The Pentateuch Leviticus

Two Warnings

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 17 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 63 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የእኛ አንድ ቃል ለዘፍጥረት ዘር ነው ፤ እንዴት አድርጎ ዘሩ በዘፍጥረት ውስጥ ወደ ክርስቶስ ወደ ዘሩ አመለከተ ? የእኛ አንድ ቃል ለዘጸዓት ነፃ አውጪ ነው ፤ ኢየሱስ ነፃ አዉጪዓችን ነው እናም ህዝቡን ከበርሃ ያወጣል ፡፡ በዘሌዋውያን መፅሀፍ ውስጥ የእኛ ቃል ለኢየሱስ አስተሰሪይ ነው ፤ በምዕራፍ 16 ሁሉንም ኃጢዓት በፍየላ ላይ በተቀመጠ ጊዜ ለሰዎቹ ምህረትን አመጣች ፡፡ ዘሌ 17 ስለ ደም ነው ፡፡

ዕብ(9፡ 11-14) የሚለው የኢየሱስ ደም ሁላችንንም አንድ ጊዜ አጠበንም ዋጀንም ፤ ዋይሰርቤ የሊዎን ሞሪርስን ስራ “ደም” የሚለው ቃል በሁሉም መፅሀፍ ውስጥ 460 ጊዜ፣ 362 ጊዜ በብሉይ ኪዳን እና 13 ጊዜ በዘሌ 17 ውስጥ እንደሚገኝ የተናገረውን ጠቅሶዓል ፡፡ዕብ(10፡ 10) የሚለው “ በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋ አንድ ጊዜ ፈጽሞ በማቅረብ ተቀድሰናል ፡፡” 1ጴጥ (3፡ 18) በተጨማሪ ክርስቶስን የገለፀው “ ስለ አመጸኞች አንድ ጊዜ በኃጢዓት ምክንያት ሞቶአልን “ 1ዮሐ (2፡ 2) የሚለው ኢየሱስ ለሁሉም አለም ኃጢዓት ቁጣ ማቀዝቀዢያ ነበር ፡፡ ዋና ጥቅሱ ዘሌ(17፡ 11) ነው “ የስጋ ህይወት በደሙ ውስጥ ነውና ደሙም ከህይወቱ የተነሳ ያስተሰረያልና በመሰዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተሰሪያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት ፡፡”

እንደገና አስሮ የሚያነሳሳበት ጊዜ ከብሉይ ኪዳን ጥቅሶች ውስጥ እነዚህን ዋና ጥቅሶች ይይዛል፡ መክ(7፡ 20) - ኃጢዓት ፤ ዘዳ(24፡ 16) - ሞት ፤ ዘሌ(17፡ 11) - ደም ፤ ዶር. ማርቲን ደሀን የተናገረው “ ማንም ሰው ደሙ መዘዋወር እስካላቆመ ድረስ ሞቶ አያውቅም “ ፤ ኢሳ(53፡ 5) - እምነት ፤ ኤር(31፡ 33) - ህይወት ፡፡

ትምህርት

ዘሌዋውያን(17፡ 1-2); ሙሴን ለአሮን፣ ለልጆችና ለሁሉም እስራኤላዊያን እንዲነግር ነገረው ፤ በእነዚህ ቁጥሮች ውስጥ እግዚአብሄር ሁለት ዋና ማስጠንቀቂያዎች ሰጠ ፡፡

ዘሌዋውያን(17፡ 3-4); አንደኛው ማስጠንቀቂያ - የተከለከሉ መስዋዕቶች ፤ ከመገናኛው ድንካን መጋቢያ ዉጪ የትም ቦታ የሚቀርብ መስዋዕት በኃይለኛው የተከለከለ ነበር ፤ የኔልሰን ሀተታ የሚጠቅሰው ይህ ማስጠንቀቂያ ሁለት ነገሮችን አድርጎአል ፤ የመጀመሪያው እግዚአብሄር ሰዎችን በራሳቸው እንስሳትን እንዲገድሉአቸው አልፈለገም ፤ አላማ እና ተጠያቂነት እንዲኖረው ያስፈልጋል ፡፡ ሁለተኛው ለጣዖት መስዋዕት እንዳይሰው እግዚአብሄር እየከለከላቸው ነበር ፤ በእውነት ለእግዚአብሄር የሚሰዋው ቢሆን እንካን ይህንን ለማድረግ ወደ መቅደሱ መምጣት ያስፈልጋቸዋል ምክንያቱም እግዚአብሄር ቀናተኛ አምላክ ነው(ዘጸ 20፡ 4-5; 34፡ 14; ኢሳ 42፡ 8) ፡፡

ዘሌዋውያን(17፡ 5-6); መስዋዕት በሀገሪቱ ሁሉ መሰዋት አይችል ፤ አሁን በካህኑ ፊት በመገናኛው ድንካን መግቢያ ላይ አቅርበዋል ፡፡ የህብረት መስዋዕት ማለት ከእግዚአብሄር ጋር ግንኙነት ነበራችሁ ማለት ነው ፤ በዓል ነበር ፡፡ የህብረት መስዋዕት ከነበረ ለምንድን ነበር በውጪ ለማድረግ የፈለጉት ? ከሌሎች ሰዎች ጋር ማድረግ ይፈልጋሉ ፤ ራሳቸው የሚያደርጉት ከሆነ ሀሳቡን ይስታሉ ፡፡ ካህኑ በእግዚአብሄር መሰዊያ ላይ ለእግዚአብሄር እንደ ጣፍጭ ሽታ ደሙን ይረጨዋል ፡፡

ዘሌዋውያን(17፡ 7); “መስዋዕቶቻቸውን ደግሞ ተከትለው ላመነዘሩባቸው ለሰይጣናት አይሰው ፡፡“ ይህ ማለት ትክክል ያልሆነ ጥቂት መስዋዕት አቅርበው ነበር ፤ የፍየል ሰይጣን ግብፃዊያንና ሌሎች የቀድሞ ባህሎች የሚያመልኩት አምላክ ነበር ፤ አምላኩ በፍየል እና በግማሽ ፍየል ቅርፅ ይወከላል ፡፡ በዘፍ(47፡ 1-6) እስራኤል በጌሳም በተቀመጡ ጊዜ ይህን ግማሽ ፍየል(የጫካ አምላክ) ወደ ማምለክ ውስጥ መግባት ጥሩ እድል ነበራቸው ፡፡

ዘሌዋውያን(17፡ 8-9); ማናኛውም ሰው እስራኤላዊ ወይም እንግዳ ከመገናኛው ድንካን ውጭ የትም ቦታ መስዋዕት የሚሰዋ “ ከህዝቡ ይወገዳል “ ፤ ብዙ አይነት ትርጉሞች “ከህዝቡ ይወገዳል” ለሚለው አሉት ፤ ሀረጉ ምናልባት መግደል፣ ግንኙነት አይኖረውም ወይም ሌላ ቦታ ይወሰዳል ማለት ይሆናል ፡፡ ማስጠንቀቂያው ለእነሱ ሀሰት የሆነ አምልኮአቸውን እንዲያቆሙና በዚያ ፋንታ ለእግዚአብሄር መስዋዕታቸውን እንዲያመጡ ነበር ፡፡

ዘሌዋውያን(17፡ 10-16); ሁለተኛው ማስጠንቀቂያ ደምን እና በድንን መብላት የተከለከለ ነበር ፤ እግዚአብሄር በማናኛውም ደም በሚበላ ላይ ከህዝቡ እንደ ሚያስወግደው ቃል ገባ ፡፡ ይህ ርኩስ እና ንፁህ ወደ ሚለው ጉዳይ ይመለሳል፡ ደም ተተኪ ነበር; ለሰዎች ስርየትን ያደርጋል ፤ ለማናም ለእስራኤል ሰዎች ደም እንዲበሉ አልተፈቀደም ነበር (ቁጥር 12) ፡፡ በዮሐ(6፡ 54) ኢየሱስ የተናገረው “ ስጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ህይወት አለው” በእየሱስ ደም ውስጥ መካፈል ህይወት ይሰጠናል ፡፡ ዕባ(9፡ 22) የሚያሳስበን ምህረት መቀበል ከመቻላችን በፊት ደም መፍሰስ ሆኖአል ፤ ህይወት ከሀሰት አምልኮ እና ለጣዖት ከተሰዋ አልመጣም ስለዚህ ደምን ያለአግባብ መጠቀም የለብንም ምክንያቱም ከየት እንደመጣ ስለሚገባን ፡፡

ዘሌዋውያን(17፡ 13-16); ማንም የዱር እንስሳት ወይም ወፍ አድኖ ቢገድል በቆሻሻ ደሙን እንዲቀብር ታዘዘ ፤ ማክ አርቱር የተናገረው ለአዳኞች የገደሉትን ደሙን ለአዳን አምላክ እንደ መስዋዕት ማፍሰስ የተለመደ ነበር ፤ ለእግዚአብሄር ሰዎች በኃይል የተከለከለ ልምምድ ነበር ፡፡

ዘሌ 17 ሁለት ማስጠንቀቂያዎች ሰጥቶአል፡ በሀሰት አምልኮ እንዳትሳተፉ በተጨማሪም ደምን ያለእባብ እንዳትጠቀሙ ፤ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ታላቁ ካህን ስለ እነርሱ ደም ጥንቃቄ ወስዶአል ፤ ከኢየሱስ ጋር ተመሳሳይ ነው ፡፡ ደምን ያላአግባብ የምንጠቀም እና በራሳችን የምናደርገው ከሆነ አይሰራም ፡፡

መዝጊያ

ይህንን ክፍል በኢየሱስ ደም ኃይል ውይይት ቢዘጋ አስፈላጊ(ተገቢ) ነው ፡

  • 1ጴጥ(1፡ 19)፡ የኢየሱስ ደም የከበረ ነው ፡፡
  • ሮሜ(5፡ 9)፡ በኢየሱስ ደም ነፅተናል(ፀድቀናል) ፡፡
  • ኤፌ(1፡ 7)፡ በኢየሱስ ደም ቤዛነት አለን ፡፡
  • ራዕ(1፡ 5)፡ በኢየሱስ ደም ነፃ ሆነናል ፡፡
  • ዕብ(13፡ 12)፡ በኢየሱስ ደም ፀድቀናል ፡፡
  • 1ዮሐ(1፡ 7)፡ በኢየሱስ ደም ታጥበናል ፡፡
  • ሐዋ(20፡ 28)፡ ኢየሱስ በደሙ ገዝቶናል ፡፡

ዘሌ 17 አፅዕኖት የሰጠው ምንም ነገር እንዳላደረግን ነው ፤ ኢየሱስ ነፃነታችንን ገዛው ፡፡ ቅድስናን፣ መስተካከልን(ምክንያትን) እና ቤዛነትን ሰጠን ፤ ኢየሱስ አነፃን፣ አጠበን በተጨማሪም ነፃ አደረገን ምክንያቱም በራሱ ደም ገዝቶናል ፡፡ ትክክለኛ አስተሰሪይ ነው ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 278.

  2. Martin R. DeHaan, “The Chemistry of the Blood,” available from https://www.jesus-is-savior.com/BTP/Dr_MR_DeHaan/Chemistry/01.htm.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 177.

  4. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Leviticus, p. 144; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/leviticus.pdf.

  5. Nelsons, p. 177.

  6. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 155.

ጥያቄዎች

  1. እግዚአብሄር በመገናኛው ድንካን ፊት እንጂ ሰው የትም ቦት መስዋዕት እንዲያቀርብ አልፈቀደም ፤ ይህ ለምን ነበር ? (ዘሌ 17፡ 7; ዘጸ 20፡ 3-6)
  2. በመገናኛው ድንካን መግቢያ በር ላይ መስዋዕታቸውን በማምጣት የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ካልተከተሉ ምንድን ነበር የሚያስከትለው ውጤት ? (ዘሌ 17፡ 4; 8-9) ይህ ለምን ነበር በኃይል የጠነከረው(አስገዳጅ የነበረው) ?
  3. በዘሌ (17፡ 13) መሰረት በያዙዓቸው ለመግባባት አዳዮቹ እንዴት እንዲያደርጉ ያደርጋሉ ?
  4. ደም አትብሉ የሚለው ትዕዛዝ በእነርሱ መሀከል ያሉትን እንግዶች እንደሚያካትት እወቁ ፤ በዘሌ17፡ 11 የደም አላማ ምንድን ነበር ? ለበሉት የሚያመጣው ውጤት ምንድን ነበር ? (ዘሌ17፡ 10)
  5. በዘሌ 17 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Leviticus 17:11

“For the life of a creature is in the blood, and I have appointed it to you to make atonement on the altar for your lives, since it is the lifeblood that makes atonement.”

ሁለት ማስተጠንቀቂያዎች፥ ህይወት ያለዉ በደም ዉስጥ ነዉ!

ኦሪት ዘሌዋዉያን 17 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

እግዚዓብሔር እንደገና ህዝቡን ትዕዛዝ ሰጠዉ። በዚህ ጊዜ፥ እንዴት በተለየ መንገድ በፊቱ መሥዋዕትን እንደሚያቀርቡ ዘርዝሮ አስቀመጠላቸዉ። በዚህ ምዕራፍ ዉስጥ "ደም" የሚለዉ ቃል አስራ ሰባት ጊዜ ተጠቅሷል። የደም ኃይል፥ በሁለትም በብሉይ እና በአዲስ ኪዳን ይቅርታን ያመጣል።

በህይወትህ ዉስጥ ደሙ እንደስርየት ያገለግላል። እግዚዓብሔር ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ልኮ፥ በእርሱ ደም ይቅርታን ገዝቷል። በሌላ ያልሆነ፥ ነገር ግን በክርስቶስ ብቻ የሚገኝ የተትረፈረፈ ህይወት አለን! በክርስቶስ ደም ምክንያት የተትረፈረፈ ህይወት እንዲኖርህ ፈልገዉ!

"የሥጋ ሕይወት በደሙ ውስጥ ነውና፤ ደሙም ከሕይወቱ የተነሣ ያስተሰርያልና በመሠዊያው ላይ ለነፍሳችሁ ማስተስረያ ይሆን ዘንድ እኔ ለእናንተ ሰጠሁት።"

ኦሪት ዘሌዋዉያን 17:11

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የዮሓንስ ወንጌል 10:10፦ "ሌባው ሊሰርቅና ሊያርድ ሊያጠፋም እንጂ ስለ ሌላ አይመጣም፤ እኔ ሕይወት እንዲሆንላቸው እንዲበዛላቸውም መጣሁ።"

ወደ እፌሶን ሰዎች 1:7፦ "በውድ ልጁም፥ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት መጠን፥ በደሙ የተደረገ ቤዛነታችንን አገኘን እርሱም የበደላችን ስርየት።"

1ኛ ዮሐንስ መልዕክት 2:2፦ "እርሱም የኃጢአታችን ማስተስሪያ ነው፥ ለኃጢአታችንም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን ለዓለሙ ሁሉ ኃጢአት እንጂ።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 63