The Pentateuch Leviticus

Holy Conduct of Priests

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 21 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 67 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ብዙ ሀተታ ሰጪዋች ዘሌ 21 ለካህናቱ እንደ ትዕዛዝ መምሪያ እንደሆነ ይገልፃሉ ፤ አዎ ከዘሌ 10 ልብሶች ተሰጥቶአቸዋል ፣ ጥቂት ዝርዝር ስራዎች ተሰጥቶአቸዋል በተጨማሪም ተቀብተዋልም ተለይተዋልም ፤ ነገር ግን አሁንም ብዙ ተጨማሪ ነበር ፡፡ ለሁሉም ቀን ህይወታቸው መምሪያ ያስፈላጋቸው ፤ ካህናት ማግባት ይችሉ ነበር ወይስ አይችሉም ? ይህ ሁሉ የሚመክርው ምንድን እንዲመስል ነበር ?

ማክአርቱር የሚለው “ ከሁሉም እስራኤላዊያን ይልቅ የላቀ የቅድስና ስርዕት ፀባይ የሚያስፈልጋቸው ህጎች ለካህናቱ ተሰጡ ፡፡” በህይወታቸው እና በእስራኤላዊያን ህይወት ውስጥ የሆነውን ምህረት ለማየት ታላቅ ካህናትና ካህናት ምንድን ነበር የሚጠበቅባቸው ስለዚህ በዚህ አገላለፅ ከፍ ማለት አለብን ፤ ካህናት ፍፁም አልነበሩም ፤ ተሳስተዋል ፤ የተጠየቁትን እናውቃለን ፡፡

ትምህርት

ዘሌዋውያን(21፡ 1-2); እግዚአብሄር ሙሴን ካህናቱን የአሮንን ልጆች እንዲነግራቸው አዘዘው ፤ ከእናታቸው፣ ከአባታቸው፣ ከወንድ ልጃቸው፣ ከሴት ልጃቸው፣ ከወንድማቸው ወይም ከቅርብ ቤተሰባቸው ዉጪ ከሞተ ዘመዳቸው ስነስርዕት ጋር በመሆን ራሳቸዉን ርኩስ አያደርጉም ነበር ፤ (ቆይቶ የአሮን ካህናት ልጆች ናዳብና አብዩዱ ባለመታዘዛቸው ሲሞቱ እናያለን በዚህም አልዓዛርና ኢታምር ታዛዥ ሆኑ ፡፡)

ዘሌዋውያን(21፡ 3- 4); ሌላው የተለየው ማንም የሚጠነቀቅላት የሌላት ወጣት ያላገባች እህት ብትኖራቸው ፤ በህግ ብትሞት ምን ይሆናል ? ካህናቱ ምንም ማድረግ የለባቸው ፤ የእነርሱን ጥንቃቄ በመውሰድ ራሳቸውን ማርከስ የለባቸው ፡፡

ዘሌዋውያን(21፡ 5); ካህናቱ ያላአግባብ አያዝኑም ነበር ፡፡ ልክ አምላክ እንደሌላቸው የሀዘን የተለየ ሁኔታ ውጤት የላቸውም ነበር ፤ ካህናቱ ቅዱስ እንዳልሆኑ የሚያመለክትን ማንኛውንም ነገር አያደርጉም ፤ የዚህ ምሳሌ 1ነገ(18፡ 28) ሊመስል ይችላል ፡፡

ዘሌዋውያን(21፡ 6); ካህናቱ ለእግዚአብሄር ቅዱስ እንዲሆኑ እግዚአብሄር ያስቀመጠላቸውን ስርዕት ይከተላሉ ፤ መላጣ ራስ በማድረግ፣ የፂማቸውን ጠርዝ በመላጨት፣ መልክትና ስንጥቅ በማድረግ የእግዚአብሄርን ስም ያሰድቡ ነበር ፤ ካህናቱ በዚህ መንገድ ወደ እግዚአብሄር አይመጡም ፤ የእሳት መስዋዕት(ለእግዚአብሄር ምግብ) ለማቅረብ ቅዱስ መሆን ነበረባቸው ፡፡ ሲሄዱ ተምረውት እንደነበር የሚመስል ነው ፤ ይህ በዘሌ 10 ሆነ አሁን ሙሴ ስለሆነው ፃፈ ፡፡

ዘሌዋውያን(21፡ 7-8); ካህናት በሴተኛ አዳሪነት የረከሰች ወይም በባላ የተፈታችን ሴት ማግባት አይችሉም ፤ ለምን ? ወደ እነርሱ ሌላ ስጋ ያመጣል; ርኩስ ነበር (ዘፍ 2፡ 24; ማር 10፡ 8) ፤ የሚያገቡ ከሆነ እርግጠኛ መሆን ነበረባቸው ማንም ይሁን ያገቡት ልክ እንደነሱ ወደ ቅዱሱ ማህበር ይገባል ፡፡

በአገልግሎት እና በትዳር መሀከል ጭንቀት(ውጥረት) አለ ፤ ቤተሰብ አለን ለዚህ አገልግሎትም ተጠርተናል ፤ ጥንቀት(ውጥረት) ይኖራል ይህን መጠበቅ አለባችሁ ፡፡

ስለ ማግባት ባሰባችሁ ጊዜ 2ቆሮ (6፡ 14-18) አስቡ ፤ ያላመነ እንዳታገቡ በተጨማሪም ሰዎችን ለመቀየር እንዳታገቡ; ይህ አደገኛ ትምህርት ነው ፡፡ እስራኤል ደግሞ ደግሞ ከእነዚህ አለሞች እንዳይቀየጡና እንዳይቀላቀሉ ተነገረ ፤ ይህ ማለት ዛሬ ከእምነት ስርዕት አትቀላቀሉ ማለት ነው(ያ ማለት እስልምና እና ክርስትና) ዘር (ጎሳ) አይደለም ፤ እግዚአብሄር ለካህናቱ የተናገራቸው “ ራሳችሁን እንዳታረክሱ ለብቻችሁ ተቀመጡ ቅዱስ እንደሆናችሁ ተረዱ ! ተለይታችኃል ፡፡”

ዘሌዋውያን(21፡ 9); የካህን ሴት ልጅ እንድ ጊዜ ከሳተች ትሞታለች ከዚያም ትቃጠላለች ፤ ለምህረት እድል አልነበረም ፤ ይህ እግዚአብሄር ለመቅደስ መሪዎቹ ለካህናቱ ወደ ሚፈልገው ስርዓት ወደ ኃላ ይወስዳል…ቅዱስነት፡፡

ዘሌዋውያን(21፡ 10-12); ታላቁ ካህን አሮን ላጁ በሞተ ጊዜ ከስራ ቦታው መውጣትም ራሱንም ማርከስ አይችልም ፤ ጥሪው ታላቅ ነበር ምክንያቱም የተቀደሰው ቅዱሱ ዘይት በራሱ ላይ ነበር ፤ ልጁን ለመቅበር ስራውን ትቶ መውጣት አይችልም ፤ አሮን ልጆቹን ይወዳቸዋል ስለዚህ የአገልግሎት/ትዳር ውጥረት ልክ በዚያ ክስተት ላይ ትልቅ ነበር ፡፡

ዘሌዋውያን(21፡ 13-15); ካህኑ የሚያገባ ከሆነ ድንግል የነበረች ሴት ማግባት ነበረበት ፤ ቅዱስ ህብረት ለማድረግ ያስፈልገዋል ፤ በእግዚአብሄር እና በእስራኤል መሀከል የፍቅር ግንኙነት ነበር (ሕዝ 16፡ 8-14) ፤ እግዚአብሄር የተናገረው “ አንቺን እስራኤልን ላገባሽ መረጥኩሽ ፤ ፍፁም የምንስማማ ነን ፡፡“ እግዚአብሄር የመረጣቸውን ህዝብ አገባ (ኤር 31፡ 32; ኢሳ 54፡ 5) ፡፡

የእግዚአብሄርና የእስራኤል ይህ ስዕል ሊሰበር አይችልም ፤ የአንድ ስጋ ስምምነት ነው ፤ እግዚአብሄር ከእነርሱ አይለይም ፤ አልፈፀመም ፤ እስራኤላዊያንን አይፈታቸውም ፡፡ ደግመው ደግመው እንደገና እስራኤል ከእግዚአብሄር ተመልሰው መጋዝ ቀጠሉ (ሆሴ 2፡ 7) ፤ እግዚአብሄር ሳያቐርጥ መልሶ ፈለጋቸው ከዚያም “ እዚህ አለሁ” አላቸውም ፤ የካህን ትስስር ከሚስቱ ጋር ወይም በቅርብ ሚስቱ ከምትሆን ጋር ፍፁም መሆን ያስፈልገዋል ፡፡

ዘሌዋውያን(21፡ 16-23); ችግር ከነበረው ካህኑ እግዚአብሄርን የሚወክልበት አማራጭ አልነበረውም ፤ ችግር ከነበረበት ካህኑ ወደ እግዚአብሄር መገኘት ለመምጣት ብቁ አይደለም ፡፡

መዝጊያ

ኢየሱስ ጉድለት በነበራቸውን ሰዎች ተያዘ ! ኢየሱስ አስቂኝ በመሰሉ ሰዎች ተያዘ (ሉቃ 14፡ 21) ፤ ከእነኚህ ሰዎች በኃላ አስቦበት ሄደ ፡፡ ኢየሱስ ፍፁም ካህን ነበር (ዕብ 7፡ 26) ፤ ፍፁም ተጠቂም ነበር (ዕብ 9፡ 14) ፤ በዚህ ነው ከሱጋ መገናኛት የምንችለው ፤ ፍፁሙ ሊቀ ካህን ያለምንም እንከን ራሱን አቀረበ (1ጴጥ 1፡ 19) ፤ ኢየሱስ ፍፁም ነበር ፤ ኢየሱስ አሁን በመቅደሱ ውስጥ መቀመጥ ችሎአል ፤ የሚታመን ፤ ንፁህ ፡፡ የተበላሹ(ችግርኛ) ሰዎችን ዉጪ እንዲቀመጡ መፍቀድ ይችላል (1ጴጥ 2፡ 220 ፤ እንደ ተጎጂ ሳይሆን ኢየሱስ ተቃራኒ አደረገ ! ኢየሱስ ሂዎቱን ሰጠ እሱ ለሚያስፈልጋቸው ተስፋ ቆራጮችም መጣላቸው ፡፡

ከብሉይ ኪዳን ወደ አዲስ ኪዳን የተቀየረ አስደናቂ መልክ ነው ፤ መቅደስ አያስፈልገንም ፤ ሮሜ(5፡ 8) የሚለው “ ገና ኃጢዓተኞች ሳለን “ ፤ የኩራት ጉድለት እያለን ፤ የዝሙት ጊድለት እያለን ፤ የትዕግስት ማጣት ጉድለት እያለን ፡፡ ጉድለት ሰይሙ - ችግር የለውም ! በእነዚህ ጉድለቶች ብንያዝም ፣ በእነዚህ ኃጢዓቶች ብንያዝም(አካላዊ ጉድለት አይደለም) እግዚአብሄር ፍቅሩን ለእኛ አሳይቶናል ክርስቶስ ለእኛ ሞተ ፡፡ ሊቀ ካህኑ አሁን ወደ እኛ መጥቶአል ! በእኛ መንገድ ወደ አባቱ ለመድረስ ተጨማሪ የምናገኝበት መንገድ የለም ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 158.

ጥያቄዎች

  1. ለካህናቱ ለምን የተለዩ ህጎች እንደ ነበሩዓቸው ምንድን ታስባላችሁ (ዘሌ 21፡ 1-24) ? ይህ ከባድ ወይም ተገቢ ያልሆነ ይመስላል ? ታስተራችሁን ወይም መንፈሳዊ መሪያችሁን በተመሳሳይ ግምት ታስባላችሁ ? (1ጢሞ 3፡ 2-10; ቲቶ 1፡ 6-9) ፈፅማችኃል ?
  2. ታላቁ ካህን ከካህኑ እንካን ከእርሱ የሚፈለግ በብዙ የሚበልጥ ነበረው ፤ ለምንድን ነበር መሞተ ወይም በሞቱ ዘመዶች ቤተሰቦቹን ጨምሮ ላይ እንዲገኝ ያልተፈቀደለት (ዘሌ 21፡ 10-12) ?
  3. ታላቁ ካህን ድንግል ማግባት ነበረበት; ባልቴት ማግባት አይችልም፣ የተፈታች ሴት ማግባት አይችልም ወይም በሴተኛ አዳሪነት የረከሰች ማግባት አይችልም ፤ ታላቁ ካህን የክርስቶስ አይነት ከሆነ የእርሱ ሙሽራ ወደ ማን ታመለክታለች ( 2ቆሮ 11፡ 2; ኤፌ 5፡ 27; 31-32) ? ይህ ስርዓት እግዚአብሄር ከእኛ ስለ ሚፈልገው ምንድን ይገልጥልናል ?
  4. ለእግዚአብሄር መስዋዕት በመሰዋዕት በጉድለት ማገልገል የቻለ ከአሮን ዘር ውስጥ መሀከል ካህን የለም (ዘሌ 21፡ 16-23) ፤ እንደ አማኝ ይህ እንዴት ነው የኛ መልክ የሆነው (ኢሳ 53፡ 5; ኤፌ 4፡ 15-25; ዕብ 10፡ 14) ?
  5. የእግዚአብሄርን መቅደስ ማርከስ ማለት ምን ማለት ነው (ዘሌ 21፡ 12) ? የመንፈስ ቅዱስ መቅደሶች ከሆንን ይህን መቅደስ ያረከሰው ምንድን ይመስላል (1ቆሮ 3፡ 16-17) ?
  6. በዘሌ 21 በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin

“The LORD spoke to Moses: ‘Tell Aaron: None of your descendants throughout your generations who has a physical defect is to come near to present the food of his God. No man who has any defect is to come near: no man who is blind, lame, facially disfigured or deformed.’”

ኦሪት ዘሌዋዉያን 21 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

በትዉልድ ዉስጥ የአሮን ዘሮች አካላዊ እንከን ቢኖርባቸዉ፥ ለእግዚአብሔር የምግብን መሥዋዕት ለመስጠት አይቀርቡም ነበር። መሥዋዕት ወደሚቀርብበት ስፍራ እና ወደመጋረጃዉ መጠጋት አይችሉም ነበር። ዛሬ ስለመሲሁ፣ ታላቁ ሊቀ-ካህን ኢየሱስ ክርስቶስ ደም አመስግን! አንተ ከእግዚዓብሔር ጋራ ለዘልዓለም እንድትኖር እንከን እና ነቀፋ በሌለብት ደም ከኃጥያት ሁሉ አንፅቶሃል!

ኢየሱስ ክርስቶስ አካላዊ እንከን ያለባቸዉን ለመፈወስ እና ለማገልገል መጥቷል። ክርስቶስ ኢየሱስ አንተን በወደደበት መንገድ አንተም ሰዎችን የምትወድ ሁን! በተክለ ሰዉነታቸዉ እንኳን ከአንተ የሚለዩትን እንኳን ቢሁኑ! ኢየሱስ የከፈለዉ የሁሉንም ነዉ!

"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለአሮን እንዲህ ብለህ ንገረው፦ ከዘርህ በትውልዳቸው ነውር ያለበት ሰው ሁሉ የአምላኩን እንጀራ ያቀርብ ዘንድ አይቅረብ። ዕውር፥ ወይም አንካሳ፥ ወይም አፍንጫ ደፍጣጣ፥ ወይም ትርፍ አካል ያለው፥"

ኦሪት ዘሌዋዉያን 21:16-18

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የማቴዎስ ወንጌል 4:24፦ "ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፥ ፈወሳቸውም።"

ወደ ዕብራዉያን 9:14፦ "ነውር የሌለው ሆኖ በዘላለም መንፈስ ራሱን ለእግዚአብሔር ያቀረበ የክርስቶስ ደም እንዴት ይልቅ ሕያውን እግዚአብሔርን ልታመልኩ ከሞተ ሥራ ሕሊናችሁን ያነጻ ይሆን?"

1ኛ ጴጥሮስ መልዕክት 1:18-19፦ "ከአባቶቻችሁ ከወረሳችሁት ከከንቱ ኑሮአችሁ በሚያልፍ ነገር በብር ወይም በወርቅ ሳይሆን፥ ነውርና እድፍ እንደ ሌለው እንደ በግ ደም በክቡር የክርስቶስ ደም እንደ ተዋጃችሁ ታውቃላችሁ።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 67