The Pentateuch Leviticus

Sin Offering

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 4-5 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 53 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በዘሌዋውያን 4 ውስጥ እግዚአብሄር ሙሴን ተጨማሪ ትዕዛዞች ሲሰጠው እናያለን ፡፡ ሙሴ መቅደሱን ገንብታአል ስለዚህ አሁን እሱና እስራኤላውያን እንዴት እንደሚጠቀሙት ማወቅ ያስፈልጋቸዋል ፤ እግዚአብሄር እንዴት ከእርሱ ጋር እንደሚገናኙና ግንኙነት እንደሚኖራቸው ሙሴን መመሪያ እየሰጠው ነበር ፡፡ እግዚአብሄር የሚለው “ ለእኔ ተቀባይነት እንዲኖርህ የምፈቅድልህ ነገሮች አነዚህ ናቸው “ ፤ እስካሁን ያየናቸው፡

ዘሌዋውያን 1- የሚቃጠል መስዋዕት ; ዘሌዋውያን 2- የእህል መስዋዕት; ዘሌዋውያን 3- የህብረት/የደህንነት መስዋዕት ፡፡

በዘሌዋውያን 4 ውስጥ እግዚአብሄር በጣም በተለየ ያደርግ ጀመረ ፤ በኃጢዓት ምክንያት በተለየ ያደርገው ነበር ነበረ ፡፡ ሮከር የፃፈው “ ለኃጢዓት የኤችቲ ስር በብሉይ ኪዳን ውስጥ 595 ጊዜ ተፈጥሮአል ከዚህም ዘሌዋውያን ከሌሎቹ ብሉይ ኪዳን መፅሀፍ በ116 ቃሎች በላይ በመሆን(በመከሰት) ይበልጣል ፡፡” ዘሌዋውያን የኃጢዓትን ጉዳይ ለመድረስ(ለማሳየት) የሚሄድ ነው ፤ ዛሬ በዘሌ 4 እና 5 ውስጥ የኃጢዓትን መነሻ(መሰረታዊ) ቃሉን 53 ጊዜ እናያለን ፤ እግዚአብሄር ህዝቡን ከኃጢዓት በእውነት ይቅርማለት እንደቻለ ማስታዎስ አለብን ፤ ይህ ሁሉ መስዋዕት በሞት ውስጥ ስርየትን ስለ መቀበል ነው ፡፡ ዛሬ በእስራኤላዊያን ጊዜ ኃጢዓተኞች የነበሩ የሰዎችን ቡድን እንለያለን፡፡

ትምህርት

ዘሌዋውያን (4፡ 1-2); ያልታሰበ(ያልታወቀ) ኃጢዓት ምንድን ነው ? ኮንስታብል የፃፈው “ ይህ ክፍል (ያልታወቀ ኃጢዓት) የሚይዙት ኃጢዓት፡ በስህተት፣ በጉድለት ውስጥ፣ በግድፈት ውስጥ/ባለማዎቅ፣ ትኩረት ባለመስጠት ውስጥ፣ በቸልተኝነት፣ ወይም በግደየለሽነት የተፈፀመን ነው ፡፡”

ዋይሰርቤ የፃፈው “ እስራኤላዊያን የረከሱ ወይም ያልታዘዙ ሆኑ ይህንም አላወቁም ፤ ይሁን እንጂ አለማዎቅ ጥፋተኝነትን አያጠፋም ፡፡” ምንም እንካን ኃጢዓት ሳይታሰብ ቢሆንም አሁንም ጥፋተኞች ናችሁ ፤ መዝ 19፡ 12 “ ስህተትን ማን ያስተውላል ? ከተሰወረ ኃጢዓት አንጻኝ ፡፡” የኔልሰን ሀተታ የሚለው “ ምናልባት ለባሹ ልብሱን አፈር እንደነካው (እንዳለው) ሳያውቅ እንደሚለብሰው ኃጢዓት አድራጊው ሳያውቀው የሆነ ኃጢዓት አሁንም የእግዚአብሄርን ቅዱስነት ያስከፋልም በምድር የሚገለጥበትንም ቦታ ይበክላል ፤ እንደገና መጠቀም ይሆናል ሁለቱም መልበስና መቅደሱ መንፃት ይፈልጋሉ ፡፡”

ዘሌዋውያን(4፡ 3-4); የተቀቡት ካህናት በእስራኤላዉያን ሸክም ውስጥ ነበሩ ስለዚህ አንድኛቸው ኃጢዓተኛ ቢሆኑ በሁሉም ላይ ጥፋተኝነት ያመጣ ነበር ፤ የኃጢዓት መስዋዕት ማቅረብ ያስፈልገዋል ፤ ካህኑ እጁን በራሱ ላይ በማስቀመጥ በሬውን ያርደው ነበር ፡፡

ዘሌዋውያን(4፡ 5- 7); ካህኑ ወደ መገናኛው ድንካን ደሙን ያመጣው ነበር ፤ ደም የትኛውም ቦታ በዘሌዋውያን ውስጥ አለ(ዘሌ 3፡2; 4፡ 5) ፡፡ ስርየት ለመቀበል ሞት ያስፈልጋል ይህም ሁል ጊዜ ደም መፍሰስን ይጠይቃል ( ዘጸ 12፡ 13; ኢሳ 1፡ 11; ዘፍ 25፡ 30; ዘሌ 17፡ 11; ዕብ 9፡ 22; ሮሜ 5፡ 9; እና 1ቆሮ 11፡ 25) ፡፡

ካህኑ ጣቱን በደሙ ውስጥ በጥልቅ ያስገባል ከዚያም ሰባት ጊዜ ይረጨው ነበር ፤ይህ ደም ከበሬው ነበር (ቁጥር 5)፡፡ ካህኑ ይህን በመሸፈኛው ፊት ያደርጋል ፤ ከዚያም ካህኑ ጥሩ ሽታ ያለው ዕጣን በመሰዊያው ላይ ጥቂት ደም ያስቀምጣል ፤ በመጨረሻም ካህኑ የቀረውን ደም የሚቃጠል መስዋዕት መሰዊያዉ በታች ያፈስሰው ነበር ፡፡ ጥሩ ሽታ ያለው ዕጣን መሰዊያው የተለመደ የደም አይደለም ነገር ግን አስፈላጊ ነበር ምክንያቱም ይህ የካህናቱ ኃጢዓት ነበር ፡፡ ሌለኛው ብቸኛ ጊዜ በጥሩ ሽታ ዕጣን መሰዊያው ላይ ደም የሚረጨው የስርየት ቀን ነበር (ዕብ 9፡ 4) ፡፡

ዘሌዋውያን(4፡ 8-10); መስዋዕት አቅራቢው ስቡን ያስወግድ ነበር ፤ ይህ ለህብረት ወይም ለደህንነት መስዋዕት ንፅፅር ነው ፡፡

ዘሌዋዉያን(4፡ 11-12); የቀረው የበሬው አካል ከመኖሪያ ዉጪ መጣል(መወሰድ) ያስፈልገዋል ፤ ዕብ (13፡ 11-15) “ ሊቀ ካህናቱ ስለ ኃጢዓት ወደ ቅድስት የእንስሶችን ደም ያቀርባልና ፤ ስጋቸው ግን ከሰፈሩ ዉጭ መከራን ተቀበለ ፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ደግሞ በገዛ ደሙ ሕዝቡን እንዲቀድስ ከበር ውጭ መከራን ተቀበለ ፡፡ እንግዲህ ነቀፌታውን እየተሸከምን ወደ እርሱ ወደ ሰፈሩ ውጭ እንውጣ ፤ በዚህ የምትኖር ከተማ የለችንምና ነገር ግን ትመጣ ዘንድ ያላትን እንፈልጋለን ፡፡ እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሄር የምስጋና መስዋዕት ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ በእርሱ እናቅርብለት ፡፡” ኢየሱስ ከመኖሪያ ዉጪ ተሰቃየ በዚህም በደሙ እኛን መቀደስ ቻለ ፤ ኢየሱስ የትም ቦታ በመፅሀፍ ውስጥ አለ ፤ ሁሉም ወደሱ ያመለክታሉ ፤ የመፅሀፍ ፃሀፊዎች በመንፈስ ቅዱስ በኩል ይህን በአንድ አስተሳስረዋል ፡፡

ዘሌዋውያን(4፡ 13-21); ሙሉ ማህበረሰቡ ስህተት ቢሰሩና ማንም ባያውቅ በዚህም ወይፈን እንደ መስዋዕት ለማቅረብ ይሰበሰባሉ ፤ ወይፈን ያቀርቡና ካህናቱ ባደረጉት ሂደት ውስጥ ይሄዱ ነበር ፡፡

ሽማግሌዎቹ እጆቻቸዉን በበሬው ላይ እጃቸውን በማስቀመጥ ሁሉንም ጉባኤ ይወክላሉ ፤ ደሙን ጥቂጡን በቀንዶቹ ላይ እና የቀረውን በመሰዊያው ላይ ይረጨታል ፤ በመቀጠልም ስቡን በማስወገድና የቀረውን ከመኖሪያቸው ውጪ ያቃጥሉታል ፤ እንደ ካህናቱ የኃጢዓት መስዋዕት ተመሳሳይ ሂደትን ተከተሉ ፡፡ የአይሁድ ባህል በዚህ ታሪካ የሚለው ስብሰባው የመጨረሻ የፍርድ ስብሰባ ነበር ፤ ማህበረሰቡ ሀያማኖታዊ መሪዎችን ይከተላል ፡፡ በዚህ ማህበረሰብ ውስጥ ለዚህ እንደ ካህናቱ ተመሳሳይ ደረጃ የሆነ መስዋዕት ያስፈልጋል መጠነኛ የሆነ ስልጣንም ነበር ፡፡

ዘሌዋውያን(4፡ 22-26); እዚህ ጋር እንዴት እስራኤላዊያን ከመሪያቸው ኃጢዓቶች ጋር ያወሱ(መፍትሄ ያደርጉ) እንደነበር እናያለን ፤ አስታውሱ እነዚህ ሁሉ ድንገት ሳይታሰብ ከሚደረጉ ኃጢዓቶች አንፃር ነው ፡፡ አሁንና ወደፊት ከዚህ ቦኃላ በዕጣኑ መሰዊያ ዙሪያ የፈሰሰ ደም አናይም ፤ አሁን በሚቃጠል መስዋዕት መሰዊያው ዙሪያ ፈስሳአል ፡፡

ዘሌዋውያን(4፡ 27-30); የአገሩ ሰው በሪ ወይም ካህን ያልሆነ ማንኛውም ሰው ነበር ፡፡ ሴት ወይም ወንድ ፍየሎች ተቀባይነት ነበራቸው ፤ ለምን በዚህ ጊዜ ሴት ፍየል ተቀባይነት ነበረው ? ምናልባት የአገሩ ሰዎች ለመምረጥ ብዙ ኃብት አይኖራቸው ይሆን ?

ዘሌዋውያን(4፡ 31); ይህ ሁሉ ለመሆን ቀጠለ በዚህም ካህኑ ስርየትን ማድረግ ይችላል ከዚያም ሰዎቹ ይቅር ያባላሉ ፡፡ ይቅርታ እንዴት ይሆናል ? ሁል ጊዜ በደም በኩል ነው ፤ ካህንም ሁኑ፣ የማህበረሰቡ አካልም ሁኑ፣ መሪ ወይም የአገሩ ሰዉ ሁኑ ሁሉም ምህረት ሊደረግለት የሚችለው በኃጢዓት መስዋዕት ነበር ፡፡

ዘሌዋውያን(5); የጥፋትኝነት መስዋዕት ፤ ይህ ሁሉ እኛን ነፃ ወዳደረገን አስተሰሪያችን ክርስቶስ ያመለክታሉ ፡፡

መዝጊያ

ዕብ(10፡ 19-22) “ እንግዲህ ወንድሞች ሆይ በመረቀልን በአድስና በህያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በስጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን በእግዚአብሄርም ቤት ላይ የሆነ ታላቅ ሊቀ ካህን ስላለን ከክፉ ህሊና ለመንፃት ልባችንን ተረጭተን ሰውነታችንንም በጥሩ ውኃ ታጥበን በተረዳንበት እምነት በቅን ልብ እንቅረብ ፡፡”

በክርስቶስ በኩል ወደ እግዚአብሄር ለመቅረብ አንድ አድስ መንገድ አለን ! በክርስቶስ ደም ምክንያት ይቅር(ምህረት ተደርጎልናል) ተብለናል ፤ ክርስቶስ ለኛ ባደረገው ምክንያት ልባችን ተረጭቶአል ሰውነታችንም በንፁኅ ዉኃ ታጥቦአል፡፡

  1. Mark F. Rooker, The New American Commentary: Leviticus (Nashville: Broadman & Holman Publishers, 2000), p.106.

  2. Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes; available at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/leviticus.pdf, p. 47

  3. Warren W. Wiersbe, The Exposition Bible Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2007), p. 203.

  4. Earl D. Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson), p.156

ጥያቄዎች

  1. በዘሌ (4፡ 5-6) ላይ የኃጢዓት መስዋዕት ደሙን በመቅደሱ ውስጥ በመውሰድ በመጋረጃው ፊት ይረጫል፤ ይህ ለምን እንደተደረገ የእናንተ ሀሳብ ምንድን ነው ? የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ፡ 1ጴጥ (1፡ 2) እና ዕብ(10፡ 22) ፤ እነዚህን ጥቅሶች ከዘሌዋውያን ጋር በማገናኘት እንዴት ትገልፁአቸዋላችሁ ?
  2. የኃጢዓት መስዋዕት አካሉ ከመኖሪያ ውጭ በመወሰድ በእሳት ይቃጠል ነበር (ዘሌ 4፡ 11-12) ፤ ዕብ(13፡ 11-13) አንብቡ ፤ እነዚህ ጥቅሶች እንዴት ለሆነ ትልቅ ነገር ያጣቅሳሉ(መነሻ ይሆናሉ) ? ቁጥር 13 ምን ማለት እንደሆነ ምን ታስባላችሁ ?
  3. የኃጢዓት መስዋዕት ጥቂት አካሎችን በተለይም ኩላሊቶቹ እና ጉበቱ ከስቡ ጋር በማስወገድ ለእግዚአብሄር በመሰዊያውላ ይላ ይሰዋሉ (ዘሌ 4፡ 8-10) ፤ የእነዚህ ክፍሎችና ስቡ በሰዉነት ውስጥ አገልግሎታቸው ምንድን ነው ? እነዚህ አካሎች በመሰዊያው ላይ የተሰውበት አላማ ይታያችኃል ?
  4. እግዚአብሄር ለመስዋዕት እንስሳት ማቅረብ ለሚችሉት ብቻ ሳይሆን ለድሀዎቹም ስርየትን እንዲያገኙ አደረገ (ዘሌ 5፡ 7፣ 11) ፤ ኃጢዓታቸዉን ያዉቁ ለነበሩት ሰዎች ሁሉ አንዴ እግዚአብሄር ስርየትን እንዲገኝ ፈለገ ይህ ሆኖአል ? ዛሬ ለሰዎች ሁሉ ይህ እዉነት ነው ብላችሁ ታምናላችሁ ?
  5. ስለ መስዋዕት ስለ አሰዋው ዘዴ(ሁኔታ) ከመማር ውጭ የአዲስ ኪዳን ማጣቀሻዎችን በሙሉ መረዳት አይቻልም ፤ የዘሌዋውያንን የመጀመሪያዎቹን ጥቂት ምዕራፎች በማጥናት ምንድን አድስ ማስተዋል ተማራችሁ ?
  6. በዘሌ(4-5) ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልት አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Leviticus 5:10

“He must prepare the second bird as a burnt offering according to the regulation. In this way the priest will make atonement on his behalf for the sin he has committed, and he will be forgiven.”

ኦሪት ዘሌዋዉያን 4-5 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

በዛሬዉ ንባብ፦ "ማናቸውም ሰው ሳያውቅ ኃጢአት ቢሠራ፥ ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።" የሚለዉ ሃረግ ተደጋግሞ ተጠቅሷል። ይህ ምን ማለት እንደሆነ ልንረዳዉ ይገባል። ስርየት ማለት እርቅ ማለት ነዉ! እግዚአብሔር አምላክ፥ ኃጥያት ቢኖርም እንኳን የሰዉ ዘር ወደ እርሱ ተመልሶ ፍቅር የሰፈነበት፣ ሰላማዊ ግንኙነት ያለብት ህብረት እንዲኖረዉ መንገድን ያዘጋጃል። እግዚአብሔር ስለሚወዳችሁ ከእናንተ ጋራ መታረቅን ይፈልጋል።

በብሉይ ኪዳን ሊቀ-ካህናት፥ በኃጥያት ምክንያት ለራሳቸዉ እና ለህዝቡ የኃጥያት ስርየት መስዋዕትን ያቀርቡ ነበር። በአዲስ ኪዳን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ለአንተ እና ለብዙዎች ህይወቱን ቤዛ አድርጎ ሰጥቷል። ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝህ አድረገህ ካመንክ፥ ኃጥያትህ ይቅር ተብሎልሃል። ዛሬ፥ በዚህ የተስፋ ቃል እረፍ። የእግዚአብሔር ልጅ ስለሆንክ ይቅር ተብለሃል። ከእግዚዓብሔር ጋራ ስለመታረቅ ነፃ ስጦታ እርሱን አመስግን!

"እንደ ሥርዓቱም ሁለተኛውን ለሚቃጠል መሥዋዕት ያዘጋጀዋል። ካህኑም ስለ ሠራው ኃጢአት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።"

ኦሪት ዘሌዋዉያን 5:10

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የማርቆስ ወንጌል 10:45፦ "እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።"

ወደ ሮሜ ሰዎች 5:11፦ "ይህም ብቻ አይደለም፥ ነገር ግን አሁን መታረቁን ባገኘንበት በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በእግዚአብሔር ደግሞ እንመካለን።"

ወደ ዕብራዉያን 7:27፦ "እርሱም እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ሊያቀርብ አያስፈልገውም፤ ራሱን ባቀረበ ጊዜ ይህን አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎአልና።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 53