The Priestly Ministry Inaugurated
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 8-9 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ዘሌዋውያን በተጨባጭ በቐሚነት እስራኤላዊያን እንዴት ከእግዚአብሄር ጋር እንዲሰሪ ያሳየ የተግባር መመሪያ ነው፡፡ መቅደሱን ለመስራት የተራዱትን ባስልእልንና ኤልያብን ታስታውሳላችሁ ? እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ከእርሱ ጋር ለመገናኘት መቅደሱን እንዴት እንደሚጠቀሙበት ነግሮአቸው ነበር ፡፡ ዘሌዋውያን 8 እና 9 የአሮንና የልጆቹን መሰጠት ይሸፍናል ፡፡
ትምህርት
ዘሌዋውያን(8፡ 1-5); ለመሰጠት ሁሉም ጉባኤ ተሰበሰበ ፤ ካህናቱ በእምነት ቀንም ማታም ሊያገለግሉ እግዚአብሄር ለይቶአቸው ነበር ፤ ሚናቸው እግዚአብሄርን ብቻ ማገልገል ሳይሆን እስራኤላዊያንን ማገልገል ነበር ፡፡
ዘሌዋውያን(8፡ 6-9); አሮንና ልጆቹ በዉሃ ታጠቡ ፤ አሮን በቅዱሱ ልብስ ውስጥ፡ መታጠቂያ፣ ቀሚስ(ካባ)፣ ኢፉድ፣ የደረት ኪስ፣ ኡሪምና ቱሚም እና ከወርቅ ሜዳሊያው ጋር ጥምጣም ለበሰ ፤ እነዚህ ዝርዝሮች የአሮንን ዩንፎርም ጥንቅር ናቸው ፡፡ አስታውሱ የእኛ ቃል ለዘፍጥረት ዘር ነው፣ ለዘጸዓት ነፃ አዉጪ ነው እና ለዘሌዋውያን አስተሰሪይ ነው ፡፡ መሲሁ ብቸኛው የሚመጣውና ለኃጢዓታችን ናስሀ የሚያስገኘን ነው ፤ ግን ለአሁን ካህናቱ የማሰርየቱን ሂደት ጥንቃቄ የሚወስዱ ነበሩ ፡፡
ዘሌዋውያን(8፡ 10-36); አሮንና መቀደሱ ተቀቡ ፤ የአሮን ልጆች ለበሱም የተለያዩ መስዋዕቶች አቀረቡ ፡፡ ዝግጁ ነበሩ ! ቅባቱ ተካሄደ ፤ካህናቱ ተሰጡ ፤ የመለያው በግ ይበላ ነበር ፤ አንድ ጊዜ ካህናቱ ከተለዩ ለሰባት ቀን የትም እንዳይሄዱ ነገሩአቸው ፡፡
ዘሌዋውያን(9፡ 1-3); በስምንንተኛው ቀን ከሰባቱ የመለየት ቀኖች በኃላ ሙሴ በአራት ዋና መስዋዕቶች ውስጥ ሄደ(ተጋአዘ) ፤ የመጀመሪያዎቹ ሁለቱ መስዋዕቶች ወይፈን(የኃጢዓት መስዋዕት)ና በግ(የሚቃጠል መስዋዕት) ነበሩ፡፡ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነበር አሮን ለሁሉም እስራኤላዊያን ድምፅ የሆነበት ፡፡ አንድ ወንድ ፍየል(የኃጢዓት መስዋዕት)፣ ጥጃ እና ጠቦት(ለሚቃጠል መስዋዕት) በተጨማሪ ይሰዋ ነበር ፡፡
ዘሌዋውያን(9፡ 4); ሁለተኛው አይነት መስዋዕት ሁለት የተለያዩ መስዋዕትን ያካትታል፡ በሬና በግ(የህብረት መስዋዕት) እና በዘይት የተቀላቀለ እህል(የእህል መስዋዕት) ፡፡ አስታውሱ መቅደሱ ከስራ በፊት በፍፁም አልተከፈተም ! ሁሉም ቦታ ዝግጁ ነበር ፡፡ ለመጀመር የመጀመሪያዎችን አራት መስዋዕቶችን ያደርጋል ፤ ለኃጢዓት ስርየትና ከእግዚአብሄር ጋር ደህንነትን በማክበር መሀከል መመጣጠን ነበር ፡፡
ይህ በዘጸ(32፡ 1-4) ላይ ወርቅ ጥጃ በመስራት የቆሸሸው አሮን ነበር ፤ በሁሉም መንገድ ዘፍጥረት ውስጥ ስንመለስ የተመረጡት ስህተት እንደሰሩ አይተናል ፤ እግዚአብሄር የማይወደዱ ሰዎችን ይጠቀማል ፡፡ አሁን ሊቀ ካህኑ አራቱን መስዋዕት በማቅረብ ወደ እግዚአብሄር መገኘት ይቀርብ ነበር ፤ ሁለቱ መስዋዕት ለኃጢዓት ስርየት እና ሁለቱ መስዋዕት ከእግዚአብሄር ጋር ህብረት ለማድረግ ነበር ፡፡ ታስታውሳላችሁ የእግዚአብሄርን ቅጣት ለአሮን ኃጢዓት ወርቅ ጥጃ በመስራቱ ? እግዚአብሄር ቀጥሎ ከእስራኤላዊያን ጋር አብሮ እንደማይጋአዝ ሙሴን ነግሮታል ፡፡ ተመልከቱ በመቅደሱ ውስጥ ወደ እግዚአብሄር መገኘትን መቅረብ ያገኘው ማን እንደነበር - አሮን ! እግዚአብሄር የሚዋጅ አምላክ ነው !
በጥፋተኝነት ቦታ መኖር አንችልም ! አስተሰሪያችን ለዛ ጥንቃቄ ያወስዳል ! ከእግዚአብሄር ጋር በደህንነትና በህብረት መሄድ አለብን ፡፡ በበፊት ጉዞአችን “ወርቃማው ውልደት” ለመከተል ፍቃደኞች ነን ? ኢየሱስ ነው ! ነን ?
ዘሌዋውያን(9፡ 5-7); ማህበሩ መጣ በእግዚአብሄርም ፊት ቆሙ ፤ ሙሴ ሁሉንም አራቱን መስዋዕቶች ማድረግ ጀመረ ፡፡ ታስታውሳላችሁ በእስራኤል ውስጥ ስለ እያንዳንዱ ተለያዩ የሰዎች ቡድን ስናዎራ፡ ካህናቱን፣ ማህበረሰቡ፣ መሪዎች እና የአገሩ ሰዎች ? አሮን መጀመሪያ ለራሱ መስዋዕት ያቀርባል ከዚያም ለህዝቡ መስዋዕት ያቀርባል ፤ በዚህ ምክንያት ሌላ አገልግሎት እንድንሰራ ለእኛ ስርዓት ከእግዚአብሄር ጋር ትክክለኝ ግንኙነት ሊኖረን ይገባል ፡፡
ዘሌዋውያን(9፡ 8-11); የኃጢዓት መስዋዕት ለአሮን ተካሄደ ፤ የሰሩትን ሁሉ ስናየው ጥቂት የሆነ የሚያስጠላ እርካታ ይሆን ነበር በመጨረሻም ለሚፈለገው አላማ ተጠቀመባቸው ፡፡ ይህ እግዚአብሄር እንዳዘዘዉ ሆነ ፤ አሮን ስጋውን አቃጠለው ከመኖሪያቸውም ውጪ ደበቀው ፤ ኢየሱስ ከመኖሪያ ውጪ ተሰዋ(ዕብ 13፡ 11-13) ፡፡ አሮን ሁለተኛ እድል ተሰጠው እናም ኢየሱስ አንዴ ብዙ ሰጠን !
ዘሌዋውያን(9፡ 12-16); የሚቃጠለው መስዋዕት ተደረገ(ተካሄደ) ፤ ለምን ? የሚቃጠል መስዋዕት የሁል ጊዜ መስዋዕት እና ከመኖሪያቸው ውጪ አይወጣም ፡፡ የኃጢዓት መስዋዕት ብቻ ከመኖሪያቸው ውጪ ይወጣል ፡፡ ዘሌ(16፡ 5) በስርየት ቀን ፍየል እንደ ኃጢዓት መስዋዕት እንደ ቀረበ ገለጸ ፤ እዚህ በዘሌ 9 ምንድን ነበር እየተካሄደ የነበረው ለስርየት ቀን ጥላ ነበር ፡፡
ዘሌዋውያን(9፡ 17-21); የእህል መስዋዕት ተደረገ ፤ ሁል ጊዜ በማክበር ሁኔታ ውስጥ መቀመጥ አትችሉም በተጨማሪም ሁል ጊዜ በንስሀ ሁኔታ ውስጥ መቀመጥ የለባችሁም ፤ መመጣጠን አለበት ፡፡ ይህ የአሮን የመጀመሪያው ቀን ስራ ነበር የኃጢዓት መስዋዕት፣ የሚቃጠል መስዋዕት፣ የእህል መስዋዕትና የህብረት መስዋዕት አቀረበ ፡፡
ዘሌዋውያን(9፡ 22); አሮን ህዝቡን ሲባርክ ይህ የመጀመሪያ ጊዜ ነበር ፤ መነው ይህን ለአሮን የነገረው ? ይህ የነበር ተቀብቶ ስለ ነበርነው ፤ የእግዚአብሄር መንፈስ እርምጃውንና እጆችን ይመራው ነበር ፡፡አሮን ህዝቡን ለመባረክ እጁን አነሳ ፤ ዘኁ (6፡ 24-26) የአሮናዊን በረከቶች የገለፀ ነው ፡፡
ዘሌዋውያን(9፡ 23); አሮን በሁሉም ሂደት ውስጥ ሄደ እናም አሁን አሮንና ሙሴ ወደ መገናኛው ድንካን ገቡ(ሄዱ) ፤ ከዚያም በመቀጠል ሁለቱም በመውጣት እንደገና ህዝቡን ባረኩ ፡፡ የእግዚአብሄር ክብር ለሁሉም ህዝብ ተገለጠ ! እናም ሙሴ ብዙ የእግዚአብሄርን ክብር የለመደ ነበር ፡
- ዘጸ 3 - በሚነድድ ቁጥቐጦ
- ዘጸ 24 - በደመና
- ዘጸ 33 - በሲና ተራራ አለት
- ዘጸ 40 - መቅደሱ ተሞላ
- ዘጸ 40 - ህዝቡ በደመና አምድና በእሳት አምድ ተመርተው ነበር
በ 1ነገስት 8 ውስጥ ቤተ መቅደሱ በእግዚአብሄር ክብር ተሞልቶ ነበር ፤ እግዚአብሄር ህዝቡ ክብሩን እንዲለምዱት ይፈልጋል ፡፡ በዮሐ (1፡ 14) ውስጥ ቃል ስጋ ሆነ በዚህም ክብሩን ለመድነው ! ከክርስቶስ ጋር በራሳችን ግንኙነት ውስጥ ክብሩን መለማመድን እናገኛለን ፡፡ማቴ(24፡ 29-30) ተመልሶ በክብር ይመጣል ይላል ! “ የምድር ወገኖች ሁሉ……..የሰው ልጅንም በኃይልና በብዙ ክብር ……ሲመጣ ያዩታል “ ልክ እንደዚህ በዘሌ 9 ውስጥ “ የእግዚአብሄርም ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ “ ፤ የሚመጣው መሲህ መልክ ነው !
ዘሌዋውያን(9፡ 24); እሳት ከእግዚአብሄር መጣ ፤ ሁሉም ህዝብ ይህን አዩ(አይጠዋል) ! (7.5 ኢንች በ 4.5 ኢንች) የሆነው መሰዊያ በእሳት ተሞላ ! ይህ እኔ የምፈልገው ነው ፡፡ ክብሩንና እሳቱን መቅመስ(መለማመድ) እፈልጋለሁ ! ከኢየሱስ ጋር ግንኙነት በሚኖራችሁ ጊዜ ይህን መለማመድ(መቅመስ) ትችላላችሁ ! ያጠመቀን በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት ነው ፡፡
ብዙ ጊዜ በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሄርን በእሳት ውስጥ እናየዋለን ፤ በዘዳግም ውስጥ እግዚአብሄርን እንደሚባላ እሳት እናየዋለን; በመዝሙር 18 ውስጥ የእሳት መልክ እናያለን; በሕዝቄል(1፡ 4) እግዚአብሄር ኃላና ፊት የሚያንፀባርቅ ከእሳት ጋር እንዳለ ታላቅ ደመና የሚመስል ነው በተጨማሪም ሚል (3፡ 2) እንደሚያጠራ እሳት ነው፡፡ በማቴ (24፡ 29-30) እሳት እንደሚመጣ አስባለሁ ፤ ክርስቶስ ተመልሶ ይመጣል ፤ ክብር እና እሳት ይወርዳል ፤ ዝግጁ ናችሁ ? መንገዱ መዘጋጀት የምትችሉት በአሮን ትምህርት መስዋዕት ውስጥ እንደ ሆነ አምናለሁ፡ የኃጢዓት መስዋዕት፣ የሚቃጠል መስዋዕት፣ የእህል መስዋዕት እና የህብረት መስዋዕት ፡፡ በክርስቶስ ስርየት እና ከእርሱ ጋር ባለ ህብረት ዝግጁ መሆን እንችላለን ፡፡
መዝጊያ
ክብር እና እሳት ለመለማመድ(ለመቅመስ) እራሳችሁን ለእርሱ ለማቅረብ ፍቃደኞች መሆን አለባችሁ ፤ ይህን ስታደርጉ በፍፁም ለምዳችሁት በማታውቁት ትቀምሱታላችሁ ፡፡ አሮንና ሙሴ በሄዱበት በኩል ምክንያት ሁሉም እስራኤላውያን የእግዚአብሄርን ክብር መቅመስ(መልመድ)(ማየት) አገኙ ፡፡
ጥያቄዎች
-
ለመለየት በበዓል የሚቀባው ሙሴ ማን ነበር ? የዚህ መለየት አስፈላጊነቱ ምንድን ነበር ? ሁሉም ነገር በዚህ መንገድ የታዘዘው ለምን ነበር ? (ዘሌ 8፡ 34)
-
በእስራኤል የካህናቱ ስራ ምንድን ነበር ?
-
ሙሴና አሮን መስዋዕቱን ካቀረቡ በኃላ ወዴት ሄዱ ? በወጡ ጊዜ ምንድን ሆነ ? (ዘሌ 9፡ 22-23)
-
ሙሴ አሮንን ለኃጢዓቱና ለሚቃጠል መስዋዕት ወዴት እንዲሄድ ነገረው ? (ዘሌ 9፡ 7)
-
በዘሌ 9፡ 22 አሮን እጁን አንስቶ ህዝቡን ባረከ ፤ ምናልባት በዘኁ (6፡ 24-26) በተፃፉት ቃሎች ባረካቸው ፤ አነዚያ ተመሳሳይ ተስፋ እንዳለን እንዴት እናውቃለን ? (ኤፌ 1፡ 3; ዕብ 8፡ 6-7)
-
በዘሌ(8-9) ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Leviticus 9:23b-24
“When they came out, they blessed the people, and the glory of the LORD appeared to all the people. Fire came from the LORD and consumed the burnt offering and the fat portions on the altar. And when all the people saw it, they shouted and fell facedown on the ground.”
ኦሪት ዘሌዋዉያን 8-9 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
የእግዚአብሔር ክብር እንዲገለጥ፥ ሙሴ፣ አሮን እና የአሮን ልጆች ልክ እግዚአብሔር እንዳዘዛቸዉ አደረጉ! ሰባት ቀን የሚወስደዉ የሹመት ሂደት፥ አካታች እና ዝርዝር ያለዉ ቢሆንም እያንዳንዱን ነገር በሚገባ ታዘዋል። በስምንተኛዉ ቀን እግዚአብሔር ቃሉን በመጠበቅ፥ የእግዚአብሔር ክብር እንደ እሳት ወረደ! ይህም በፊታቸዉ ወድቀዉ፥ እንዲጮሁ አድርጓቸዋል! እግዚአብሔርን በትህትና እና በደስታ አመለኩት።
እግዚአብሔር ለአንተ በክርስቶስ ሞት፣ መቀበር እና ትንሳኤ ክብሩን አሳይቶሃል። በትህትና እና በደስታ፥ ዝቅ ብሎ እግዚአብሔርን ከማምለክ ፈፅሞ እንዳታቋርጥ! እግዚዓብሔርን በምታመልክበት ጊዜ፥ የሚለዉጠዉን ክብሩን ትለማመዳለህ!
"ሙሴና አሮንም ወደ መገናኛው ድንኳን ገቡ፤ ወጡም፥ ሕዝቡንም ባረኩ፤ የእግዚአብሔርም ክብር ለሕዝቡ ሁሉ ተገለጠ። እሳትም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ፥ በመሠዊያውም ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ስቡንም በላ፤ ሕዝቡም ሁሉ አይተው እልል አሉ፥ በግምባራቸውም ወደቁ።"
ኦሪት ዘሌዋዉያን 9:23-24
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘሌዋዉያን 9:6፦ "ሙሴም፦ ታደርጉት ዘንድ እግዚአብሔር ያዘዘው ይህ ነው፤ የእግዚአብሔርም ክብር ይገለጥላችኋል አለ።"
የማቴዎስ ወንጌል 17:5-6፦ "እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ። ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር።"
ወደ ሮሜ ሰዎች 6:4፦ "እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን።
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 56
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።