Separation of the Priests
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ስለ ዘሌዋውያን ሁሉንም በሚያውቅ የአይሁድ ሰው ባገኝን ጊዜ ታስታውሳላችሁ ? ለማስተማር እና ከሌሎች ጋር ለመጋራት እንደ በቃችሁ እንዲሰማችሁ እፈልጋለሁ ፡፡ ዛሬ በዘሌ 22 ማስተማር እንደምትችሉ እንዲሰማችሁ እፈልጋሉ ፤ ተስፋ አደርጋለሁ በፍርሀት እንደማትሮዩ ፤ ዕብ(5-6) የሚለው ቀላል ነገሮችን ከዚህ በኃላ ልንማር እንደማይገባን ነገር ግን ጥልቅ እና በእግዚአብሄር ያደጉ ነገሮችን ልንማር ይገባናል ፡፡
በእነዚህ ጥናቶች የምጠቀማቸው ማብራሪያዎች ዝርዝር አኚህ ናቸው፡
- የዮሐንስ ማክአርቱር የመፀሀፍ ቅዱስ ሀተታ ሰጪ(ማብራሪያ)
- የኔልሰን አድስ መፅሀፍ ቅዱስ ማብራሪያ ተታ ሰጪ(ማብራሪያ)
- አድስ የአሜሪካ መፅሀፍ ቅዱስ ማብራሪያ በማርቆስ ኤፍ. ሮከር(በዘሌዋውያን ላይ ብቻ የፃፈውን)
- የአለም መፀሀፍ ቅዱሳዊ ማብራሪያ በዮሐንስ ኢ. ሀርትልይ
- ጅፕስ የህግ ማብራሪያ
ከላይ የተዘረዘሩትን ማብራሪያዎች ከማንበባችሁ በፊት የመጀመሪያው ቦታ መሄድ የሚያስፈልጋችሁ መንፈስ ቅዱስ ነው ፤ መፅሀፍ የሚለው ማንም ሊያስተምራችሁ አያስፈልግም; መንፈስ ቅዱስ ያስተምራችኃል (ዮሐ 14፡ 26)፡፡
ትምህርት
ዘሌዋውያን(22፡ 1); አስታውሱ ዘሌ 22 እንዴት ካህናቱ እንደ ቅዱስ ሰው ሕይወታቸውን እንዲኖሩ የተሰጣቸው መመሪያ ነው ፤ አንዳንድ ጊዜ በአገልግሎታችሁ መንገድ ውስጥ ደግምችሁ ደግማችሁ በምትሄዱ ጊዜ ህይወት የሌለው ሊሆንባችሁ ይችላል ፤ ሙሴ ካህናቱን ህይወት የሌላቸው እንዳይሆኑ አስጠነቀቀ ፡፡ ዋይሰርቤ የፃፈው “ ኖቨሊስት ጆርጅ ማክዶናልድ የተናገረው ከቅዱስ ነገሮች ዉጪ ጋር እንደ ተለመደ አደራረግ ለመለኮት የደነደነ ምንም ነገር የለም ፡፡” ዋይርስቤ የሚለው ካህናቱን ህይወት የሌላቸው ከመሆን ለመጠበቅ በሰዎስት ነገሮች ውስጥ እንሄዳለን፡ መጀመሪያ ንፁህ ያልሆንን ካህናት አለመሆናችንን እርግጠኞች እንሁን ፡፡
ዘሌዋውያን(22፡ 2-4); ሙሴ አሮንንና ልጆቹን ከቅዱስ መስዋዕት ጋር አክብሮት በተሞላበት እንዲያደርጉ ነገራቸው ፡፡ ማንኛውም ንፁህ ያልሆነ ቅዱስ መስዋዕቱን ከቀረበ ይጠፋል ፤ አንዳንድ ጊዜ ያ ማለት ይሞታል በተጨማሪም አንዳንድ ጊዜ ያ ማለት በማስወገድ ሌላ ቦታ ይቀመጣል ፡፡ ማንም የአሮን ዘር የቆዳ በሽታ(ለምፅ) ወይም ፈሳሽ ያለበት ንፁኅ እስኪሆን ድረስ ቅዱሱን መስዋዕት መብላት አይችልም ፡፡
ዘሌዋውያን(22፡ 5-7); ካህኑ ርኩስ ነገር ካሰራ እስከ ማታ ድረስ ርኩስ ይሆናል ከዚያም ቅዱሱንም መስዋዕት አይበላም ነበር በዉሃ ሰውነቱና ካልታጠበ በቀር ፡፡ የመንፃቱ ሂደት የውሃው ድርሻ ብቻ አልነበረም የጊዜም ነበር ፤ ፀሀይ መጥለቐ በመጣ ጊዜ ብቻ ንፁህ ይሆን ነበር ፡፡ ከዚያም የእርሱ ምግብ የነበረውን ቅዱሱን መስዋዕት መብላት ይችላል ፡፡
ዘሌዋውያን(22፡ 8); ካህኑ በተፈጥሮው የሞተን እንስሳት ወይም በዱርአዎሬዎች የተቦጨቀውን አይበላም ነበር ፤ ዝም ብሎው ህዝብ ይችላል ግን ካህናቶቹ ተለይተዋል ፡፡ አስታውሱ የእግዚአብሄር ጠቅላላ አላማው እነርሱን መለየት ነበር ፡፡
ዘሌዋውያን(22፡ 9); እግዚአብሄር ካህኑን ትዕዛዙን እንዲጠብቅ ፈለገው ፤ ካህኑ በእዉነቱ ከአሰልቺ በላይ መሄድ ይችላል ህይወቱም ይቆሽሻል ፤ ግብዝነት ተብሎ ይጠራል ፡፡ ግብዝነት በቤተ ክርስቲያን ላይ እየሄደ ነው ፤ ለዚያ ነው የእግዚአብሄር እንቅስቃሴ እንደ ሚያስፈልገን የማምነው ፡፡ አንድ ሰው ካህን ለመሆን ንፁህ ያልሆኑት የእነዚህ ነገሮች አካል መሆን አይችልም ፤ በማቴ (23፡ 25-27) ኢየሱስ ኃይማኖታዊ ግብዝነትን ገልፆአል ፡፡
ዘሌዋውያን(22፡ 10-16); ሁለተኛ ያልተለዩ(ያልበቁ) እንግዶች ሊሆኑ ይችላሉ ፤ ካህኑ ሌሎችን መባረክ ቢፈልግም ትዕዛዙ ሰዎቹን እንዳይመግብ ይናገራል ፤ ካህናቱ እንግዶችን መመገብ አይችሉም ፡፡ የቅርብ ቤተሰባቸው ብቻ የተሰዋውን ምግብ መብላት ይችላሉ ፤ አንዳንድ ጊዜ የተለየ መሆን ማለት በእውነት ማድረግ የምትፈልጋአቸውን ነገሮች አይሆንም ማለት ነው ፡፡ ካህናቱ የሆነን ሰው(ባሪያን) ከገዙት መካፈል አይችልም ፡፡ የካህኑ ሴት ልጅ ከቤተሰብ ውጭ(በህግ ወንደ) ያለ የሆነን ሰው ካገባች አንድኛቸውም መብላት አይችሉም ፡፡ ሴቲቱ ልጅ ባላ የሞተባት ሴት ወይም የተፋታች ከሆነ ጥንቃቄ የምታደርግላቸው ልጆች ከሌሉዓት እና ለመኖር ወደቤት ከተመለሰች አባታ ከእርሱዋ ጋር ምግቡን መካፈል(መጋራት) ይችላል ፡፡ ካህናቱ ቅዱሱን መስዋዕት አይንቁም ነበር ፡፡
ዘሌዋውያን(22፡ 17-30); ሰዎስተኛ ተቀባይነት የሌለው መስዋዕት እንዳልፈቀደ እርግጠኛ መሆን አለበት፤ የህብረት መስዋዕት ጉድለት የሌለበት በግ ወይም እንስሳ መሆን ነበረበት ፡፡ የሆነ ሰው “ በማቅለል ጆሮ የሌለው በግ ቢሆንም ችግር የለውም ” በሚሆን አስተሳሰብ ተቀባይነት የሌለው መስዋዕት ያመጣል ፡፡ ጠንቃቆች ካልሆንን ወጥ ከሆነው ስርዓት ወደ ኃጢዓት ልንሄድ እንችላለን (ሚል 1፡ 13) ፤ 2ሳሙ( 24፡ 24) እግዚአብሄር የምርጣችን ዋጋ እንደሚገባው ይናገራል ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር በጉዞአችሁ ጫፎችን ለመቁረት መሞከርን አቁሙ ፤ ፍፁሙ ብቻ ተቀባይ ነው ፡፡
ዘሌዋውያን(22፡ 31-33); እግዚአብሄር የተናገረው “ ትዕዛዞቼን ጠብቁም አድርጉአቸውም ፤ እኔ እግዚአብሄር ነኝ ፤ ቅዱስ ስሜን እንዳተረክሱ ፡፡“ እንደ ኔልሰን ማብራሪያ “ የእግዚአብሄር ሰዎች፣ ስሙ፣ የአሁን ድርጊቱ ህዝቡን በመቀደስ እና የቀድሞው ድርጊቱ ከግብፅ ባርነት በመታደግ ሁሉም እንደ እስራኤል የአምልኮ መሰረት ተሰጣቸው፡፡” እግዚአብሄር “ እኔ የእናንተ አምላክ ነኝ ! ማለትን ቀጠለ እንድታደርጉዓቸው በጠየኩዓችሁን በአነዚህ ስርዓቶች እመኑኝ ! ከግብፅ ያወጣኃችሁ እኔ ነኝ ፡፡”
መዝጊያ
ምርጣችሁን እግዚአብሄር የሰጣችሁ የት ነው ? በሪቫይቭ ት/ቤት እና በንባባችሁ የት ናችሁ ? ወደ ገበታው መታዘዛችሁን አምጥታችኃል ?
ዘሌ 22 ምርጣችንን እንድናመጣ እና ከመመሪያው ጋር እንድናጣበቅ ያስታውሰናል ፤ የእግዚአብሄር ቃል ምንድን ይላል ? ቅዱስ ካህን ያስፈልገናል ፡፡ ሁሉም የገለፁት አንድ ካህን አለ፡
ዕብ (7፡ 26)፡ “ ቅዱስና ያለ ተንኮል ነውርም የሌለበት ከኃጢዓተኞችም የተለየ ከሰማያትም ከፍ ከፍ ያለ እንደዚህ ያለ ሊቀ ካህናት ይገባናል ፡፡”
ዕብ(9፡ 14)፡ “ ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሄር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሄርን ልታመልኩ ከሞተ ስራ ሕሊናችሁን ያነፃ ይሆን ? “ አሁን ሕያው እግዚአብሄርን እንድናገለግልግል ተፈቅዶልናል !
ኤፌ(5፡ 27)፡ “ እድፈት ወይም የፊት መጨማደድ እንዲህ ያለ ነገር ሳይሆንባት ቅድስትና ያለ ነውር ትሆን ዘንድ ክብርት የሆነችን ቤተ ክርስቲያን ለራሱ እንዲያቀርብ ፈለገ ፡፡”
ያለ ነቀፋ እና በቅዱስነት ለመኖር በሊቀ ካህኑ ላይ የተመሰረትን ነን ስሙም ኢየሱስ ነው ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2007), p. 225.
Wiersbe, p. 226.
Wiersbe, p. 226.
Wiersbe, p. 226.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 185.
ጥያቄዎች
-
በበዓላት መቆሸሽ(ርኩሰት) ሁኔታ ላይ አለማገልገል ለካህኑ ምንድን ነበር ጥቅሙ (ዘሌ 22፡ 2-3) ? እስራኤል ወደ እግዚአብሄር ስለ ሚቀርብ ስዕል በምንድን ያውቁ ነበር (ዘሌ 22፡ 9) ?
-
አሮጌው ኪዳን ለተሸለው አድስ ኪዳን ጥላ እንደነበር እንዴት ልናውቅ ቻልን ? (ቆላ 2፡ 16-17; ዕብ 8፡ 4-13; 10፡ 1)
-
በዘሌ (22፡ 7) እግዚአብሄር የተናገረው አንድ ሰው እንደገና ፀሀይ በጠለቀች ጊዜ ንፁህ መሆን ይችላል የአይሁዶችን ቀን መጀመሪያ ያመለክታል ፤ ምንድን ተስፋ ያሳስበናል ከእግዚአብሄር በአድስ ምህረት እያንዳንዱ ቀን መጀመር ስንችል (ሰቆ ኤር 3፡ 22-23) ?
-
በዘሌ (22፡ 10-13) የተጠቀሰውን የተቀደሰውን መስዋዕት መብላት የሚችለው ወይም የማይችለው ማነው ? በእስራኤል ከአሜሪካ ታሪክ በሚበልጥ ለባሮያዎች የለየ አስተሳሰ አለ ፤ በዘሌ (22፡ 11) ለባሪያዎች የእግዚአብሄርን ርህራሄ እንዴት ታዩታላችሁ ?
-
በዘሌ (22፡ 31-33) መሰረት ስሙን እናክብር ለቃሉም ታዛዝ እንሁን ፤ በህይወታችሁ ዛሬ እንዴት ትኖሩታላችሁ ?
-
በዘሌ 22 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Leviticus 22:3
“Say to them: If any man from any of your descendants throughout your generations is in a state of uncleanness yet approaches the holy offerings that the Israelites consecrate to the LORD, that person will be cut off from My presence; I am Yahweh.”
ኦሪት ዘሌዋዉያን 22 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት መፈፀም ጠንከር ያለ ጉዳይ ነዉ። "ያ ሰው ከፊቴ ተለይቶ ይጥፋ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።" የሚለዉ ሃረግ፥ ቅን፣ አፍቃሪ እና ፀጋ የሞላበት አባት እግዚዓብሔር ሲናገር መስማት ለአንዳንዶች ይህን መረዳት ሊከብዳቸዉ ይችል ይሆናል። እንዲህ ቢሆንም ቅሉ፥ እስራኤላዉያን ትዕዛዛትን ለመከተል ይህን ያክል የጠነከረ እና የከረረ ነበር።
ከእግዚአሔር መገኘት ተለይቶ መጥፋት ምን ማለት እንደሆነ አስባችሁት ታዉቃላችሁ? ሙሉ በሙሉ የጨለመ፣ ተስፋ የሌለዉ እና የብርሃን ጭላንጭል የማይታይበት ነዉ! ዛሬ፥ ስለ እግዚዓብሔር ህልዉና አመስግን! መንፈስ ቅዱስ፥ ሁልጊዜ እና ቀኑን ሙሉ ከእናንተ ጋራ ስለሆነ በምትሄድበት ቦታ ሁሉ እርሱን አመስግን! በእርሱ ህልዉና የተነሳ፥ እረፍትን፣ ሰላምን እና ሁሉን ከሚያዉቅ እና ሁሉን ከሚችል አዳኝ ተስፋን ታገኛለህ። የክርስቶስ ስርየት ምስጋና ይግባዉና ከእርሱ መገኘት ምንም ነገር አይለየንም።
"እንዲህ በላቸው፦ ማናቸውም ሰው ከዘራችሁ በትውልዳችሁ ርኵሰት እያለበት የእስራኤል ልጆች ለእግዚአብሔር ወደሚቀድሱት ወደ ቅዱስ ነገር ቢቀርብ፥ ያ ሰው ከፊቴ ተለይቶ ይጥፋ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።"
ኦሪት ዘሌዋዉያን 22:3
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 16:11፦ "የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ።"
መዝሙረ ዳዊት 139:7-10፦ "ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።"
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39፦ "ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎች አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 68
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።