Sabbath Years and Jubilee
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 25 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና ስለ ሰንበት ጥቅም እና እስራኤላዊያን እንዲያክሩአቸው ስለታዘዙዓቸው ሰባት በዓላት ተምረናል ፡፡ የሰንበት እና የበዓላቱ አላማ እግዚአብሄር አድርጎላቸው የነበረውን እና ለእስራኤላዊያን የሚያደርግላቸውን ማስታዎስ ነበር ፤ በተጨማሪም ሁሉም በዓል ወደ መሲሁ ያመለክታሉ ፡፡ እንደ ክለሳ ሰባቱ በዓላት፡
- ፋሲካ
- ያልቦካ(እርሾ የሌለው) የቂጣ በዓል
- የበኩራት ፍሬ በዓል
- ጴንቴኮስታ
- የመለከት በዓል
- የስርየት ቀን
- የዳስ በዓል
እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን አድስ ቀን አቆጣጠር ሰጣቸው ፡፡ ዛሬ ከ50 አመታት በላይ በሚሸፍን ትምህርት ይህ ምን እንደሚመስል ዘለን እንገባለን ፡፡
ትምህርት
ዘሌዋውያን(25፡ 1-2); የምድር ባለቤት እግዚአብሄር እንደሆነ እናውቃለን (ቁጥር 2) ፤ በተጨማሪም እግዚአብሄር የሰዎች ባለቤት እንደሆነ እናያለን (ቁጥር 55) ፤ ዋይርስቤ እግዚአብሄር የእውነት “የምድር አምላክ” እንደሆነ ጠቅሶአል ፡፡ እንደ ምድር ጌታ እግዚአብሄር ምን እንደሚያደርግ ህዝቦቹ እንዲያውቁ እርግጠኛ መሆን ይፈልጋል ፤ ቁጥር 1-17 እና 18-22 ለምድር ለቀረው የእግዚአብሄርን ደንቦችን መስመር ያሳያሉ ፡፡
ዘሌዋውያን(25፡ 3); እስራኤላዊያን “ለስድስት አመታት ማሳቸውን ይዘራሉ” ለዕፅዋትም ስድስት አመታት ፍሬውን ይገርዛሉ ፡፡
ዘሌዋውያን(25፡ 4); ሰባተኛው አመት እርፈታቸውን የሚፈፁምበት ይሆናል ፤ እስራኤላዊያን ለስድስት አመታት በምድሪቱ ይሰራሉ ፤ በሰባተኛው አመት ግን የሚያደርጉት ስራ አልነበረም - ማሳቸውንም አይዘሩም ነበር ወይም በሰባተኛው አመት የወይን ቦታዎችን ይከረክማሉ ፤ ምድሪቱን አይነኩም ነበር ፡፡
ዘሌዋውያን(25፡ 5); በራሱ ያደገውን እንካን እንዳያጭዱ ታዘዙ ፡፡
ዘሌዋውያን(25፡ 6-7); ራሳቸውን፣ ባሮቻቸውን፣ የእርሻ ሰራተኞቻቸው፣ ከእነርሱ ጋር የተቀመጡት እንግዶች እን ከብቶቹ ምድሪቱ በሰንበት አመት ያፈራችውን(የሰጠችውን) መመገብ ይችላሉ ፤ ለምድሪቱ እረፍት መስጠት ለምን ጤነኛ ሆነ ? ሳታቐርጥ ከሰራህባት ወደ ታች ትቀንስላች በዚህም ምክንያት ምንም ቀሪ የተፈጥሮ ምግብ አይኖራትም ፡፡ ኮንስታብል እንደ ተናገረው እግዚአብሄር “ ለሞት በምድሪቱ እንዲሰሩ” አይፈልግም ፤ በሰባተኛው አመት መስራት ማቆም ለምን ነበር ትቅሙ ? ራሳቸውን እንደገና የሚሰበስቡበትና የሚታደሱበት ጊዜ ነበር ፡፡
ዘሌዋውያን(25፡ 8-17); ምድሪቱ እንድታርፍ ብቻ አልነበረም የሚደረገው ነገር ግን ሁለቱም የመሬት እና የገንዘብ ብድር ይተው ነበር (ዘዳ 15፡ 1-11) ፡፡ እያንዳንዱን አመት በዳስ በዓል ጊዜ ሁሉም እስራኤል ይሰበሰባል ከህጉም መፅሀፍ ይነበባል (ዘዳ 31፡ 9- 13) ፤ እግዚአብሄር እስራኤላዊያን ወደ ህጉ እንደሚለሱ ይፈልጋል ስለዚህ ለሌላው ስድስት አመታት ያደርጉታል ፡፡ የትምህርት ጊዜው ሲያልፍ እስራኤላዊያን ህጉን እና በዓላቱን ይረሱዓቸዋል አይከተሉዓቸውምም (ኤር 25፡ 8-11) ፤ ሁሉንም ማድረግ አቆሙ ፤ ጠቅላላ ምድሩ በጠላቶቻቸው የተያዘ ይሆናል፡፡ ለምን ? ምክንያቱም የእግዚአብሄርን ህግ አላከበሩም ፡፡ እግዚአብሄር ስርዓት በሰጠን ጊዜ (ዘሌ 18) ካልተከተልነው ሁል ጊዜ ዉጤት አለው (ዘሌ 20) ፤ ምድሪቱን እንዲያሳርፉ እግዚአብሄር ነገራቸው ፤ በዚያ ፋንታ በሀሰት አምላክ ተጫወቱ በተጨማሪም ለሞት በመስራት ስለ ምድሪቱ ስራ ራሳቸውን አደነደኑ ፤ ስለዚህ እግዚአብሄር ለ 70 አመታት ከምድሪቱ ውጪ ላካቸው ፡፡
ዘሌዋውያን(25፡ 18); “ ስርዓቴንም አድርጉ ፍርዶቼንም ጠብቁ አድርጉትም “ ፤ በግልፅ ያ አልሆነም ፤ ምክንያቱም የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ አልጠበቅም የቁጥር 19 በረከትንም አጡት ፡፡
ዘሌዋውያን(25፡ 19); “ ምድሪቱም ፍሬዋን ትሰጣለች እስክትጠግቡም ድረስ ትበላላችሁ ፤ በእርሱዋም ውስጥ በጸጥታ ትኖራላችሁ ፡፡” ምድራቸውን አጡዓት ምክንያቱም ሰንበትን አልጠበቅም ፤ ምድራቸውን አጡ ምክንያቱም ስራ መስራታቸውን ስለቀጠሉ ፡፡
ዘሌዋውያን(25፡ 20-21); እግዚአብሄር ለሰዎስት አመት የሚበቃ በስድስተኛው አመት ብዙ ፍሬ በመስጠት ለእስራኤላዊያን እንደ ሚጠነቀቅላቸው ቃል ገባላቸው !
ዘሌዋውያን(25፡ 22); እስራኤላዊያን ለሰዎስት አመታት መሰጠት ለምንድን አስፈለጋቸው ? በሰባተኛው አመት ስላልዘሩ በስምንንተኛው አመት ይዘራሉ ነገር ግን እስከ ዘጠነኛው አመት ፍሬው አይመጣም(አይደርስም ነበር) ፤ ለስድስተኛው፣ ለሰባተኛው እና ለስምንንተኛው አመታት መሰጠት ያስፈልጋቸዋል ፡፡ እግዚአብሄር የሚሰጣቸው ለሰባቱ አመታት ብቻ አልነበረም ለሚመጡት 50 አመትም እንጂ (ዘሌ 25፡ 8) ! ነገር ግን እስራኤላዊያን የእግዚአብሄር ቃልን አልታመኑም ፡፡ እነዚህ ሁሉ ለሰባት አመቱ ጊዜ ቆይታ ብቻ ነበር ነገር ግን ወደ ቁጥር 8 በመመለስ የኢድቤልዩ አመት ላይ እንመልከት ፡፡
ዘሌዋውያን(25፡ 8-12); ሙሴ ሰባት አመታትን ሰባት ጊዜ ሰባተኛው አመት የሰንበት አመት የነበረውን ዋና ሀሳብ አስቀመጠ ፤ በ 50ኛው አመት በስርየት ቀን መለከት ይነፋል ፤ ታላቁ ካህን ለስርየት እንስሳትን ለመሰዋት በእግዚአብሄር ፊት የሚሄድበት ቀን ነበር ፡፡ በእስራኤላዊያን ቀን አቆጣጠር እንካን ቅዱስነት ነበር ፤ የኢድቤልዩ አመት ቅዱስ ነበር ፡፡
ዘሌዋውያን(25፡ 13-17); ዋይርስቤ እግዚአብሄር የኢድቤልዩ አመት ጊዜ እግዚአብሄር የጠራቸውን አራት ቃላቶች ለይቶአል ፡፡
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Leviticus, p. 200; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/leviticus.pdf
ምህረት(ንስሀ) (ቁጥር 9)፡ በስርየት ቀን እግዚአብሄር ለንስሀ ጠራቸው ፡፡
መተው(መላቀቅ) (ቁጥር 10)፡ ሁሉም አካል መላቀቁን እርግጠኞች መሆን ነበረባቸው !
እረፍት (ቁጥር 11)፡ አይዘሩም፣ አያጭዱም ወይም አይሰበስቡም ነገር ግን ተሰጥቶአቸው የነበረውን ይበላሉ ፡፡
መታደስ (ቁጥር 13-17)፡ ሁለቱም ንብረትና ምድር ፡፡
ዘሌዋውያን(25፡ 18-23); ፍሬ የሰንበትን አመቶች እና ኢድቤልዩ አመትን ከማድረግ(ከማክበር) መጣ ፤ እግዚአብሄር ምድር ይዞዓል ስለዚህ ለዘለቄታው አልተሸጠም ፡፡ድሀና ሀብታም እኩል ነበር ፤ ለረጅም ጊዜ ማንም ከሌላው የሚበልት ሊኖረው አይችልም ምክንያቱም በኢድቤል አመት ሁሉም ነገር ተስተካክሎአል ፡፡ አንድ ሰው በንስሀ፣ በመለቀቅ፣ በእርፍትና በመታደስ ሂደት ውስጥ በሚሄድ ጊዜ እንደገና ይነቃቃሉ(ይነሳሳሉ) !
መዝጊያ
በመጨረሻ ይህን መነቃቃት እንዴት እንዳገኛችሁት ማወቅ ትፈልጋላችሁ ? ኢሳያስ ተንብዮ የነበረው የሚመጣው መሲህ እነዚህን ነገሮች እንደሚያደርግ ነበር ፡፡ ለድሆች መልካም ዜናን እንዲያመጣ፣ የተሰበሩ ልቦችን እንዲፈውስ፣ ለምርኮኞች ነፃነትን እንዲያውጅ እና ለታሰሩት ነፃነትን እንዲያደርግ የእግዚአብሄር መንፈስ መሲሁን ቀባው (ኢሳ 61፡ 1) ፡፡ በኢድቤልዩ አመት ምንድን እንደሆነ ኢሳያስ ገልፆታል ! “የእግዚአብሄር ሞገስ አመት ብሎ በማወጅ “ አልፎአል ፤ የኢድቤልዩ አመት የእግዚአብሄር ሞገስ አመት ነበር !
እስራኤላዊያን በንስሀ፣ በመለቀቅ፣ እረፍትና መታደስ ጊዜ ውስጥ ሄደዋል ስለዚህ ሁሉንም እንደገና መጀመር ይችላሉ ፤ በዚህም ሁሉንም እንደገና የምንጀምርበት መንገድ በ(ሉቃ 4) መሰረት ወደ ክርስቶስ በመመለስ እንደሆነ አምናለሁ ፤ ለነፃነት ወደ እርሱ እንመለስ ! የኢድቤልዩ አመትን በራሳችን ህይወት ውስጥ የምንለምድበት መንገድ በክርስቶስ በኩል ነው ፡፡
Warren Wiersbe, Be Holy. (Wheaton, IL: Victor Books, 1996), p.149.
Wiersbe, p.153.
ጥያቄዎች
-
ሰንበታዊው አመት መቼ ይከሰታል ? ኢዩድቤሌዩ አመት መቼ ይከሰታል ? (ዘሌ 25፡ 2; 8-9)
-
እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን በሰባተኛው አመት የእረፍት መፈጸሚያ ለምድሪቱ ሰንበት እንዲሰጡ ለምንድን አዘዛቸው (ዘሌ 25፡ 4)? ይህን ትዕዛዝ ለሚታዘዙ የእግዚአብሄር በረከት ምንድን ነበር ?(ዘሌ 25፡ 20-22)
-
በዘሌ (25፡ 23) እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ምድሪቱ የእርሱ እንደሆነች እና እንግዶች እንደሆኑ አስታወሳቸው ፤ ያ እንዴት ተስፋ ይሰጣቸዋል ? ይህ አለም የእኛ ቤት አለመሆኑን ማወቅ እንዴት ተስፋ ይሰጠናል ?(ዘጸ 19፡ 5; 1ቆሮ 29፡ 15; ዕብ 11፡ 13-16)
-
እስራኤላዊያን በእምነት ለምድሪቱ የሰንበት አመታትን ጠብቀው ነበር ? ቅጣታቸው ምን ነበር (ዘሌ 25፡ 4; 26፡ 34, 43; 2 ዜና 36፡ 21; ኤር 25፡ 11) ? የእግዚአብሄርን ምድር መልካም ባላደራዎች እንዴት ትሆናላችሁ ?
-
ስለ ምድሪቱ ትዕዛዙን ለሚጠብቁ እግዚአብሄር የሰጠው አስደናቂ ተስፋ ምንድን ነበር (ዘሌ 25፡ 18-22) ? በእናንተ መታዘዝ እና በእርሱ ታማኝነት ምክንያት እግዚአብሄር ለእናንተ ያደረገላችሁ እና የፈፀመላችሁ ተስፋ ምንድን ነው ?
-
በዘሌ 25 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Leviticus 25:4-5; Leviticus 25:17-18
“But there will be a Sabbath of complete rest for the land in the seventh year, a Sabbath to the LORD: you are not to sow your field or prune your vineyard. You are not to reap what grows by itself from your crop, or harvest the grapes of your untended vines. It must be a year of complete rest for the land. ” — Leviticus 25:4-5 “You are not to cheat one another, but fear your God, for I am Yahweh your God. You are to keep My statutes and ordinances and carefully observe them, so that you may live securely in the land.” — Leviticus 25:17-18
የሰንበት ዓመታቶች እና
ኢዮቤልዩ
ኦሪት ዘሌዋዉያን 25 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እግዚአብሔር ለሙሴ ግልፅ በሆነ መንገድ ምድራቸዉን በየሰባት ዓመቱ የሰንበት እረፍትን እንዲያደርጉ ትዕዛዝን ሰጥቶታል። ይህ እንዴት እንደሚከናወን ዝርዝር መመርያዎችን በመስጠት አብራርቶላቸዋል። እስራኤላዉያን በስድስተኛዉ ዓመት፥ ለየሰንበት ዓመት እና እንደዉም ለቀጥዩ ዓመት የሚሆን በቂ የሆነ ሰብል ይሰበስባሉ። ሁለቱንም ዓመትም ይህንን መጠቀም ይችላሉ። እስራኤላዉያን ደንቦቹን፣ ህግጋቶቹን እና ስርዓቶቹን በትክክል ከጠበቁ በሰጣቸዉ ምድር ላይ በሰላም እንደሚኖሩ የተስፋ ቃል ገባላቸዉ። የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚሰጣችሁ በመታመን፥ ለአንድ ዓመት ሙሉ አካላዊ ሥራን አለምስራት አስባችሁታል? እና ደግሞ አማራጫቸዉስ ምንድን ነበረ? ያሉበትን ሁናቴ በራሳቸዉ እጅ እንዳለ፥ መስራት የሚያሻቸዉን ነገር እና የተሻለ ብለዉ የሚያስቡትን መከወን ይችሉ ነበር።
በተመሳሳይ መንገድ፥ የጌታን መንገድ ፍለጋ በተከተልህ እና እርሱ እንደሚዘጋጅ በምትታመንበት ጊዜ፥ እንድታርፍ ጌታ አዝዞሃል። እና ታድያ፥ ከራሳችን እጅ ነገሮችን ማዉጣት፣ በእግዚአብሔር የተስፋ ቃል በማያወላዳ እምነት መታመን እና በእርሱ መንገድ መመላለስ ምጥ የሚሆንብን ለምንድን ነዉ? ዛሬ፥ ለማረፍ ጌታን ፈልግ፥ ለቀንህ እርሱ ባለዉ እቅድ እና መንገድ ታመን! ከራስህ እጅ አዉጣዉና በእምነት ተመላለስ።
"በሰባተኛው ዓመት ግን ለምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት፥ ለእግዚአብሔር ሰንበት፥ ትሁን፤ እርሻህን አትዝራ፥ ወይንህንም አትቍረጥ። የምድራችሁን የገቦ አትጨደው፥ ያልተቈረጠውንም የወይንህን ፍሬ አታከማች፤ ለምድሪቱ የዕረፍት ሰንበት ዓመት ይሁን።"
ኦሪት ዘሌዋዉያን 25:4-5
"እኔም እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ሰው ባልንጀራውን አያታልል፥ ነገር ግን አምላክህን ፍራ። ሥርዓቴንም አድርጉ፥ ፍርዶቼንም ጠብቁ አድርጉትም በምድሪቱም ውስጥ በጸጥታ ትኖራላችሁ።"
ኦሪት ዘሌዋዉያን 25:17-18
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 147:7-9፦ "ለእግዚአብሔር በምስጋና ዘምሩ፥ ለአምላካችንም በመሰንቆ ዘምሩ፤ ሰማዩን በደመናት ይሸፍናል፥ ለምድርም ዝናብን ያዘጋጃል፤ ሣርን በተራሮች ላይ ያበቅላል፤ ለምለሙንም ለሰው ልጆች ጥቅም። ለሚጠሩት ለቍራዎች ጫጩቶች ለእንስሶችም ምግባቸውን ይሰጣል።"
የማቴዎስ ወንጌል 6:24፦ "ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው ማንም የለም፤ ወይም አንዱን ይጠላል ሁለተኛውንም ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሁለተኛውንም ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።"
የማቴዎስ ወንጌል 11:28-29፦ "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ። ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 70
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።