Laws of Holiness
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 19 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እስራኤላዊያን እንዴት መኖር እንዳለባቸው ሙሴ ስለፃፈው በሌላ ቀን ውስጥ አድርጋችሁታል ፤ ትናትና ዘሌ 18 በተጨማሪም ከማን ጋር ወሲብ ማድረግ እንደምትችሉ እና አንደማንችል ዝርዝር አጥንተናል ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን እንደ ተለየ ርስት፣ ቅዱስ ህዝብ እና የንጉስ ካህናት ለያቸው ፡፡
አዚህ ጋር የዘሌዋውያን ዋና አለን፡ ዘሌ (20፡ 26) “ እኔ እግዚአብሄር ቅዱስ ነኝና ለእኔም ትሆኑ ዘንድ ከአህዛብ ለይቻችኃለሁና ቅዱሳን ትሆኑልኛላችሁ ፡፡”
ይህ የሆነበት መንገድ በስርየት ነበር ፤ ምህረት ለመቀበል መስዋዕት አቀረቡ ፡፡ በዘሌ 19 ይህ ህዝብ እንዴት በቅዱስነት ይጋዝ ነበር የሚለውን እንመለከታለን ፤ ዛሬ እስራኤላዊያን ቅዱስነትን ለመለማመድ የሚያደርጉአቸውን ዝርዝር እሰጣችኃለሁ ፡፡
ትምህርት
ዘሌዋውያን(19፡ 1-2); ሁሉም እርግጠኛ በመሆን እንዲረዱት እፈልጋለሁ ! ይህ መልዕክት ለካህናቱ ብቻ አይደለም ለሁሉም ለእስራኤላዊያንም ነበር፡ “ ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ !“
ዘሌዋውያን(19፡ 3-34);
- ቤተሰባችሁን አክብሩ (ቁጥር 3)፡ ዘጸ 20፡ 12 እዩ ፡፡
- ሰንበቶቼን ጠብቁ (ቁጥር 3)፡ በሰንበት ስራ የለም (ዘጸ 20፡ 8) “ የእናንተ አምላክ እግዚአብሄር ነኝ !” ለምን ነበር እስራኤላዊያን እነዚህን ህጎች መጠበቅ ያለባቸው ? አምላካቸው እግዚአብሄር ስለሆነ ነው ፤ ቅዱስ ነው እናም ስርዓታቸውም ስለሆነ ፡፡
- ጣዖቶችን እንዳያመልኩ ጥለው እንዲሄዱ (ቁጥር 4)፡ ለምን ? ይህ ይኖሩበት የነበረው ባህል አካል ነበር(ቁጥር ዘጸ 20፡ 4) ፡፡
- የህብረት/የደህንነት መስዋዕት(ቁጥር 5-8)፡ ይህ በመጀመሪያው ቀንና በሁለተኛው ቀን ይበላል ፤ ታስታውሳላችሁ የማመስገን መስዋዕት፣ የስለት መስዋዕት እና በፍቃድ የሚደረግ መስዋዕትን ? እግዚአብሄር የስቡን አካል ማግኘት ነበር ፍላጎቱ ፤ ካህኑ ጡቱን በመውሰድ ይወዘውዘዋል ከዚያ በመቀጠል ቀኝ ጭኑን በመውሰድ ከፍ ዝቅ ያድረገዋል ፤ መሰዋእት አቅራቢውም ይሳተፋልም ይበላልም ፡፡ በሰዎስተኛው ቀን ከተበላ የሚያስቀይም ነበር ፤ እግዚአብሄር አስቀምጦት ከነበረው መስመር(መመሪያ) ዉጪ የሚሄድ ይሆናል ፡፡
- ለድሀ ሀሳብ(ትኩረት) እንዲኖራችው (ቁጥር 9-10)፡ ሙሴ ሁሉንም የማሳቸውን ጫፍ ሙሉ እንዳያጭዱት ፃፈ ይህ የእንግዳ ግንዛቤ እንዲሆን ነበር ምክንያቱም እስራኤላዊያን በበርሃ እየተንከራተቱ ነበር ምንም ማሳ ባይኖራቸውም አሁን ፤ እየመጣ ስለነበር እግዚአብሄር እያዘጋጃቸው ነበር ፤ በሩት (2፡ 8-23) ሩት ይህ ነገር በደንብ ለመለማመድ አግኝታዋለች ፡፡
- ታማኝነትንና ሀቀኝነት እንዲያሳዩ ከስራም አንፃር እንካን ቢሆን (ቁጥር 11-13)፡ ተጨማሪ መመሪያዎች፡ አትስረቁ፣ አትካዱ እና አትዋሹ ወይም በሀሰት አትማሉ (ያዕ 5፡ 4; ማቴ 20፡ 1) ፤ ሁል ጊዜ ከላይ እና የሚበልጠውን እንጂ በአጭር እንደ ሚቀየሩ ሰዎች ያልሆነውን መሆን እንፈልጋለን ፡፡
አካላዊ ተፅዕኖዎችን(ተግዳሮቶችን) ተከላከሉ(ቁጥር 14-15)፡ በትክክል ፍረድ ! ባህላችን ሰዎችን የምንለይበት በለበስነው ወይም ባለን ገንዘብ መጠን መሰረት ነው ፤ እግዚአብሄር የሚለው በእነዚህ ነገሮች መሰረት አትፍረድ ፡፡ ከአለም የተለየን መሆን አለብን ፡፡
በንግግራችሁ ፍትህና እዉነት ይኑር(ቁጥር 16-17)፡ ሀሜትን አታሰራጩ ፤ ለእኛ ይህ አንዱ አደገኛ ነገር ሊሆን ይችላል ፤ የሆነ ሰው ባሳሳተን ጊዜ ስለዚያ ነገር ከጋደኞቻችን ጋር ማውራት እንፈልጋለን ፡፡
ባልንጀራችሁን እንደራሳችሁ አድርጋችሁ ውደዱ (ቁጥር 18)፡ በአዲስ ኪዳን በጣም የተጠቀሰ የብሉይ ኪዳን ፅሁፍ ነው ፤ ቂም በቀል የኛ አይደለም; በቀል የእግዚአብሄር ነው (ዘዳ 32፡ 35) ፤ ባልንጀራችሁን እንደ ራሳችሁ ውደዱ (ማቴ 22፡ 37-40) ፤ የእግዚአብሄር ስርዓት እንድን ወደው ነው ይህ ከሆነ ባልንጀራችንን መውደድ እንችላለን ፡፡ አለምን አትቀላቅሉ ፤ እግዚአብሄር የሚለው ነገሮች እንዲቀላቀሉ እንደማይፈልግ ነው ፤ ለምን ? ዘዳ(7፡ 3-6) የሚለው እዚህ አለም ላይ በምንቀየጥ ጊዜ ከእግዚአብሄር ይመልሰናል ፡፡ ይህ ከአገልጋይ ጋር የሚደረግን ግንኙነት የሚመለከቱ ህጎችን ይዞአል (ቁጥር 20-22) ፡፡
የአምስት አመት የሚበላ ፍሬ ዛፍ (ቁጥር 23-25)፡ አንዳንድ የመፅሀፍ ቅዱስ ሀተታ ሰጪዎች የሚሉት ከርኩስነተ ለማገገም ሰዎስት አመታት ይወስዳል ፤ የአራተኛው አመት የመጀመሪያ ፍሬ እንደ ምስጋና መስዋዕት ለእግዚአብሄር ይቀርባል ፤ በአምስተኛው አመት ፍሬውን መብላት ይቻላል ፡፡ እኛን ለመቀየር እግዚአብሄር በእኛ ያለውን ትዕግስት መልክ ነው ፤ እንደ ተለያችሁ ወዲያውኑ ፍሬ ካላያችሁ ዘና በሉ (አትጨነቁ) ፤ የአምስት አመት የፍሬ ዛፍ አይነት ገፅታ አላችሁ ፡፡
ሀዘንን ስለ ማክበር (ቁጥር 28)፡ ለማዘን ተገቢ ያልሆኑ መንገዶች ነበሩ ልክ ቆዳቸውን በመፈንከት ወይም በመቁረጥ ሰውነታቸዉን ማዝጎርጎር (ኤር 16፡ 6; ኤር 47፡ 5) ፤ ተገቢነት ያለው ሀዘን በኢሳ(22፡ 12) እናያለን ፡፡
ወደ ጠንቐዮችና ወደ መተተኞች አለመሄድ (ቁጥር 31) ፡፡
ታላቆችን ማክበር (ቁጥር 32) ፡፡
የሌላ አገር ተወላጁን በፍቅር ተመለከቱት (ቁጥር 33-34) ፡፡
መዝጊያ
በእነዚህ ስርዓቶች እንሄዳለን ምክንያቱም ይህ እንዴት እንድንነፐር እግዚአብሄር የሚፈልገው ነው ፤ ግን በይበልጥ ኢየሱስ ልክ እንደዚህ እንድንኖር ይፈልጋል ፤ ኢየሱስ የተናገረው “ እኔ ህግና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ ልፈፅም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም “ (ማቴ 5፡ 170 ፡፡
ኢየሱስ ዘሌ 19 ሊፈፅም መጣ ፤ ኢየሱስ በትምህርቱ በአድስ ኪዳን ውስጥ ቢያንስ ሰባት የተለያዩ ጊዜ ዘሌ 19 ጠቅሶታል ለምሳሌ ;
ዘሌ (19፡ 2)፡ “ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ ፡፡”
ማቴ (5፡ 48)፡ “ እንግዲህ የሰማይ አባታችሁ ፍፁም እንደሆነ እናንተ ፍፁማን ሁኑ ፡፡”
ዘሌ (19፡ 3)፡ “ እናትና አባቱን ይፍራ ፡፡ “
ማቴ(19፡ 19)፡ “ አባትና እናትህን አክብር ፡፡”
እንዲህ አይነት በብሉይ ኪዳን ህግ እና በኢየሱስ ትምህርት መሀከል ቐሚ ግንኙነት አለ ፤ ኢየሱስ ሊያጠፋው አልመጣም; በዘሌ 19 ተናግሮት የነበረውን ሁሉንም ሊፈፅም መጣ ፡፡
ጥያቄዎች
-
በዘሌ 19 ህጎቹ ተደገሙም ተለዩም በተጨማሪም አድስ ህጎች ተሰጡ ፤ ለእግዚአብሄር ቀድሞ ተናግሮት የነበረውን ማስታወስ እና ነገሮችን መለየት ለምን የሚጠቅም ነው ? በህይወታችሁ ውስጥ የዚህ ምሳሌ ምንድን ነው ?
-
“ ባልንጀራህን (ጎረቤትህን) እንደ ራስህ ውደድ “(ዘሌ 19፡ 18) የሚለው ትዕዛዝ ብዙ ጊዜ በአድስ ኪዳን የተጠቀሰ የብሉይ ኪዳን ህግ ነው (ማቴ 5፡ 43-44; 22፡ 39; ማር 12፡ 31) ፤ እናንተን ይህ እንዴት ያስቸግራችኃል ? “ ባልንጀራችሁን እንደራሳችሁ ውደዱ” የምትችሉበት ተግባራዊ መንገዶች ምንድን ናቸው?
-
ዘሌ (19፡ 23-25) ስለ ዛፍ ፍሬ አንብቡ ፤ ለዚህ ዛፍ የጊዜ ሁኔታው ምንድን ነበር ? በህይወታችሁ ይህ እንዴት ያስቸግራችኃል ?
-
በዘሌ(19፡ 33-34) ከስደት አንፅር በዚህ አለም ላይ ለሚሆነው ሁኔታ ይህን እንዴት ልታደርጉት ትችላላችሁ? በግላችሁስ እንዴት ልታደርጉ ትችላላችሁ ?
-
የታሰበው ኢየሱስ ህግን ሊያጠፋ እንዳልመጣ ነገር ግን ሊፈፅመው መጣ እንጂ (ማቴ 5፡ 17-20) ፤ እነዚህ ትዕዛዞች እስካሁን ለእናንተም ዛሬ ተፈፃሚ ናቸው ? የፀጉራችሁን ጎን አትቆረጡ(ቁጥር 27) ወይም ንቅሳት አይኑራችሁ ስለሚለውስ ? በማቴ(5፡ 20) ለእናንተ “ ከፈሪሳዊያን እና ከህግ መምህሮች ካልበለጠ” የእናንተ ፅድቃችሁ ምንድነ ነው ?
-
በዘሌ 19 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Leviticus 19:1-2
“The LORD spoke to Moses: ‘Speak to the entire Israelite community and tell them: Be holy because I, Yahweh your God, am holy.’”
ኢየሱስ ህግን ለመፈፀም መጥቷል!
ኦሪት ዘሌዋዉያን 19 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እግዚአብሔር የእስራኤልን ማህበረሰብ ሁሉ በቀጥታ እንዲናገራቸዉ መሴን አዞታል። አስርቱን ትዕዛዛት እንደገና ነገራቸዉ። በእያንዳንዱ ትዕዛዛት ላይ "እኔ እግዚአብሔር አምላካቹህ ነኝ" የሚለዉ ሃረግ ተደጋግሟል። በአንድ ምዕራፍ ዉስጥ አንድ ነገር ተደጋግሞ ሲጠቀስ በአትኩሮት ተመልከቱት። "እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝ" የሚለዉ "ያለና የሚኖር" ተብሎ ሊተረጎም ይችላል። እናም የነዚህ የቅድስና ህግጋትን አመንጪ እርሱ እንደሆነ ያመላክታል። እንደገናም እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ እስራኤላዉያን እንዲቀደሱ አዟቸዋል።
ክርስቶስ እንደተመላለሰ እንድትመላለስ ተጠርተሃል። እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነና ነኝ ያለዉን ስለሆነ፥ ሌሎችን እንድትወድ ደግሞም ህይወትህን ለክርስቶስ እንደ ጣፍጭ የመዓዛ ሽታ እንድታኖር ግድ ይልሃል!
"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ ለእስራኤል ልጆች ማኅበር ሁሉ እንዲህ በላቸው፦ እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።"
ኦሪት ዘሌዋዉያን 19:1-2
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘሌዋዉያን 19:18፦ "አትበቀልም፥ በሕዝብህም ልጆች ቂም አትያዝ፥ ነገር ግን ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።"
የማቴዎስ ወንጌል 5:48፦ "እንግዲህ የሰማዩ አባታችሁ ፍጹም እንደ ሆነ እናንተ ፍጹማን ሁኑ።"
ወደ ኤፌሶን ሰዎች 5:1-2፦ "እንግዲህ እንደ ተወደዱ ልጆች እግዚአብሔርን የምትከተሉ ሁኑ፥ ክርስቶስም ደግሞ እንደ ወደዳችሁ ለእግዚአብሔርም የመዓዛ ሽታ የሚሆንን መባንና መሥዋዕትን አድርጎ ስለ እናንተ ራሱን አሳልፎ እንደ ሰጠ በፍቅር ተመላለሱ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 65
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።