Day of Atonement
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 16 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዘሌ 16 የዘሌዋውያን መሀል ነው በጠጨማሪም በኦሪት መፅሀፍ መሀል ውስጥ እና ዋና ነው ፤ እስካሁን ስለ እንስሳቶች፣ ስለ ቆዳ በሽታ እና የሰውነት ፈሳሾች አውርተናል አድካሚም ነው ፡፡ በዜ 14 ከምንገዶቹ(ከአማራጮቹ) ጋር ለለምፃሞች የሚነፁበት የተደረጉ ተስፋዎችን አሳይቶናል ፡፡ ዘሌ 16 ለዘሌዋውያን መፅሀፍ ለላን አንድ ቃል አስተሰሪይ ወደ ሚለው ያመለክታል ፤ ይህ ቃል አስተሰሪይ ማለት ተተኪ(ተቀያሪ) ማለት ነው ፡፡ የሚገባንን ወሰደ ፤ ማላከክ ማለት ጥፋተኝነትን ማስተላለፍ ነው ፤ ኃጢዓተኞች ነን ነገር ግን ኢየሱስ ጥፋታችንን ወሰደ ፤ ኢየሱስ ሞትን ወሰደ ስለዚህ ህይወት ይኖረናል ፡፡ አስተሰሪይ ወደ መሲሁ የሚያመለክት ቃል ነው ፤ በዚህ ምዕራፍ ስርየት ወደ ህይወት እንደመጣ እናያለን ፡፡
ትምህርት
ዘሌዋውያን(16፡ 1-2); እግዚአብሄር ከሁለቱ የአሮን ልጆች ናዳብና አብዩዱ ሞት ቦኃላ ለሙሰ መቼም ቢሆን ቢፈልግም(ልጆቹ አድርገውት እንደ ነበር) አሮን ወደ ቅዱስ ቦታ መሄድ አይችልም ብሎ ተናገረው ፡፡ በእግዚአብሄር ጨዋታ የምትጫዎቱ ከሆነ ትሞታላችሁ ፡፡ እግዚአብሄር እንዴት ወደ ቅዱስተ ቅዱሳኑ በትክክል እንደሚቀርቡ እንዲያውቁ ነበር የፈለቻቸው ፤ እግዚአብሄር ደረጃ አስቀመጠ ፤ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ይህ የስርየት ቀን ነበር(ዮም ኪፑር) ይህን በአድስ ኪዳን ውስጥም እንደ ፆም ይታይ ነበር(ሐዋ 27፡ 9) ፡፡
ዮሐንስ ማክአርቱር ለስርየት ቀን 15 ደረጃዎችን ግልጽ አድርጎአል ፤ ለመከተል ቀላል ለማድረግ ከትክክለኛ የትቅስ ቁጥሮች ጋር ከዘሌ ምዕራፍ 16 እያንዳንዱ ደረጃ ከታች ተዘርዝሮአል ፡፡
- ታላቁ ካህን በተለየ መንገድ ይታጠባልም ይለብሳልም (ቁጥር 4) ፡፡
- ታላቁ ካህን ለራሱና ለቤተሰቡ እንደ ኃጢዓት መስዋዕት በሬ ያቀርባል (ቁጥር 3, 6, 11) ፤ ይህ ደም ጥፋተኝነትንና ሞትን ይመለከታል ማለትም ለአሮንና ለቤተሰቦቹ እንደ ኃጢዓት መስዋዕት ፤ በትህትና ለእግዚአብሄር ታዛዥ ነበር ፡፡
- ታላቁ ካህን ቅዱስተ ቅዱሳን ከበሬ ደም፣ ከዕጣን፣ ከሚነድድ ከሰል ከሚቃጠል መስዋዕቱ መሰዊያ ላይ በማድረግ ይገባል(ቁጥር 12-13) ፤ ቅዱስተ ቅዱሳን ውስጥ የሚገባው እሳት ከራሱ ከእግዚአብሄር መምጣት ነበረበት ፡፡
- ታላቁ ካህን የበሬውን ደም በኪዳኑ ታቦት ላይ ባለው በስርየት መቀመጫ ላይ ሰባት ጊዜ ይረጫል (ቁጥር 14) ፤ የስርየት መቀመጫ “ የማስተሰሪይ ቦታ” ማለት ነው ፤ የተተካው ደም ከስርየት መቀመጫው ላይ ይቀመጥ ነበር ከዚያም ለራሱ እናም በመጨረሻም ለሁሉም ለእስራኤል ህዝብ ስርየት አመጣ ፡፡
- ታላቁ ካህን ቅዱስተ ቅዱሱን በመጠው ወደ አደባባዩ ተመልሶ ይሄዳል ፤ ለሁለት ፍየሎች እጣ ያዘጋጃል፡ አንዱ እጣ ለእግዚአብሄር እና ሌለኛው ለሚለቀቅ (ቁጥር 7-8) ፤ ይህ ለጠቅላላ አመቱ በጣም ጠቃሚ የኃጢዓት መስዋዕት ነበር ምክንያቱም ሁሉንም ኃጢዓታቸውን ይሸፍናል በዝርዝር ተረጋግጦ ወደቀዎበት የነበረውን እንካን ይሸፍናል !
- ታላቁ ካህን ለህዝቡ እንደ ኃጢዓት መስዋዕት አንድ ፍየል ይሰዋል ፤ ለህዝቡ መስዋዕት ከማቅረቡ በፊት አሮን ለራሱ ኃጢዓት ትኩረት ማድረጉ ትክክለኛ ፕሮቶኮል ነበር (ቁጥር 5፣ 9፣ 15; ዘኁ 6) ፡፡
ታላቁ ካህን በቅዱሱ ቦታ እንደገና ቅዱስተ ቅዱስ በመግባት በስርየት መቀመጫው ላይ ደሙን ይረጫል (ቁጥር 15-17; ዘጸ 30፡ 10) ፡፡
በመቀጠል ታላቁ ካህን ወደ ሚቃጠል መስዋዕት መሰዊያው በመመለስ በበሬውና በፍየሉ ደም ያነፃዋል (ቁጥር 11, 15, 18-19) ፡፡
ያልተገደለው ፍየል (የተለቀቀው ፍየል) ወደ በርሃ “ይለከው” ነበር (ቁጥር 20-22) ፤ አሮን በፍየሉ ራስ ላይ እጆቹን በማድረግ በላው ላይ የእስራኤል ኃጢዓት ይናዘዝበታል ፤ የተለቀቀው ፍየል በበርሃ ውስጥ ሁሉንም ኃጢዓት ይሸከማል ፡፡
ፍየል ጠባቂው ወደ በርሃ የሚለቀቀውን ፍየል የመራው ራሱን መታጠብ ያስፈልገው ነበር (ቁጥር 26)፡፡
ታላቁ ካህን የተለየ ልብሱን ያወልቃል ፤ ከዚያም እንደገና ይታጠባል የተለመደ የታላቅ ካህን ልብሱን ይለብሳል (ቁጥር 23-24) ፡፡
ታላቁ ካህን አንድ ለራሱ እና አንድ ለህዝቡ ሁለት ወጠጤዎች(በግ) እንደ ሚቃጠል መስዋዕት ያቀርባል (ቁጥር 24) ፡፡
የኃጢዓት መስዋዕቱ ስብ ይቃጠላል (ቁጥር 25) ፡፡
የኃጢዓት መስዋዓት ወይፈኑ እና የኃጢዓት መስዋዕቱ ፍየሉ ለመቃጠል ከመኖሪያ ውጭ ይወጣሉ (ቁጥር 27) ፡፡
የኃጢዓት መስዋዕቱን ያቃጠለው ሰው ራሱን ማንፃት ይኖርበታል (ቁጥር 28) ፡፡
ዛሬ መቅደስ የለም ፤ ዛሬ የእውነት ቤተ መቅደስ የለም ፤ መቅደስ(የመገናኛ ድንካን) ወይም ቤተ መቅደስ ከሌለ የሚሰው ፍየሎች የሉም ፡፡ የአይሁድ ሰዎች ለኃጢዓታቸው የሚሰው የቀጠለ እንስሳት የላቸውም ፤ ያ የሆነበት ምክንያት እነዚህ ሁሉ ወደሚበልጥ ነገር ስላመለከቱ ፡፡ይህ የስርየት ቀን ወደ መጨረሻ ተተኪ አስተሰሪይ ኢየሱስ ክርስቶስ ያመለክታል ፤ በዚህ ሁሉ ውስጥ መሄድ መቀጠል አይጠበቅብንም መክንያቱም መሲህ አለን ፡፡ ለዚያን ጊዜ ይህ ጥሩ ነበር ነገር ግን ዛሬ አናደርገው ፤ እንዴት አድርጌ አውቃለሁ ? ምክንያቱም የቀጠለ ቤተ መቅደስ ስለሌለ ስለዚህ የአይሁድ ሰዎች የቀጠለ አስተሰሪይ መፈለግ አይችሉም(በእነዚህ መስዋዕቶች ውስጥ) ፡፡ ኢየሱስ ለሁሉም አንድ ጊዜ ይህን ተቀብሎአል ፤ ኢየሱስ በደሙ በኩል ህይወትን አመጣ(ዘሌ 17፡ 11) ፡፡
አሁን የተለቀቀው ፍየል በክርስቶስ መነፀር ምን እንደሚመስል እናያለን ፡፡
ማቴ(20፡ 28)፡ ለብዙዎች ራስን እንደ ቤዛ ለመስጠት ኢየሱስ መጣ ፤ ኢየሱስ የተለቀቀ ፍየል ነበር ፤ ለእኛ በእኛ ኃጢዓት ተወሰደ ከዚያም ለእኛ ተገደለ ፡፡
ዮሐ(1፡ 29) አጥማቂው ዮሐንስ ኢየሱስን “ የአለምን ሁሉ ኃጢዓት የሚያስወግድ የእግዚአብሄር በግ” በማለት አስታወቅ ፡፡
2ቆሮ (5፡ 21) የተተኪውን አስተሰሪይ የቀጠለ መልክ ይሰጠናል ፤ ኢየሱስ ኃጢዓት የማያውቀው በእኛ ኃጢዓት ተወሰደ ፡፡ ኃጢዓታችንን ባልሰጠነው ጊዜ ነገሮች በእኛ ውስጥ ይቆያሉ ከዚያም ፍሳሾች መሆን ይጀምራሉ ፤ ኃጢዓትን በራሳችን ለመሸከም በምንሞክር ጊዜ ነገሮችን በራሳችን እናመጣለን ፡፡
ገላ(1፡ 4)፡ የቀጠለ ቤተ መቅደስ ወይም መገናኛ ድንካን ከሌለ ለእኛ ኃጢዓታችንን የሚወስድልን ያስፈልገናል ፤ ኢየሱስ ሲናገር “ ለእናንተ እወስድላችኃለሁ የእናንተም አስተሰሪይ እሆናለሁ ፡፡”
ገላ(3፡ 13)፡ ክርስቶስ ዋጀን ፤ ርግማናችንን ወሰደ ፡፡
ዕባ(9፡ 28)፡ ኢየሱስ አንድ ጊዜ ቀርቦአል ከዚያም ለሁሉም ኃጢዓት መስዋዕትነቱን ከፍሎአል ፤ እስራእላዊያን ይህንን ሂደት ደግመው ደግመው ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር ነገር ግን ኢየሱስ አላደረገም ፤ ኢየሱስ እንደገና በሚመጣ ጊዜ ድነትን ይዞ ይመጣል ፡፡
ዕብ(10፡ 1-10)፡ የስርየት ቀን መስዋዕት በየአመቱ ማድረግ ይጠበቅባቸው ነበር ምክንያቱም ኃጢዓታቸውን ለጊዜው ይቅር ሰለሚባሉ ፤” በዚህም ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስን ስጋ አንድ ጊዜ ፈፅሞ ተቀድሰናል ”(ቁጥር 10) ፡፡
1ጴጥ (2፡ 24)፡ ኢየሱስ በተሰቀለ ጊዜ ኃጢዓታችንን ተሸከመ ስለዚህ “ ለፅድቅ እንድንኖር; በቁስሉ ተፈውሳችኃል ፡፡“
የስርየት ቀን ትርጉም ስርቶአል ምክንያቱም ወደ እነዚህን ሁሉ ነገሮች ወደ አደረገው ኢየሱስ ያመለክታል ስለዚህ ምህረት ማግኘት እንችላለን ፡፡
መዝጊያ
ዘሌ (16፡ 12) የሚለው “ በእግዚአብሄር ፊት ካለው መሰዊያ ላይ የእሳት ፍም አምጥቶ ጥናውን ይሞላል ከተወቀጠውም ከጣፋጩ ዕጣን እጁን ሙሉን ይወስዳል ፤ ወደ መጋረጃውም ውስጥ ያመጣዋል ” ፤ ታላቁ ካህን የወይፈኑን ደም ወደ መጋረጃው ውስጥ ይወስዳል (ቁጥር 12) ፡፡ በማቴ (27፡ 51) ውስጥ ኢየሱስ ደም በፈሰሰ ጊዜ መጋረጃው ለሁለት ተቀደደ ምክንያቱም ከዚህ ቦኃላ ቤተ መቅደስ አያስፈልግም ፡፡ ዕብ(9፡ 15) የሚለው “ ስለዚህም የፊተኛው ኪዳን ሲጸና ሕግን የተላለፉትን የሚቤዥ ሞት ስለ ሆነ የተጠሩት የዘላለምን ርስት የተስፋ ቃል እንዲቀበሉ እርሱ የአዲስ ኪዳን መካከለኛ ነው ፡፡” አሁን መልሱ ኢየሱስ ነው ፤ በሞቱ፣ በፈሰሰው ደሙ ምክንያት ቤዛነትን መቀበል ቻልን ፡፡
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), pp. 153-154.
ጥያቄዎች
-
በአመት አንድ ጊዜ እስራኤላዊያን በስርየት ቀን ይሳተፋሉ ፤ አላማው ምን ነበር(ዘሌ 16፡ 29-30) ? በትክክል ከኃጢዓታቸው ለምን ያህል ጊዜ ይነፃሉ ነበር ? (ዕብ 10፡ 1-4)
-
ታላቁ ካህን “ቅዱሱን ልብሱን” ሊኖ ልብሶቹ ሌሎች ካህናት እንደለበሱት እና የተጠለፈ ጥልፍ ኢፉድ አይደለም ወይም ከከበሩ ድንጋዮቹ ጋር የደረት ኪስ ከመልበሱ በፊት ይታጠብ ፤ ይህ እንዴት አድርጎ ወደ ፊሊ(2፡ 5-7) እና ዕብ ( 2፡ 17) ያመለክተናል ?
-
አንዱ በሬ ለራሱና ለቤተሰቦች የህዝቡን ኃጢዓት ከማሰርየቱ በፊት እንደ ኃጢዓት መስዋዕት በታላቁ ካህን ይቀርባል ፤ እንደኛ ታላቅ ካህን በግልፅ ወይም በምሳሌ ኢየሱስ ለምንድን በሬ አላቀረበም ? (ዕብ 4፡ 1; 7፡ 26-28)
-
የተለቀቀችው ፍየል አላማ ምንድን ነበር ? (ሉቃ 23፡ 13-25)
-
ታላቁ ካህን ዕጣኑን በእግዚአብሄር ፊት በእሳት ላይ ያስቀምጠዋል (ዘሌ 16፡ 12-13) ከዚያም የዕጣኑ ደመና የስርየት መቀመጫውን ይሸፍናል ፤ ዕጣኑ ምንድን ይወክላል ? (መዝ 141፡ 2; ሉቃ 1፡ 10; ራዕ 5፡ 8; 8፡ 3-4)
-
እንደ ዘሌ (16፡ 15) የኃጢዓት መስዋዕቱን የሚያቀርበው ማነው ? እንዴት አድርጎ ይህን ክርስቶስ እንደ ዕብ (7፡ 27; 9፡ 14; ,25-24) መሰረት ፈፀመው ?
-
መጋረጃው ኃላ ወደ ቅድስተ ቅዱስ ታላቁ ካህን ብቻ መግባት ይችላል (ዘሌ 16፡ 17; ዕብ 9፡ 7) ፤ እንዴት፣ መቼ እና ለምንስ ይቀየራል ? ( ማቴ 27፡ 51; ዕብ 4፡ 16; 10፡ 19-20)
-
በዘሌ 18 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Leviticus 16:30
“Atonement will be made for you on this day to cleanse you, and you will be clean from all your sins before the LORD.”
ኦሪት ዘሌዋዉያን 16 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
ለእስራኤላዉያን የስርየት ቀን ወሳኝ የሆነ አመታዊ በዓል ነዉ። ምናልባት ኃጥያታቸዉ እስከ አሁን ባደረጉት የተለያየ መሥዋዕት ያልተከደና ከሆነ ይህ ቀን ያነፃቸዉ እና በእግዚአብሔር ፊት ንፁሃን እንዲሆኑ ያስችላቸዋል። እስራኤላዉያን ብዙ ስርዓት ዉስጥ አልፈዋል። መተላለፋቸዉን በፍየል ላይ አስቀምጠዉ፥ ኃጥያታቸዉ እንዲወገድ ወደ ምድረበዳ ይለቁታል።
በአዲስ ኪዳን፥ ኃጥያትህን የሚያስወግድ የእግዚዓብሔር በግ ኢየሱስ ነዉ። በመሲሃችን ክርስቶስ እንደሚያምን ሰዉ፥ ከአሁን በኋላ ነፃነትን እና ይቅርታን ለማግኘት በነዚያ በዓላት እና ስነ-ስርዓት ማለፍ አይጠበቅብንም። ከኃጥያትህ እስራት ነፃ ወጥተሃል! በክርስቶስ መሥዋዕትነት ምክንያት በፅድቅ መኖር ትችላለህ። ይህ አሁን የምንደሰትበት እና የምናመሰግንበት ነገር ነዉ!
"ይህም የዘላለም ሥርዓት ይሁንላችሁ፤ በዚህ ቀን ትነጹ ዘንድ ማስተስረያ ይሆንላችኋልና በሰባተኛው ወር ከወሩም በአስረኛው ቀን ራሳችሁን አስጨንቋት፥ የአገር ልጅም በእናንተ መካከል የተቀመጠም እንግዳ ሥራን ሁሉ አትሥሩበት፤ በእግዚአብሔርም ፊት ከኃጢአታችሁ ሁሉ ትነጻላችሁ።"
ኦሪት ዘሌዋዉያን 16:29-30
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘሌዋዉያን 16:22፦ "ፍየሉም ኃጢአታቸውን ሁሉ ወደ በረሀ ይሸከማል፤ ፍየሉንም በምድረ በዳ ውስጥ ይለቅቀዋል።"
የየሐንስ ወንጌል 1:29፦ "በነገው ዮሐንስ ኢየሱስን ወደ እርሱ ሲመጣ አይቶ እንዲህ አለ፦ እነሆ የዓለምን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ።"
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:21፦ "እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 62
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።