The Pentateuch Leviticus

The Burnt Offering

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Atonement Leviticus 1-3 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 52 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ የእኛ አላማ ወደ መሲሁ የሚያመለክት አንድ ቃል በእያንዳንዱ መፅሀፍት ውስጥ መለየት ነው ፡፡ ለዘፍጥረት የኛ ቃል ዘር ነው(ዘፍ 3፡ 15) ፤ ለዘጸዓት የእኛ ቃል ነፃ አዉጪ ነው (ይሁ 5) ፡፡ አህን ዘሌዋውያን ላይ ነን ፤ ዘሌዋውያን ማለት “ የተጠራው” ወይም “የተባለው” ማለት ነው ፡፡

በዘሌዋውያን መፅሀፍ ውስጥ የእኛ ቃል ለኢየሱስ አስተሰሪይ ነው ፤ ሁሉም አሮጌው ኪዳን ወደ መሲሁ የሹዋ ያመለክታሉ ፡፡ ዘሌዋውያን ከሌዋዊያ - ካህናት ጋር ይገናኛል እና የሙሴያዊ ኪዳን መስፈርቶችን የያዘ ነው ፡፡ ጎርደንዌንሁም የፃፈው “ ዘሌዋውያን ለካህናት እንደ መመሪያ የሚገለፅ ከሆነ ስህተት ይሆናል ፤ በእኩል የሚያይ ነው ሌዋዊያን በድርሻቸው በአምልኮ ይጫወታሉ” ፤ ይህ ለሁሉም ሰው ነው ፡፡

እስራኤላዊያን በምድረበዳ መቅደስ ነበራቸው ከዚያም እግዚአብሄር ብዙ ህጎች እንደሚሰጣቸው ተናገረ ልክ; መቼ ወደ መቅደስ እንደሚሄዱ ? ምን እንደ ሚያመጡ ? ካህናቱ ምንድን ማድረግ እንደሚያስፈልጋቸው ? እንዴት መልበስ እንዳለባቸው ? በዚህ መፅሀፍ ውሰጥ በጥቂት ምዕራፎች ብቻ ለሌዋዊያን ቀጥታ ተስጥታአል ፡፡ ቀሪዋቹ ሁሉንም ሰዎች እንዴት ወደ እግዚአብሄር መገኘት ሚያቀርቡ ትዕዛዞችን የተመለኩቱ ነበሩ ፡፡ ማርክ ኤፍ. ሮከር የፃፈው “ ይህ የአይሁድን ልጆች ሚያስተምሩበት አንዱ መፅሀፍ ነው ፡፡“

ሳልሀመር የሚለው አንዱ የዘሌዋውያን ዋና ጭብጡ ቅዱስነት ነው ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን የለያቸው እንደ; 1) የተለየ ርስት; 2) የንጉስ ካህናት; እና 3) ቅዱስ ህዝብ (ዘፀ 19፡ 5-6) ፤ በዘሌዋውያን ውስጥ እግዚአብሄር ይህ እንዴት እንደሚሆን መመሪያ ሰጣቸው ፡፡ እስራኤላዊያን በበርሃ ውስጥ ነበሩ በዚህም እንዴት ከመቅደሱ ጋር እንደሚገናኙ አያውቁም ፤ መመሪያ ያስፈልጋቸዋል ፡፡

ትምህርት

ዘሌዋውያን (1፡ 1-2); የሙሴ አድማጮች እስራኤላዊያን ነበሩ ፡፡ ኔልሰን እንደ ፃፈው “ መስዋዕት” ማለት “ ለእግዚአብሄር የሚቀርበውን ማምጣት(ማቅረብ) ነው” ፤ አስታውሱ እስራኤላዊያን እንዴት ወደ እግዚአብሄር እንደሚቀርቡ አያውቁም ፤እግዚአብሄር እንዴት ወደ ዙፋኑ እንደሚቀርቡ እጣስተማራቸው ነበር ፡፡ እስራኤላዊያን እዚያ ቦታ ላይ መንጋዎችና እንሰሶች ነበሩአቸው ፡፡

ዘሌዋውያን (1፡ 3); ኖህ በመሰዊያዉ ላይ የሚቃጠል መስዋዕት አቀረበ (ዘፍ 8፡ 20) ፤ አብርሃም ለሚቃጠል መስዋዕት ያቀረበው ልጁን ይስሐቅን ነበር (22፡ 1) ፤ የሙሴ የህግ አባት ዮቶር ለእግዚአብሄር የሚቃጠል መስዋዕት አመጣ (ዘጸ18፡ 11-12) ፤ መቅደስ በቦታው ባይኖራቸውም የሚቃጠል መስዋዕት የሚለው ሀሳብ ለእነሱ እንግዳ አልነበረም ፡፡ መስፈርቱ ከመንጎቹ ወይም ከእንሰሶቹ እንከን የሌለበት ወንድ ነበር ፡፡ በብዙ ጊዜ ትምህርት ይህ ሸክም ይሆን ነበር ፤ በመጨረሻም 613 የሚሆኑ ህግና ደንቦች ይሰጡዓቸዋል ፡፡

ዘሌዋውያን(1፡ 3-9); ለሚቃጠል መስዋዕት ሂደቱ ፡፡

  1. መስዋዕቱን ማቅረብ (ቁጥር 3)
  2. በእንሰሳው እራስ ላይ እጆችን ማድረግ (ቁጥር 4)

መስዋዕቱን ማረድ (ቁጥር 5) ፤ መስዋዕት አቅራቢው እዚህ ጋር ገደላ ያደርጋል(ያርዳል) ካህኑ አይደለም ስለዚህ ካህኑ ይቆጣጠራል ፡፡

ደሙ ይሰበሰባል ከዚያም በመሰዊያው ላይ ይረጫል (ቁጥር 5) ፤ ካህናቱ ይህን ያደርጋሉ ፤ ይህ ሁሉ ስለ ደሙ ነው ምክንያቱም ከደሙ ውጪ ስርየት የለም ፡፡

መስዋዕት አቅራቢው የሚቃጠል መስዋዕቱን ይገፋልም ወደ ትናንሽ ይቆራርጣል (ቁጥር 6) ፤ የእግዚአብሄርን መገኘት ለመቅመስ (ለመለማመድ) ከመስዋዕቱ ጋር ያለው ስራውን ይሰራል ፡፡

ካህናቱ እሳት ያዘጋጃሉ (ቁጥር 7) ፡፡

ከዚያም የመስዋዕቱን ቁርጥራጮች እሳቱ ላይ ይደረድሩታል (ቁጥር 8)

መስዋዕት አቅራቢው ሌሎቹን አካሎቹን በውሃ ያጥባል (ቁጥር 9) ፤ ህዝቡ የሚያተኩሩበት አቅጣጫ ያስፈልጋቸዋል ፡፡

ከዚያም ካህናቱ ሁሉንም ያቃጥሉታል (ቁጥር 9) ፤ መንፃት በእሳት ነበር ፤ ይህ እስራኤላዊያን በመገኘቱ ውስጥ እግዚአብሄር ለመቅረብ የሚያደርጉት ነበር ፡፡

ዘሌዋውያን(1፡ 10); ለበግ ወይም ለፍየል መስዋዕት ለበሬ መስዋዕት የተጠቀሙበትን ተመሳሳይ ሂደት (ከላይ ተመልከቱ) ይጠቀሙ ነበር ፡፡ እግዚአብሄርን መውደድ እና ጎረቤታችሁን(ባልንጀራችሁን) መውደድ ከሁሉም መስዋዕትና ከሌላ መስዋዕት ይልቅ በጣም ጠቃሚ ነው(የተሸለ ነው) ማር (12፡ 33) ፤ ነገር ግን እነዚህ ሁሉ ነገሮች ፍፁም ወደ ሆነው አስተሰርይ ክርስቶስ ያመለክታሉ ፡፡

ለሁሉም ዘሌዋውያን ያለው አንድ ቃል አስተሰርይ ነው ፡፡ አስተሰርይ በሚለው ቃል ላይ ፈጣን የሆነ ገላጭ ሀሳብ ልሰጣችሁ እፈልጋለሁ፡

እስራኤላዊው እጁን በእንሰሳዉ ራስ ላይ ሲያስቀምጥ ተቀባይነት ማግኘት ይችላል “ ያስተሰረይለትም ዘንድ የሰመረ ይሆንለታል “ (ዘሌ 1፡4) ፡፡

አስተሰረይ ማለት “ የሚሸፍን” ማለት ነው ፡፡

ኮንስታብል ሰዎስት “የአስተሰረይ” ትርጎሞችን ያብራራል

ተቀያሪ- እንስሳው በመስዋዕት አቀራቢው ቦታ ያገለግል ነበር ፤ ለመስዋዕት አቅራቢው ፍፁም የሆነው የእንስሳው ደም ያስተሰረያል ፡፡

ማስተላለፍ(ማመካኘት)-(መስዋዕት አቅራቢው እጆቹን በእንስሳው ራስ ላይ ባደረገ ጊዜ) እግዚአብሄር የእስራኤላዊያንን ጥፋት በማስተላለፍ በእንስሳው ላይ አስቀመጠው ፡፡

ሞት - ስርየትን ለመስራት ይህ ያስፈልግ ነበር ፤ ደም ማፍሰስ ስርየት አመጣ ፡፡

ለእግዚአብሄር ተቀባይ ለመሆን በዚህ ጠቅላላ ሂደት ውስጥ ያልፉ(ይሄዱ) ነበር ፡፡

ዘሌዋውያን 2; የምግብ/የእህል መስዋዕት ፡፡

ዘሌዋውያን 3; የህብረት/የደህንነት መስዋዕት ፡፡

መዝጊያ

ዘሌዋውያን ያለማቐረጥ ወደ አስተሰሪያችን ክርስቶስ ያመለክታል ፡፡

  1. Gordon J. Wenham, The Book of Leviticus (Grand Rapids, MI: Wm. B. Eerdmans, 1979), p. 3.

  2. See the discussion and critique of the Documentary Hypothesis in Mark F. Rooker, Leviticus, pp. 23–38.

  3. John H. Sailhamer, The Pentateuch as Narrative (Grand Rapids, MI: Zondervan), p. 323

  4. Earl D. Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson), p.153.

  5. Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Expository (Bible Study) Notes; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/leviticus.pdf, p. 13.

ጥያቄዎች

  1. ሰው የሚቃጠል መስዋዕት በማምጣት እጆቹን በእንስሳው ራስ ላይ ያኖረዋል በዚህም ጥፋቱን ወደ እንስሳው ያስተላልፋል ፤ እንደ ዘሌ (1፡ 4) የዚህ አላማ ምንድን ነበር ? በኢሳ(53፡ 12) ይህን እውነት ማየት ትችላላችሁ ?
  2. “ ደስ የሚል ሽታ(መዓዛ) በእሳት መስዋዕት ለእግዚአብሄር ያቀርበዋል ” በዘሌ(1-3) የተደገመ ነው (ዘሌ 1፡9፣ 13፣ 17፣ ወዘተ) ፤ በኤፌ(5፡ 2) ተመሳሳይ ሀረግ ይገኛል ፡፡ ግንኙነቱ ይታያችኃል ? አዎ ከሆነ ምንድን ነው ?
  3. እግዚአብሄር በዘሌ (2፡ 13) ላይ በሙሴ በኩል ህዝቡን የእህል መስዋዕቱ በጨው የጣፈጠ መሆን እንዳለበት አዘዛቸው በእውነቱ ሁሉም መስዋዕት ከጫው ጋር ይቀርብ ነበር ፤ ማር (9፡ 49-50) እንዴት ከዚህ ያቀራረብ ዘዴ ጋር ይገናኛል ?
  4. እንዴት አስተሰሪይን ትገልፁታላችሁ ? በከይሌ ትምህርት የማስተሰሪያው መስዋዕት በሚካሄድበት ጊዜ ስለ ሰዎስት ነገሮች ያወራል ፤ ጥቀሱዓቸውም ግለፁኣቸውም ፡፡
  5. በዘሌ(1-3) ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Leviticus 1:1-2, 3b

“Then the LORD summoned Moses and spoke to him from the tent of meeting: ‘Speak to the Israelites and tell them: When any of you brings an offering to the LORD from the livestock, you may bring your offering from the herd or the flock....He must bring it to the entrance to the tent of meeting so that he may be accepted by the LORD.’”

ኦሪት ዘሌዋዉያን 1-3

የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

ኦሪት ዘፀዓት እንደ መገናኛዉ ድንኳን የመምርያ ንድፍ ሃሳብ ሲሆን ኦሪት ዘለዋዉያን ደግሞ የመምሪያዉ ንድፈ ሃሳብ ነዉ። የህጉ የማጣቀሻ መፅሃፍ ነዉ። መፅሃፉም ስለ ሚቃጠል መሥዋዕት፣ የእህል ቁርባን፣ የደህንነት ወይም የማህበር መሥዋዕትን ምንነት በማብራራት ይጀምራል። ህዝቡም፥ እጅግ ዉድ የሆነ ንብረቱን እና እንስሳቱን ወደ መሰዊያዉ ስፋራ እያመጣ ለእግዚአብሔር ይሰዋ ነበር። መሥዋዕቶቹም ለእግዚአሔር፥ ደስ የሚል የመዓዛ ሽታ ሲሆኑ ህዝቡም በእርሱ ዘንድ ተቀባይነትን እንዲያገኙ አስችሏቸዋል። በመሰዊያዉ ስፋራ ላይ ያላቸዉን ለመሰዋት ይህ ብቻዉን በቂ ነበረ።

እንዲሁም ክርስቶስን ለመከተል ያላቸዉን ሁሉ የሚጥሉ ደቀ-መዛሙርት ይህንን መስዋዕት ይካፈላሉ። እግዚአብሔርንም ደስ የሚያሰኝ ነዉ። እግዚአብሔርን በምታመልኩበት ጊዜ፥ ራሳችሁን ህያዉ መስዋዕት አድርጋችሁ እንድታቀርቡ ተጠርታችኋል። ምንም ነገር ማስቀረት የለባችሁም! እርሱን ለማምለክ መስዋዕት ማድረግ የሚገባችሁ፥ ነገር ግን እርሱን ላለማድረግ ወደኃላ ይዛችሁ ያስቀራችሁት አንዳች ነገር ይኖር ይሆንን? አስታዉሱ፥ በፊቱ በምትጥሉበት ጊዜ እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል።

"እግዚአብሔርም ከመገናኛው ድንኳን ውስጥ ሙሴን ጠርቶ እንዲህ ሲል ተናገረው፦ ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራችው፦ ከእናንተ ማናቸውም ሰው ለእግዚአብሔር መባ ሲያቀርብ መባችሁን ከእንስሳ ወገን ከላሞች ወይም ከበጎች ታቀርባላችሁ። መባውም የሚቃጠል መሥዋዕት ከላሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌለበትን ተባቱን ያቀርባል፤ በእግዚአብሔር ፊት እንዲሠምር በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ፊት ያቀርበዋል።"

ኦሪት ዘሌዋዉያን 1:1-2፣ 3

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የማርቆስ ወንጌል 8:34፦ "ሕዝቡንም ከደቀ መዛሙርቱ ጋር ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ በኋላዬ ሊመጣ የሚወድ ቢኖር፥ ራሱን ይካድ መስቀሉንም ተሸክሞ ይከተለኝ።"

የዮሐንስ ወንጌል 12:3፦ "ማርያምም ዋጋው እጅግ የከበረ የጥሩ ናርዶስ ሽቱ ንጥር ወስዳ የኢየሱስን እግር ቀባች፤ በጠጕርዋም እግሩን አበሰች፤ ቤቱም ከናርዶስ ሽቱ ሞላ።"

ወደ ሮሜ ሰዎች 12:1፦ "እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 52