Punishment for Molech Worship & Sexual Offenses
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዘሌ 18 እስራኤላዊያን ከማን ጋር ወሲባዊ ግንኙነት ማድረግ እንደሚችሉና እንደማይችሉ አጥንተናል ፤ በመቀጠል በዘሌ 19 ለቅዱስነት ህጎች ላይ ተመልክተናል ፤ አሁን በዘሌ 20 በሚመሳሰል ነገር ሮጠዋል ፡፡ ወደ ቅጣት እንገባለን - እንደ ስርዓቱ የማይኖሮ ከሆነ ምን ይፈጠራል(ይሆናል) ፡፡
ትምህርት
ዘሌዋውያን(20፡ 1-2); ይህ መልዕክት ለሌዋውያን ካህናት ብቻ አልነበረም ለሁሉም እስራኤላዊያን እንጂ ፡፡ ሞሎክ ማን ነበር ? ሞሎክ ከነዓናዊያን የሚያመልኩትና እንደ መስዋዕት በዚህ ስዕል እጆች ላይ ልጆቻቸውን የሚያስቀምጡለት አንደ እሳት የጋለ ሞቃት የብረት ምስል ነበር (2ነገ 23፡ 10; 2ዜና 33፡6; ኤር 32፡ 35) ፡፡
ዘሌዋውያን(20፡ 3-5); በመሰረቱ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን እያላቸው የነበረው “ ተመልሳችሁ የምታደርጉ እና የማትሰሙኝ ከሆነ ትቀጣላችሁ ፤ ትሞታላችሁ ፡፡” እስራኤላዊያን የልጅ መስዋዕት አይተው ይንን ሰው ባይገድሉት እግዚአብሄር በዚያ ቤተሰብ ላይ ይዞርበታል(ይከብድበታል) ፡፡
ልጁን በሚሰዋው ሰው ላይ እስራኤላዊያን ፊታቸውን የማያዞሩበት ምክንያት ቅድሚያ አሰጣጣቸው የተጣመመ ስለነበር እና ከእግዚአብሄር ይልቅ ለቤተሰቦቻቸውና ለጋደኞቻቸው ስለተጠነቀቁ ነበር ፤ ኢየሱስ ይህን በሉቃ (14፡ 26) አሻሽሎታል “ ማንም ወደ እኔ የሚመጣ ቢኖር አባቱንና እናቱን ሚስቱንም ልጆቹንም ወንድሞቹንም እህቶቹንም የራሱን ህይወት ስንካ ሳይቀር ባይጠላ ደቀ መዝሙሬ ሊሆን አይችልም ፡፡” እንዴት ሰዎች እንደ ሚቀበሉን እና በሚያስፈሩን ምክንያቶች መሰረት ሁሉንም ነገር ለማጥራት እናዘንብል ፤ ያንን ማድረግ አንችልም የኢየሱስ ደቀመዝሙር እንሁን ! “ ትቆረጣላችሁ” የሚለው ሀረግ ትርጉሙ እንደ እግዚአብሄር ስርአት ስርዓት ለማይኖሩት የሚቀጥል ቅጣት ይሆናል ማለት ነው ፤ እንደ እግዚአብሄር ስርዓት በማትኖሩ ጊዘተ ወደ ኃጢዓት ይመራችኃል ፡፡ ኃጢዓት ብዙ ጊዜ በፍላጎት ይጀምራል ፤ ከዚያም ወደ ማጭበርበር ይህም ወደ አለመታዘዝ ይመራል በመጨረሻም ወደ ሞት (ያዕ 1፡ 15) ፡፡
ጎርደን ዌንሀም ከዘጸዓት፣ ከዘሌዋውያን እና ከዘኃልቁ የሚያስወግሩ ቅጣቶችን ያጋራል ፡
- እስራኤላዊው በሬ ከሰረቀ -ተወግሮ ይገደላል
- ጥንቆላ ወይም አስማትን የሚለማመድ- ተወግሮ ይገደላል
- የእግዚአብሄርን ስም በክፉ የሚያነሳ - ተወግሮ ይገደላል
- በሰንበት የሚያርስ - ተወግሮ ይገደላል
- ጣዖት አምልኮ - ተወግሮ ይገደላል
- ዝሙት - ተወግሮ ይገደላል
ዘሌዋውያን(20፡ 6); “ወደ ጠንቐዮች ወይም መናፍስት ጠሪዎች” የዞረ ሰዉ እግዚአብሄር እንደ ቅጣት “ ፊቱን ያከብድበታልም ለይቶም ያጠፋዋል “ ፤ ከእግዚአብሄር ቅዱስነት ስርዕት ተቃራኒ ሄዱ ማለት ቅጣት የማይቀር ነበር በተጨማሪም እስራኤላዊያንን ከእግዚአብሄር ስርዓት ለየ ፡፡ እንደ ማስበው በዚህ አለም ብዙ ተፅዕኖ ቢደረግብን ብዙ ሰዎች ስለ ስርዕቱ ብዙ እንደማያስቡ እናውቃለን ፤ ወዲያውኑ መፅሀፍ ቅዱስ እውነት አይደለም ትላላችሁ ከስርዓቱም ርቃችሁ ትጠፋላችሁ ከዚያም ከእግዚአብሄር ቅዱስነት ራሳችሁን ትለያላችሁ ፡፡
ዘሌዋውያን(20፡ 7-8); ሙሴ ህዝቡን እራሳቸውን እንዲቀድሱና ቅዱስ እንዲሆኑ ነገራቸው ! ወደ እግዚአብሄር ስርዓት መሄድ በመረጡ ጊዜ ይቀደሳሉ ፡፡ እግዚአብሄር ህዝቡን የተለዩ አደረገ !
ዘሌዋውያን(20፡ 9-10); ሙሴ እንደ ተናገረው ጮሆ ቤተሰብን መራገም በሞት የሚያስቀጣ ነበር ( 2ሳሙ 16፡ 5; ኢዮ 3፡ 1) የዚያም ሰው ደም በራሱ እጅ ላይ ነበር ( ምሳ 20፡ 20; ማር 7፡ 9-10) ፡፡ እስራኤላዊያን ቤተሰቦቻቸውን ያከብሩ እንጂ አይረግሙም ነበር ፤ ወንድና ሴት በዝሙት ሲያዙ፡ ሁለቱም ይገደላሉ ፤ እንደሚገደሉ ማዎቃቸው ከማድረግ ይጠብቃቸዋል ብላችሁ ታስባላችሁ !
ዘሌዋውያን(20፡ 11-12); አንድ ሰው ከአባቱ ሚስት ጋር ከተኛ ሊገደል ይገባዋል (ዘሌ 18) ፤ ህጉን ያውቁታል ደማቸው በራሳቸው እጅ ላይ ነበር ፡፡ አንድ ሰው በህግ ከሴት ልጁ ጋር ከተኛ ሁለቱም ሊገደሉ ይገባቸዋል ፤ ህጉን ያውቁታል (ዘሌ 18); የጥፋተኞች ሞታቸው በራሳቸው ላይ ነው ፡፡
ዘሌዋውያን(20፡ 12-14); አንድ ወንድ ከወንድ ጋር ከተኛ ይገደል ፤ በዚህ አገላለፅ እንደ እስራኤላዊያን ኃጢዓት ካደረጉ እንደ ቅጣት ይሞታሉ ፤ እንደ እስራኤላዊያን ከተሳሳቱ ይሞታሉ ፤ በዚያ ምንም የተስፋ ሙሉ ዕድል አልነበረም - ስርዓቱን ከመጠበቅ ዉጪ ይህ ነበር የሸክሙ ጠቅላላ ዕድል ፡፡
አንድ ሰው አንድን ሴትና እናቶአን ካገባ በእሳት ይቃጠሉ ፤ ሀተታ ሰጪዎች የሚሉት ምናልባት ሊሆን የሚችለው መጀመሪያ ተወገሩ ከዚያም በእሳት ይቃጠሉ ነበር ምክንያቱም በዚህ ሁኔታ መቅበር አይፈልጉም ፡፡ ይሁዳ የትዕማርን ሴተኛ አዳሪነት ከሰሰ ከዚያም መቃጠል እንዳለባት ተናገረ ነገር ግን ከእርሱዋ ጋር ተኝቶ የነበረው እርሱ ነበር ይህ ማለት እሱም ደግሞ መቃጠል ይገባዋል (ዘፍ 38፡ 24) ፡፡
ዘሌዋውያን(20፡ 15-18); አንድ ሰዉ ከእንስሳት ጋር ግንኙነት ከነበረው ሁለቱም እንስሳይቱም ሰዉየውም ይገደሉ ፤ አንዴት ሴት ከእንስሳት ጋር ግንኙነት ከኖራት ሁለቱም እንሰሳውም ሴትዬይቱም ይገደሉ ፡፡ አንድ ሰዉ እህቱን ካገባ የተዋረዱ ናቸዉና በህዝብ ፊት ይጥፉ ፤ ከአንዱም አክስት ጋር ወሲባዊ ግንኙነት አይሆንም ነበር ፡፡ ሁል ጊዜ ቅጣት ይኖራል ሞት ወይም ከነገድ መቆረጥ ፡፡
ዘሌዋውያን(20፡ 19-25); “ ይህን ኃጢዓት ካደረጋችሁ ከእናንተ ጋር ይያያዛል “ በዚህ ማጠቢያ ዝርዝር ውስጥ መሄድ እንችላለን ፤ ቃል እገባላችኃለሁ እስራኤላዊ ኃጢዓት ካደረጉ ከእነርሱ ጋር ይያያዛል ስለዚህ ደንቡንና ትዕዛዙን ይጠብቁ ነበር ፤ ለምን ? እስራኤላዊያን በንፅህና እና በቅዱስነት እንዲቀጥሉ ፡፡ ወደ ምድሪቱ ለመግባት መዘጋጀት ያስፈልጋቸዋል ስለዚህ “ አትተፋቸዉም” ፤ ርኩሱን ከንፁሁ መለየት ነበረባቸው ፤ በመሰረቱ እግዚአብሄር የተናገረው “ የተበከላችሁ እንዳትሆኑ” (ዘሌ 10፡ 10) ፤ የረከሰውን እና ንፁሁን አስታውሱ ፡፡
ዘሌዋውያን(20፡ 26); ለምንድን ነበር እስራኤላዊያን በእነዚህ ዝርዝሮች ውስጥ የሄዱት እና ስለ እነዚህ ቅጣቶች የሚያወሩት ? ምክንያቱም እግዚአብሄር ቅዱስ እንደሆነ ቅዱስ እንዲሆኑ ! እግዚአብሄር የእርሱ እንዲሆኑ ለያቸው !እያወራን ያለነው ስለ ዘሩ፣ ስለ ነፃ አዉጪው እና አስተሰሪያችን ስለሆነው ኢየሰሱስ ነው ፤ እግዚአብሄር እነዚህን ሁሉ አደረገ ስለዚህ የሱ ለመሆን የተለየን መሆን እንችላለን ! ይህ አልቆመም ፡፡ እግዚአብሄር “ ጥሩ በእስራኤላዊያን ጨርሻለሁ” ብሎ አልተናገረም ፤ እግዚአብሄር አሁንም ለእስራኤላዊያን እቅድ አለው ! እቅዱም “እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ ቅዱስ እንድትሆኑ እፈልጋለሁ “ ፤ እግዚአብሄር ስርዓት አለው እንድንከተለውም ይፈልጋል ፡፡
ችግር የነበረው እስራኤላዊያን ስርዓቱን ለመጠበቅ ከባድ ጊዜ ነበራቸው ፤ ለምሳሌ እንደ እግዚአብሄር ስርዓት እንዲኖር የተሾመው ሳኦል አላደረገም (1ሳሙ 28፡ 3-9) ፡፡ ነገሮች ጥሩ ባልመሰሉ ጊዜ ሳኦል ያደረገውን ተመልከቱ ፤ ሳኦል ጫና በተሰማዉ ጊዜ ከእግዚአብሄር መልስ አልሰማም በዋሻም ነበር ፤ ለመናፍስት ጠሪ ላከ ፤ የሳዖል መልስ ለእግዚአብሄር መታገስ(መጠበቅ) አልነበረም ፡፡
ዘሌዋውያን(20፡ 27); “ መናፍስት ጠሪ ይገደል ፡፡“ ሳኦል የሚያውቀውን ስርዓት ተው ፤ ይመስለኛል ከሁላችንም ጋርም ጉዳዩ ይህ ነው ፤ ስርዓቱን እናዉቃለን ነገር ግን በመንገዳችን ላይ ኃጢዓት ስናገኝ ፈቅደን እንቀጥላለን ፡፡
መዝጊያ
እግዚአብሄር ይመስገን መልስ አለን ! ከዚህ ቦኃላ በኃጢዓት መኖር የለብንም ፡፡ ከዚህ ቅጣት ጋር መነጋገር አያስፈልገንም ፤ ሐዋሪያው ጳውሎስ ተስፋንና ነፃነትን ገልፆአል በሮሜ(8፡ 1) “ እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸዉም ” ፤ ምክንያቱም ኢየሱስ የኃጢዓት መስዋዕት ሆኖአል ቀድሞ የተወሰነልን ይህ ቅጣት እና ይህ ሞት ያለፈ ነው ፡፡ ከዚህ ቦኃላ እነዚህን ጨዋታዎች የለብንም “ ማድረግ ይገባኛል ወይስ አይገባኝም ?” እግዚአብሄር ቀድሞ የዚህን ሁሉ ጥንቃቄ ወስዶአል ፤ በመስቀል ላይ የፈሰሰው ደም እናንተንና እኔን ነፃ አድርጎናል ፡፡ በዚህም ውስጥ እያንዳንዳችን እናንተና እኔ ኃጢዓት እንሰራለን ፤ ነገር ግን ኃጢዓት ውስጥ መቆየት የለብንም ፤ ወደ ስርዓቱ ተመልሰን መምጣት እንችላለን ሁል ጊዜ የሚያስፈልገንን ነፃነት እና ምህረት በሚፈቅድልን በክርስቶስ መስቀል ምክንያት ፡፡ ዘማዊ በሆነ ሰው፣ ጠጪ በሆነ ሰው ወይም ውሸታም በሆነ ሰው ደረጃ ላይ መቆየት የለብኝም ፤ የኃጢዓተኛ ምልክት በሆነ ደረጃ ላይ መቆየት የለብኝም ፡፡
አሁንም ኃጢዓተኞች ብንሆን እንካን ክርስቶስ ለኛ ሞቶአል ፤ ከእርሱ ጋር ትስስር(ዝምድና) ሊሰጠን መጣ ፡፡
Gordon J. Wenham, The Book of Leviticus (Grand Rapids, MI: Wm. B. Eerdmans Publishing, 1979), pp. 277ff
ጥያቄዎች
-
ዘሌ(20፡ 5-6) “ ራሳቸውን የሚያቀርቡ” ሰዎችን ይገልፃል ፤ የተገለፁት ሁለት ሁኔታዎች ምንድን ናቸው ? “ለሞሎክ መስዋዕታቸውን መስጠት” የሚለው ሀርግ ምን ማለት ነው ?
-
ዝሙት ብዙ ቅጣቶችን ተሸክሞአል (ዘሌ 20፡ 10) ፤ ያዕቆብ ለ “አመንዝራዎች” የፃፈውን ጠቅሶላቸዋል (ያዕ4፡ 4) ፤ ከማን ጋር ነበር ዝሙት የሚፈፅሙት ? በእኛ በአሁኑ ባህል ይህ ምንድን ይመስላል (1ዮሐ 2፡ 15) ?
-
እግዚአብሄር የጠላቸውን የአህዛብን ልምድ ከሰማ በኃላ (ዘሌ 20፡ 1-23) ሙሴ እስራኤላዊያንን ከአህዝባ እንደለያቸው አሳሰባቸው (ዘሌ 20፡ 24, 26) ፤ ስለ ንፁህ እና ርኩስ እንስሳት፣ ወፎች እና ስለ ሚሳቡ ነገሮች ለማውራት “ እንግዲህ” የሚለውን ቃል ለምንድን ተጠቀመ (ዘሌ 20፡ 25) ? አማኞች ዛሬ ከአለም እንዴት ይለያሉ (ዮሐ 17፡ 14-18; 2ቆሮ 6፡ 14; 7፡ 1) ?
-
በዘሌ (20፡ 21) መሰረት ለአንድ ወንድ የወንድሙን ሚስት ማግባት በጣም የተጠላ ነው ፤ ይህ ያልተፈቀደ ብቻ ሳይሆን የታዘዘውስ መቼ ነው (ዘፍ 38፡ 8; ዘዳ 25፡ 5; ማር 12፡ 19; ሉቃ 20፡ 28) ? የወንድም ሚስት የራስ ማድረግ የተከለከለ እንደሆነ ለሂሮድ በነገረው ጊዜ ለመጥምቁ ዮሐንስ ምንድን ሆነ (ማር 6፡ 16-18)?
-
ሁለቱም ዘሌ(20፡ 22) እና ዘፍ(4፡ 11-12) ምድርን እንደ ሰዉ መጠቀምን ይገልፃሉ (የሰውን ባህሪይ ሰጡት) ፤ ይህ ጥቅስ ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
-
በዘሌ 20 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Leviticus 20:10
“If a man commits adultery with a married woman – if he commits adultery with his neighbor’s wife – both the adulterer and the adulteress must be put to death.”
ኦሪት ዘሌዋዉያን 20 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እስራኤላዉያን የተለዩ እንዲሆኑ፥ እግዚዓብሔር እንደ ነጭ እና ጥቁር የደመቁ ደንቦችን ሰጥቷቸዋል። እርሱ ቅዱስ እንደሆነ እነሱም ቅዱስ እንዲሆኑ ጓጉቷል። ለምሳሌ ያክል፥ አንድ ሰዉ ከአገባች ሴት ጋራ ዝሙት ቢፈፅም ሁሉቱም እንዲሞቱ ይደረግ ነበረ። ኦ! ዛሬ፥ ከእነዚህ ትዕዛዞች ባህላችን እንዴት የራቀ ነዉ! ይህ የብሉይ ኪዳን ህግ እንደሆነ ሊስታዋል ይገባል።
አዎ፥ በክርስቶስ ይቅር የተባልክ እና በኢየሱስ ደም የተሸፈንክ ነህ! ኣዎ፥ ፀጋዉ በአንተ ላይ ነዉ! ነገር ግን እንደ አዲስ ኪዳን አማኝ፥ ፈተናን በመቋቋም፣ ከክፉ ነገር በመሸሽ፣ እና በእግዚአብሔር ዓይን ትክክለኛ የሆነን ነገር በመስራት መኖር ይገባሃል። እባክህ፥ ለሰይጣን እድል ፈንታ አትስጠዉ! ባለትዳር ከሆናችሁ፥ እባካችሁን የትዳር አጋራችሁን እየወደዳችሁ፥ አክብሯቸዉ። ለስጋ ምኞትህ ተላልፈህ እንዳትሰጥ ራሳህን በየቀኑ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ሙላ!
"ማናቸውም ሰው ከሌላ ሰው ሚስት ወይም ከባልንጀራው ሚስት ጋር ቢያመነዝር አመንዝራውና አመንዝራይቱ ፈጽመው ይገደሉ።"
ኦሪት ዘሌዋዉያን 20:10
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:18፦ "መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ ይህ ማባከን ነውና፤"
የያዕቆብ መልዕክት 4:7፦ "እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል፤"
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:25-26፦ "ባሎች ሆይ፥ ክርስቶስ ደግሞ ቤተ ክርስቲያንን እንደ ወደዳት ሚስቶቻችሁን ውደዱ፤ በውኃ መታጠብና ከቃሉ ጋር አንጽቶ እንዲቀድሳት ስለ እርስዋ ራሱን አሳልፎ ሰጠ፤"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 66
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።