The Pentateuch Leviticus

Bodily Discharges

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 61 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዘሌ 11 ርኩስ እና ንፁህ እንስሳቶችን ገልፆአል ፤ ዘሌ 12 በሴቶች የወር አበባ ጊዜና ልጅ ከመውለድ ቦኃላ መንፃትን ያወራል ፤ ዘሌ 13 ስለ ቆዳ በሽታ ያወራል ፤ ከዚያም በዘሌ 14 የተሻለ ተገኘ ለሰዎች የቆዳ በሽታቸው እንዲድን የመንፃት ሂደት ተገልፆ ነበር ፡፡ አስታውሱ ካህኑ ወደ ለምፃሙ ሄደ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን እንደመጣው ልክ እንደ ኢየሱስ ፡፡ የመንፃትን መንገድ(ልምድ) ከርኩስ ወደ ንፁኅ የሚሄድበትን ሂደት ተወያይተናል ፡፡

ትምህርት

ዘሌዋውያን(15፡ 1); ለነብዩ እና ለካህኑ ለሙሴና ለአሮን እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ይናገራቸዋል ፡፡

ዘሌዋውያን(15፡ 2-15); እነዚህ ቁጥሮቸ ለወንዶች ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ፈሳሽን ይደርሳል ፤ አስታውሱ የካህኑ ሚና ቅዱሱን ከተለመደው፣ ንፁሁን ከርኩሱ መሀከል መለየትን እንደሚይዝ (ዘሌ 10፡ 10) ፡፡ መቼም ቢሆን አንድ ሰው ከሰውነቱ ፈሳሽ ካለው ርኩስ ነበር ፤ ሀተታ ሰጪዎች ምናልባት ይህ ተቅማጥ ወይም ሆድ ድርቀት ነበር ይላሉ ፤ ማንኛውም ሰው ርኩስ የሆነውን ሰው እና ንብረቱን(የአልጋ ልብስ፣ የቤት ዕቃ፣ ኮርቻ) የነካ ይታጠባል እናም በተጨማሪ እስከማታ ድረስ የረከሰ ነበር ፡፡ ሀተታ ሰጪ ዮሐንስ ማክአርቱር የተናገረው ማንኛውም አይነት ርኩሰት - በዓላት፣ ተፈጥሮ፣ አካላዊና መንፈሳዊ በመቅደሱ እንዳያመልኩ ሰዎችን ይከለክላሉ ፤ በማቴ (23፡ 25-28) ኢየሱስ የውስጥ ንፅህናን በመተው በውጭ ንፅህና ባተኮሩት በፈሪሳዊያንን ላይ ኃዘንን ፈረደባቸው(ወሰነባቸው) ፡፡ ልክ እንደ መንፈሳዊ ፍሳሽ ስለዚህ አካላዊ ስዕል ፍሳሽ አለ ፤ መንፈሳዊ ፈሳሽ እንደ ሀይማኖታዊ መርዝ ነው ፤ ፈሳሽ መንፈሳዊ ወይም አካለዊ ይሁን ከተፈጥሮ ዉጪ ነው ፡፡ ሰውየው ከፈሳሹ በዳነ ጊዜ ሰባት ቀን ይጠብቃል፣ ራሱንና ልብሱን ያጥባል ከዚያም ሁለት ግለገል ርግብ/ዋኖስ በመገናኛ ድንካኑ ላይ መስዋዕቱን ለካህኑ ያመጣል ፡፡

ዘሌዋውያን(15፡ 16-18); አነዚህ ቁጥሮች ተፈጥሮአዊ የሆነ የወንዶችን ፍሳሾች ይደርሳሉ ፤ ይህንን መስፈርት ካነበባችሁ ቦኃላ ወንድና ሴት ወሲብ ማድረጋቸው መጥፎ ነበር ምክንያቱም እንደ ርኩስ ይታሰቡ ስለነበር የሚለውን እይት መውሰድ ትችላላችሁ ፤ ነገር ግን አስታዉሉ ማንም ምንም መስዋዕት አያቀርቡም ፤ በትዳር ውስጥ ወሲብ ማድረግ ችግር የለውም ተፈጥሮአዊ ያልሆነ አይደለም ፤ መታጠብና እስከ ማታ ድረስ ብቻ ይረክሳሉ፡፡ ዋይሰርቤ የተናገረው “ እግዚአብሄር ትዳርን የመሰረተው ለሰው በረከትና ጥቅም ነው “ ፤ አነዚህ ቁጥሮች በረከት ነበሩ ፡፡ ይህ እግዚአብሄር እንዴት እንዳቀደው ነበር ፤ ወሲብ ሀጢዓት አይደለም ፡፡ ይህ ፍሳሽ ቆሻሻ ነበር ግን ሁላችሁም ማድረግ የነበረባችሁ ማፅዳት ነው ፡፡

ዘሌዋውያን(15፡ 19-24); አነዚህ ቁጥሮች የሴቶችን ተፈጥሮአዊ ፈሳሾችን ደርሰዋል ፤ በወር አበባ ጊዜ ሴቲቱና ሁሉም የተጠቀመችባቸው ንብረቶቻ(አልጋ ልብሳ፣ እቃዎቻ) እንደ እርኩስ ትቆጠራለች በተጨማሪም ማንኛውም እሳን የነካ ሁሉ ርኩስ ይሆናል ፡፡ በ 2ሳሙ (11፡ 4) ከርኩስነት ራሳን ለማንፃት ቤርሳቤት ስትታጠብ ዳዊት አያት ፤ በዘፍ(31፡ 26-35) ያዕቆብ ቤተሰቡን ወደ አባቱ ምድር ተመልሶ በሚወስድ ጊዜ ራሄል የላባን የቤተሰቡን ጣዖት ወሰደችው ፤ በግመላም ላይ መቀመጫዋ ስር አስቀመጠችው ፤ ላባን በፔሬድ ምክንያት ርኩስ እንደሆነች ነገረችው ለማግኘት አልጠየቃትም ፡፡ ላባ እሳን እና እቃዋን ከነካ ርኩስ እንደሚሆን ያውቃል ፡፡

አንድ ሰው በወር አበባዋ ጊዜ ከእርስዋ ጋር ከተኛ እናም ደም ከተገኘበት ለሰባት ቀን ረክሶ ይቆያል በተጨማሪም እያንዳንዱ የነካው አልጋ ርኩስ ይሆናል ፡፡ ዋይሰርቤ ሲናገር “ እግዚአብሄር ወሲብን የፈጠረው ለመደሰት(ለፍላጎት)ና ፍጥረትን ለማስቀጠል ነገር ግን ደስታ(ፍላጎት) ቶሎ ቶሎ የሚቀጣ ባሪያ እና የሚያሰቃይ መሆን የለበትም “ ፤ ወሲባዊ ጋንኙነት የማይኖርባቸው ጊዜ ነበሩ ፡፡ ዕብ(13፡ 4) የሚያዘን የትዳር አልጋችን እንዳይቆሽሽ እንድንጠብቅ ንፁህ እንዲሆን ነው ፡፡

ዘሌዋውያን(15፡ 25-30); አነዚህ ቁጥሮች የሴቶችን ተፈጥሮአዊ ያልሆነ ፈሳሾችን ደርሰዋል ፤ አንድ ሴት ከወር አበባ ጊዜዋ የረዘመ የሚፈስ ደም ወይም በሌላ ጊዜ የሚፈስስ ደም በሚኖራት ጊዜ ርኩስ ነች እናም የነካችው ማንኛውም ነገር ርኩስ ነበር ፡፡ዋይሰርቤ ያስቀመጠው “ የረዘመ(የሚቆይ) ደም መፍሰስ በሁለቱም አካለዊ ህመም እና ኃይማኖታዊ ጥፋት ይሆናል ለሴቶቹ የሚቀጥል ርኩስነት ይሆናል ፡፡” ከፈሳሻ በዳነች ጊዜ ከሰባት ቀን በኃላ ስርየት እንዲያደርግላት ለካህኑ በመገናኛ ድንካኑ ላይ እንዲሰዋው ሁለት ግልገል ርግብ/ዋኖስ ታመጣለች ፤ ለዚህ ምሳሌ በማር(5፡ 25-34) ተሰጥቶአል ፡፡ አንዲት ሴት ለ12 አመታት ደም የሚፈሳት ለመዳን ብዙ ዶክተሮችን ብታማክርም ያላትን ሁሉ ብታጠፋም በጣም የባሰ ሆነባት ፤ ስለ ኢየሱስ ሰማች ስለዚህ መጨናነቁ(ግፊያው) ውስጥ ገባች ፤ ሁሉም የናካችው ርኩስ ሆናአል ! የኢየሱስን ቀሚስ በነካች ጊዜ በስርዓቱ ረክሶአል ፤ ነገር ግን ቀሚሱን በነካች ጊዜ ወዲያውኑ የሚፈስሰው ደማ ቆመ ፤ ከመቅሰፍታ(ከበሽታዋ) እንደ ዳነች አወቀች ፡፡ ለሌሎች ፈውስ በምንፀልይ ጊዜ ተስምታአቸዋል(አውቃችኃል) ወይም ምንም አልተሰማችሁም ብሎ መጠየቅ ችግር የለውም! ኢየሱስ ማነው እንደ ነካው ጠየቀ ምክንያቱም ኃይል ከእርሱ ወጥቶ እንደነበር ሰለሚያውቅ ፡፡ በኢየሱስ ባላት እምነት ምክንያት ድና በሰላም እንድትሄድ ነገራት ፡፡

መዝጊያ

እውነታው ሁላችንም በሰዎች ነገር ውስጥ መሄዳችን ነው ፤ አነዚህ ሁሉ ዝርዝሮች ለምን ኖሩን ? ለእኛ በቅዱስና በተለመደ፣ በርኩስና በንፁህ መሀከል ያለውን ልዩነት መረዳት የሚያደርገው ምንድነው ጥሩነቱ ?ዮሐንስማክአርቱር የተናገረው “ እግዚአብሄር ህዝቦችን በራሱ መገኘት መኖርን እንዲለምዱ አንዴ በተመለከተ ጊዜ እነዚህ ህጎች የግል መንፃት ወደ ልብ ንፅህና አስፈላጊነትን በማመልከት በጣም ጥብቅ(ጎጂ) ወይም ደግሞ በጣም ጥቂት እንዳይሆን ለመጠገን ግልፅ ይሆናል ፡፡“ እግዚአብሄር የጠየቀው ማክበር አለብን ምክንያቱም ቅዱስ እንድንሆን ይፈልጋል ፤ አነዚህ የፈሳሾች ዝርዝር ተፈጥሮአዎና ተፈጥሮአዊ ያልሆኑት በትክክለኛው የሰው ህይወት ቅዱስ እንድንሆን ያመለክቱናል ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), pp. 152–153.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 1273–274.

  3. Wiersbe, p. 274.

  4. Wiersbe, p. 275.

  5. MacArthur, p. 153.

ጥያቄዎች

  1. ጠቅላላ በዘሌ 15 ውስጥ ማንኛውም ሰው በፈሳሽ ርኩስ የሆነን ሰው ቢነካ ወይም የተቀመጠበትን ወይም ያረፈበትን ቢነካ እነርሱም እርኩስ ይሆናሉ ፤ ከዘሌ 29፡ 37 ይለያል ፤ ተለይቶ የነበረውን መሰዊያ አንድ ሰው ከነካው ምንድን ይሆናል ?
  2. በዘሌ 15፡ 25 እና 27 አንድ ሴት በማያቐርጥ ፈሳሽ ደም የረከሰች ነበርች በተጨማሪም የነካችው ሁሉ ርኩስ ይሆናል ልብሱንም መቀየር እና መታጠብ ይኖርበታል ፤ በማር(15፡ 25-34) አንዲት ሴት በዚህ ሁኔታ የኢየሱስን ልብስ ነካችው ፤ ርኩስ ሆኖአል ብላችሁ ታስባላችሁ ? አዎ ከሆነ ለምን አልሆነም ከሆነ ለምን ?
  3. ዘሌ 15፡ 12 ከፈሳሽ ጋር የሆነ ሰው የነካው የሸክላ እቃ እንዲሰብሩ ለምን እንዳዘዘ ምን ታስባላችሁ ? በ 2ቆሮ (4፡ 7-10) አማኞች እንደ ሸክላ እቃ ተጠቅሰዋል ፤ በእርኩስነታችን(በኃጢዓታችን) ለምን አልጠፋንም? (1ዮሐ 1፡ 9)
  4. አንደ ዘሌ (15፡ 31) በዘሌ ምዕራፍ 15 ያሉት ህጎች ምንድን ነበር አላማቸው ? እንዴት ክርስቶስ “ከርኩስነታችን” ለየን በዚህ ምክንያት አንሞትም ? (ሮሜ 6፡ 21-22; 1ዮሐ 1፡ 7)
  5. በዘሌ 15 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Leviticus 15:30-31

“The priest is to sacrifice one as a sin offering and the other as a burnt offering. In this way the priest will make atonement for her before the LORD because of her unclean discharge. You must keep the Israelites from their uncleanness, so that they do not die by defiling My tabernacle that is among them.”

ኦሪት ዘሌዋዉያን 15 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር ያያል፥ ከዓይኖቹም ምንም የተሰወረ ነገር የለም። ከአካላችን ፍስሳት በሚወጣበት ጊዜ እንኳን፥ እግዚዓብሔር ያዉቃል! ያያል! የራሱ የሆነዉን ህዝብ፥ ቅዱስ ወደ ሆነዉ የእርሱ ህልዉና እንዲመለስ መንገድን ያበጃል።

በተመሳሳይ መንገድ፥ ካህናት የእስራኤላዉያን ስርየት ሲያካሂዱ እንደነበረ ሁሉ፥ ኢየሱስም ለአንተ ስርየትን አድርጎልሃል። ከእርሱ የተሰወረ እንደሆነ የምታስበዉን ኃጥያት እግዚአብሔር ያየዋል! እንዲህም ይላል፥ "አንተን ይቅር ብዬ ከራሴ ጋራ ለማስታረቅ ዝግጁ ነኝ"። ንፁህ ልብ እና እጅ እንዲኖርህ ይናፍቃል! ወደ እርሱ ተመለስ! እርሱም የሆንከዉን አንተነትህን ተቀብሎ፥ ፀጋ በሞላበት ፍቅሩ ያነፃሃል!

"ካህኑም አንደኛውን ለኃጢአት መሥዋዕት፥ ሌላውንም ለሚቃጠል መሥዋዕት ያቀርባል፤ ካህኑም ስለ ፈሳሽዋ ርኵስነት በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይላታል። እንዲሁም በእነርሱ መካከል ያለችውን ማደሪያዬን ባረከሱ ጊዜ፥ በርኵስነታቸው እንዳይሞቱ የእስራኤልን ልጆች ከርኵስነታቸው ለያቸው።"

ኦሪት ዘሌዋዉያን 15:30-31

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 24:3-4፦ "ወደ እግዚአብሔር ተራራ ማን ይወጣል? በቅድስናውስ ስፍራ ማን ይቆማል? እጆቹ የነጹ፥ ልቡም ንጹሕ የሆነ፥ ነፍሱን ለከንቱ ያላነሣ፥ ለባልንጀራውም በሽንገላ ያልማለ።"

ወደ ዕብራዉያን 4:13፦ "እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።"

1ኛ ጴጥሮስ መልዕክት 1:22-23፦ "ለእውነት እየታዘዛችሁ ግብዝነት ለሌለበት ለወንድማማች መዋደድ ነፍሳችሁን አንጽታችሁ እርስ በርሳችሁ ከልባችሁ አጥብቃችሁ ተዋደዱ። ዳግመኛ የተወለዳችሁት ከሚጠፋ ዘር አይደለም፥ በሕያውና ለዘላለም በሚኖር በእግዚአብሔር ቃል ከማይጠፋ ዘር ነው እንጂ።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 61