The Guilt Offering & Continual Fire
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 6 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዘሌዋውያን ውስጥ በሁሉም የመስዋዕት አይነት ውስጥ እያረስን(በጥልቀት እያየን) ነው ፤ እስካሁን የሸፈነው፡
ዘሌ 1- የሚቃጠል መስዋዕትን
ዘሌ 2- የእህል መስዋዕትን
ዘሌ 3- የህብረት መስዋዕትን
ዘሌ 4- የኃጢዓት መስዋዕትን(የካህናቱን፣ የማህበረሰቡን፣ የመሪዎችን፣ የአገሩ ሰዎችን)
ዘሌ 5- ህግ የጣሰ ወይም የትፋተኝነት መስዋዕትን
አስታወሱ እግዚአብሄር አንዴት በአምልኮ ከእርሱ ጋር እንዲገናኙ እስራኤላዊያን ለመናገር ይህን መመሪያ ሰጠ ፤ ማወቅ ያለባችሁ ምህረት ያስፈልጋችኃል ይህም በአስተሰሪያችን በክርስቶስ መስዋዕትነት በኩል ብቻ የተቀበላችሁት ነው ፡፡
እስራኤል በዚህ አገላለፅ ውስጥ ለረጅም ጊዜ በግብፅ ነበሩ እና አሁን ደግሞ በበርሃ ውስጥ ይጋአዙ ነበር ፤ የኔልሰን ሀተታ የሚለው “ እስራኤል በበርሃ ውስጥ የሚጋአዝ ስደተኛ ህዝብ ነበር “ ፡፡ በበርሃ ውስጥ ሲጋአዙ ቤት አልነበራቸውም ህግም የላቸውም ነበር ፤ ስለዚህ እግዚአብሄር እነዚህን ደንቦች(ህጎች) ሰጣቸው እንዲመራቸውም መስዋዕት አስፈለገው ፡፡ በዘሌዋውያን 5 መጨረሻ ላይ አንድ ሰው ጥፋተኝነቱን ሲያዉቅ ወይም በጥፋተኝነት ሲጠረጠር ህግ የመተላለፍ/የጥፋተኝነት መስዋዕትን ነበር ፡፡
ትምህርት
ዘሌዋውያን(6፡ 1-4); እግዚአብሄርን ሙሴን ለጥፋተኝነትን መስዋዕት ትዕዛዝ ሰጠው ፡፡ አስታውሱ ይህ ለእነኝህ ስደተኞቹ እስራኤላዊ መመሪያና በሙሴና በእግዚአብሄር መሀከል የቀጠለ ቃለ ምልልስ ነበር ፡፡ የበርሃን ቃለ ምልልሶች ማሰብ ትችላላችሁ ? እስራኤላዊያን ጎረቤታቸውን ባታለሉ ጊዜ እግዚአብሄርን ያስከፉታል ! አስከፊው ስህተት እንደነበር ያሳውቃል ከዚያም ሰርቆት የነበረውን ምንም ይሁን ይመልሳል ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያን መውጫ ይሰጣቸው ነበር ፡፡
ዘሌዋውያን(6፡ 5); አንድ እስራኤላዊ ካታለለ ወይም ከጎረቤቱ ከሰረቀ ሙሉ ካሳ ማድረግ ይኖርበታል ! በተጨማሪም በዋጋው ላይ አምስት መጨመር- 20 ፐርሰንት በመሰደው ላይ መጨመር ይኖርበታል ፤ ይህ የሚሆነው ጥፋቱን ባመነበት(ባወቀበት) “ በዚያ ቀን” ነበር ! ይህ ለዘኪዎስም ሆኖአል (ሉቃ 19፡ 8) ፤ ከአታለላቸው ወይም ከሰረቃቸው አራት እጥፍ አስበልጦ መልሶ ሊከፍል ፍቃደኛ ነበር ! ጥፋተኛ እንደሆኑ ሲያውቁ ሰርቀውት በነበረው ላይ 20 ፐርሰንት ጨምረው ምንም ይሁን መመለስ አለባቸው ፡፡ እኛ ሁላችን በተሳሳተ መንገድ ለመሄድ እድሎች አሉን ፤ እንደ ማነሳሻ ዮሴፍ በእሱ ስር የሌለውን ለመቀበል እድል ባገኘ ጊዜ እንዴት እንደመለሰ እንመልከት (ዘፍ 39፡ 9; 1ዮሐ4፡ 20) ፡፡
ዘሌዋውያን(6፡ 6-7); ካሳ ከተደረገ ቦኃላ የሚያደርጉት ተጨማሪ ነበር ፤ ሮከር የፃፈው “ከአንድ የቅርብ ሰው ጋር ብቻ ካሳው ከተደረገ ቦኃላ በእግዚአብሄር አስተያየት መታየት የሚችል መሆን አለበት (ቁጥር 6) “ አሜሪካ ቤተ ክርስቲያን ከዚህ ምሳሌ መማር ትችላለች ! ተሳስቶ ባገኘነው ጊዜ ልናርመው(ልናስተካክለው) በመጀመሪያ ወደ ወንድማችን ልንሄድ ያስፈልገናል ፡፡ቁርባን በምንካፈል ጊዜ እንድናደርግ የታዘዝነው አይደለምን (1ቆሮ 11፡ 17-34)?
ካህኑ መስዋዕቱን እንደገማች ሆኖ ያገለግላል “በእርሱ ዋጋ ጥናት መሰረት” ፤ ለፈፀሙት ስህተት ደረጃ ለእግዚአብሄር ትክክለኛነት እንዲኖረው ለጥፋተኛነት መስዋዕት እንከን የሌለበት በግ ያመጡ ነበር ፡፡ ያደረጉዓቸው 1) እቃዉን መመለስ; 2) አንድ አምስተኛ የዋጋውን መጨመር እና 3) ትክክለኛ የጥፋተኝነት መስዋዕት ለእግዚአብሄር ማድረግ፡፡ ኃጢዓት ሁል ጊዜ ባዙ ያስወጣናል ! መስዋዕትነት ስርየትን ያደርጋል ፤ እስራኤላዊያን በመስዋዕቱ ደም በኩል ምህረትን ያገኛሉ ፡፡ እግዚአብሄር ይመስገን ! ትንሽ ቅርፅ ሰጣቸው ፡፡
ዘሌዋውያን(6፡ 8-13); በዘሌ 1 ስለ ሚቃጠል መስዋዕት አውርተናል ፤ እሳቱ ያለማቐረጥ ይበራልም ወደ ዉጭም አይወጣም ! ይህ በዘሌዋውያን ውስጥ ስንቀጥል ዋና(ጭብጥ) ይሆናል ፡፡ ካህናቱ ይህን ስራ ለመስራት ተቀብተዋል እናም አመዱን ከማዉጣት በፊታቸው ልብሳቸዉን ይቀይሩ ነበር ፤ መልኩኑ ባነሳሳሁት ጊዜ እሳት እና መንፈስ ቅዱስን አሰብኩ ፡፡
በመፅሀፍት ውስጥ በዚህ የእሳት ስዕል ውስጥ መጋአዝ እፈልጋለሁ፡
- ዘሌ(9፡ 24); ከእግዚአብሄር ትክክለኛው እሳት በመሰዊያው ላይ ፤ የሚቀጥል እሳት ነበር የሚቀጥልን አምለኮን ያመለክታል ፡፡ ለክርስቶስ፣ ለአስተሰሪያችን እና ለእርቅ የቀጠለ አስፈላጊነቱን ይወክላል ፡፡
- ሉቃ(3፡ 16); ዮሐንስ አጥማቂው ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት እንደሚያጠምቅ ተናገረ ፤ እሳት ገለባን፣ ጥፋተኝነትን እና ኃጢዓት የሚያቃጥል ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ የአሜሪካ ቤተ ክርስቲያን በኑሮአችን ውስጥ እሳቱ ገለባዎን እንዲያቃጥለው አትፈልግም ፤ በኑሮአችን ውስጥ የእግዚአብሄር እሳት በሚያቃጥል ጊዜ ነፃነት ይኖራል ፡፡
- ሮሜ(12፡ 1-2); ሰዉነታችሁን እንደ ህያው መስዋዕት አቅርቡ፡፡ በፍፁም የእሳትን ጥምቀት የማትፈቅዱ ከሆነ በኃጢዓት ትያዛላች(ትሰምጣላችሁ) ፤ የእሳት ጥምቀት በመንፈስ ቅዱስ ጥመቀት ውስጥ እንድትሰሩ ያስችላችኃል ፡፡
- ኤር(20፡ 9); የእግዚአብሄርን መልዕክት የማትጠቅስ ከሆነ በልብህ ውስጥ ልክ እንደ እሳት ይሆናል በአጥንቶችህ ውስጥ ይነድዳል ፡፡
- መዝ(39፡ 3); ልቤም በውስጤ ሞቀብኝ ፡፡
አምስት ጊዜ በቁጥር(8-13) ውስጥ “ እሳቱ ዘወትር ይንደድ; እንዳይወጣ” የሚለው ንግግር ተመዝግቦአል ፤ የኔልሰን ሀተታ የገለፀው “ የማያቐርጠው እሳት የሚያመለክተው ለስርየትና ከእግዚአብሄር ጋር ለእርቅ ያለማቃረጥ ያስፈልጋል ይህም የመስዋዕቱ አላማ ነበር ፡፡”
ዘሌዋውያን(6፡ 14-23); የእህል ቁርባን(ጥራጥሬ፣ የምግብ መስዋዕት) ተገልፆአል ፡፡
ዘሌዋውያን (6፡ 24-30); የኃጢዓት መስዋዕት ተገልፆአል ፡፡
መዝጊያ
ስህተት እንዳደረግን በተሰማን ጊዜ ለጥፈተኝነታችን እውቅና እንሰጣለን አንዳንድ ጊዜ ጠላታችን በዛ ውስጥ እንድንቆይ ይፈቅዳል ከዚያም በጥፋቱ እንድንቀጥል ምክንያት ይሆናል ፤ ነገር ግን ደሙ ነፃ አውጥቶናል ! ስቴቨንኮሌ የፃፈው “ ሰይጣን በመምጣትና ጥፋጠኛ በመሆን እንድንከሰስ ይወዳል ከዚያም በአጭር የወደቀ በተጎጂነት ቦታ እንቀመጣለን ፡፡”
በራዕ(12፡ 10) ውስጥ ሰይጣን የወንድሞች ከሳሽ ነው ፤ በዘካ(3፡ 1) ስይጣን ታላቁን ካህን ኢያሱን ከሰሰው ፡፡ በዚህ የጥፋተኝነት ቦታ መኖር አንችልም ! ኢየሱስ ነፃ አድርጎናል ! በጥፋተኝነት የምትያዙ ከሆነ የኢየሱስ ደም አይበቃም እያልን ነው ፡፡
2ቆሮ(3፡ 17) “ ጌታ ግን መንፈስ ነው ፤ የጌታ መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ ፡፡” በመንፈስ ቅዱስ እና በእሳት እንደ ተጠመቅን የምናወራ ከሆነ በአርነት እየሄድን እንደሆነ እናወራለን ፡፡ አነዚህ የጥፋተኝነት መስዋዕት በዘሌ 6 ውስጥ ነፃነትን አመጣ ፤ ነገር ግን እስራኤላዊያን ለእያንዳንዱ ጊዜ የጥፋተኝነት መስዋዕት ያደርጉ ነበር ፡፡ ይህን እንድ ጊዜ ብቻ እናደርጋለን ፡፡
Earl D. Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson, Inc., 1999), p. 158.
Mark F. Rooker, The New American Commentary Series: Leviticus (Nashville: Broadman & Holman Publishers, 2000), p. 126.
Radmacher, Allen, and House, eds., p. 160.
ጥያቄዎች
-
ዘሌ(6፡ 2) የሚለው አንድ ሰው ኃጢዓት ቢያደርግ ከእግዚአብሄር አንፃር ኃጢዓት እያደረገ ነው ፤ ለምንድን ነው ሁሉም ኃጢዓት ከእግዚአብሄር አንፃር የሆነው ?(መዝ 51፡ 4; ሉቃ 5፡ 21)
-
ከጎረቤት የሆነ ነገር ለሚሰርቅ ወይም ስለ ሚጥል ቅጣቱ ምንድን ነበር ? (ዘሌ 6፡ 4-6; ሉቃ 19፡ 8) ዛሬ አማኞች በዚህ ልክ ራሳቸውን ታዛዥ ቢያደርጉ ምን ይሆናል ?
-
ለጥፋተኛው አካል ካህኑ እንዴት አድርጎ ስርየት ያደርጋል (ዘሌ 6፡ 7) ? ኃጢዓት በሰራን ጊዜ እንደ አማኝ ምንድን እናደርጋለን ?(1ዮሐ 1፡ 9)
-
በመሰዊያው ላይ ያለው ሳያቐርጥ የሚነደደው ለምን ነበር ? (ዘሌ 6፡ 12-13)
-
የኃጢዓት መስዋዕት ክፍል ሊበላ የሚችለው መቼ ነበር ? መበላት የማይችለው መቼ ነበር ?
-
በዘሌ 6 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Leviticus 6:7
“In this way, the priest will make atonement on his behalf before the LORD, and he will be forgiven for anything he may have done to incur guilt.”
በእሳት መጠመቅ
ኦሪት ዘሌዋዉያን 6 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
ኃጥያት ከሰራችሁ በኋላ ያለዉን የበደለኝነት ስሜት ተለማምዳችሁ ታዉቃላችሁ? ቸል ብለን ለማለፍ ብንፈልግም ወይም ከእኛ እንዲርቅ ብንመኝም፥ የበደለኝቱ ስሜት ጊዜ እየወሰደ፥ እየከበደም ይመጣል። እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ ሲል ተናገረዉ፦ "ማናቸዉም ሰዉ ኃጥያትን ቢሰራ" በማለት ትዕዛዝን ሰጠዉ። እዚህ ጋ ማስተዋል ያለባችሁ ነገር እግዚአብሔር ያለዉ "ኃጥያትን ቢሰራ" ነዉንጂ ምናልባት የሚሰራ ከሆነ አይደለም። እግዚአብሔር ኃጥያትን እንደሚሰሩ አዉቋል። ስለዚህም እግዚአብሔር ለሙሴ የበደል መሥዋዕትን ትዕዛዝ ሰጠዉ። ይህም ህዝቡ ይቅርታን እንዲያገኝ እና በደልን ወደ ራሳቸዉ እንዳያመጡ ነዉ።
በተመሳሳይ መንገድ፥ ኢየሱስ የኃጥያትን ስርየት ለማድረግ መጥቷል። የበደለኝነት እና የሃፍረት ክብደትን ከምትሸከም ይልቅ፥ እግዚአብሔር ይቅር እንደተባልክ አዉቀህና በነፃነት መመላለስ እንደምትችል እንድትረዳ ይፈልጋል። ወደ እርሱ ተመለስ፥ ኃጥያትህን ተናዘዝ ከዚያም ይቅርታን ታገኛለህ። እግዚአብሔር ይወድሃል! ተሸክመህ ስትባክን የነበረዉን የበደለኘነት ስሜት አራግፈህ እንድትኖር ይፈልጋል። ዛሬ ከእርሱ ጋራ በግልፅ አዉራ! የፍቅሩ ወንዝ እንዲያጥብህ አድርግ!
"ካህኑም በእግዚአብሔር ፊት ያስተሰርይለታል፥ ስለዚያም ስላደረገው በደል ሁሉ ይቅር ይባላል።"
ኦሪት ዘሌዋዉያን 6:7
ተጨማሪ ጥቅሶች
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:17፦ "ጌታ ግን መንፈስ ነው፤ የጌታም መንፈስ ባለበት በዚያ አርነት አለ።"
2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:9-10፦ "በምንም ከእኛ የተነሣ እንዳትጎዱ እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ አዝናችኋልና። እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ የሆነ ኀዘን ጸጸት የሌለበትን፥ ወደ መዳንም የሚያደርሰውን ንስሐ ያደርጋልና፤ የዓለም ኀዘን ግን ሞትን ያመጣል።"
1ኛ የዮሐንስ መልዕክት 1:9፦ "በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 54
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።