The Pentateuch Leviticus

Unlawful Sexual Relations

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 64 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዘሌዋውያን ውስጥ ተጨማሪ በሙሴ ከተፃፉት ውስጥ እንቀጥላለን ፤ ቀላል አይሆንም እስኪ ታማኝ እንሁን ፡፡ ወደ ዘሌ 18 ዘለን ስንገባ በዘሌ 17 የሚገነባ ነው ፤ አስታዉሱ ቃላችን ለዘሌዋውያን አስተሰሪይ ነው ፤ ደሙ ለእኛ እንደ ተተኪ ያገለግላል ምህረት እንድናገኝ ያደረገን ደሙ ነው ስለዚህ ተቀድሰን መኖር እንችላለን ፡፡ ዘሌ 18 በዘሌ 17 ደም መሰረት በቅዱስነት እየሄድን እንደሆነ እርግጠኛ የሚያደርገን ነው ፡፡

ሰባት ጊዜ እግዚአብሄር እግዚአብሄር ህዝቡን ነገራቸው “ እንደሌላ ህዝብ እንዳትኖሩ ፤ የእኔ ርስት ናችሁ፣ የንጉስ ካህናትና ቅዱስ ህዝብ ናችሁ ፤ እንደዚህ ኑሩ “ ፤ ዘሌ 18 በእውነት ቅዱስ ሆነው እንዲኖሩ ለእስራኤላዊያን ጠባቂ ነገሮች(መቀሳቀሻ መንገዶች) መስጠት ጀመረ ፡፡

ትምህርት

ዘሌዋውያን(18፡ 1-4); ያሕዌ በሙሴ በኩል ለእስራኤላዊያን ተናገረ ፤ እነዚህ አድስ መመሪያዎች እስራኤላዊያን የሚጠቀሙበትን ወይም ከየት እንደመጡ አይመስሉም ፡፡ እግዚአብሄር በመሰረቱ የተናገረው “ የመጣችሁበትን ወይም የምትሄዱበትን ሳይሆን የእኔን ህዝብ እንድትመስሉ እፈልጋለሁ ፤ የተለየ መምስል ያስፈልጋችኃላ ፡፡” እግዚአብሄር ለምን እንደተጋለጡ ያውቃል ስለሆነም አዘዛቸው ፡፡

እግዚአብሄር ለምን እንደ ማያደርጉ ነገራቸው ፤ አሁን ምንድን እንደሚያደርጉ እየነገራቸው ነበር ፤ እግዚአብሄር የተናገረው “ ትዕዛዜን ተለማመዱት” ፤ እግዚአብሄር “ተለማመዱት” የሚለውን ቃል የተጠቀመበት ምክንያት ምናልባት ሁል ጊዜ ትክክል ሆኖ እንደማያገኙት መረዳት ትችላላችሁ ፡፡ እግዚአብሄር የተናገረው “ ትዕዛዙ ይህ ነው! እኔ እግዚአብሄር ነኝና ይህ የእናንተ ትዕዛዝ ነው! “

ዘሌዋውያን(18፡ 5); የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ካከበሩ ይኖራሉ ፤ እነዚህን ነገሮች ካደረጋቸው ድነት ይኖራችኃል እያለ ነው ? አይደለም ፤ ማክአርቱር የፃፈው “ መታዘዝ ከኃጢዓትና ከሲዖል አያድንም ነገር ግን ለዳኑት ዋጋ አለው ፡፡“ ይህ በእምነታችሁ እንድትጋዙ አመላካች ነው፡

  • ዘዳ(4፡ 40) - ህጌን እና ትዕዛዜን ስለጠበቅህ ልጆችህ ይኖራሉ ፡፡
  • ዘዳ(30፡ 11-20) - ይህን ታውቃለህ ! የራቀ አይደለም ! ማድረግ ትችላለህ ! ካላደረከው ግን ትጠፋለህ ፡፡
  • ዘፍጥረት - ዘሩ ክርስቶስ በራዕይ መፅሀፍ ውስጥ ሁሉንም መንገድ የሚያዝ ነው ፡፡
  • መዝ 90 - አማካኝ ዘመን ከ70-80 አመታት ነው ፡፡
  • ሮሜ (7፡ 10-12) - የማንጠነቀቅ ከሆነ ኃጢዓት ወደ ሞትና ጥፋት ይመራናል ፡፡
  • ገላ(3፡ 23-26) - ህጉ እስከ ክርስቶስ ጠባቂያችን ነበር; ህጉ ወደ ኢየሱስ ያመለክታል !
  • ዘሌ(18፡ 5) - ኢየሱስ ብቃታችን(ፈፃሚያችን) ነው ምክንያቱም ህጉንና ትዕዛዙን መጠበቅ የሚችለው እሱ ብቻ ነው !

ሁሉንም ደንቦቹን(ህጎቹን) መጠበቅ አናችልም (ሮሜ 3፡ 23) ነገር ግን ከህግ ርግማን ኢየሱስ አነፃን በተጨማሪም በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን አሁን የእግዚአብሄር ልጆች ነን (ገላ 3፡ 10-14, 23-26) ፡፡ ብዙዎቻችን ለመቀበል ነገሮችን በማድረግ እንጠብቃለን ነገር ግን ስጦታን የመቀበል ጉዳይ ነው ቀድሞ ተሰጥቶናል ፡፡

ዘሌዋውያን(18፡ 6); የትዳር መቀደስ ወይም ቅዱስነት ምንድን ይመስላል ? የማይመስለውን ነገር ላይ እስኪ እንመልከት ፤ ምሳሌ የሚሆነው ከቤተሰብ አባል ጋር ወሲብ አይደረግም ፡፡ ወሲብ አንድ ወንድና አንድ ሴት አንድ ስጋ የሚሆኑበት የሚያቀራርብ ድርጊት ነው (ዘፍ 2፡ 21-25) ፤ 1ቆሮ (6፡ 16) የሚያወራው የሆነ አካል ጋር ወሲብ ካደረገ ከእሳ ወይም ከእርሱ ጋር አንድ ስጋ ይሆናሉ ፡፡

ዘሌዋውያን(18፡ 7); እግዚአብሄር ለወሲብ መስመር መሰረተ ፤ እግዚአብሄር አንድ ወንድና ሴት በግልፅ አብረው እንዲስማሙና አንድ ስጋ እንዲሆኑ አዘጋጀው ፤ ለዚያ ነው በወንድና በወንድ ወይም በሴትና በሴት መሀከል የሚሆን ወሲብ የእሱ ድዛይን ያልሆነው - ተገቢነት(ተስማማነት) አይኖረውም ፡፡ ኢስቪ ትርጉም የሚለው “ የአባታችሁን እርቃን እንዳትገልጡ የእናታችሁ እርቃን ነውና “ (ዘፍ 9፡ 20-25) ፤ በዘፍ 9 በሆነው(በተፈጠረው) ካም ተረገመ ፡፡ ብዙ ሀተታ ሰጪዋች የተወሰነ የተመሳሳይ ፆታ ወሲባዊ ባህሪይ በካምና በአባቱ መሀከል ተከናውናል ብለው ያምናሉ ፤ ትኩረት ባያገኝም ወንድ የወንድን እርቃን እንዲያይ አልተሰራም ፡፡

ዘሌዋውያን(18፡ 8-18); ከእናታችሁ (ቁጥር 7)፣ ከእንጀራ እናታችሁ (ቁጥር 8)፣ ከህታችሁ (ቁጥር 9) ወይም ከልጅህን ሴት ልጅህ ጋር ወሲብ እንዳታደርግ ፡፡

ይህ ዛሬም ትልቅ ጉዳይ ነው ! በሚያሳዝን ሁኔታ በአያቶች እና በቤተሰቦች ማለባበስ በጣም የተለመደ ነው ! ታካሚዎቻቸውን እንደ ጥቅም የሚወስዱ ሀኪሞችን በዜና እናያለን ፤ ይህ እግዚአብሄር እንዳዘጋጀው አይደለም ፡፡

እስራኤላዊያን እነዚህ ነገሮች ልክ ሊሆኑ ከሚችሉበት አምላክ የለሽ የግብፅ ባህል ወጡ ፤ አነዚህ መመሪያዎች ለእነርሱ አድስ ይመስሉ ነበር (ይሁን እንጂ ዛሬም ለእኛ የተለመደ ስሜት ነው) ፤ እግዚአብሄር በጣም ዝርዝር ያደረገው ለእስራኤላዊያን ይህ አድስ የመኖሪያ መንገድ ነበር ፡፡ ከአባት ወይም ከእናት ልጅ፣ ከጉድፈቻ እህት (ቁጥር 11) ወይም አክስት - የአባትህ እህት(ቁጥር 12) ጋር ወሲብ እንዳታደርግ ፡፡

አንዳንድ ጊዜ በአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን የማይመች የሚያደርገንን የመፅሀፍ ክፍል መዝለል እንፈልጋለን ፤ ሙሴ እነዚህን ትዕዛዞች የፃፈ አባቱና እናቱ በእዉነታው አክስትና የአጎት ልጅ ሆነው ነው ፡፡ እምበረም(የሙሴ አባት) ዮካብድን አገባ የአጎቱን ልጅ ፤ ይህ ህግ አልነበራቸውም ነበር ፤ አድስ ነበር ! ከአክስታችሁ ከእናታችሁ እህት(ቁጥር 13)፣ ከህግ አክስታችሁ (ቁጥር 14)፣ ከህግ ሴት ልጃችሁ (ቁጥር 15)፣ ከህግ እህታችሁ (ቁጥር 16)፣ ከሴትና ከሴት ልጅዋ (ቁጥር 17) ወይም ከሴትዋ እና ከህቱዋ (ቁጥር 18)(ያ ማለት ልያና ራሄል) ጋር ወሲብ አታድርጉ ፡፡

ዘሌዋውያን(18፡ 19-20); ተጨማሪ መመሪያዎች፡ በሴት ወር አበባ ደም ጊዜ ወሲብ አይደረግም (ቁጥር 19) እና በተጨማሪ ከጎረቤታችሁ ሚስት ጋር ወሲብ አይደረግም (ቁጥር 20) ፡፡

ዘሌዋውያን(18፡ 21); ሞሎክ ከበሬ ራስ እና ከተዘረጋ እጆች ጋር ጡናቻ ባለው ስዕል የተወከለ የከነዓናዊያን አምላክ ነበር ፤ ስዕሉ ባዶ ነበር ፡፡ በእሳት ያበሩለታል በተጨማሪም በግልፅ በተዘረጋው እጆቹ ላይ ልጆቻቸውን በማስቀመጥ ይሰዋሉ ፤ ይህ በተጨማሪ ምናልባት እንደምንም ከከነዓናዊያን ወሲባዊ ፍላጎት ጋር ይገናኛል ፡፡

ዘሌዋውያን(18፡ 22-23); ተጨማሪ መመሪያዎች፡ ወንድ- ለወንድ ወሲባዊ ግንኙነት አይደረግም (ቁጥር 22) ፤ ተመሳሳይ ወሲባዊ ግንኙነት(ግብረሰዶማዊ) ርኩስ እንደ መሆን ይገለፃል ፤ የእግዚአብሄር አይደለም ፡፡ ጥናቶች ያገኙት ገብረሰዶማዊ ወንድ አማካኝ የእድሜ ርዝማኔ ከተቃራኒ ወሲባዊ ግንኙነት ከሚያደርጉ ወንዶች አማካኝ በ20 አመታትን የሚያንስ ነው ፡፡ ለምን ? ምክንያቱም እግዚአብሄር ካዘጋጀው እቅድ ዉጪ አንድ ስጋ ለመስራት ስለሞከሩ ስለዚህ አይሰራም ፡፡

ምናልባት ሌሎች ሀገሮች እና ሌሎች ህዝቦች ይህን ያደርጉታል ነገር ግን እስራኤላዊያን አይደሉም ፤ እስራኤላዊያን የእግዚአብሄር ህዝብ ናቸው ፡፡ ይህ እውነት በጠቅላላው መፅሀፍ ውስጥ ነው በብሉይ ኪዳን ብቻ ሳይሆን በአዲስ ኪዳንም እንጂ ፤ በተጨማሪም ከእንስሳት ጋር ወሲብ አይደረግም (ቁጥር 23) ፡፡

ከእንስሳት ጋር ወሲብ ማድረግ ጤነኝነት ያልሆነ ነው !

ዘሌዋውያን(18፡ 24-30); እስራኤላዊያን እንደ ሌሎች ህዝብ ራሳቸዉን የበከሉ አልነበሩም ! እግዚአብሄር የተናገረው “ ህጌን ጠብቁ ፤ ትዕዛዜን ጠብቁ ፤ የግብፅ ህዝቦች እነዚህን ነገሮች አደረጉ ነገር ግን በራሳቸው ራሳቸውን አልበከሉም ምክንያቱም የእናንተ አምላክ እኔ እግዚአብሄር ነኝ ! እኔ ስርዕት ነኝ ! ቅዱስ እንደሆንኩ ቅዱስ ሁኑ ! አንድ ስጋ ሁኑ……ወንድ ከሴት ጋር…..ባዘጋጀሁት መንገድ ፡፡“ ገምቱ ለምን ? ይህ ሁሉ ወደ ክርስቶስ ያመለክታል (ኤፌ 5፡ 25-33) ፤ ክርስቶስንና ቤተ ክርስቲያንን ! በባህላችን ውስጥ ወሲብ ማድረግ ከምንችላቸው ጋር ጨዋታ በምንጫዎትበት ጊዜ ክርስቶስ መሪ(ራስ) አይደለም እያልን ነው ፡፡

መዝጊያ

በዘሌ 18 ውስጥ ያለው መምሪያ እንደ ያህዌ ተከታዮች በመጨረሻም ወደ ኤፌ 5 ክርስቶስ የኑሮአችንና የትዳራችን ራስ እንደሆነ ያመለክታል ፤ እነዚህ ሁሉ ወደ ደሙና በመስቀል ላይ በፈሰሰው ደሙ በኩል የክርስቶስን ምህረት በቅዱስነት እንድንሄድ ወደ ፈቀደልን ወደኃላ ዘሌ 17 ይመልሳሉ ፡፡

2 R. S. Hogg, et al., “Modelling the Impact of HIV Disease on Mortality in Gay and Bisexual Men,” International Journal of Epidemiology, v. 26, Issue 3, 1 June 1997, pp. 657–661; available at https://doi.org/10.1093/ije/26.3.657.

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 156.

ጥያቄዎች

  1. በዘሌ(18፡ 1-5) እግዚአብሄር በቀሪዎቹ ምዕራፍ ስለሚናገረው መቅደም ነበር ፤ ከዚህ ምንድን ልትለቅሙ ትችላላችሁ ? (2ቆሮ 6፡ 17-18)
  2. ሮሜ (10፡ 5-10) አንብቡ ፤ እነዚህ ቁጥሮች በዘሌ (18፡ 5) እንደ ተጠቀሰው ቅድስናን በህግ እና ቅድስናን በእምነት እንዴት ያነፃፅሩታል ? (ገላ 3፡ 12)
  3. በዘሌ(18፡ 5; 18፡ 27-29) ያሉትን የእግዚአብሄር ትዕዛዝን የሆነ ሰው ባይታዘዛቸው ውጤት ነበራቸው ባላችሁ ታስባላችሁ ? በእርሱ “ ድብጋጌዎች እና ህጎች” መሰረት በመኖር እስራኤላዊያን መንድን ያገኛሉ ?
  4. ዘሌ 18 በተከለከለ ወሲባዊ ባህሪይ ላይ ህጎችን ሰጥቶአል ፤ እነዚህ ነገሮች እስከ ዛሬ የተከለከሉ ናቸው (1ቆሮ 6፡ 12; 10፡23) ? በኤፌ(5፡ 25-33) መሰረት እግዚአብሄር በአንድ ወንድ እና በአንድ ሴት መሀከል በትዳር ውስጥ የሚያስተላልፈው ምንድን ነው ? ትዳርን ቅዱስ አድርጎ መጠበቅ ለምን ለእግዚአብሄር በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ይህ እንዴት እንደሚረዳችሁ ታዩታላችሁ ?
  5. በተከለከለ ወሲባዊ ባህሪ ውስጥ ካለ ሰው ጋር ክርስቶስን ለማጋራት ዘሌ 18 እንዴት ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ ? በእናንተ ተፅዕኖ ዙሪያ ውስጥ ካለ ሰው ጋር እንዴትና መቼ ይህን ርዕስ ትጠጉታላችሁ(ታነሱታላችሁ) ?
  6. በዘሌ 18 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Leviticus 18:3, 5

“Do not follow the practices of the land of Egypt, where you used to live, or follow the practices of the land of Canaan, where I am bringing you. You must not follow their customs… Keep My statutes and ordinances; a person will live if he does them. I am Yahweh.”

ህጋዊ ያልሆኑ ፆታዊ ግንኙነቶች፥ ክርስቶስ እና ቤተ-ክርስትያን

ኦሪት ዘሌዋዉያን 18 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

እግዚዓብሔር በሙሴ በኩል የእርሱን ትዕዛዛት እንዲከተሉ እስራኤላዉያንን አዟቸዋል። በዋናነት ግን እግዚአብሔር እንዲህ ብሏል፥ "ቀድሞ የነበራችሁን ልምምድ አትከተሉ፥ ወደፊት የምትኖሩባት ምድር ይለማምዱ እንደነበረም እናንተ እንዳታድርጉ፥ አትከተሏቸዉም። ነገር ግን፥ አሁን እንደምትኖሩትና እንደምትመለለሱት የተሰጣችሁን ትዕዛዛትን ተከተሉ።"

አያሌ ለሆኑ ቀናት፥ ወዳሳልፍነዉ የድሮ ህይወት ለመመልከት እንፈተናለን። ወይንም ደግሞ አጥናፍ ላይ ያለዉን መመልከት እንፈልጋለን። እኛ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት ነን! አሮጌዉ አልፏል! አዲሱ ደግሞ መጥቷል። የመንፈስ ቅዱስ ኃይል ዉስጣችን ስላለ በስጋ ጉልበት ሳይሆን በዚያ ኃይል ልንመላለስ ይገባል። ዛሬ፥ ቀድሞ ትመላለስ እንደነበረዉ አትመላለስ! ሰማያዊ ጥሪ አለህ! በክርስቶስ መንገድ ለመራመድ በዉስጥህ የሚኖረዉ መንፈስ ቅዱስ ለዛሬ ጉልበትን ይሰጥሃል።

"እንደ ተቀመጣችሁባት እንደ ግብፅ ምድር ሥራ አትሥሩ፤ እኔም ወደ እርስዋ እንደማገባችሁ እንደ ከነዓን ምድር ሥራ አትሥሩ፤ በሥርዓታቸውም አትሂዱ።.. የሚሠራቸው ሰው በእነርሱ በሕይወት ይኖራልና ሥርዓቴንና ፍርዴን ጠብቁ፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።"

ኦሪት ዘሌዋዉያን 18:3፣ 5

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17፦ "ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።"

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 4:12-13፦ "መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ።"

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3:18-20፦ "ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው። እኛ አገራችን በሰማይ ነውና፥ ከዚያም ደግሞ የሚመጣ መድኃኒትን እርሱንም ጌታን ኢየሱስ ክርስቶስን እንጠባበቃለን፤"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 64