Setting Up the Tabernacle
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 40 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
የዘፍጥረትን መፅሀፍ አጥንተን ጨርሰናል አሁን ደግሞ የዘጸዓት መፅሀፍ እንጨርሳለን ፤ ትናትና ዘጸዓት 39 ሸፍነናል እስራኤላዊያን የካህናቱን ልብስ እንዲሰሩ ተነገሩ ፡፡ አሁን በመጨረሻ ሁሉንም የምናስቀምጥበት ጊዜ ነው ስለዚህ በቤተ አምልኮቱ ውስጥ የእግዚአብሄር መገኘት መኖር ይችላል ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት(40፡ 1-4); ይህ የነበረው ከወጡበት ከአንደ አመት ቦኃላ ነበር ፤ እግዚአብሄር ሙሴን ቤተ አምልኮቱን(መገናኛ ድንካን ማደሪያውን) እንዲተክል፣ ታቦቱን እንዲያመጣና ጠረንጴዛውን ከመብራቱ ጋር እንዲያመጣ ነገረው ፡፡ በዘጸ 40 ውስጥ ምንድነው የምትሰሙት ራሱን የድንካኑን ማደሪያ እንዴት እንዲሰራ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ነው ፡፡
ዘጸዓት(40፡ 5-8); ሙሴ እንከን የሌለበት አይምሮ ነበረው ፤ ሁሉንም በየቦታቸው አስቀመጣአቸው ፡፡ ሲናገር“እስካሁን አልተሰራም ግን ተዘጋጅታአል” ፤ መሴ በእግዚአብሄር ቅኝት ውስጥ ነበር በዚህም እነዚህ ነገሮች እንዴት በጋራ እንደሚገጥሙ ያውቃል ፡፡ ለሳህኑ የተለየ ውኃ የሆነ ነበር ? ለመሙላት መምጠጫ ሚመስል አልነበራቸው ፤ በበርሃ ነበሩ ስለዚህ ውሃ ወዳለበት ይጋአዙ ነበር ፡፡ ሁሉም እቃዎች ዝርዝር ነበራቸው ሙሴ ቤተ መቅደሱን እንዲሰሩ እንደነገራቸው በእምነት እንዲሄድ የጠየቁ ፡፡
ይህ ጠንካራ ስራ ነበር ፤ እኛ ያሉን መሳሪያዎች አልነበሩአቸውም ፤ እግዚአብሄር የነገራቸዉን እየሰሩት የነበረውን ህንፃ በእምነት ነበር የሚሰሩት ፡፡ አሁን ሙሴ ሁሉንም ነገር በአንድ አገጣጠመ ፤ ሁሉም ተጠናቆና ተገጣጥሞ አገኘው ከዚያም ቁጥር 9 ላይ እግዚአብሄር ምን እንደሚሰራ ነገረው ፡፡
ዘጸዓት(40፡ 9-13); ሙሴ ሁሉንም ቀባም ቀደሰም ስለዚህ ቅዱስ ይሆናል፡፡ አሮንና ልጆቹም ራሳቸውን በውሃ ታጠቡ ፤ እንደ ሌዋዊያን የካህናት ቤተሰብ ለማገልገል ራሳቸውን አዘጋጁ ፤ ሙሴ አሮንና አለበሰው፣ ቀባውማ ቀደሰው ፡፡ ሙሴ ያገለገለው እንደ ነብይ ሲሆን ወንዱሙ ያገለገለው እንደ ካህን ነበር ፡፡
ዘጸዓት(40፡ 14-15); ሙሴ የአሮንን ልጆችንም ቀባም አለበሰም ፤ ቅባታቸው ቐሚ የክህነት ቤተሰብ ቃል ኪዳን ነበር ፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ ባመናችሁ ጊዜ የሚኖርብን መንፈስ ቅዱስ ተሰጥቶአችኃል ፤ መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ውስጥ በመኖሩ ምክንያት ወዲያዉኑ ያቅባት አላችሁ (1ዮሐ 2፡ 20; 27) ፡፡ ቅባቱ በእናንተ ውስጥ ይቀራል(ይኖራል) ፤ በእርሱ ውስጥ ይቀራል(ይኖራል) ፤ በድፍረትና በስልጣን ፣ በጸጋና በትህትና ይጋአዛል(ትጋአዛላችሁ) ፡፡
በብሉይ ኪዳን ውስጥ አሮንና ካህናቱ ሁሉንም ነገር ቀቡ ስለዚህ የተለየ ይሆናል ፤ ነገር ግን አሁን የተቀባን ነን ከዚህ አለም የተለየን ፡፡ እግዚአብሄር መንፈስ እንደ ቀባችሁ ባወቃችሁ(በተገነዘባችሁ) ጊዜ ሰዎችን አታሳምኑም ፡፡
ዘጸዓት(40፡ 16-18); ሙሴ እግዚአብሄር እንዲሰሩ የጠየቃቸውን እንዲሰሩ ቀባቸው ፤ ሙሴ ሁሉንም ነገር እግዚአብሄር እንዳዘዘው አደረገ ፤ ሰባት ጊዜ ይህን ቐንቐ ትሰሙታላችሁ “ እግዚአብሄር እንደዘዘው” ፡፡ ቤተ መቅደሱ(የመገናኛ ድንካን ማደሪያው) ተሰራ ! ተገጣጠመም ተቀባም እናም ሁሉም ነገር በጋራ መጡ ፡፡ ሙሴ መቅደሱን ተከለ ፡፡
ዘጸዓት(40፡ 19-30); ሙሴ በመቅደሱ ውስጥ ድንካኑን ዘረጋ እና ታቦቱን(የምስክርነቱን የያዘውን)፣ የስርየት መቀመጫዉን፣ ጠረንጴዛውን(ገበታውን)፣ ህብስቱን እና መቅረዙን አመጣ ፡፡ ሁሉም ነገር በሲና ተራራ ላይ እንዲሰራ የነገረው ተፈጠረ(ሆነ) ፤ እያንዳንዱ ነገር ለምን እንደሚሰራና የት እንደሚቀመጥ በዝርዝር(በጥልቀት) ነበር ፡፡ እግዚአብሄር እያንዳናዱ ነገር የት እንደሚሆን ያውቃል-ይህ የሱ ቤት ነበር ፡፡ የወርቅ መሰዊያውን፣ የጣፋጭ ዕጣኑን፣ መጋረጃውን፣ መሰዊያውን እና ከውሃ ጋር ሳህኑን አመጡ(መገናኛ ድንካኑ ውስጥ አስገቡ) ፡፡ ሙሴ የሚያስደንቅ ርዳታ ነበረው !
ዘጸዓት(40፡ 31-34); ሙሴ፣ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ታጠቡ ፤ ሙሴ ስራ ጨረሰ (ቁጥር 33) ፡፡ በዘጸዓት መፅሀፍ ውስጥ ሙሴ እንደ ነፃ አዉጪ አገለገለ ኢየሱስ በዮሐንስ መፅሀፍ ውስጥ እናዳደረገው (ዮሐ 19፡ 28-30) ፡፡
በዘፍጥረት እግዚአብሄር የመፍጠርን ስራ ጨረሰ (ዘፍ 2፡ 2) ፤ በዘጸዓት ሙሴ የመቅደሱን ስራ ጨረሰ በዚህም እስራኤላዊያን የእግዚአብሄርን መገኘት መልመድ(ማየት) ቻሉ ፡፡በዮሐንስ ኢየሱስ ስራ ጨረሰ በዚህም እናንተና እኔ ወደ አባታችን መገኘት መምጣት ቻልን ፤ መሸፈኛው ተወገደ ስለዚህ አበቃ ፡፡ ዳመናው ድንካኑን ሸፈነው ከዚያም ክብር መቅደሱን ሞላው ፤ ኔልሰን የፃፈው “ መቅደሱን የሚሞላው የእግዚአብሄር ክብር የሚገልጠው(የሚያስረዳው) የእርሱ መገኘት ከእስራኤላዊያን ጋር መሆኑን፣ ለእነርሱ አስፈላጊነቱን እና የሚያስፈራ ድንቁን ፡፡”
ዘጸዓት(40፡ 35-38); የእርሱ መገኘት በጣም ወፍራም ስለነበር ሙሴ ሙሴ በውስጡ መሄድ አልቻለም ፡፡ የእግዚአብሄር ክብር መቅደሱን ሞላው - በሲና ተራራ በማዳመጥና በበርሃ በማዳመጥ በአንድ ሰው እምነትና መታዘዝ ምክንያት ሁሉም ሆነ ፡፡ ጠንቃቆች ልንሆን ይገባናል ምክንያቱም ኃጢዓታችን ከእግዚአብሄር ክብር ያወጣናል ፡፡ መቼም ቢሆን ደመናው ሲነሳ እስራኤላዊያን ይወጣሉ ፤ ጉዞአቸው ተጀመ ፤ ደመናው ሲነሳ እስራኤላዊያን ይከተላሉ (ዘጸ 13፡ 21-22; ዘኁ 9፡ 15-23) ፤ ደመናው ለሁሉም የእስራኤል ቤት ይታይ ነበር ፤ ሁሉም የእግዚአብሄርን መገኘት አዩ ፡፡
መዝጊያ
ይህ የዘጸዓት መጨረሻ ነው ፡፡ የእናንተ ሰውነት የመንፈስ ቅዱስ መቅደስ ነው ፤ በምትሄዱ ጊዜ የእግዚአብሄርን መገኘት ተሸክማችኃል የትም ብትሄዱ ፡፡
ፍሊፕ ራይከን የኢየሱስን ሚና በዘጸዓት ውስጥ ለመግለፅ አስር ነገሮችን ያቀርባል
- ኢየሱስ አዳኛችን ሙሴ ነው - ከፊታችን የሆደ አስታራቂያችን ነው ፡፡
- ኢየሱስ የፋሲካችን በግ ነው - ለኃጢዓታችን መስዋዕት ነው ፡፡
- ኢየሱስ ከግብፅ የወጣንበት መንገዳችን ነው - ነፃ አወጣንም በጸጋ ባህር አጠመቀንም ፡፡
- ኢየሱስ በብርሃ እንጀራችን ነው - በየቀኑ የሚያስፈላገንን ሰጥቶናል ፡፡
- ኢየሱስ ከተራራ የሆነ ድምፃችን ነው - ለኑሮአችን ህግን ይነግረናል ፡፡
- ኢየሱስ የሚቃጠል መሰዊያችን ነው - ለሱ ምስጋና እናቀርባለን ፡፡
- አየሱስ በመቅረዛችን መብራታችን ነው - የህይወታችንና የብርሃናችን ምንጭ ነው ፡፡
- ኢየሱስ የምንነፃበት ሰንናችን(ሳህናችን) ነው - የነፍሳችን ቀዳሽ(አንፂ) ነው ፡፡
- ኢየሱስ ታላቅ ሊቀ ካህናችን ነው - በዕጣን መሰዊያው ላይ ለእኛ ይፀልይልናል ፡፡
- ኢየሱስ በስርየት መቀመጫው ላይ ያለ ደም ነው - ከእግዚአብሄር ጋር ያስታረቀን ንስሀችን(መስዋዕታችን) ነው ፡፡
ህዝቡን ከግብፅ ያዳነ እና እኛን ያደነን ኢየሱስ ብቻ ነው ፡፡
Earl D. Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson, 1999),
Philip Graham Ryken, Exodus (ESV Edition): Saved for God’s Glory (Wheaton, IL: Crossway, 2015), p. 1103.
ጥያቄዎች
-
እግዚአብሄርን እንደ ካህን ለማገልገል ካህኑ የታጠበና የተቀባ መሆን ነበረበት (ዘጸ 40፡ 12; 13) ፤ ኢየሱስን የት ነው የምናየው “የታጠበ” እና “የተቀባ” ? (ማቴ 3፡ 13-17; ሉቃ 4፡18; ሐዋ 10፡ 38)
-
በዘጸ 40፡ 15 የአሮን ልጆችና በመጨረሻም ወደፊት ሁሉም ካህናቶች በእግዚአብሄር ፊት ለማገልገል መታጠብና መቀባት ነበረባቸው ፤ እኛም ካህናት ሆነን ተጠርተናል (1ጴጥ 2፡ 5; 9; ራዕ 1፡ 6) ፡፡ እግዚአብሄርን እንድናገለግል እንዴት ነው የታጠብነውና የተቀባነው ? (1ቆሮ6፡ 11; 2ቆሮ1፡ 21; ኤፌ 5፡26; ዕብ 10፡ 22; 1ዮሐ 2፡ 27; ራዕ 1፡ 5)
-
ሁሉም ነገር በመቅደሱ ውስጥ የሚጠቃሙት የተቀደሰና የተቀባ ነበር ከዚያም ቅዱስ ሆነ ፤ መቀደስ ማለት “ ለቅዱስ አላማ ማዋል፣ መለየትና ቅዱስ ማድረግ” ማለት ነው ፡፡ አሁን ቤተ መቅደስ ከሆንን (1ቆሮ 3፡ 16) እና የእግዚአብሄር መንፈስ በኛ ውስጥ የሚኖር ከሆነ እንዴት ተቀደስን ? (2ቆሮ 6፡ 16፣ 7፡ 1; ኤፌ 4፡ 20-24; ቆላ 3፡ 12-17)
-
በዘጸ (40፡ 34) ሙሴ የፃፈው የእግዚአብሄር ክብር መቅደሱን ሞላው ፤ በ2ዜና (7፡ 1) ሰለሞን አድስ የተሰራውን ቤተ መቅደስ ከሰጠ ቦኃላ እንደ ገና የእግዚአብሄር ክብር መቅደሱን ሞላው ይላል ፡፡ የእግዚአብሄር ቤተ መቅደስ ከሆንን የእኛ መሞላት ምንድን ይመስላል (ሐዋ 2፡ 1-4; 1ቆሮ 6፡ 19-20; ኤፌ 5፡ 18-20) ? ከዚያስ እንዴት ነው መኖር ያለብን ?
-
ዘጸ(40፡ 33) በምናነብ ጊዜ “ ሙሴ ስራውን ፈፀመ” የሚለው ሀረግ የሚያመለክተን ወደኃላ ዘፍ (2፡ 2) እግዚአብሄር “ ስራውን ጨረሰ ፈፀመ” ፡፡ የትም የሆነን ነገር አልቆአል ብሎ መናገር በጣም አስፈላጊ ነው(ዮሐ 19፡ 30) ? እንደዚህ ማጣቀሻ(በዚህ መነሻ መሰረት) መጨረስ ምንድን ነው ?(ለዘጸዓት የኛን ዋና አስታውሱ; ኢሳ 53፡ 4-12; ሮሜ 8፡ 1-4; 1ቆሮ 15፡ 55-57; 2ቆሮ 5፡ 17; ቆላ 2፡ 13-15)
-
በዘጸ 40 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 40:38
“For the cloud of the LORD was over the tabernacle by day, and there was a fire inside the cloud by night, visible to the entire house of Israel throughout all the stages of their journey.”
ኦሪት ዘፀዓት 40 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
ሙሴ፥ የማደርያዉ ድንኳንን ሥራ ከጨረሰ በኋላ በደመና አምሳል ተገልጦ እግዚዓብሔር በክብሩ ሞላዉ። እግዚዓብሔር በማደርያዉ ላይ፥ በቀን ደመናን እና በሌሊት ደግም እሳት በዉስጡ በማስቀመጥ፥ እርሱ ከህዝቡ ጋራ እንደሆነ እና በጉዟቸዉ ሁሉ እንደማይለያቸዉ ምልክት ሰጣቸዉ። እንደዚህ ምልክቶች፥ የሚታዩ የእግዚዓብሔር ህልዉና ማሳያዎች ሆነዉ አገልግለዋል። እግዚዓብሔር ከእነርሱ ጋራ ነበር! ክብሩም ከቧቸዋል!
አስታዉስ፥ በህይወት መንገድህ ሁሉ እግዚዓብሔር ከአንተ ጋራ ነዉ! ዓይኖችህን ከፍተህ በህይወትህ ዉስጥ ያለዉን እግዚዓብሔርን ተመልከት! እርሱነቱ የማይታወቅህ እና የማይሰማህ ከሆነ ራሱን ለአንተ እንዲገልጥልህ ፀልይ። እግዚዓብሔር የአንተ ነፃ አውጪ ነዉ!
"በመንገዳቸውም ሁሉ በእስራኤል ቤት ሁሉ ፊት የእግዚአብሔር ደመና በማደሪያው ላይ በቀን ነበረና፥ እሳትም በሌሊት በዚያ ላይ ነበረና።"
ኦሪት ዘፀዓት 40:38
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መፅሓፈ መሣፍንት 18:16፦ "እርሱም፦ የምትሄዱበት መንገድ በእግዚአብሔር ፊት ነውና በደኅና ሂዱ አላቸው።"
- መዝሙረ ዳዊት 25:4-5፦ "አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ። አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና በእውነትህ ምራኝ፥ አስተምረኝም፤ ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።"
- መዝሙረ ዳዊት 121:8፦ "ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘላለም እግዚአብሔር መውጣትህና መግባትህን ይጠብቃል።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 51
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።