The Pentateuch Leviticus

Cleansing of Skin Diseases

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 14 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 60 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ትናትና በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ብዙ ጊዜ ኃጢዓት ስለሚገልጥ ርኩስ በሽታ አውርተናል ፤ ኃጢዓትን ከቆዳ በሽታ ጋር በማገናኘት የተወሰነ ስዕል አሳይቶአል - ኃጢዓት ከቆዳ ስር ነው፣ ይሰራጫል፣ ይበክለናል(ያቆሽሸናል) እናም በመጨረሻ ያጠፋናል ፡፡ መጥፎ ዜና ነበረው ፤ ነገር ግን መጥፎ ዜና ካለ መልካም ዜና ይገኛል ፤ ዘሌ 14 መልካም ዜና ነው ፤ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ እቅድ አለው መዉጫ አለው ፤ ኢየሱስ መውጫችን ነው፡ ኢየሱስ አስተሰሪያችን ነው፣ ተተኪያችን ነው፣ ማመካኛችን ነው ፡፡ የሚገባንን ሞትን ወሰደልን እናም አሁን በደሙ በኩል ህይወት ሊኖረን ቻለ ፡፡ ዘሌ 13 የማትፈልጉአቸውን ሁሉንም ነገር ገልፆአል፤ ዘሌ 14 ስለ መልሶ መንፃት(መልሶ መገንባት) ነው ፡፡

ትምህርት

ዘሌዋውያን(14፡ 1); በዘሌዋውያን በኩል ያለማቐረጥ እግዚአብሄር ከሙሴ ጋር ተነጋገረ ሙሴም እያንዳንዱን ነገር ፃፈ ፡፡ ዋይሰርቤ እንደ ተናገረው በዚህ ምህራፍ ውስጥ በለምፅ የተጠቃን ለመታጠብ እና መልሶ ለመንፃት ሂደቱ ተገልጦዓል ፤ ኮንስታብል አነዚህ ሂደቶች የተለመዱ ግን የማያድኑ እንደነበሩ ጠቅሶአል ፤ ይህ መታጠብ ለመፈወስ ዘዴ ወይም መድሀኒት አልነበረም ይህ ልምድ ህዝቡ የነፃ እንዲሆን የሚፈቅድ እንጂ ፡፡

ዘሌዋውያን(14፡ 2-3); በቆዳ በሽታ የተጠቁ ሰዎች እንዴት መንፃት እንሚችሉ የሚገልፅ ህግ ነበር ፤ ዋይሰርቤ ይህን እንደ አምስት ደረጃ ሂደት ገልፆታል ፤ ሰውየው ከለምፁ ጋር ከመኖሪያ ዉጪ ይኖራል ካህኑ ለምፃሙን ለመመርመር ይሄዳል ፤ መፅሀፍት የሚገልጡት ኢየሱስ ለእኛ ተመሳሳይ አገልግሎት አደረገ ፤ በሉቃ(19፡ 10) ኢየሱስ ሲናገር “ የሰው ልጅ የጠፋውን ሊፈልግና ሊያድን መጥጦአልና ፡፡“ አስተሳሰባችንን ባጣን ጊዜ ጥፋት ወደ እኛ ይመጣል ? ሉቃ(7፡ 34) ሲናገር “ የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጥቶአልና እነሆ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ የቀራጮችና የኃጢዓተኞች ወዳጅ አላችሁት !” ኢየሱስ የለምፃሞች ጋደኛ መሆኑን አሳየ ፡፡ ለእነዚያ እሱ ለሚያስፈልጋቸው ከመኖሪያ ውጪ ለመሄድ ችግር አልነበረበትም ፡፡

ዘሌዋውያን(14፡ 4-7); ካህኑ የቆዳ በሽታው እንደጠፋ ባረጋገጡ ጊዜ ለመታጠብ በህይወት ያሉ ሁለት ንፁህ ወፎች ከዝግባ እንጨት ጋር፣ ቀይ ግምጃም እና ሂሶጵም እንዲያመጣ ያዝዘዋል ፡፡ ተጠቂውም የማስተሰሪያ ስዕል የነበሩትን ሁለቱን ወፎች ያቀርባል ፤ የመጀመሪያዋ ወፍ ታረደ ከዚያም በሚነፃው ላይ ደሙ ሰባት ጊዜ ይረጭ ነበር ፤ ይቺ ወፍ ሞትን ትወክላለች ፤ ከዚያ ቦኃላ ከመጀመሪያዋ ወፍ ደም ውስጥ በመንከር ክፍት በሆነው በሀገሪቱ በኩል ሁለተኛው ወፍ ይለቀቅ ነበር ፤ ይቺ ሁለተኛይቱ ወፍ በሞት የመጣውን ነፃነት ይወክል ነበር ፡፡ ይህ የተተካን አስተሰሪይ መልክ ነበር ፡፡

ነፃነታችን በክርስቶስ ደም በኩል ብቻ መጣ ፤ ዮሐ 3፡ 13 እና 31 ኢየሱስ ከሰማይ እንደመጣ ይገልፃሉ ፤ ዮሐ 6፡ 38 እና 42 ኢየሱስ የአባቱን ፍቃድ ለማድረግ ወደ ምድር እንደመጣ ይናገራል ፡፡ ስርየት አለልን ምክንያቱም የሰው ልጅ ወደ ምድር መጥቶአል፣ ለእኛ ሞቶአል፣ ተቀብሮአል ከዚያም በሰዎስተኛው ቀን ተነስቶአል (1ቆሮ 15፡ 1-4) ፤ በዚህ ሂደት መንፃትን ታያልችሁ ፡፡ ዕብ( 9፡ 22) የሚለው “ እንደ ህጉም ከጥቂቶች በቀር ነገር ሁሉ በደም ይነፃል ደም ሳይፈስ ስርየት የለም ፡፡”

በ 2ነገ (5፡ 10-14) ንዕማን ለምፃም ነበር ነብዩ ኤልሳ እንዳዘዘው በዮርዳኖስ ወንዝ ሰባት ጊዜ ታጠብ ከዚያም ነፃ ፤ አንዳንድ ጊዜ በሆነ መንገድ ከእግዚአብሄር መልስ እንፈልጋለን ነገር ግን እግዚአብሄር በፈለገው ሊያደርግ ይችላል ፡፡

ዘሌዋውያን(14፡ 8-9); በመቀጠል ሰውየው ልብሱን በማጠብ፣ ሁሉንም ፀጉሩን በመላጨት እና በውሃ በመታጠብ ራሱን ያነፃል ፤ ከዚያም ወደ መኖሪያ እንደገና መግባት ይችላል ግን ለሰባት ቀን ከድንካኑ ዉጪ ይቆያል፡፡ በሰባተኛው ቀን እንደገና ሁሉንም ፀጉሩን በመላጨት፣ ልብሱን በማጠብ እና በውሃ በመታጠብ እንደገና ራሱን ያነፃል ፡፡

ዘሌዋውያን(14፡ 10- 11); በስምንንተኛው ቀን የሚፈለግበትን መስዋዕት እንከን የሌለባቸው ሁለት ወንድ ጠቦት፣ እንከን የሌለባት አንድት ሴት ጠቦት እና የህል መስዋዕት በካህኑ ፊት በመገናኛው ድንካን ፊት ያቀርባል ፡፡ እንደገና ሂደቱ በራሱ ማንንም አያድንም አያነፃም ፤ ይህ መታጠብን(መንፃትን) የሚለመድት ሂደት ነበር ፤ ሂደቱ በመጀመሪያ ቀን አሮን ያቀረበውን አራቱን መስዋዕት ይመስላል ፡፡

ዘሌዋውያን(14፡ 12-18); መስዋዕቱ እንዴት እንደሚደረግ ቁጥሮቹ በዝርዝር ይገልፃሉ ፤ የሚያስፈልጉት መስዋዕት የካሳ መስዋዕትን(የመተላለፍ ወይም የጥፋተኝነትን መስዋዕት) ይይዛል ፡፡ ካህኑ አንድ ወንድ ጠቦት እና የወይራ(የሎግ መስፈሪያ) ዘይት በመውሰድ በእግዚአብሄር ፊት ይወዘውዛቸዋል (ቁጥር 12) ፤ በተጨማሪም የኃጢዓት መስዋዕትና የሚቃጠል መስዋዕት ያደርጋል (ቁጥር 13) ፤ በመቀጠል ካህኑ በቀኝ ጆሮው ጫፍ ላይ፣ ቀኝ አውራ ጣቱ ላይ እና በቀኝ የእግር አውራ ጣቱ ላይ ጥቂት ደም ንፁህ በሚሆነው ሰው ላይ ያስቀምጣል ፡፡ በቀጣይ ካህኑ ጥቂት የወይራ(የሎግ መስፈሪያ) ዘይት በመውሰድ በእግዚአብሄር ፊት ሰባት ጊዜ ይረጫል ጥቂቱ ደግሞ በቀኝ ጆሮው፣ አውራ ጣቱ ላይ እና እግሩ ትልቅ ጣት ላይ ያደርጋል እናም የቀረውን በሰውየው ራስ ላይ ያደርጋል ፡፡

ዘሌዋውያን(14፡ 19-20); ከዚያም ካህኑ ለሰውየው ስርየት ለማድረግ የኃጢዓት መስዋዕት ከሚቃጠል መስዋዕት እና ከእህል መስዋዕት ጋር ይሰዋል ፤ ካህኑ ለሰውየው ስርየት ባደረገለት ጊዜ ንፁህ ያደርገዋል ፡፡ በወይራ(በሎግ መስፈሪያ) ዘይት ህዝቡን የመቀባት የካህናቱ ስዕል ለእነረሱ የተለመደ ሆናል ፡፡ በማር(6፡ 13) ኢየሱስ ደቀመዛሙርቱን በዘይት ባዙ ሰዎችን እንቀቡና እንዲፈውሳቸው ሾማቸው ፤ ኢየሱስ እግዚአብሄር ለካህናቱ ሰጥቶአቸው ከነበረው ህግ አንፃር ተመለከተም ወደ በራሱ አገልግሎትም ውስጥ ተሸከማቸው ፡፡ ይህ ሁሉ ትልቅ ማረጋገጫ እንድናስብ ያደርገናል ፤ በሄዱበት ውስጥ በጣም ብዙ ነበር ፤ ከዚያም ይህ ሂደት ሲያበቃ ካህኑ ስርየት ያደርጋል ሰውየውም ንፁህ ይደረጋል(ይሆናል) ፡፡

ዘሌዋውያን(14፡ 21-57); እነዚህ ጥቅሶችም በዝርዝር አይሸፍኑም እንጂ የተለያዩ ሌሎች የተለመዱ መታጠብን ይገልፃሉ ፤ ቁጥር 21-32 ለሆነ ሰው የተገለፁት መስዋዕቶች ማቅረብ ካልቻለ ለመንፃት የሚያደርገውን ይሰጣል ፤ ቁጥር 33-57 የተበከለ እቃ እንዴት መንፃት እንደሚችል እንዲሁም ከዚያስ ቦኃላ መስዋዕቱ እንዴት እንደሚቀርብ ይገልፃል ፡፡

መዝጊያ

ሉቃ(17፡ 11-19) በኢየሱስ ስለተፈወሱት አስር ለምፃሞች ታሪክ ይናገራል ፤ አንዱ ብቻ ነበር እንደተፈወሰ ያወቀው ከዚያመ ለኢየሱስ ክብር ሊሰጥ ተመልሶ የመጣው ፤ ኢየሱስም “ እምነትህ አድኖሀል” ብሎ ነገረው ፤ ይህ ለምፃም መልካሙን ዜና ቀምሶታል ፡፡ እምነት ሲኖራችሁ መልካም ዜና ይኖራችኃል ፤ እምነት ሲኖራችሁ ያ እምነት ደህና ያደርጋችሃል(ያድናችኃል) ፡፡ ህይወትን ለመቅመስ(ለማግኘት) ከኃጢዓትና ከሞት መሄድ ትችላላችሁ ምክንያቱም በመሲሁ እምነት አላችሁ ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 271.

  2. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Leviticus, p. 116; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/leviticus.pdf.

  3. Wiersbe, p. 271–272.

ጥያቄዎች

  1. ለምፅ ያለባቸው ሰዎች ከመኖሪያ ዉጭ ይኖራሉ ስለዚህ ካህናቱ እነርሱን ለመመርመር ከመኖሪያው ዉጭ ይሄዳሉ (ዘሌ 14፡ 3) ፤ ለምፅ ላለበት ሰው ይህ እንዴት ተስፋ ይሰጣል ? ሌሎች እንደ ርኩስ ለሚቆጥሩዓቸው ኢየሱስ እንዴት መለሰላቸው ? ዛሬስ እንዴት ይመልሳል ? (ሉቃ5፡ 32; 7፡ 34; 19፡ 10; ሮሜ 5፡ 8)
  2. ለመንፃት በብዓላት ላይ የአንዳን ወፍ ደም ማፍሰስ ለምን ነበር አስፈላጊነቱ ? (ዘሌ 14፡ 5-7; ዕብ 9፡ 22)
  3. ርኩስነቱን ለማስወገድ እና እንደገና በህብረተሰቡ ውስጥ ለማስተዋወቅ አንድ ሰው የሚሄድባቸው ሰዎስት የሚከበሩ በዓላት ምንድን ነበሩ ? (ዘሌ 14፡ 2-8; 9; 10-32) በምን ቀን ነበር የሚያደርጉት ?
  4. ለምፅ እንደ ርኩስ ይቆጠር ነበር ፤ ሁኔታው ሲጠራ እንደ “ንፁህ” ይቆጠራሉ ፤ ዛሬ ልባችን እንዴት ነው የታጠበው ወይም የጠራው ? (ሐዋ 15፡ 9; 2ቆሮ 7፡ 1; ኤፌ 5፡ 26; ያዕ 4፡ 8; 1ዮሐ 1፡ 7; 9)
  5. ማስታዎሻ፡ ሁኔታዎቻቸው ሲፈወሱ እውር ወይም አንካሳ እንደ “ዳነ” ሲቆጠር ከዚያም ለምፃቸው እንደ “ነፃ” ይቆጠራል ፡፡
  6. በዘሌ 14 ላይ በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ(አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Leviticus 14:18-19a

“The rest of the oil in his palm the priest shall put on the head of the one to be cleansed and make atonement for them before the LORD. Then the priest is to sacrifice the sin offering and make atonement for the one to be cleansed from their uncleanness.”

ኦሪት ዘሌዋዉያን 14 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

እግዚአብሔር ልዩ ልዩ የሆኑ እና ብቁ ያልሆኑ ሰዎች ሳይለይ ወደ እሱ የሚቀርቡበትን መንገድ አዘጋጅቷል። የሂሶጵ ተክል ከቆዳ በሽታ ጋራ በተገናኘ ለእስራኤላዉያን ጥቅም ላይ ዉሎ ነበር። እንደገና ንጹህ ለመሆን ቤት እና ሽገትም እንዲሁ ይጠቀሙ ነበር። የፍርድ ዒላማ መሆን አቁሟል! ሂሶጵ የጥሩነት እና የመንፈሳዊ ንፅህና ምልክት ነበር።

የእግዚአብሔር ፍቅር የኃጥያታችን ስርየት ነዉ። እርሱ መንገድ፣ እዉነት፣ ህይወትም ነው! መንገዳችንን ማየት በማንችልበት ጊዜ እንኳን እርሱ መንገድ ያበጅልናል! ምንም ዓይነት ነገር ብትሰራ ወይም የህይወት ጠባሳ ብትሸከም፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋ እና ፍቅር የተሸፈንክ ነህ! እንደ በረዶ ነጭ እና ንፁህ አድርጎ ይቆጥርሃል! ዛሬ፥ እርሱ ለአንተ ያልዉን ፍቕር ተቀበል!

"በካህኑም እጅ ውስጥ የቀረውን ዘይት በሚነጻው ሰው ራስ ላይ ያደርግበታል፤ ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል። ካህኑም የኃጢአቱን መሥዋዕት ያቀርባል፥ ከርኵሰቱም ለሚነጻው ሰው ያስተሰርይለታል፤ በኋላም የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያርዳል።"

ኦሪት ዘሌዋዉያን 14:18-19

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 51:7፦ "በሂሶጵ እርጨኝ፥ እነጻማለሁ፤ እጠበኝ፥ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናለሁ።"

የዮሐንስ ወንጌል 14:6፦ "ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።"

የዮሐንስ ወንጌል 19:28-30፦ "ከዚህ በኋላ ኢየሱስ አሁን ሁሉ እንደተፈጸመ አውቆ የመጽሐፉ ቃል ይፈጸም ዘንድ፦ ተጠማሁ አለ። በዚያም ሆምጣጤ የሞላበት ዕቃ ተቀምጦ ነበር፤ እነርሱም ሆምጣጤውን በሰፍነግ ሞልተው በሁሶፕም አድርገው ወደ አፉ አቀረቡለት። ኢየሱስም ሆምጣጤውን ከተቀበለ በኋላ፦ ተፈጸመ አለ፥ ራሱንም አዘንብሎ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠ።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 60