The Pentateuch Leviticus

The Fellowship Offering

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 7 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 55 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

የተለያዩ የመስዋዕት አይነቶች እያየን ነው፡ የጥፋተኛነት መስዋዕት፣ የሚቃጠል መስዋዕት፣ የኃጢዓት መስዋዕት፣ የእህል መስዋዕት እና የህብረት ደህንነት መስዋዕት ፡፡ ዝግ ማለትና እስካሁን የተማርነውን ምልከታ እንድንወስድ እፈልጋለሁ ፡፡

እግዚአብሄር በሲና ተራራ ለሙሴ በነገረው ጊዜ የተናገረው “ በእኔ መርጫቸዋለሁ ፣ የእኔ ርስት፣ የእኔ ካህናት፣ የእኔ ቅዱስ ህዝብ ናቸው ለዚህ ነው የእኔ ህዝብ የምፈልጋቸው ፤ የመጀመሪያ መስዋዕታቸውን እንዲያመጡልኝ እፈልጋለሁ ስለዚህ ከኃጢዓታቸው መንፃት ይችላሉ ከዚያም እኔን በብዙ ይለምዱኛል(ይቀምሱኛል) ፡፡”

እግዚአብሄር ሙሴን እንዴት ካህናቱ፣ መሪዎች ወይም የአገሩ ሰዎች ምህረትን መለማመድ(ማግኘት) እንደሚችሉ ነገረው ፤ ሁሉም ስለ ደም ነበር ስርየት ስለሚሰጠው ፤ በሞት ውስጥ ህይወት አለ ፡፡

አዚህ ጋር በእነዚህ እያንዳንዳቸው መስዋዕት ክርስቶስ እንዴት እንደተወከለ ነው ፡

የሚቃጠል መስዋዕት

ዘሌ 1

ስርየት

ክርስቶስ ኃጢዓት አያዉቀውም

የእህል መስዋዕት ወይም የጥራጥሬ ቁርባን

ዘሌ 2

መሰጠት / መንፃት

ክርስቶስ ለአባቱ አላማ ሙሉ ለሙሉ የተሰጠ ነው

የህብረት መስዋዕት ወይም የደህንነት መስዋዕት

ዘሌ 3

ህብረት

ክርስቶስ ከእግዚአብሄር ጋር በሰላም ነበር

የኃጢዓት መስዋዕት

ዘሌ 4

ይቅርታ ማግኘት

ክርስቶስ በምትክነት(በመተካት) ሞተ

የጥፋጠኝነት መስዋዕት ወይም የካሳ መስዋዕት

ዘሌ 5-6

ንስሀ

ክርስቶስ ሁሉን ለንስሀ ከፈለ

ዛሬ ስለህብረት መስዋዕት እንወያያለን ደስ የሚያሰኝ ነው ፤ አዎ መስዋዕት አለ በተጨማሪ ደግሞ ቡድን አለ ፡፡ ቀስ ባልን ጊዜ ክርስቶስ በዚህ ሁሉ ውስጥ እንዳለ እናያለን ፡፡

ትምህርት

ዘሌዋውያን(7፡ 1-2); የካሳ መስዋዕት(የትፋተኝነት መስዋዕት) የጠፋን ወይም የተሰረቀን ነገር እንደገና መመለስ ነው ስለዚህ ይህ እንደገና መመለስ ለትክክለኛ ባለቤቱ መመለስ ነው ፡፡ ይህ በሚቃጠል መስዋዕት መሰዊያው ላይ የሚቀርብ ነው ፡፡

ዘሌዋውያን(7፡ 310); አቅራቢው( ኃጢዓተኛው እስራኤላዊው) ስቡን ያቀርባል ፤ ካህኑ ያቃጥለዋል ፡፡ እንደ ኃጢዓት መስዋዕት ካህኑ የካሳ መስዋዕቱን ስጋውን መብላት ይችላል ፤ በእውነቱ ካህናቱ በካሳ መስዋዕት በኩል ክፍያ ያገኙ ነበር ፤ ለካህናቱ የእህል መስዋዕት ክፍያቸው ነበር ፡፡

ዘሌዋውያን(7፡ 11); የህብረት መስዋዕት( የደህንነት መስዋዕት) አማዮች ከእግዚአብሄር ጋር በሰላም የሚያከብሩት ነበር ፤ ይህ መልካም(ጥሩ) መስዋዕት ፡፡ አንዳንድ ጊዜ በኃጢዓታችን ላይ ትኩረት ማድረግ ቀላል ነው ነገር ግን እግዚአብሄር ያደረገልንን ነገሩን ለማክበር ማስታዎስ ያስፈልጋል ፡፡

ዘሌዋውያን(7፡ 12); የህብረት መስዋዕት ለምስጋና ስጦታ የቀረበ ነበር ! ኔልሰን የፃፈው “ ምስጋና መስጠት በእግዚአብሄር ፀጋና ምህረት የተደገፈ የሰው የእምነት ቃል ነው እናም የህያው እግዚአብሄር ምስጋና ነው ፡፡“ ብዙዎቻችን በለቅሶዎቻችንና በኃዘናችን ተንደባለናል ፤ ምን ማለት እንደሆነ አስቡ ይህ እይታ ያለን ከሆነ “ እግዚአብሄር ይመስገን በህይወት አለሁ ! እግዚአብሄር ይመስገን ንስሀን ሰጠኝ(አስተካከለኝ) !”

የህብረት መስዋዕት ከዘይት ጋር በተቀላቀለ ባልቦካ ቂጣ፣ በዘይት በተሸፈነ ስስ ባልቦካ ቂጣ ወይም በዘይት በደንብ በተቦካ ጥሩ የቂጣ ዱቄት በማቅረብ አክብረዋል ፡፡ ኔልሰን የፃፈው “ ምስጋና የማቅረብ መስዋዕት እግዚአብሄር መን እንደሆነ እና ምን እንዳደረገላቸው ህዝቡ የሚያዉጁበት ነበር ፡፡” ከሌሎቹ መስዋዕት በሚበልጥ የህብረት መስዋዕት በማቅረብ የታወቀ ሰው መሆን እፈልጋለሁ ፤ ሙሴ “ ለአደረገው እግዚአብሄርን እንድታመሰግኑት እፈልጋለሁ” ብሎ ተናግሮ ነበር ፡፡

ዘሌዋውያን(7፡ 13); ቂጣውና ስጋው እንደመስዋዕት ያገለግሉ ነበር ፤ እስራኤላዊያን ሰላማቸውን ከእግዚአብሄር ጋር ያከብሩና ለእግዚአብሄር ሕዝባዊ ምስጋናቸውን ይገልፁ ነበር ፤ አመስግናለሁ ብቻ አይደለም የሚሉት ምስጋናቸውን ለእግዚአብሄር የሚገልፁት በማቴሪያል ነገሮችም እንጂ ፡፡ ያዕቆብ መስዋዕት አቀረበ ዘመዶቹም ምግብ እንዲበሉ ጋበዛቸው (ዘፍ 31፡ 54) ፤ የህብረት መስዋዕት ምግቡን አብሮ መብላትና መስዋዕቱን ይይዛል ፡፡ ሰለሞን የህብረት መስዋዕት -22,000 ከብቶች እና 122,000 በጎች ቤተ መቅደሱን ለማስመረቅ አቀረበ (1ነገ 8፡ 62-63) ፤ በመጀመሪያ ሙሴ የድንካኑን ማደሪያ(መቅደስን) ሰራ ቆይቶ ሰለሞን ቤተ መቅደስን ሰራ ፡፡

ዘሌዋውያን(7፡ 14-15); የማንሳት መስዋዕት(ቁርባን) (የመወዝወዝ መስዋዕት አያደለም) ስጦታዎችን ሰጪ እንደሆነ እውቅና ለመስጠት በእግዚአብሄር ፊት ይወዘወዛል ፤ ምስጋና በማቅረብ ውስጥ ከፍ የሚሉ የተወሰነ አይነት ምግቦች ነበሩ ፤ ትራፊ ሊኖር አይችልም ፡፡

ዘሌዋውያን(7፡ 16);ኮንስታብል የፃፈው “ ሰዎስት አይነት የህብረት መስዋዕቶች አሉ ፡ 1) የምስጋ መስዋዕት ላልተጠበቀ በረከት የተገለፀ ምስጋና ሲሆን; 2) የስዕለት መስዋዕት ለመባረክ ሲጠይቁ መሀላ በተደረገ ጊዜ ለተሰጠ በረከት የተገለፀ ምስጋና እና 3) የፍቃድ መስዋዕት ከምንም በረከት አንፃር ዉጪ የሆነ ለእግዚአብሄር የተገለፀ ምስጋና ናቸው ፡፡” የመሀላ(የስለት) ወይም የፍቃድ መስዋዕት ከሆነ ያቀረበው ምናልባት ትራፊ ለአንድ ቀን ብቻ ይተርፋል(ያቀራል) ፡፡ እስራኤላዊያን ከእግዚአብሄር ሰላም(ደህንነት) እንዲኖራቸውና ይህን እንዲያከብሩት እድል ተሰጣቸው ፡፡ ከእግዚአብሄር ሰላም ናችሁ ? ሊኖራችሁ የሚችለው ብቸኛው መንገድ በክርስቶስ በኩል ነው !

ቆላ(3፡ 15) “ በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ ፡፡“ በሰላም በሆንን ጊዜ ውጤቱ አመስጋኝነት ነው ፤ የክርስቶስ ሰላም ከሌላችሁ ወደ እርሱ በመመለስ እንዲቆጣጠራቸሁ ለመስጠት ጊዜ አለ ፡፡ መፅሀፍ የሚከተሉትን ይነግረናል፡

ሮሜ(3፡ 23) - ሁላችን ኃጢዓተኞች ነን

ሮሜ(6፡ 23) - የኃጢዓት ደሞዝ ሞት ነው; ሰላም የለም

በክርስቶስ የተገኘውን ሰላም እንድንቀምሰው እፈልጋለሁ ! ስጋት(ጭንቀት) በሚኖር ጊዜ ለእርሱ ስጡት ! ስለዚህ ወደ ጭንቀት የሚመሩትን እነዚህን ነገሮች ለመቐቐም እንዴት እናድርግ ?

ሮሜ(5፡ 8) - የሱ ፍቅር ኃጢዓትንና ሞትን በሩቅ ወስዶአል ፡፡

በቤታችሁ ይህን ማድረግ መሞከር አቁሙ ! ይወስደዋል ! ለዚህ ነው ስለ ዘሌዋውያን የምወደው ፤ ለእኛ ሰላም ለሰጠን ወደ ክርስቶስ ስርየት ያመለክተናል ፡፡ የደህንነት መስዋዕት መለማመድ(ማድረግ) በምትችሉ ጊዜ

ኤፌ(2፡ 8-9) - በእምነት በፀጋ ድናችኃል; ይህ ስጦታ ነው ፡፡

ሮሜ(10፡ 9-10) - ጌታ እንደሆነ በኢየሱስ የምታምኑና ናስሀ የምትገቡ ከሆነ ትድናላችሁ ህይወት

መዝጊያ

ሮሜ(10፡ 9-10) በተለማመዳችሁት ጊዜ የህብሬን መስዋዕት ትለማመዳላችሁ; በዚህም ህይወትን እና ሰላምን ትለማመዳላችሁ ፡፡

  1. Earl D. Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson, Inc., 1999), p. 161.

  2. Radmacher, p.161.

  3. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes (available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/leviticus.pdf), pp.225-226.

ጥያቄዎች

  1. በጥፋተኝነት መስዋዕትና በኃጢዓት መስዋዕት መሀከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው ? (ዘሌ 4; 5፡ 14-19) የትኛው በጣም ቅዱስ ተደርጎ የታሰበ ነው ? (ዘሌ 7፡ 1)
  2. ጥቂት መስዋዕቶች በተለየ ቦታና ጊዜ ይፈለጉ ነበር ፤ ስለ ደህንነት መስዋዕትና የምስጋና መስዋዕት ልዩ የነበረው ምንድን ነበር ? (ዘሌ 7፡ 11-14)
  3. ለምንድን ነበር በፍፁም የማይቃጠለው ? (ዘሌ 7፡ 26; 17፡ 11) ይህን ላደረገ ምንድን ነበር ቅጣቱ ? (ዘፍ 9፡ 4-6)
  4. ክርስቶስ እንዴት የሚቃጠል፣ የእህል፣ የደህንነት፣ የኃጢዓት እና የጥፋተኝነትን መስዋዕት አማላ ? (ሮሜ 5፡ 1; 4፡ 25; 1ቆሮ 15፡ 20; 2ቆሮ 5፡ 21; ኤፌ 5፡ 2)
  5. በዘሌ 7 በትምህርት ወይም በጥናት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Leviticus 7:28-29

“The LORD spoke to Moses: ‘Tell the Israelites: The one who presents a fellowship sacrifice to the LORD must bring an offering to the LORD from his sacrifice.’”

የህብረት መሥዋዕት

ኦሪት ዘሌዋዉያን 7 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

የእስራኤል ህዝቦች፥ ስለ የደህንነት ወይም አንዳንዴ ደግሞ የህብረት መሥዋዕት የሚባለዉን ዝርዝር ትዕዛዛትን ተቀበሉ። የደህንነት መሥዋዕት አትኩሮቱ ሙሉዕነት ወይም ሙሉነት ላይ ነዉ። እስራኤላዉያን መሥዋዕትን ወደ እግዚአብሔር ይዙዉ በሚቀርቡበት ጊዜ ሙሉነት ይሰማቸዉ ነበረ። እግዚአብሔር ከእናንተ ጋራ ሰላም መሆኑን በማወቃችሁ፥ ከእርሱ ጋራ ሙሉዕነትን ገንዘብ በማድረግ፥ የአዕምሮ ሰላም እና ሃሴት እንዲሰማችሁ ያደርጋል። ልክ እንደዚሁ፥ ጳዉሎስም አማኞችን በፀሎት እና በምልጃ ከምስጋና ጋራ ልመናችሁን ለእግዚአብሔር አስታዉቁ እያለ ያዛቸዋል። ከዚያም የእርሱ ሰላም ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠራችኋል።

ኢየሱስ ሙሉዕነትን ወደ ህይወትህ የሚያመጣ ሰላምህ ነዉ። ሁሉንም ነገር በራስህ አቅም ለመቆጣጠር መፍጨርጨሩን ትተህ፥ እያንዳንዱን የህይወትህ ቅፅበት ለእግዚዓብሔር አሳልፈህ ከሰጠህ፥ የእርሱ ሰላም ወደ አንተ ይመጣል። ለእግዚአብሔር አሳልፈህ መስጠት ያለብህ አንተ በራስህ መንገድ ለመቆጣጠር እየሞከርክ ያለውኸዉ ነገር ምንድን ነዉ? ዛሬ፥ የደህነነትን መሥዋዕት የምታቀርብበት፥ ራስህንም የምታስገዛበት ቀን ይሁን!

"እግዚአብሔርም ሙሴን እንዲህ ብሎ ተናገረው፦ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ ብለህ ተናገራቸው፦ ለእግዚአብሔር የደኅንነት መሥዋዕት የሚያቀርብ ሰው ቍርባኑን ለእግዚአብሔር ከደኅንነቱ መሥዋዕት ያመጣል።"

ኦሪት ዘሌዋዉያን 7:28-29

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • መዝሙረ ዳዊት 29:11፦ "እግዚአብሔር ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፤ እግዚአብሔር ሕዝቡን በሰላም ይባርካል።"

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 2:17-18፦ "መጥቶም ርቃችሁ ለነበራችሁ ለእናንተ ሰላምን፥ ቀርበው ለነበሩትም ሰላምን የምስራች ብሎ ሰበከ፤ በእርሱ ሥራ ሁላችን በአንድ መንፈስ ወደ አብ መግባት አለንና።"

ወደ ፊልጲስዩስ ሰዎች 4:6-7፦ "ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ። ነገር ግን እንደ ክርስቶስ ስጦታ መጠን ለእያንዳንዳችን ጸጋ ተሰጠን።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 55