Skin Diseases
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 13 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ትናትና የርኩስን እና ንፁህ የምድር እንስሳቶች የውሃ እንስሳቶች፣ የሚንቀሳቀሱ እንስሳቶች፣ ነፍሳት እና አእዋፍን መዘርዘርን አድርገናል ፤ እግዚአብሄር ህዝቡን ለመለየት ንፁህና ንፁኅ ያልሆኑ እንስሳቶችን ተጠቀመ; ይህ የእግዚአብሄር ቅዱስ ህዝብ ነበር ፡፡ ዛሬ በሌላ ዝርዝር በኩል እንቀጥላለን፡ በሽታዎች ፡፡ በዘሌ 10 አስታውሱ እግዚአብሄር ለአሮን ተናገረው ከዚያም ካህናት አልኮል መጠጣት እንደማይችሉ ነገረው ምክንያቱም ቅዱሱን ከተለመደው፣ ርኩሱን ከንፁሁ መካከል መለየት ስለሚለዩ ፡፡
ትምህርት
ዘሌዋውያን(13፡ 1); ለሙሴና ለአሮን ስለ ተለያዩ የቆዳ በሽታዎች ነገራቸው ከዚያም ካህናቱ እያንዳንዱን ሁኔታ እንዴት እንደሚለዩ ዝርዝር መመሪያ ተሰጣቸው ፡፡ ካህናቱ በሰዎች ላይ እና አቐማቸውን ምን ነበር ርኩስ ምን ነበር ንፁህ የሚለውን ለማጥናትና ለመለየት ኃላፊነት ነበረባቸው ፡፡
ዘሌዋውያን(13፡ 2-8); ኮንስታብል የጠቀሰው ለተለያዩ የቆዳን በሽታዎችን ለመለየትት አምስት የመለያ መስፈርቶችን እግዚአብሄር ሰጣቸው ፤ የመጀመሪያው መለያ መስፈርት ለሽፍታ ነበር ፤ ማንኛውም በአካሉ ላይ እባጭ፣ ብጉር ወይም ቐቁቻ ሰውየው ርኩስ ነው ወይስ ንፁህ ነው የሚለውን መጨረሻ በሚወስኑት በካህናቱ ይመረመራል ፡፡
ዘሌዋውያን(13፡ 9-17); አነዚህ ቁጥሮች ለቆዳ በሽታዎች ሁለተኛውን መለያወች መስፈርት ይሸፍናሉ ፤ ሰውየው በቆዳው ላይ ነጭ እባጭ፣ ነጭ ፀጉር ወይም በእባጩ ውስጥ የተላጠ ስጋ ከነበረው ካህኑ ርኩስ ነው ብሎ ያውጃል(ያረጋግጣል) (ቁጥር 10-11) ፤ የተላጠው ስጋ ከተቀየረ እና ነጭ በሆነ ጊዜ ካህኑ ንፁህ ማለት ይችላል (ቁጥር 17) ፡፡
ዘሌዋውያን(13፡ 18-23); እነዚህ ቁጥሮች ሰዎስተኛውን መለያዎች መስፈርት በቆዳ ላይ ያለን ቁስል እና በምን አይነት ሁኔታ ካህኑ ርኩስ ወይም ንፁህ እንደሚለው ይሸፍናሉ ፡፡
ዘሌዋውያን(13፡ 24-28); አነዚህ ቁጥሮች አራተኛውን መለያዎች መስፈርት በሰዉየው አካል ላይ ቃጠሎ(ትኩሳት) መለየትን ይሸፍናለ ፡፡ ቃጠሎው(ትኩሳቱ) በመረመረበት መሰረት ካህኑ ሰውየውን ርኩስ ይለዋል ፤ ቃጠሎው ሲድን ካህኑ ሰውየውን እንደገና ንፁኅ ይለዋል ፡፡
ዘሌዋውያን(13፡ 29-37); እነዚህ ቁጥሮች አምስተኛውን መለያዎች መስፈርት የተለያየ ቦታ ላይ የሆነን ተላለፊ ቁስልን ይሸፍናሉ ፤ የተጎዳውን ቦታ ከመረመረ ቦኃላ ካህኑ ሰውየውን ርኩስ ወይም ንፁህ ብሎ ይወስናል ፡፡
ዘሌዋውያን(13፡ 38-44); ካህናቱ ሰዎቹን በሽፍታ ወይም በራሰ በራነት ንፁሁን ወይም ርኩሱን ለመለየት መረመሩ ፡፡
ዘሌዋውያን(13፡ 45-46); የሆነ ሰው ርኩስ ከተደረገ ልብሳቸው የተቀደዱ መሆን አለባቸው፣ ፀጉራቸውንም የተላጩ ይሁኑ፣ አፋቸውን የተሸፈነ መሆን አለበት(የላይኛውን ከንፈራቸውን ወይም አፍንጫ ስር ያለ ፂም) ከዚያም “ርኩስ ርኩስ !” እያሉ መጣራት አለባቸው ይህ የሚሄዱ ሞት እንደነበሩ የማዘናቸው ምልክት ነበር ፡፡ የቆዳ በሽታ ወይም ለምፅ ባለበት ሰው ዙሪያ መሆን ማንም አይፈልግም ነበር ፤ ዋይሰርቤ ሲናገር እዚህ ጋር ሰውየው ከመኖሪያ ዉጪ ይወሰዳል እናም ከመኖሪያ ዉጪ የነበረ ሰው ከእግዚአብሄር መገኘት የራቀ ነበር ፡፡ የመጨረሻው ስዕሉ ያ ሰው በኃጢዓቱ ምክንያት ተለየ ፤ ብዙ ስነ መለኮታዊያን ያሉት በዚህ አገላለፅ በሽታው የሆነ ኃጢዓት ቅርፅ ውጤት ነበር፡፡
ዘሌዋውያን(13፡ 47- 59); እነዚህ ቁጥሮች ካህናቱን የተለያዩ ልብሶችን እንደ ርኩስ ወይም ንፁህ እንዲመረምሩ መሩዓቸው ከዚያም ርኩስ የሆኑ ልብሶች እንዲቃጠሉ ጠቅሶዓል ፡፡
ይህ ዝርዝር የሚያሳየን ለእስራኤል ለምፅ እንዴት አደገኛ አንደነበር በተጨማሪም በመፅሀፍ ውስጥ ጠቀሜታውን ነው ፤ በዘጸ(4፡ 7) ሙሴ እጁን በብብቱ ውስጥ አስቀመጠ ከዚያም በለምፅ ተሸፈነች ፤ በመቀጠል እጁን በኮቱ ውስጥ እንደገና ሲያስቀምጠው ለምፁ ዳነ ፤ በዘኁ(12፡ 10) ማሪያም ሙሴን በተናገረች ጊዜ በለምፅ ተመታች ፤ በ 2ነገ 5 ንዕማን በቆዳ በሽታ የተመታ አስደናቂ ጦረኛ ነበር (ስለዚህ ብዙ በቀጣይ ክፍል) ፡፡ ስለዚህ ስለ ቆዳ በሽታ በዚህ ሁሉ መረጃ ምን እናድርግ ?
ዋይሰርቤ እንዴት ሁሉንም እንደምንወስድ እና ለእስራኤላዊያን እንደምናደርገው በተጨማሪም ለእኛ ገልፆአል ፤ እንደ ዋይሰርቤ በሽታ የኃጢዓት ማሳያ ነበር ፡፡
- የኃጢዓት ምልክቶች ከቆዳ የበለጠ የጠለቁ ናቸው ፤ በዘሌ (23፡ 3-4) ካህናቱ ከቆዳ የጠለቀ እንደነበር ለማየት በሽታውን መርምረዋል(ይመረምራሉ) ፡፡ ኤር(17፡ 9) የሚያስጠነቅቀን “ የሰው ልብ ከሁሉ ይልቅ ተንኮለኛ እጅግም ክፉ ነው ፤ ማንስ ያውቀዋል ? “ በሮሜ (7፡ 18) ጳውሎስ እንደ ተናገረው በስጋው ጥሩ ነገር አልኖረም ምንም እንካን ጥሩ ለማድረግ ቢፈልግም ለማድረግ ችሎታው አልነበረውም ፡፡
- ኃጢዓት ይስፋፋል ተብሎ ይጠበቃል(ይታሰባል) ፤ ዘሌ(13፡ 5-7, 34-36) የሚስፋፋ በሽታ ርኩስ እንደሆነ ይናገራል; ነገር ግን በሽታው ካልተስፋፋ ሰውየው ደህና ነበር ፡፡ በያዕ(1፡ 14-15) እንዴት ፍላጎት እና ክፉ ሀሳብ መፈለግ ከዚያም ኃጢዓት እንደሚወለድ በመጨረሻም ወደ ሞት እንደሚመራ ገልፆታል ፡፡
- ኃጢዓት በግልፅ ይበክላል ፤ በዘሌ( 13፡ 44-45) የሚያወራው ካህናቱ ርኩስ ብለው የፈረዱበት ሰው “ርኩስ” እያለ መጮህ ነበረበት ፡፡ በኢሳ( 6፡ 5) ኢሳያስ ራሱን ገለፀ “ከንፈሩ በረከሰ ህዝብ መሀከል” እኖራለሁና “ ከንፈሬ የረከሰ ሰው ነኝ” ከቆይታ ቦኃላ የተናገረው “ ሁላችን እንደ ረከሰ ሰው ሆነናል “ ኢሳ(64፡ 6) ፡፡ ኃጢዓት ሁል ጊዜ ወደ ብክለት ይመራል ፤ በመዝሙር 51 ዳዊት ኃጢዓት አይኖቹን(ቁጥር 3)፣ አይምሮውን(ቁጥር 6)፣ ጆሮቹንና አጥንቱን(ቁጥር 8)፣ ልቡን (ቁጥር 10) እና አፉን(ቁጥር 13-14) እንደጎዳው ገለፀ ፡፡
ኃጢዓት ወደ ውስጠኛው ክፍል ሲሄድ በዚህም ሁሉም ነገርህ ይበከላል ፤ ለዚያ ነው ዳዊት ለመታጠብ (ቁጥር 2) እና ለመንፃት(ቁጥር 7) ያለቀሰው ፡፡ በኃጢዓት ከተበከላችሁ መታጠብ አለባችሁ ፡፡
ኃጢዓት ይለያል ፤ በዘሌ(13፡ 46) ርኩስ የሆነ ሰው ከመኖሪያ ውጭ ብቻውን ይኖራል ፤ በ 2ነገ(15፡ 5) ንጉስ ዓዛሪያስ በከባድ የቆዳ በሽታ ተጠቃ ከዚያም በራሱ በተለየ ቤት ውስጥ ኖረ ፡፡ ራሳችሁን በለያችሁ ጊዜ ኃጢዓት ተፅዕኖ እንዳለው ታውቃላችሁ ፡፡
ኃጢዓት የሚመጥነው ለእሳት ብቻ ነው ፤ የተበከለ ልብስ በእሳት ውስጥ ይቃጠላል(ዘሌ 13፡ 52፣ 55፣ 57) ፤ ማር(9፡ 44) የገለፀው ከክርስቶስ ጋር ህብረት(ግንኙነት) ከሌላችሁ ኃጢዓት ህይወታችሁን ይወስደዋል(ይቆጣጠረዋል) ወደ እሳትም ይመራችኃአል ፤ ማቴ(25፡ 41) የሚለው አነዚያ የተረገሙት “ለዘላለማዊ እሳት” ተዘጋጅተዋል ፡፡
አነዚህ ሁሉ ምልክቶች ወደ ታላቅ ጉዳይ ኃጢዓት ያመለክታሉ ፤ እስራኤላዊያን በቐሚነት የኃጢዓታቸውን ውጤት መርምረዋልም ገጥሞአቸዋልም ፡፡
መዝጊያ
በሉቃ(5፡ 12-16) የተመዘገበውን ታሪክ እስኪ እናስብ ፤ አንድ ሰው በመላው ሰዉነቱ ላይ ከባድ የቆዳ በሽታ ነበረበት ይሰራጭም ነበረ ስለዚህ ርኩስ ነበር(ቁጥር 12) ፤ ሰውየው ኢየሱስ እንዲፈውሰው ለመነው(ቁጥር 12) ፤ ርኩስ ይሁን እንጂ ሰውየው ወደ ኢየሱስ መጣ ፤ ለምፃም ከማህበረሰቡ ውጭ እንዲሄዱ ቢታመንም ኢየሱስ ነካው(ቁጥር 13) ፤ የነካው የኢየሱስ እጅ ወዲያውኑ ፈወሰው ፤ ወዲያውኑ ተፈወሰም ንፁህም ተደረገ(ቁጥር 13) ፤ ኢየሱስ ሰውየውን ለማንም እንዳይናገር ግን ለምርመራ ለካህናቱ እና በሙሴ የታዘዘውን መስዋዕት እንዲያደርግ ራሱን እንዲያሳይ ነገረው (ቁጥር 14) ፡፡ ስለ ኢየሱስ ዜና በፍጥነት ተሰራጨ ከዚያም ለመፈወስ ከፍተኛ መጨናነቅ መጣ(ቁጥር 15) ፡፡
ርኩስ የነበረው ሰውየ በክርስቶስ መነካት ውስጥ ንፁህ ሆነ ፤ ወደ እግዚአብሄር ተመለሰ ፤ በኃጢዓት ወይም በቆዳችሁ ውስጥ እየሄዳችሁ ቢሆንም ወደ እግዚአብሄር ተመለሱ ፤ ኢየሱስ በአካላዊ፣ በስሜታዊና በመንፈሳዊ ሊፈውሳችሁ ይፈልጋል ፤ ስለ እያንዳንዱአ ነገራችሁ ሊፈውሳችሁ ይፈልጋል ፤ ደህና እንዲትሆኑ ይፈልጋል ፤ ንፁኅ እንዱትሆኑ ይፈልጋል ፤ ይህ የሚሆነው በክርስቶስ ደም በኩል ነው ፡፡
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Leviticus, p. 112; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/leviticus.pdf.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 271.
Wiersbe, p. 270–271.
ጥያቄዎች
-
ለካህናቱ ስለ ጥቂት ህጎች አንብበናል ፤ የሚይዛቸውም ወይን ወይም ቢራ አለመጠጣት፣ ቅዱስን ካልተቀደሰው መለየት፣ ርኩሱን ከንፁሁ፣ በተጨማሪም ለእስራኤላዊያን ሁሉንም የእግዚአብሄርን ደንቦች ያስተምራሉ (ዘሌ 10፡ 9-11) ፤ በዘሌ 13 የካህናቱ ሌላ ህግ/ሚና ምንድን ነበር ?
-
ለቆዳ በሽታ አረቱ መመርመሪያዎች ምንድን ነበሩ ? (ዘሌ 13፡ 2-28)
-
በዘሌ (13፡ 6) ካህኑ ሰዉየውን በሰባተኛው ቀን ከመረመረ በኃላ ቁስሉ ከዳነ ሰውየው እንደ ንፁኅ ይቆጠራል ፤ ልብሱን ያጥባል ከዚያም እንደ ንፁኅ ይቆጠር ነበር ፤ ሙሉ ለሙሉ የታጠብን ወይም የነፃን እንድንሆን የሚያስደንቁ ጥቂጥ ተስፋዎች ምንድን ናቸው ? (ዮሐ 13፡ 8; 1ቆሮ 6፡ 11; ዕብ 10፡ 22; 1ዮሐ 1፡ 7)
-
በኬይል መልዕክት የጠቀሰው የቆዳ በሽታ ለትልቁ ችግር ኃጢዓት ለተባለው ምልክት መሆን እንደቻለ ነው ፤ ኃጢዓት ከቆዳ የበለጠ ጠልቆ መግባቱን እንዴት አድረገን እናውቃለን ?
-
በራሳቸው ከመኖሪያ ውጪ በሆነ ቦታ ስለሚኖሩ ስለ ቆማጣ ሰዎች ሲነበብ አስከፊ ነው በተለይ ደግሞ ተስፋ የሌላቸው ሲመስሉ ፤ በክርስቶስ ስላላችሁ ተስፋ እና በህይወታችሁ አካላዊው ወይም መንፈሳዊው ፈውሱን አጋሩ ፤ በሉቃ(5፡ 12-16) ያለው ታሪክ እናንተን እንዴት ነው የሚያበረታታችሁ ?
-
በዘሌ 13 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ (አስረዳችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Leviticus 13:46
“He will remain unclean as long as he has the infection; he is unclean. He must live alone in a place outside the camp.”
የክርስቶስ የፈዉስ ዳሰሳ ንፁህ ያደርገናል!
ኦሪት ዘሌዋዉያን 13 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
የቆዳ በሽታዎች እና ሽፍታዎች ቀላል ነገሮች አይደሉም! በፊታችሁ ላይ አንዲት ብጉር እንኳን ወጥቶባችሁ ከሆነ ምንያክል ወልካፋ ወይም የማይመች እንደሆነና ራሳችንን እንድናስታዉስ እንደሚያደርገን ታዉቃላችሁ። የቆዳ ሽፍታ፣ የቆዳ በሽታ ወይም ብጉንጅ ይዘዉ እና ከህዝቡ በግድ ተገደዉ ዉጪ እንዲኖሩ የሚገደዱበት ብሎም ህፍረትን የሚከናነቡበት መንገድ፥ ከዚያም ወደ ካህናት ራሳቸዉን የሚያቀርቡ እስራኤላዉያንን ህይወት ማሳብ እጅግ ከባድ ነዉ!
በክርስቶስ ፀጋ እና ፍቅር የተነሳ፥ በክርስቶስ አካል ዉስጥ ተቀባይነትን በማግኘት፥ ህብረትን ማድረግ ችለሃል። አይኖችህን ክፈትና በተክለ ሰዉነታቸዉ መለየት ምክንያት ህብረትን ማድረግ እንዳማይችሉ የሚሰማቸዉን ዉጭ ያሉትን ሰዎች ተመልከት! ወይም ማን ያዉቃል ህብረትን ማድረግ እንደማትችል እየተሰማህ ያለኸዉ አንተ ልትሆን ትችላለህ። አስታዉስ፦ አንተ ለዘልዓለም የእግዚአብሔር ቤተሰብ አካል ነህ! ከፍቅሩ ማንም ሊለይህ አይችልም! ዛሬ፥ የእርሱ ፍቅር በአንተ ላይ ይብራ!
"ደዌው ባለበት ዘመን ሁሉ ርኩስ ይሆናል፤ እርሱ ርኩስ ነው፤ ብቻውን ይቀመጣል፤ መኖሪያውም ከሰፈር በውጭ ይሆናል።"
ኦሪት ዘሌዋዉያን 13:46
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 139:14፦ "ግሩምና ድንቅ ሆኜ ተፈጥሬአለሁና አመሰግንሃለሁ፤ ሥራህ ድንቅ ነው፥ ነፍሴም እጅግ ታውቀዋለች።"
የማቴዎስ ወንጌል 5:44-45፦ "እኔ ግን እላችኋለሁ፥ በሰማያት ላለ አባታችሁ ልጆች ትሆኑ ዘንድ ጠላቶቻችሁን ውደዱ፥ የሚረግሙአችሁንም መርቁ፥ ለሚጠሉአችሁም መልካም አድርጉ፥ ስለሚያሳድዱአችሁም ጸልዩ፤ እርሱ በክፎዎችና በበጎዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና፥ በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባልና።"
ወደ ሮሜ ሰዎች 8:38-39፦ "ሞት ቢሆን፥ ሕይወትም ቢሆን፥ መላእክትም ቢሆኑ፥ ግዛትም ቢሆን፥ ያለውም ቢሆን፥ የሚመጣውም ቢሆን፥ ኃይላትም ቢሆኑ፥ ከፍታም ቢሆን፥ ዝቅታም ቢሆን፥ ልዩ ፍጥረትም ቢሆን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚአብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቼአለሁ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 59
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።