The Pentateuch Leviticus

Clean and Unclean Animals

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 11-12 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 58 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዘሌ 8 ውስጥ አሮንና ልጆቹ ተለዩም ጥሪያቸውንም ተቀበሉ ፤ በዘሌ 9 በመጀመሪያ በስራቸው ቀን አራቱን መስዋዕት አደረጉ ፡፡ አሮን ህዝቡን ባረከ በመቀጠል አሮንና ሙሴ በመገናኛው ድንካን ጋር ቆመው ህዝቡን ባረኩ ፤ ሁሉም ነገር በጥሩ እየሄደ ይመስላላ አስከ ዘሌ 10 ናዳብና አብድዩ በራሳቸው የሆነ ነገር ለማድረግ እስኪወስኑ ፤ ያልተገባ(ትክክል ያልሆነ) መስዋዕት አመጡ ከዚያም እግዚአብሄር በእነርሱ ላይ እሳት አመጣ ገደላቸውም ፡፡ እነዚህን ሁለት ካህነት በማጣት እስራኤል አዘነ ፤ አሮን በፆም አዘነ ነገር ግን የሚሰራው ስራ ነበረው ፤ እንደ ካህን የአሮን ሚና መለየት ነበር በዘሌ(10፡ 8-9) እንደተገለፀው ፡፡ ካህናት ወደ መገናኛው ድንካን በሚገቡ ጊዜ ወይን/ቢራ መጠጣት አይችሉም ፤ ቅዱሱን ከተለመደው፣ ንፁሁን ካልነፃው መሀከል ይለዩ ነበር ፤ የእግዚአብሄርን ደንብ ለህዝቡ ያስምሩ ነበር ፡፡ በዘሌ 11 እግዚአብሄር ለሙሴና ለአሮን ከእስራኤላዊያን ጋር እንዲካፈሉ የአመጋገብ ደንብ ሰጣቸው ፡፡

ትምህርት

ዘሌዋውያን(11፡ 1-8); እግዚአብሄር የምድር እንስሳቶችን የአመጋገብ መመሪያ ገለጠ ፤” የተሰነጠቀ ሰኮና ያለውንና የሚያሞሰካውን እንስሳ” ይበላል (ቁጥር 3) ፤ ነገር ግን ከእንስሳቶች ውስጥ የተሰነጠቀ ሰኮና ወይም የሚያሞሰካ ግን የማይበሉ ግመል፣ ሽኮኮ፣ ጥንቸል ወይም እሪያ ፡፡ ዘዳ(14፡ 4-5) መብላት የሚችሉትን እንስሳቶች ዝርዝር ሰጥቶአቸዋል፡ “ በሬ፣ በግ፣ ፍየል፣ ዋላ፣ ሚዳቆ፣ የበርሀ ፍየል፣ አጋዘን፣ አጭ፣ በራይሌ፣ ድኩላ ፡፡”

ንፁህ ያልሆነ እንስሳት በድን መብላት ወይም መንካት አይችሉም ፤ ንፁህ ማለት ለእግዚአብሄር የሚመች (እግዚአብሄር የሚቀበለው); ንፁህ ያልሆነ ማለት ለእግዚአብሄር የማይመች ማለት ፡፡ “ንፁኅ ያልሆነ” የሚለው ቃል በዘሌዋውያን ውስጥ 32 ጊዜ የተጠቀሰ ነው ፤ ካህናቱ ንፁህ ወይም ንፁህ ያልሆነ ምን ነበር የሚለውን የመለየት ስራ ተሰጥቶአቸዋል ስለዚህ ወደ መገናኛው ድንካና ሳይጠጡ መማጣት ነበረባቸው ፡፡ ንፁህ አይምሮ፣ ግልፅ ሀሳብ ሊኖራቸው ይገባል ይህም የእግዚአብሄር መንፈስ እንዲሰራ ይፈቅዳል ፡፡

እስራኤል የሚበሉት ይህ በጣም የሚጠቅመው ለምን ነበር ?ዮሐንስ ማክአርቱር የተናገረው “ ለዚህ ያለምክንያት ወይም በግንዛቤ እጥረት የእግዚአብሄርን ፍፁም ስርአት ያከብሩ ነበር ፡፡” እግዚአብሄር ለምን የሆነ ነገር እንዲበሉ ወይም እንዳይበሉ እነርሱ ለመረዳት ወይም ለመለየት አልነበረም ፤ ልክ እንደዚህ ዝም ብለን ማክበር ነው ፡፡ በእምነት የመጋአዝ ውበት ይህን ሁሉ ለመጥቀስ መሞከር ሳይሆን ታዛዥ መሆን እንጂ ፡፡ የእስራኤል ምግብ የተለየ ነበር በዚህ ምክንያት በሌሎች ህዝቦች እና እንዴት የሀሰት ጣዖቶቻቸውን እንደሚያገለግሉ እስራኤል ንቅንቅ የሚሉ አይሆኑም ፤ ብዙ ሌሎች ኃይማኖቶች በኃይማኖታዊ አገልግሎታቸው ውስጥ እንስሳት ተዋህደዋል ፡፡ እግዚአብሄር ከድሮ መንገዳቸው እስራኤልን እየለያቸው ነበር ፤ የተመረጡ ህዝቡን ከትክክል መንገድ ሚያወጣ እና ወደ ሌሎች ህዝቦች ሀሰተኛ ጣዖቶች ሊመሩዓቸው የሚችሉትን አስወገደ ፡፡

የኔልሰን ሀተታ አይሁድ እና ሙስሊም ለምን አሳማ/የአሳማ ስጋ እንዳይበሉ እንዳልተፈቀደ ይገልፃል ፤ መጀመሪያ ብዙ ጊዜ የአሳማ ስጋ አይበስልም ነበር; በሚገባ ያልበሰለ የአሳማ ስጋ ወደ ሰው በሽታ ሊያስተላልፍ ይችላል ፤ ሁለተኛው ብዙ ጊዜ አሳማዎች ለሌላ አምልክ ወይም አምላክ ለሌላቸው ጣዖቶች የተሰዋ ነበር ፡፡ መጎምጀት ኃጢዓት አልነበረም ነገር ግን ሰይጣን እስራኤላዊያንን ለማታለል ይሞክራል ፤ ዋይሰርቤ ሲናገር ይህን ንፁህ ያልሆነን እንሰሳት መካፈልን የማይታዘዙ ከሆነ በሀሰት ጣዖት መካፈል ያበቃል(ያልቃል) ፡፡ አሳማ መብላት ወደ ሞት ሊመራ ይችላል እናም የትም ቦታ በዚያ አጠገብ ያሉትን ህዝቡን እግዚአብሄር አልፈለገም ፡፡ እግዚአብሄር እንዳትቀምሱ ብሎ በተናገረ ጊዜ አዞአቸዉ የነበረውን በመታዘዝ እንዲያምኑ እየጠየቃቸው ነበር ፤ እግዚአብሄር ህዝቡን የተለዩ እና ልዩ ለማድረግ በግልፅ እየሞከረ ነበር ፡፡

ዘሌዋውያን(11፡ 9-12); እግዚአብሄር በመቀጠል ንፁህና ንፁህ ያልሆነ የውሃ እንስሳቶችን ለየ ፤ እስራኤላውያን በውሃ ውስጥ ላባዎች እና ቅርፊቶች ያላቸውን ማንኛውንም ነገር መብላት ይችላሉ እነዚያ እንደ ንፁህ ይወሰዳሉ ፤ ነገር ግን ምንኛውም ነገር በባህር ወይም በወንዝ ውስጥ ላባዎችና ቅርፊቶች የለሉዓቸው ንፁህ እንዳልሆነ ይወሰዳሉ ከዚያም መበላት አይችሉም( ለምሳሌ የአሳ ዘር፣ ትንሽ አሳ፣ ስምንት እግር የባህር እንሰሳ እና አባብ የሚመስል አሳ)፡፡

ዘሌዋውያን(11፡ 13-19); እግዚአብሄር በመቀጠል ንፁህ ያልሆኑ አእዋፍን ለየ፡ “ የምትጸየፋቸው እነዚህ ናቸው ፤ አይበሉም የተጸየፉ ናቸው ፡፡” አስከፊ ምናልባት ቀፋፊ ወይም ፀያፍ፣ የሆነ ነገር ንፁህ ካልሆነ በጣም ሲያስከፋ የሚለውን ያመለክታል ፤ ንስር፣ ገዲ፣ ዓሳ አዉጪ፣ ጭላት፣ ጭልፊት፣ ቁራ፣ ሰጎን፣ ጠላቐ፣ ዝዪ፣ በቐል፣ ጉጉት፣ እርኩም፣ ጋጋኖ፣ የውኃ ዶሮ፣ ይብራ ጥምብ አንሳ አሞራ፣ ሽመላ፣ ሳቢሳ፣ ጅንጁላቴ ወፍ እና የሌሊት ወፍ ንፁኅ አልነበሩም ስለዚህ ተከለከሉ ፡፡

ዘሌዋውያን(11፡ 20-23); እግዚአብሄር በተጨማሪ ንፁህ እና ንፁህ ያልሆኑ የሚበሩ ነፍሳትን ለየ ፤ የሚበርሩ ነፍሳት በአራት እግሮቻቸው የሚሄዱ ንፁህ ያልሆኑና አፀያፊ ነበሩ ፤ ነገር ግን የሚበርሩ ነፍሳት ከእግራቸው በላይ በምድር ላይ እንዲዘሉ የሚፈቅድ የተያያዘ ጭኖች ያላቸው ንፁህና መብላት ይችላሉ ፡፡ እስራኤላዊያን አንበጣ፣ ትልቅ የአንበጣ አይነት፣ ዋዝንቢት እና ፌንጣ እንዲበሉ ተፈቀደላቸው ፡፡

ዘሌዋውያን(11፡ 24-40); ማንም የሞተ እንስሳ ጥንብ የነካ እስከሚመሽ ድረስ ንፁህ አይሆንም ነበር ልብሶቹን መታጠብ ያስፈልግ ነበር (ቁጥር 24-25) ፤ በቁጥር 26 ማንም ሰኮናቸው ያልተከፈለ እና የማያሞሰኩ እንስሳትን የነካ እስከማታ ድረስ ርኩስ ነበር ፡፡ ሰምሶን በመፅሀፍ ውስጥ ለዚህ ምሳሌ ነበር ፤ ናዝራዊ ነበር ማለት ለእግዚአብሄር የተለየ ነበር - አነዚህን ዝርዝር ያውቃል ፤ መሳ(14፡ 5-9) የሚለው ሳምሶን አንበሳውን ገደለው፡ እዚህ ጋር ስህተት የለም ፤ ነገር ግን ከሆነ ጊዜ ቦኃላ ተመልሶ ከአንበሳው በድን ጥቂት ማር ወሰደ ፤ በላውም ለቤተሰቡም ሰጣቸው ፤ ርኩስ እንደነበር ያውቃል ፡፡ ይህ ወደ እሱ ማስተላለፍ(ወደ ውርሱ) ሊመራ ችላል ?

በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱ እንስሳቶች ርኩስ ነበሩ ስለዚህ ሙጭልጭላ፣ አይጥ፣ እንሽላሊት፣ ኤሊ፣ አዞ፣ ገበሎ እና አርጃኖ ርኩስ እና የተከለከሉ ነበሩ ፡፡ ከእነዚህ ርኩስ እንስሳቶች በአንዱ እንስራቸው ከተነካ እንዲሰብሩት ታዘዋል (ቁጥር 33) ፤ ጥንባቸዉ(በድናቸው) በእቶናቸው ወይም በምድጃቸው ላይ ከወደቀ ይሰባበር ነበር(ቁጥር 35)፡፡

ዘሌዋውያን(11፡ 41-46); እግዚአብሄር የሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶች (ቁጥር 41) በተጨማሪም በሆዳቸው የሚሄዱ ወይም በአራት እግሮቻቸው ወይም በብዙ እግሮች የሚጋአዙ (ቁጥር 42) አፀያፊና መበላት እንደማይችሉ ተናገረ ፡፡

የእነዚህ ገደቦች ሁሉ የመጨረሻው አላማው እስራኤልን ቅዱስ ህዝብ እንዲሆኑ እና እንደ ንፁኅ ህዝብ እንዲሰሩ እንጂ ንፁህ እንዳልሆነ ህዝብ እንዳይሰሩ; እንደማንኛውም ህዝብ እንዲሆኑ ሳይሆን እንደ ቅዱስ ህዝብ እንዲሆኑ ነበር ፡፡ ይህ የአመጋገብ ደንብ እግዚአብሄር ልዩነት ለማድረግ እስራኤል የተመረጠ ህዝብ ስለነበር ፤ ቅዱስ መሆን ነበረባቸው ምክንያቱም እግዚአብሄር ቅዱስ ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ እግዚአብሄር ወደ ሚለው ስንመጣ ልክ እንደዚህ ነገሮችን እንፈል ነገር ግን እግዚአብሄር የሚለው“ ይህን አይመስልም ፡፡”

መዝጊያ

እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን በዘሌ 11 የተዘረዘሩትን የምግብን መመሪያዎችን በመከተል ቅዱስ እንዲሆኑ ጠራቸው እስራኤል የተለየ ነበር ፤ ይህ ዝርዝር ሸክም አልነበረም ይህ ማለት እድለኛ መሆን ነበር ፡፡ በ 1ጴጥ (1፡ 13-16) ቅዱስ እንድንሆን ተጠርተናል ምክንያቱም እግዚአብሄር ቅዱስ ነው ፡፡

ለዚህ ትምህርት በእስራኤል ያለውን ባህል፣ የአይሁድ ሰዎችን እና የሚመጣውን መሲህ መረዳት ጠቃሚ ነው ፤ የእኛ አንድ ቃል ለዘሌዋውያን አስተሰሪይ ነው እንዴት ደሙ ለእኛ በመተካት አገለገለ ፡፡ ማመካኘት የእኛ የሆነውን ጥፋተኝነት በመውሰድ ሌላ ላይ ማስቀመጥ ነው ፤ ይህ ሁሉ ወደ መሲሁ ያመለክታሉ(አመልክተዋል) ፡፡

  1. John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 2005), p. 148

  2. MacArthur, p. 148.

  3. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 168.

  4. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 266.

ጥያቄዎች

  1. “ ርኩስ” እና “ንፁህን” ተረጉሙ ፤ ዘሌ (11-12) ለእስራኤል ንፁኅ እና ቅዱስ እንዲሆኑ የእግዚአብሄርን ፍላጎት እንድትረዱት እንዴት ይረዳችኃል ? (ዘሌ 11፡ 44-45)
  2. በዘሌ 11 “ርኩስ” የሚሆን እንስሳት በልታችሁ ታውቃላችሁ ? ኢየሱስ ህጉን ሊፈፅም መጣ እንጂ ሊያጠፋው አይደለም (ማቴ 5፡ 17-20) ፤ የምግብ ህጎች ርኩስ/ንፁህ እንስሳት በማለት ዛሬ ተፈፃሚነው ብላችሁ ታስባላችሁ ? (ሮሜ 14፡ 17)
  3. እግዚአብሄር እስራኤላዊያን እንዲበሉት ስለ ፈለጋቸው እንስሳት የተለየ ያደረገው ለምን ነበር ? እንደ እርኩስ የገለፃቸውን እንስሳቶች እስራኤላዊያን እንዳይበሉ እግዚአብሄር ለምን እንደፈለገ ምን ታስባላችሁ ?
  4. በመውለድ ጊዜ አንድ ሴት ለምንድን ነበር እንደ ርኩስ የምትቆጠረው ? (ዘሌ 12፡ 1-2; 6-7)
  5. ሉቃ (2፡ 21-24) አንብቡ ፤ በዘሌ 12 ያለውን ህግ በመጠበቅ ዮሴፍና ማሪያም ከወለዱ በኃላ ምንድን አደረጉ ?
  6. በዘሌ (11-12) ላይ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ (አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Leviticus 11:44-45

“For I am Yahweh your God, so you must consecrate yourselves and be holy because I am holy. You must not defile yourselves by any swarming creature that crawls on the ground. For I am Yahweh, who brought you up from the land of Egypt to be your God, so you must be holy because I am holy.”

ንፁህ እና ርኩስ

እንስሳዎች

ኦሪት ዘሌዋዉያን 11-12 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

እግዚአብሔር ቅዱስ ስለሆነ እስራኤላዉያንም ቅዱስ እንዲሆኑ ይፈልጋል። ይህ ለእስራኤላዉያን የተለየ ምግብ ማለት ነዉ። እግዚአብሔር የእርሱ ህዝብ የተለየ እንዲሆን አድርጓል! እናም ይህ የተለየ ምግብ መብላት ዉጫዊ የሆነ የመታዘዝ እና የቅድስና ድርጊት ነዉ።

እንደ ክርስቶስ ኢየሱስ ተከታይ፥ የተመረጥክ እና ቅዱስ ነህ! አንተ ከዚህ ዓለም እና ኃጥያት ብቻ የምትለይ ሳትሆን ለእግዚአብሔር ለራሱ ዓላማም የተለየህ ነህ! በምትበላዉ እና በማትበላዉ ነገር ላይ ልብህን ከምትጥል፥ ርህራሄን፣ ትህትናን፣ በጎነትን፣ ትዕግስትን እና ራሳን መግዛትን ለመልበስ በየወቀኑ ወስን! ዛሬ፥ ምንም ነገር ብታደርግ፥ የምታደርገዉን ሁሉ ለእግዚአብሔር ክብር አድርግ!

"እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና፤ ሰውነታችሁን ቀድሱ፥ ቅዱሳንም ሁኑ፥ እኔ ቅዱስ ነኝና፤ በምድርም ላይ በሚሳብ ተንቀሳቃሽ ሁሉ ሰውነታችሁን አታርክሱ። እኔ አምላካችሁ እሆን ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋችሁ እግዚአብሔር ነኝ፤ እንግዲህ እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተ ቅዱሳን ሁኑ።"

ኦሪት ዘሌዋዉያን 11:44-45

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ኦሪት ዘዳግም 7:6፦ "ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አንተ ቅዱስ ሕዝብ ነህና፤ በምድር ፊት ከሚኖሩ አሕዛብ ሁሉ ይልቅ ለእርሱ ለራሱ ሕዝብ ትሆንለት ዘንድ አምላክህ እግዚአብሔር መረጠህ።"

ወደ ቆላስይስ 3:12፦ "እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ፤"

1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 10:31፦ "እንግዲህ የምትበሉ ወይም የምትጠጡ ብትሆኑ ወይም ማናቸውን ነገር ብታደርጉ ሁሉን ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 58