቱ ሰላም አደርጋለሁ ፤ ያለማንም አስፈሪነት ትቀመጣላችሁ ፤ አደገኛ እንስሳቶችን አስወግድላችኃለሁ ፤ በምድራችሁ ውስጥ ሰይፍ አያልፍም ፡፡ ዛሬ ስለ እስራኤል ብታወሩ ይህን አታዩትም ፤ አሁን በእስራኤል ሰላም የሌለው እነዚህን ነገሮች አላደረጉም ይሆናል ፡፡ የእግዚአብሄር መገኘት በእነርሱ መሀከል በቁጥር የሚበልጡዓቸውን ጠላቶቻቸውን እንዲያሳድዱአቸው እና እንዲያሸንፉአቸው ያስችላቸዋል፡ “ ከእናንተ አምስቱ 100 ያሳድዳሉ 100 ደግሞ 10,000 ያሳድዳሉ ፡፡”
ዘሌዋውያን(26፡ 9); እግዚአብሄር እንደ ሚያበዛቸው ቃል ገባ ስለዚህ በቁጥር በመብዛት የቀድሞውንም ቃል ኪዳኑን በአይምሮአቸው አገኙት ፤ በዘፍ(1፡ 28) እግዚአብሄር አዳምንና ሂዋንን ባረካቸው “ ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉአት ጋዙአትም “ ፤ በዘፍ(12፡ 1-3) እግዚአብሄር አብራም ቃል ገባለት “ ታላቅ ህዝብም አደርግሀለሁ እባርክሀለሁ ስምህንም አከብረዋለሁ ፤ ለበረከትም ሁን ፤ የሚባርኩህንም እባርካለሁ የሚረግሙህንም እረግማለሁ የምድር ነገዶች ሁሉ በአንተ ይባረካሉ “ ፤ በዘፍ( 15፡ 5) እግዚአብሄር አብራምን ዘሩ እንደ ሰማይ ከዋክብት እንደሚበዛ ቃል ገባለት ፡፡
ዘሌዋውያን(26፡ 10-13); እግዚአብሄር እንደማይተዋቸው ነገር ግን ከእነርሱ ጋር እንደሚኖር እና በመሀከላቸው እንደሚሄድ ቃል ገባላቸው ፤ እግዚአብሄር እንደማይተወን ቃል ገብቶአል ፡፡ የመተው መንፈስ የሚሰማችሁ ከሆነ ከጠላት እንጂ ከኢየሱስ አይደለም ፡፡ በዘጸ 32 አሮን እና ሁሉም እስራኤላዊያን የወርቅ ጥጃ በመስራት ተሳሳቱ ፤ የተሳሳቱ ያሁን እንጂ እግዚአብሄር የተናገረው “ እኔ… የእናንተ አምላክ እሆናለሁ እናንተም ህዝብ ትሆኑኛላችሁ ፡፡“ ጳዉሎስ የእግዚአብሄርን ገደብ ከጣዖት አምልኮ አንፃር እና በህዝቡ መሀከል የሚኖረውን ቃላ ኪዳኑን በ 2ቆሮ (6፡16) ላይ ደግሞታል ፡፡ እግዚአብሄር የባርነት ትስስራቸዉን በግብፅ ሰበረ ስለዚህ በነፃነት መኖር ቻሉ ፡፡ ለእኛም ተመሳሳይ አደረገልን ፤ እግዚአብሄር በእያንዳንዱአ ቀን ከእኛ ጋር ትስስር እንዲኖረው ይፈልጋል ስለዚህ መገኘቱን መለማመድ እንችላለን ፡፡ ለዚህ ስምምነት ያላደረጋችሁት ለምን ነበር ?
ዘሌዋውያን(26፡ 14-17); በቁጥር 14 መጀመሪያ ላይ እግዚአብሄር እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን መታዘዝ ቢተው እና ከእርሱ ጋር ያለቸውን ኪዳን ቢሰብሩ የሚገጥማቸውን ዉጤት ገልፆአል ፡፡ ማክአርቱር የተናገረው “ የሚያቆሽሽ በሽታ “ ቲቢ ወይም ለምፅ ሊሆን ይችላል ፤ አይኖቻቸው ማየት ይደክማሉ በዚህም ህይወታቸው እየራቀ ይሸሻችኃል ፤ የምትዘሩትን ዘር ጠላቶቻችሁ ይበሉታል ፤ እግዚአብሄር ከእናንተ በዞረ ጊዜ በጠላቶቻችሁ ትሸነፋላችሁ ፤ ማንማ ሳያሳድዳቸው ይሸሻሉ ፡፡
ዘሌዋውያን(26፡ 18-22); እነዚህ ሁኔታዎች እስራኤል እግዚአብሄርን እንዲያከብር ምክንያት ካልሆኑ ለኃጢዓታቸው “ሰባት ጊዜ” እንደሚቀጣ ቃል ገባ ፤ “ሰባት ጊዜ” የሚለው ሀረግ በቁጥር 21፣ 24 እና 28 ተደግሞአል፡፡ እግዚአብሄር ሰማዩን እንደ ብረት(ዝናብ የሌም) ያደርገዋል እናም ምድርም እንደ ናስ(ጠንካራ መሬት) ስለዚህ ፍሬ መስጠት አትችልም ፡፡ እስራኤላዊያን ወደ እግዚአብሄር በጠላትነት ካደረጉ ለኃጢዓታቸው “ሰባት ጊዜ” መቅሰፍቱን ያበዛዋል ፤ እግዚአብሄር እነርሱን እና ከብቶቻቸውን እንዲያጠቁ የሜዳ እንስሳቶችን ይልክባቸዋል ይህም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ መውረድን ያመለክታል(ያመጣል) ፡፡
ዘሌዋውያን(26፡ 23-26); እስራኤል የእግዚአብሄርን ቅጣት ለመቀበል እምቢ ካለ ለኃጢዓታቸው ሰባት ጊዜ እመታችኃለሁ ፤ “የቃል ኪዳንም በቀል ይበቀላችሁ ዘንድ” የሌሎች ህዝቦች ሰይፍን ያመጣባቸዋል ፤ እግዚአብሄር በመሀከላቸውም ቸነፈርን ይልክባቸዋል ለጠላትም እጅ ይሰጣቸዋል ፤ እንጀራ የሚያቀርቡበትን ይቆርጣል(ያቆማል) በዚህም ምክንያት አስር ሴቶች ተመሳሳይ ምጣድ ይጠቀማሉ ፤ ለሚበላም የሚበቃ ምግብ አይኖርም ፡፡
ዘሌዋውያን(26፡ 27-33); እስራኤል የማይታዘዝ ከሆነ እግዚአብሄር “በኃይለኛ ጠላትነት ” ያደርጋልም ለኃጢዓታቸው “ ሰባት ጊዜ” ይቀጣቸዋል ፤ የወንድ ልጆቻቸውን እና ሴት ልጆቻቸውን ስጋ እስኪበሉ ርሀቡ ታላቅ ይሆናል ፤ እንደዚህ አይነት መናቆር(ጭራቅነት) በ 2ነገ፣ በ ሰቆ ኤር እና በኤር ተገልፆአል ፡፡ እግዚአብሄር ኪዳኑን ለመጠበቅ የውድቀታቸውን ዉጤት ፃፈው ፤ ትልቅ ቦታዎቻቸውን ያጠፋል፣ መሰዊያዎቻቸውን ይቆራርጣል ከዚያም በጣዖቶቻቸው ላይ የሞተ ሰዉነታቸውን ይከምራል ፡፡ እግዚአብሄር ይተዋቸዋል ! ለኪሳራ(ለውድመት) ከተማቸውን ይቀንሳል፣ የመስዋዕታቸውን ጣፋጭ ሽታ ለማሽተት አይፈቅድም፣ ምድሪቱን ያጠፋል፣ የወደመች እንድትሆን ከተማቸው ይፈቅዳል፣ በህዝቦች መሀከል ይበትናቸዋል በተጨማሪም ከኃላቸው እንዲያሳድዳአቸው ሌሎችን ህዝቦች ይፈቅድላቸዋል ፡፡
ዘሌዋውያን(26፡ 34-39); እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ወደ ግዞት(ወደ ሶሪያዊያን እና ባቢሎናዊያን) በተናቸዉ ስለዚህ ምድሪቱን መለሰ ምክንያቱም ሰንበቱን ስለአላከበሩ ፤ እነዚያ ከኃ የቀሩት ሁሉ የጠላቶቻቸው አስፈሪነት ነበር የቅጠል ድምፅ እንካን ፍርሀት አመጣባቸው ፡፡ በጠላቶቻቸው ፊት ሲሸሹ እርስ በእርሳቸው ተደነቃቀፉ ፤ በኃጢዓታቸው ምክንያት በሌሎች ህዝቦች መሀከል ተንገላቱ ፡፡
ዘሌዋውያን(26፡ 40-46); እግዚአብሄር እስራኤላዊያን በእርሱ ላይ ሀጢዓት እንደሚሰሩ ያዉቅ ነበር ስለዚህ ከእርሱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚመልሱበትን አማራጭ አቀረበ፡ “ ነገር ግን ኃጢዓታቸውን እና የአባቶቻቸውን ኃጢዓት - በእኔ ላይ ያደረጉትን ጠጣርነትን(ደንዳናነትን) ቢናዘዙ “ ፤ ኃጢዓታቸዉን በተናዘዙ ጊዜ እግዚአብሄር ከያዕቆብ፣ ከይስሐቅ እና ከአብርሃም ጋር የነበረውን ኪዳን እንደሚያስታውስ ቃል ገባ ፡፡ እግዚአብሄር እንደ ማይተዋቸው፣ እንደ ማያጠፋቸው ወይም ከእስራኤላዊያን ጋር የነበረውን ኪዳን እንደማይሰብር ቃል ገባ ምክንያቱም ከግብፅ ካወጣቸው አባቶቻቸው ጋር የነበረውን ኪዳን ስለሚያስታውስ ፤ እግዚአብሄር የተናገረው ምንድን ነበር ? እግዚአብሄር ሁለተኛ እድል እንደሚሰጣቸው ቃል ገባላቸው ፡፡
መዝጊያ
መስቀሉ ሁለተኛ እድላችን ነው ፡፡ ለእስራኤላዊያን እግዚአብሄር ሳያቐርጥ ፍቅሩን ለእነርሱ ማፍሰሱ ትርጉም አይሰጣቸውም ፤ ሁል ጊዜ ይስቱ ነበር ነገር ግን እኛም እስታለን ፡፡ በብሉይ ኪዳን ደም ነበራቸው ምክንያቱም ምህረት ለመቀበል በስርየት ቀን እንስሳትን ይሰዋሉ ፤ ነገር ግን ያንን አናደርግም ምክንያቱም ኢየሱስ እንደ ተናገረው እሱ ሁለተኛ እድላችን ነው ፡፡ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ሌላ እድል እየሰጠን ነው ፤ ዛሬ ፀሎቴ ያንን እድል እንድትቀበሉ እና ወደ እርሱ እንድትመለሱ ነው ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 190.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), pp. 301–302.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 163.
ጥያቄዎች
-
ሙሴያዊ ኪዳን ምንድን ነበር (ዘሌ 26; ዘዳ 28) ? ይህ እግዚአብሄር ከአብርሃም ጋር ካደረገው ኪዳን(ዘፍ 17፡ 1-14) እና ከሌሎች መፅሀፍ ቅዱሳዊ ኪዳኖች ጋር እንዴት አድርጎ ይለያል ? (ዘፍ 9፡ 8-17)
-
በዘሌ (26፡ 1-3) እግዚአብሄር ያዘዘውን እስራኤላዊያን ከታዘዙ ለታዛዥነታቸው በቁጥር(4-13) በተጠቀሱትን ተስፋዎች ይሸለማሉ ፤ ለመያዝ ከባድ የሆነ መታዘዝን መሰረት ያደረገ የሚቀያየር ሽልማት ትፈልጋላችሁ ? አሁን ለእግዚአብሄር በመታዘዛችሁ ሽልማታችሁ ምንድን ነው (ማቴ 25፡ 21; ገላ 6፡ 9; ቆላ 3፡ 23-24) ? ይህ እንዴት እግዚአብሄር ለጠየቃችሁ ታዛዥ እንድትሆኑ ያበረታታችኃል ?
-
እግዚአብሄር በቁጥር (1-3) ለትዕዛዙ በቁጥር (14-39) ለአለመታዘዛቸው ዉጤት ምን እንደሚያደርግ ገልፆአል ፤ ይሁን እንጂ በቁጥር(40-42) ከቅጣታቸው ይቅርታ እንዲቀበሉ እድልን ሰጣቸው ፤ የዘላለም ቅጣታችን እና ወቃሻችን ዛሬ የመጨረሻ ይቅርታችን ምንድን ነው ? (ዮሐ 3፡ 16; 14፡ 6; ሐዋ 4፡ 11-12; 1ዮሐ 1፡ 9)
-
ጳውሎስ ዘሌ(26፡ 12) በ 2ቆሮ (6፡ 16) ጠቅሶታል ፤ እነዚህ ጥቅሶች እንዴት አድርገው ያስቸግሩአችኃልም ያበረታቱአችኃል ? ቆሮንቶስ ላይ ለመጥቀስ ይህን ጥቅስ ጳዉሎስ ለምን እንደመረጠ ምንታስባላችሁ ?
-
በዘሌ 26 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Leviticus 26:11-13
“I will place My residence among you, and I will not reject you. I will walk among you and be your God, and you will be My people. I am Yahweh your God, who brought you out of the land of Egypt, so that you would no longer be their slaves. I broke the bars of your yoke and enabled you to live in freedom.”
የኪዳን በረከቶች እና ቅጣት
ኦሪት ዘሌዋዉያን 26 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እስራኤልዉያን የሰጣቸዉን ደንቦች ከተከተሉ እና ትዕዛዛቱን በሚገባ ከጠበቁ፥ እግዚአብሔር አምልክ አብዝቶ እንደሚባርካቸዉ የተስፋ ቃል ሰጥቷቸዋል። የሚባርከዉም የእጃቸዉን ስራ ብቻ ሳይሆን ትልቅ የሆነዉን ሰላም እና ነፃነት ወደእነሱ እያመጣ ህልዉናውንም ደግሞ ከህዝቡ ጋር በማድረግ ነዉ። እግዚዓብሔርን መከተል ወይም ደግሞ የራሳቸዉን መንገድ የመምረጥ እድል ነበራቸዉ። አምላክ እግዚአብሔር ግን ኃጥያታቸዉን በመናዘዝ፣ የደም መሥዋዕትን በማቅረብ እና ወደ እርሱ እንዲመለሱ በመፍቀድ ሁለተኛ እድልን ሰጥቷቸዋል። እግዚአብሔር፥ የራሱ ህዝብ የሆኑቱ እንዲከተሉት እና እንዲያምኑት አጥብቆ ይፈልጋል።
ዛሬም ይህ እዉነት ነዉ! ጌታ፥ በእያንዳንዱ ቀን እርሱንና መንገዱን እንድትከተል በክርስቶስ ደም በኩል ይጓጓል። በእርሱ ነፃነት፣ ፍቅር እና ሰላም አለ! እንደ አማኝ መንፈስ ቅዱስ በአንተ ዉስጥ በማደር፥ ሁልጎዜ ከአንተ ጋራ ይሆናል! ዛሬ፥ በዚህ የተስፋ ቃል እረፍ! አምላክህ እና ጌታህን እግዚአብሔርን በሙሉ ልብህ፣ ነፍስህ፣ ሃሳብህና ኃይልህ ለመፈልግ ምርጫህ አድርግ።
"ማደሪያዬንም በእናንተ መካከል አደርጋለሁ፤ ነፍሴም አትጸየፋችሁም። በመካከላችሁም እሄዳለሁ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ፥ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ። ባሪያዎች እንዳትሆኑአቸው ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ፤ የባርነታችሁን ቀንበር ሰብሬአለሁ፤ ቀና ብላችሁ እንድትሄዱ አድርጌአችኋለሁ።"
ኦሪት ዘሌዋዉያን 26:11-13
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ትንቢተ ኢሳይያስ 57:15፦ "ለዘላለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።"
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:16፦ "የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?"
1ኛ ዮሐንስ መልዕክት 4:12፦ "እግዚአብሔርን ማንም ከቶ አላየውም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ሆኖአል።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 71
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።