Unauthorized Offering
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 10 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዘሌዋውያን ወደ መሲሁ ያመለክታል ፤ የትኛውም ቦታ ብትመለከቱ የእኛን አንድ ቃል አስተሰሪይን ታያላችሁ ፡፡ ዜዋውያን 9 የአሮንን የመጀመሪያ ቀን በስራው ላይ ሁሉንም መስዋዕትን ሲሰራ ይገልፃል፡ ለራሱ የኃጢዓት መስዋዕትና የሚቃጠል መስዋዕት ከዚያም በመቀጠል እስራኤላዉያንን የሸፈነ የህብረት መስዋዕትና የእህል መስዋዕት አድርጎአል ፤ ከዚያ ቦኃላ አሮን ህዝቡን ባረከ ከዚያም እሱና ሙሴ እንደገና ህዝቡን ባረኩ ፤ ከዚያም እሳትና የእግዚአብሄር ክብር ወረደ ፤ ሁለቱም የመሲሁን መምጣት ያመለክታሉ ፡፡
በዘጸ(28፡ 4) ለካህናቱ የተለየ ልብስ ተዘጋጆቶአል ፤ በዘሌ 8 ውስጥ አሮን እና ልጆቹ የእግዚአብሄርን ስራ እንዲሰሩ ተለዩም ታዘዙም ፡፡ በዘሌዋውያን 10 ግን በዚህ የተለየ ቅባት እሳት ሲወርድ እያዩ የአሮን ልጆች የራሳቸውን ነገር እንዲያደርጉ አሁንም ተመርጠዋል ፡፡
ትምህርት
ዘሌዋውያን(10፡ 1); ናዳብና አብድዩ ለእግዚአብሄር እንዲያደርጉ ያላዘዛቸውን ያልተፈቀደ/እንግዳ እሳት አቀረቡ ፤ ጠቃላላ መቅደሱ አንድ ታላቅ ትዕዛዝ ነበረው ፤ አነዚህ ካህናት ሁሉንም ትእዛዞችን መከተል ሰልችተው ነበር ?
ዘሌዋውያን(10፡ 2); “ እሳትም ከእግዚአብሄር ፊት ወጥቶ በላቸው በእግዚአብሄርም ፊት ሞቱ ፡፡“ ወዲያውኑ እንደ ምሳሌ ነበር፡ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ የማትከተሉ ከሆነ ትሞታላችሁ ፡፡ ዋይሰርቤ በዚህ ሁኔታ እነዚሕ ሁለት ሰዎች እንዴት ስህተት እንደነበሩ ይገልፃል ፤ የመጀመሪያ ይህን መስዋእት ለማድረግ የተሳሳቱ ሰዎች ነበሩ ፤ ሊቀ ካህኑ አባታቸው አሮን ይህን መስዋዕት ማድረግ የሚችለው እሱ ብቻ ነበር (ዘጸ 30፡ 7-10) ፤ ሁለተኛው የተሳሳተ መሳሪያ ተጠቀሙ በስም የራሳቸውን የእሳት ሳህኖች (ዘጸ 40፡ 9) ፤ ሰዎስተኛው የተሳሳተ ጊዜ ነበር ፤ ይህ የሚቀርበው በስርየት ቀን ነበር (ዘሌ 16፡ 11) ፤ አራተኛው የመጡት በተሳሳተ ስልጣን ነበር ፤ የመጡት በእግዚአብሄር ስልጣን አልነበረም በራሳቸው እንጂ ፤ አምስተኛው የተሳሳተ አሳት አመጡ ፤ አሳቱ ከራሱ ከመሰዊያው ላይ መምጣት አለበት እሳት ከሰማይ በወረደ ጊዜ ታጥናአል (ዘሌ 16፡ 12) ፤ ስድስተኛው የተሳሳተ ፍላጎት ነበራቸው; ለራሳቸው ክብር ለማግኘት ይሞክሩ ነበር (ዘሌ 10፡ 3) ፤ ሳባተኛው ወደ ገበታው በተሳሳተ ጉልበት መጡ ፤ ሙሉ በሙሉ የጠጡ እንደነበር ጥሩ እድል አለ(ዘሌ 10፡ 9) ፡፡
ዘሌዋውያን(10፡ 3); ሙሴ በተናገረ ጊዜ “ እግዚአብሄር ወደ እኔ በሚቀርቡ እቀደሳለሁ በሕዝቡም በሕዝቡም ሁሉ ፊት እከብራለሁ “ አሮን ዝም አለ ፡፡ ምናልባት የዝምታው ምክንያት ድንጋጤው ነበር ? አሮን እና ሁሉም ካህናቱ የመጠበቅ(የመጠገን) ኃላፊነት ነበረባቸው ፤ ያዕ(3፡ 1) የሚያስጠነቅቀው “ ወንድሞች ሆይ ከእናንተ ብዙዎች አስተማሪዎች አይሁኑ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃላችሁና ” ፤ ዛሬ ፅጋ አለ ነገር ግን አስተማሪዎች ብዙ ተጠያቂነት አለባቸው ፡፡ የ1ቆሮ(10፡ 12) ማስጠንቀቂያን በስርዓት ልንወስደው ይገባናል “ ስለዚህ እንደቆመ የሚመስለው እንዳይወድቅ ይጠንቀቅ ፡፡“ በኩራት በምንጋዓዝ ጊዜ ኃጢዓት ማዘግየት ይችላል ከዚያም ወደ ውድቀት ይመራናል ፤ ዕብ (12፡ 28-29) የሚመክረው “ እግዚአብሄርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ…..”
ዘሌዋውያን(10፡ 4-5); ሙሴ ሚሳኤልንና ኤልጻፋንን ከመቅደሱ አርቀው ከካምፑ ዉጪ እንዲያወጡዓቸው ወንድሞቻቸውን እንዲ ሸከሙዓቸው ጠራቸው ! የሞቱት ሰዎች በቅርብ ቤተሰብ ሊሸከሙ አልቻሉም ምክንያቱም ንፁህ አልሆኑም(ዘሌ 21፡ 1-2) ፡፡
እንደ ቀሪ አሮንም ሙሴም ፍፁም አልነበሩም፡ ሁለቱም ስተው ነበር ፤ አሮን የወርቅ ጥጃ ሰራ( ዘጸ 32) ግን አሁን ሊቀ ካህን ነበር ፤ ዘኁ 20 ሙሴ ቆሸሸ እናም ወደ ተስፋይቱ ምድር እንዲገባ አልተፈቀደለትም ፡፡ 1ሳሙ 6፡ 19 ላይ ከ5,000 ሰዎች ውስጥ እግዚአብሄር 70 ሰዎችን በሞት መታቸው ምክንያቱም ወደ ኪዳኑ ታቦት ተመልክተዋልና ፤ እግዚአብሄር መቼ ሰዎችን በሞት እንደሚመታና መቼ እንደማይመታ እንዴት እንደሚመርጥ መረዳት ከባድ ነው፡፡ ለምን እነዚያን 70ዎቹን ? ለምን ናዳብንና አብዩዱን በሞት መታቸው ? ሙሴ ለምን ወደ ተስፋይቱ ምድር መሄድ አልቻለም ግን አሮን አሁንም ሊቀ ካህን መሆን ችላል ?
ዘሌዋውያን(10፡ 6-7); ሙሴ አሮንንና ልጆቹን አልዓዛርንና ኢታምርን ለልጆቹና ለወንድሞቻቸው እንዳያዝኑ ነገራቸው ፤ ይሁን እንጂ አሳዛኝ በሆነው ሞታቸው ማህበረሰቡ ያዝንላቸዋል ፤ በዚያ ፋንታ አሮን እና የተረፉት ልጆቹ የእስራኤልን ቤት ያገለግላሉ ፡፡ ከመገናኛውን ድንካን እንዲወጡ አልተፈቀደላቸውም ምክንያቱም የእግዚአብሄር የቅባቱ ዘይት በእነሱ ላይ ነበር ፤ የሚሰሩት ስራ ነበራቸው ፡፡
የእግዚአብሄር ጥሪ በህይወታችሁ ከቤተሰባችሁ የሚበልጥ ነው ፡፡ በሉቃ(9፡ 59-60) መከተል ለሚችሉት ስለቤተሰባቸው እና ስለ እግዚአብሄር መንግስት ጠንካራ መልዕክት ሲሰጣቸው እናያለን ፤ ኢየሱስ ሐዋሪያቱን እሱን ለመከተል ሁሉን ነገር ወደ ኃላ እንዲተው ነገራቸው ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በአሜሪካ እግዚአብሄር እንድነሰራ የጠራንን በማጣመም ለማመልከት ቤተሰባችንን እናነሳለን(ከፍ እናደርጋለን) ፡፡ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ በሃሳብ ውስጥ ትልቅ ስዕል እንዳለው ማስታዎስ ጠቃሚ ነው ፡፡
ዘሌዋውያን(10፡ 8-11); እግዚአብሄር አሮንን እሱና ልጆቹ ወደ መገናኛው ድንካን በሚገቡ ጊዜ ወይን/ቢራ መጠጣት እንደማይችሉ ወይም ደግሞ እንደሚሞቱ ነገረው ፤ ለአሮን ቤተሰብ ይህ ቐሚ ሁኔታ ነበር ፡፡ አሮን(እና ሁሉም ካህናት) በቅዱሱና በማናኛውም፣ በንፁሁና ባልነፃው መሀከል መለየት ነበረባቸው ፤ አሮን ንፁኅ አይምሮ ሊኖረው ይገባ ነበር ምክንያቱም የእግዚአብሄርን ሁኔታ(አቐም) ለህዝቡ የሚያስተምር ስለነበር ፤ ካህናቱ የመለየት ስጦታ ሊኖራቸው ይገባል “ መልካሙንና ክፉውን ለመለየት”(ዕብ 5፡ 13-14) ችሎታ ፡፡ ካህናት በአለም ውስጥ ካለው ከማንኛውም ይለዩ ነበር ፤ በቅዱስነት ሰርተዋል ፡፡
ዘሌዋውያን(10፡ 12-15); አሮንና የቀሩት ልጆቹ አልአዛርና ኢታምርን ለእግዚአብሄር ከመስዋዕቱ ጋር ወደፊት ቀጠሉ ፤ የእህል መስዋዕትና የሚወዘወዝ መስዋዕት አደረጉ ፡፡
ዘሌዋውያን(10፡ 16-18); ሙሴ አሮንና ልጆቹ የኃጢዓት መስዋዕቱን እንዳልበሉት ባወቀ ጊዜ ተናደደባቸው ግን በዚያ ፋንታ እንዲቃጠል የተፈቀደ ነበር(አቃጥለውት ነበር) ፡፡ ማወቅ የፈለገው ለምን በመቅደስ ውስጥ የኃጢዓት መስዋዕቱን የመብላት ትዕዛዙን አልተከተሉም የሚለውን ነበር ፡፡
ዘሌዋውያን(10፡ 19-20); አሮን ለሙሴ ክስ መለሰ (ቁጥር 19) ስለ አልተከተሉት ትዕዛዝ “ ይህም ሁሉ ደረሰብኝ ፤ ዛሬስ የኃጢዓት መስዋዕት በበላሁ ኖሮ በእግዚአብሄር ፊት መልካም ኖሮአልን ?“በማለት ጠየቀው ፡፡ ኮንስታብል የተማገረው አሮን በበጉ ሀሳብ መስዋዕቱን መብላት አልቻለም እናም እግዚአብሄርን ለማሞኘት አልሞከረም ነበር በዚያ ፋንታ መፆምን መረጠ እንጂ ፤ አሮን በእግዚአብሄር ምልከታ በልቡ መልካም ነበር ፡፡
መዝጊያ
እግዚአብሄር የሚፈልገው የእኛን መታዘዝ እንጂ መስዋዕት አይደለም ፤ በህይወታችሁ እንደ እግዚአብሄር ጥሪ ስትጋአዙ የጥሪውን አሳሳቢነት ይገነዘባል ፡፡ እንደ ጥሪ መጋአዛችሁ ትንፋሽ ነው ፤ ልባችሁና ፍላጎታችሁ እግዚአብሄርን ማገልገል ከሆነ ፀጋውን ይጨምርባችኃል ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 264.
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Leviticus, p. 84; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/leviticus.pdf.
ጥያቄዎች
-
በዘሌ 10 በአሮን ሁለት ልጆች የተደረገው ያልተፈቀደ መስዋዕት ምንድን ነበር ? ያልተገባ መስዋዕት እንዳቀረቡ ታስባላችሁ ? ክሱን ተከትሎ በአሮን ቤተሰብ(በካህናቱ) ውስጥ ፍርሀት ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ?
-
እግዚአብሄር ናዳብና አብዩዱን መግደል ለምን እንደመረጠ ምን ታስባላችሁ (ዘሌ 10፡ 2) ? ለምን እግዚአብሄር በዚህ ጊዜ በመግደል መምታት መረጠ በሌላ ጊዜ ፀጋውን በመዘርገት ሁለተኛ እድል ይሰጣል ?
-
እንደ ካህናት አሮንና ልጆቹ ትልቅ ደረጃ ላይ ተቀመጡ ፤ ያዕ (3፡ 1) እና 1ቆሮ 10፡ 12 አንብቡ ፤ እዚህ ትልቅ ደረጃ ላይ ተቀምጣችኃል ? (ማቴ 18፡ 6; ዕብ 5፡ 11-14)
-
በዘሌ (10፡ 6-7) አሮንና ልጆቹ አልአዛርና ኢታምር እንዲያዝኑ ለምን ነበር ያልተፈቀደላቸው ?
-
እንዲ በሉት የተነገሩትን አሮንና ልጆቹ የኃጢዓት መስዋዕቱን እንዳይበሉ ያደረጋቸው(ያነሳሳቸው) ምንድን ነበር ? ይህ ትክክለኛ ውሳኔ ነበር ?
-
በዘሌ 10 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Leviticus 10:1-2
“Aaron’s sons Nadab and Abihu each took his own firepan, put fire in it, placed incense on it, and presented unauthorized fire before the LORD, which He had not commanded them to do. Then fire came from the LORD and burned them to death before the LORD.”
እግዚአብሔር መታዘዝን እንጂ መሥዋዕትን አይሻም!
ኦሪት ዘሌዋዉያን 10 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
የሚደንቅ የእግዚዓብሔር ክብር በሚገለጥበት ጊዜ እንኳን፥ ካህናት የነበሩ ሁለት የአሮን ልጆች፥ የእግዚዓብሔርን ትዕዛዝ በመተላለፍ፥ ያልተገባ እሳትን ወደፊቱ አቀረቡ። እግዚዓብሔርም በቅፅበት ፍርዱን በመስጠት ወዲያዉኑ እስኪሞቱ ድረስ አቃጠላቸዉ!
እንደ የክርስቶስ የንጉስ ካህናት፥ የእግዚዓብሔርን ሥራ እየሰራህ ባለህበት ጊዜ መሃከል እንኳ "ያልተገባ እሳት" በእግዚዓብሔር ፊት ለማቅረብ ትፈተን ይሆናል። ራስ ወዳድ በመሆን ሱሰኝነት፣ ትዕቢት፣ ወይም ሌሎች ጣኦታትን ለማምለክ ልትፈተን ትችላለህ።
አስታዉስ፦ እንደ የክርስቶስ የተመረጡ ካህናት፥ ከጨለማ እና ከኃጥያት በመዉጣት የተጠራህ፥ ከክርስቶስ የሆነ ኃይል እና ፀጋ የሞላበት ወደ ሚደነቅ ብርሃን የተጠራህ ነህ! የራስህን መንገድ የመምረጥ ፈተናን ተቋቋመዉ! ዛሬ፥ ጠንክሮ ለመቆም ከእግዚዓብሄር ኃይልን የምታገኝበት ቀን ይሁን!
"አሮንም ልጆች ናዳብና አብዩድ በየራሳቸው ጥናውን ወስደው እሳት አደረጉበት፥ በላዩም ዕጣን አኖሩበት፥ በእግዚአብሔርም ፊት እርሱ ያላዘዛቸውን ሌላ እሳት አቀረቡ። እሳትም ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ በላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሞቱ።"
ኦሪት ዘሌዋዉያን 10:1-2
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ወደ ሮሜ ሰዎች 6:22-23፦ "አሁን ግን ከኃጢአት አርነት ወጥታችሁ ለእግዚአብሔርም ተገዝታችሁ፥ ልትቀደሱ ፍሬ አላችሁ፤ መጨረሻውም የዘላለም ሕይወት ነው። የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።"
የያዕቆብ መልዕክት 1:13-15፦ "ማንም ሲፈተን፦ በእግዚአብሔር እፈተናለሁ አይበል፤ እግዚአብሔር በክፉ አይፈተንምና፤ እርሱ ራሱስ ማንንም አይፈትንም። ነገር ግን እያንዳንዱ በራሱ ምኞት ሲሳብና ሲታለል ይፈተናል። ከዚህ በኋላ ምኞት ፀንሳ ኃጢአትን ትወልዳለች፤ ኃጢአትም ካደገች በኋላ ሞትን ትወልዳለች።"
1ኛ ጴጥሮስ መልዕክት 2:9-10፦ "እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤ እናንተ ቀድሞ ወገን አልነበራችሁም አሁን ግን የእግዚአብሔር ወገን ናችሁ፤ እናንተ ምሕረት ያገኛችሁ አልነበራችሁም አሁን ግን ምሕረትን አግኝታችኋል።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 57
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።