The Sabbath and The Feasts
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 23-24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዘሌዋውያን 23 እና 24 ስለ ቀን አቆጣጠር ናቸው ፤ ዋይሰርቤ የፃፈው “ ከወቅቱ ጋር እና ከህዝቡ ታሪክ ጋር የተሳሰረ ቀን አቆጣጠር እግዚአብሄር እስራኤልን ሰጣት ፤ ያልጠለመደ አቆጣጠር ነበር ምክንያቱም ለእስራኤል ባለፉት እግዚአብሄር ያደረገላቸውን የሚያጠቃልል ብቻ አልነበረም ወደ ፊት እግዚአብሄር ለእስራኤል የሚያደርግላቸውን ያጠቃልላ ተብሎ ይጠበቃልም ፡፡” ሰባት ፆሞችና በዓላት ነበሩ ፤ ከእነዚህ ፆሞችና በዓላት ውስጥ ጥቂቶቹ ከሌሎቹ በጣም ተከባሪ ነበሩ ፡፡ እነዚህን ሰባት በዓላትና ፆሞችን ማሳወቅና እያንዳንዳቸው እንዴት ወደ መሲሁ እንደሚያመለክቱ ማሳወቅ እፈልጋለሁ ፡፡
ትምህርት
ዘሌዋውያን(23፡ 1-2);ዮም ኩፐር የጠቀሳቸውን ሰዎች እንሰማለን ፤ እግዚአብሄር የተመረጠ በዓል ነው ፤ ሁሉም ወደ መሲሁ ያመለክታሉ ፤ እግዚአብሄር በራሳቸው አቆጣጥር እንዲያከብሩትና እንዲያስታውሱት የተመረጠ ጊዜ እንዲኖራቸው ፈለገ ፤ ለአንድ ቀን፣ ለብዙ ቀናት ወይም ለብዙ ሳምንታት ሊቆይ ይችላል ፡፡
ዘሌዋውያን (23፡ 3-4); ሁሌ ሰባተኛ ቀን ላይ እስራኤላዊያን የሚሰሩት ስራ የለም ፤ ለበዓላቱ ይህ በስህተት የተወሰደ አይሆንም ነበር ፤ ማንኛውንም ስራን የሚያጠናቅቅ መፈፅም አይቻልም ፡፡ ዛሬም በቀድሞዋ ኢየሩሳሌም ከተማ በሰንበት ካሜራ መሸከም እንካን አይቻልም ፤ እሁድ እንደሆነ አስተዋልን ምክንያቱም ለህይወት ኢየሱስ ተመልሶ የመጣበት ቀን ነበር ፡፡ ይህ በሆነውን ቀን ሙጭጭ ብላችሁ አትያዙት ግን የቀኑን ረፍት ዉሰዱ ፤ የራሳችሁን ሰንበት ፈልጉ ፤ እነዚህ ቅዱስ ጉባኤዎች በተመረጡ ጊዜዎቻቸው ያውጃሉ ፡፡
ዘሌዋውያን(23፡ 5); ፋሲካ በመጀመሪያው ወር በመጋቢት/ሚያዚያ በአስራ አራተኛው ቀን ምሽት ላይ እና ለአንድ ቀን ብቻ የሚከበር ነው ፡፡ እስራኤላዊያን ፍፁም ጠቦት በመግደል፣ ሂሶጰ በመውሰድ በደሙ ውስጥ ይነክሩታል ከዚያም በቤቶቻቸውም ጉበኖቻቸዎና በቐሚዎች ላይ ያስቀምጡታል ፤ በመጀመሪያ በግብፅ ነበር የተፈፀመው በዚያም ምክንያት በቤት ውስጥ ያሉትን ልጆች የሞት መንፈስ አልፋቸው ነበር ፡፡
በማቴ (26፡ 17) ኢየሱስ ፋሲካን አከበረ ፤ እንዴት ፋሲካ ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ? 1ቆሮ 5፡ 7 አድስ መጠን(ቡድን) ከመስራታችሁ በፊት አሮጌውን እርሾ አስወግዱ ይላል ፡፡ ለተሰዋው ፋሲካ በጋችን ለክርስቶስ በእርግጠኝነት ያልቦካን ነን ፤ ኢየሱስ ብሉይ ኪዳንን ሊፈፅም መጣ ፡፡
ዘሌዋውያን(23፡ 6); የቂጣ በዓል በተመሳሳይ ወር በአስራ አምስተኛው ቀን እና ለሰባት ቀን ይቆይ ነበር (መጋቢት/ሚያዚያ) ፤ በእነዚህ ቀናቶች የሚበላው እርሾ የሌለው ቂጣ ነበር ፤ እርሾ የኃጢዓት ምልክት ነበር ፤ እርሾ የለም ማለት ኃጢዓት የለም ነው ፡፡
ዘሌዋውያን(23፡ 7-8); በመጀመሪያው ቀን ቅዱሱ ጉባኤ ይደረጋል አይሰሩምም ነበር ፤ እስራኤላዊያን ለሰባት ቀናት የእሳት መስዋዕት ያቀርባሉ ፤ በመቀጠል በሰባተኛው ቀን ቅዱስ ጉባኤ ያደርጋሉ ስራም አይሰሩም ፤ ሰባተኛውና አንደኛው ቀን ተመሳሳይ ነበሩ ፡፡ በእያንዳንዶአ ቀናት እርሾ የሌለው ቂጣ ይበላሉ ፡፡ ወንዶች እንዲሳተፉባቸው የሚያስፈልጉ ሰዎስት በዓላት ናቸው ከእነርሱም ውስጥ ይህ አንዱ ነው ፤ 2ቆሮ (5፡ 21) “ እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሄር ጸድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢዓት ያላወቀዉን እርሱን ስለ እኛ ኃጢዓት አደረገው ፡፡”
እርሾ የሌለው ቂጣ የሚናገረው ክርስቶስ ኃጢዓት እንደ ሌለበት ነው ፡፡
ዘሌዋውያን(23፡ 9-14); የበኩራት ፍሬ በመጋቢት/በማዚያ ይከበር ነበር ፤ እስራኤላዊያን የገብስ ምርት ምርጣቸውን ያመጣሉ ፤ ስለ ምርታቸው በማመስገን ካህኑ ነዶውን ለእግዚአብሄር ይወዘውዛል ፡፡ በፋሲካና በቂጣ በዓል ተመሳሳይ መስመር ውስጥ ለአንድ ቀን ብቻ የበኩራት ፍሬ በኒሳን በመጀመሪያው ወር በአስራ ስድስተኛው ቀን ይከበር ነበር ፤ ማክአርቱር የሚለው “ የበኩራት ፍሬ ለእግዚአብሄር ሁሉንም ምርት መሳልን ይወክላል በተጨማሪም ሁሉንም ምርት ለማምጣት ቃል መግባት ነበር ፡፡”1ቆሮ (15፡ 20) የሚለው “አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቶአል ” ፤ የበኩር ፍሬ የክርስቶስን ትንሳኤ ያመለክታል ፤ ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ነው ፡፡
ዘሌዋውያን(23፡ 15-22); ጴንቴኮስታ የነዶ መስዋዕት ካመጡበት ቀን አንስቶ ሙሉ ሰባት ሳምንታትን እስከ ሰባተኛው ሳምንት ቀጣይ ቀን ድረስ 50 ቀናት በመቁጠር ያከብራሉ ፤ በግንቦት/በሰኔ አድስ የእህል መስዋዕት ለእግዚአብሄር ያቀርባሉ ፡፡ በግሪክ “ሃምሳ” ጴንቴኮስታ ማለት ነው ፡፡ እስራኤላዊያን ሁለት በእርሾ የተጋገረ እንጀራ፣ አራት ካርትዝ(ቀለም መያዛው አይነት እቃ) ዱቄት፣ አንድ አመት የሆናችው እንከን የሌለባቸው ሰባት ወንድ ጠቦቶች፣ አንድ ወይፈን እና ሁለት በጎች ያመጣሉ ከዚያም አንድ ወንድ ፍየል እንደ ኃጢዓት መስዋዕት እና አንድ አመት የሆናቸው ሁለት ጠቦቶች እንደ ህብረት መስዋዕት ይሰው ነበር ፡፡
ካህኑ በእግዚአብሄር ፊት ከእንጀራ ጋር እንደ በኩራት እንደ ሚወዘወዝ መስዋዕት ይወዘውዘው ነበር ፤ ምንም ስራ እንዳይሰሩ አዋጅ ያደርጋሉ ፤ ይህ የስንዴ ምርት ነበር ፡፡ የምድራቸዉን ጫፍ አያጭዱም ግን ለድሀ ሰዎች ይተውታል ፤ ሐዋ (1፡ 5) የሚለው “ ዮሐንስ በውኃ አጥምቆ ነበርና እናንተ ግን ከጥቂት ቀን በኃላ በመንፈስ ቅዱስ ትጠመቃላችሁ አለ “ ፤ ሐዋ (2፡ 4) የሚለው “ በሁሉም መንፈስ ቅዱስ ሞላባቸው መንፈስም ይናገሩ ዘንድ እንደ ሰጣቸው በሌላ ልሳኖች ይናገሩ ጀመር “ ፡፡ ይህ ለወንዶች እንዲሳተፉበት የሚያስፈልጋቸው ሌለኛው በዓል ነበር ፤ በክርስቲያን አስተሳሰብ ይህ የጀመረው በፋሲካ እን ለ50 ቀናት እንደሚቀጥል ነው ፡፡
ዘሌዋውያን(23፡ 23-25); የመለከት በዓል ለአንድ ቀን በሰባተኛው ወር በወሩ መጀመሪያ ቀን ይከበራል (መስከረም/ጥቅምት) ፤ ይህ የእረፍት፣ የመታሰቢያነት እና የድል በዓል አከባበር የሙሉ ቀን እረፍት ነበር ፡፡ የተቀደሰ ጉባኤ እና በእሳት ለእግዚአብሄር የሚደረግ መስዋዕት ነበር ፤ በእስራኤል ይህ እንደ አድስ አመት በመባል የሚታወቅ እና ጡሩንባ ሲነፉ ታዩአቸዋላችሁ ፡፡ ማቴ(24፡ 310 የሚለው “ መላዕክቱንም ከታላቅ መለከት ድምፅ ጋር ይልካቸዋል ከሰማያትም ዳርቻ እስከ ዳርቻው ከአራቱም ነፋሳት ለእርሱ የተመረጡትን ይሰበስባሉ ፡፡” በክርስቶስ የእስራኤል እንደገና መሰብሰብ እስካሁን አልሆነም ፤ ይህ የመሲሁ ሁለተኛ መምጣት ነው ፡፡
ዘሌዋውያን(23፡ 26-32); በስርየት ቀን ሁሉም ሰው ኃጢዓቱን በአንዳ ፍየል ላይ በማስቀመጥ ወደ ፍየላአን ይለቅቐታል ፤ ሁለተኛውን ፍየል ይገድሉት ነበር ፡፡ ይህ ከሰባተኛው ወር(መስከረም/ጥቅምት) በአስረኛው ቀን ለአንድ ቀን ብቻ የሚከበር ነበር ፤ ይህ የስርየት ቀን ነበር ፡፡ አይሁዶች እንደ ዮም ኪፑር ያውቁታል ፡፡ ስራ የማይሰሩበት የተቀደሰ ጉባኤ ነበራቸው ፤ እስራኤላዊያን እራሳቸውን ዝቅ ማድረግ ተለማመዱ ከዚያም የእሳት መስዋዕት አቀረቡ ፡፡ በእግዚአብሄር ፊት ለራሳቸው ስርየት ያደርጋሉ ፤ 1ቆሮ(15፡ 3) የሚለው “እኔ ደግሞ የተቀበለሁትን ከሁሉ በፊት አሳልፌ ሰጠኃችሁ፡ ክርስቶስ ስለ ኃጢዓታችን ሞተ “ ፤ ኤፌ (5፡ 2) የሚለው “ክርስቶስም እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሄርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባና መስዋዕት አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ ፡፡”
ዘሌዋውያን(23፡ 33-44); የመቅደስ(የድንካኑ ማደሪያ) በዓል የዳስ በዓል በመባል ይታወቅ ነበር ከሰባተኛው ወር(መስከረም/ጥቅምት) በአስራ አምስተኛው ቀን ለሰባት ቀናት ይከበራል ፤ በመጀመሪያው ቀን እግዚአብሄር ህዝቡን ከግብፅ ያወጣበትን እና በዳሶች ውስጥ ያስቀመጠባቸውን እያከበሩ ምንም ስራ አይሰሩም ፤ ከዛፎች ትንሽ ዳሶች ይሰራሉ ለሰባት ቀናትም በእነርሱ ውስጥ ይኖራሉ ፤ ሁሉም ወንዶች የሚገኙበት ሌላው በዓል ነበር (ዘዳ 16፡ 16) ፤ እስከዛሬም ያደርጉታል ፤ በመንገዶቻቸው ዳርቻዎች መሄድ ትችላላችሁ ከዚያም ዳሶቻቸውን ታያላችሁ ፡፡ ዘካ(14፡ 16) የሚለው “ በኢየሩሳሌም ላይ ከመጡት ከአሕዛብ ሁሉ የቀሩት ሁሉ ለንጉሱ ለሰራዊት ጌታ ለእግዚአብሄር ይሰግዱ ዘንድ የዳስን በዓልንም ያከብሩ ዘንድ በየዓመቱ ይወጣሉ ፡፡” ይህ እስካሁን አልሆነም ፤ ዘካሪያስ ትንቢት ነበር ፡፡
መዝጊያ
ወደ ኢየሱስ የሚያመላክቱ ሰባቱ በኣላት እነዚህ ናቸው ! የረጋ(የሚገባ) የሚያምር ስዕል ፤ እዚህ ነገ የምንሸፍናቸው ብዙ ተጨማሪ አሉ ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2007), p. 227.
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 160.
ጥያቄዎች
-
በዘሌ 23 እንደ ተዘረዘረው እስራኤላ የሚያከብራቸውን ሰባት አመታዊ በዓላትን ጥቀሱ ?
-
እርሾ የሌለው የቂጣ በዓል የአንድ ሳምንት ስነ ስርዓት አስፈላጊነቱ ምንድን ነበር (ዘጸ 12፡ 14-20) ? ክርስቶስ ይህን ስነ ስርዓት እንዴት ፈፀመው (1 ቆሮ 5፡ 7-8) ?
-
ከፋሲካ ቦኃላ የመከር በዓል ለምን ያክል ጊዜ ይቆይ ነበር (ዘሌ 23፡ 15-16) ? የመከር በዓላን(በተጨማሪ ጴንቴኮስታ በመባል ይታወቃል) እስራኤላዊያን እንዴት ነበር እንዲያከብሩ የታዘዙት ? በአድስ ኪዳን የተገለፀው የጴንቴኮስታ አከባበር እንዴት ነበር (ሐዋ 2፡ 1-4) ? የመከር በዓል የሚያስደስት ስነ ስርዓት ነበር፤ በመንፈስ ቅዱስ ደስታችሁን ያለማቐረጥ እንዴት ማክበር ትችላላችሁ(ሮሜ 14፡ 17) ?
-
በዘሌ 16 ከስርየት ቀን አንፃር ለካህናቱ ዝርዝር ይገኛል ፤ በዚህ ቀን ጊዜ የህዝቡ ኃላፊነት ምንድን ነበር (ዘሌ 23፡ 26-32) ?
-
በሚከተሉት ጥያቄዎች ከበዓላቱ እና ከክርስቶስ አንፃር ግንኙነቱን ተመልከቱ፡ በምንድን በዓል ጊዜ ኢየሱስ ተሰቀለ(ዘሌ 23፡ 5; ዮሐ 19፡ 14) ? በምንድን በዓል ጊዜ ተቀበረ እና ከዚያስ ተነሳ ?
-
በዘሌ (23-24) በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Leviticus 23:1
“The LORD spoke to Moses: ‘Speak to the Israelites and tell them: These are My appointed times, the times of the LORD that you will proclaim as sacred assemblies.’”
የሰንበት በዓላት(ድግሶች)
ኦሪት ዘሌዋዉያን 23-24 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
"የተቀደሰ ጉባኤ" የሚለዉ ሃረግ በአንድ ምዕራፍ ዉስጥ አስራ አንድ ጊዜ ተፅፏል። እነዚህ ጉባኤዎች ለህዝቡ በየጊዜዉ ልማድ ካደረጉት ስራቸዉ እና እንቅስቃሴያቸዉ ገለል ብለዉ፥ እግዚአብሔርን ወደ ማምለክ ልባቸዉን የሚመልሱበት ስፍራዎች ናቸዉ። እግዚአብሔር ስምቱንም ቀናቶች ቅዱስ ጉባኤ ብሎ ሰይሟቸዋል። ከእነዚህም ዉስጥ የፋሲካ በዓል፣ እርሾ የሌለበት ቂጣ በዓል እና የስርየት ቀን ይገኙበታል። እናንተም የተፈጠራችሁት እግዚዓብሔርን ለማምለክ ነዉ። ምናልባትም በፆም፣ መሥዋዕትና ስጦታ በማቅረብ፣ በእርሱ በጎነት ሃሴት በማድረግ እና በተስፋ ቃሉ በማረፍ ሊሆን ይችላል።
እንደ አዲስ ኪዳን አማኝ፥ እነዚህን የተቀደሱ ጉባኤዎችን ህግጋት የምታከብርበት ትዕዛዛት የለህም። ቢሆንም፥ ጳዉሎስ አማኞችን ሁልጊዜ ደስ እንዲላቸዉ እና በሁሉም ነገር እንዲያመሰግኑ አዟቸዋል። ዛሬ፥ በህይወትህ ዉስጥ ያለዉን የጌታን ታማኝነት አስታዉስ እና አመስግን! እምነትህን ስላጠነከሩት ፈተናዎችህ፥ በህይወትህ ዉስጥ የእግዚአብሔርን መልካምነት እና በጎነት የሚያሳዩ ያንተ ደስታዎች ጌታን አመስግን! እግዚአብሔር አምላክ፥ ዉዳሴ እና ምስጋና የሚገባዉ ነዉ!
"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ የተቀደሰ ጉባኤ ብላችሁ የምታውጁአቸው በዓላቶቼ፥ የእግዚአብሔር በዓላት፥ እነዚህ ናቸው።"
ኦሪት ዘሌዋዉያን 23:1-2
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ሰቆቃወ ኤርሚያስ 3:22-23፦ "ሔት። ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምሕረት የተነሣ ነው፤ ርኅራኄው አያልቅምና። ማለዳ ማለዳ አዲስ ነው፤ ታማኝነትህ ብዙ ነው።"
1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:31፦ "እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።"
1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:16-18፦ "ሁልጊዜ ደስ ይበላችሁ፤ ሳታቋርጡ ጸልዩ፤ በሁሉ አመስግኑ፤ ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ እናንተ ነውና።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፈት፡ ክፍል 69
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።