The Pentateuch Exodus

Making the Priestly Garments

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 39 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 50 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዘጸዓት ለማቐረጥ እንዴት የእግዚአብሄርን መገኘት እንደምንለምድ(እንደምንቀምስ) እያሳየን ነው ፡፡ እስራኤላዊያንና ሙሴ ቤተ አምልኮቱን እንዲሰሩ ታዘው ነበር ፤ በዘጸ 37 እና 38 ላይ ህዝቡ የቤተ አምልኮቱን እያንዳንዱን አካል ሰሩ ፡፡ ዘጸ 39 ለካህናቱ ልብስ እንዲሰራ ትዕዛዝ ይሰጣል ፡፡

ትምህርት

ዘጸዓት(39፡ 1); ራይኮን ሲፅፍ “ ቨርን ፖይዘረስ ካህናቱን ” ከላይ ወደ ታች የሆነ የቤተ አምልኮቱ ምስያ” እንደሆነ ገልፆታል ፡፡“ ከቤተ አምልኮቱ ውጭ ያለው የሱፍ ክር የካህናቱን ልብስ የሱፍ ክር ይመስል ነበር ፡፡ አሮን ብዙ ስህተቶችን ቢሰራም እናም የወርቅ ጣዖት የሰሩት ልጆቹም ቢሆኑም አሁን ወደ እግዚአብሄር መገኘት ስራውን ለመምራት እየሄደ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ማንንም መጠቀም ይችላል ! እሱ የሚዋጅ አምላክ ነው ! እያንዳናዳችን ስህተት ሰርተናል ፡፡ አሮን በውሃ የእግዚአብሄርን ስራ ለመስራት የነፃ ለመሆን ታጠበ (ዘጸ 40፡ 12) ፤ አሮን በልብሱ ምክንያት ትንሹ ቤተ አምልኮት ነበር ፡፡ ስለዚህ የምታስቡ ከሆነ ሁላችንም አይደለንምን ?

ዘጸዓት(39፡ 2-5); ባስልኤል የተለያዩ የካህናት ልብሶችን አሰራሮች ይሰራ ነበር ፤ የመጀመሪያው ነገር የሰራው ኤፉድ ነበር ከዚያም በመቀጠል ትካሻ ላይ የሚቀመጠውን ስስ ጨርቅ ሰራ ፡፡ በመሰረቱ ካህን የሚያገለግለው እንደ አምባሳደር ነው ፤ እግዚአብሄር በግልፅ የሚጠይቀው በአሮንና በልጆቹ በኩል ነበር(2ቆሮ 5፡ 20) አሁን ደግሞ በእኛ በኩል ነው ! በክርስቶስ ስም በመለመን ለእግዚአብሄር አስታራቂ እንሆናለን ፡፡ ከዚያም ማሰሪያውም(መታጠቂያውም) ተሰራ “ልክ እግዚአብሄር እንዳዘዘው” ፤ የሚቆርጡት ጠርዝ(ጫፍ) አልነበረም ፤ እግዚአብሄር እንዲሰሩት የጠየቃቸውን አደረጉ ፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንድትሰሩት የነገራችሁን ስሩ የሚያስጠላ ወይም ትርጉም የማይሰጥ ቢሆንም እንካ ፡፡

ዘጸዓት(39፡ 6-21); የከበረው ድንጋይ በ12 ልጆች(12 ነገዶች) ተቀረፀ ፤ እግዚአብሄር ሲናገር “ እስራኤላዊያን ማን እንደሆኑ እንድታስታውስና በእኔ ፊት ይዘኃቸው እንደትቀርብ እፈልግሀለሁ ፡፡“ በመቀጠል የደረት ኪሱ በ12 ድንጋዮች ተሰራ ይህም በካህኑ ልብ ላይ ተቀመጠ ፡፡ ካህኑ የእግዚአብሄርን ህዝብ በእግዚአብሄር ዙፋን ፊት ይወስድ ነበር ፡፡

ዘጸዓት(39፡ 22-29); በመቀጠል ካባው በጠቅላላ በሰማያዊ ተሰራ ፤ ከዚያም ሸሚዝ፣ ጥምጣምና ሱሪ ሰሩ ፡፡

ዘጸዓት(39፡ 30-31); ሜዳሊያው ጥምጣሙ ላይ ለማድረግ ተሰራ ፤ ሁሉም ነገር “ ለእግዚአብሄር ቅዱስ” ነበር ፤ ሁሉም ነገር ለዓላማ ነበር ፡፡ዳዊት ሌቪይ ያመለከተው በሰዎስት ዋና ምክንያቶች እነዚህ ልብሶች ያስፈልጉናል; 1) ቅዱስነት- መለየት; 2) ክብር- የክህነትን አገልግሎት ከፍ ማድረግ(ለማወደስ); 3) ውበት- ቤተ አምልኮቱን ማንፀባረቅ ፤ እነዚህ ሁሉ እግዚአብሄርን ያንፀባርቃሉ ፡፡

አነዚህ ካህናት ፍፁም አልነበሩም ፤ ዘጸዓት 32 ተመልከቱ አሮን የወርቅ ጥጃ ሲሰራ(ሲነድፍ)(መዝ132፡ 9) ፡፡ አሮንና ሌዋዊያን ካህናቶች አሁንም እጥረት ይሰማቸዋል በእግዚአብሄር ፊት በቅዱስነት ለመምጣት ሁሉንም ሙከራቸውን በቅድስና ሊሆኑ የሚችሉበትን በመልበስ ሁሉንም ነገር አደረጉ ፡፡ በዘሌዋዊያን አሁንም ካህናቱ ኃጢዓተኞች ነበሩ ፤ ሁል ጊዜ ስለራሳቸው መስዋዕት ያደርጉ ነበር ፡፡ የተለየ ሊቀ ካህን ያስፈልገናል ፤ አሮን ሊቀ ካህን ነበር ነገር ግን ኢየሱስ ታላቅ ሊቀ ካህን ነው (ዕብ 4፡ 14; 10፡ 21) ፡፡

ለምን ኢየሱስ ከሊቀ ካህኑ አሮን የበለጠ ነው በሚለው ውስጥ እንድትሄዱ እፈልጋለሁ (ፍሊፕ ራይከን)

  • ኢየሱስ የሚያገለግለው በሚበልጥ ቦታ ውስጥ ነው ፤ ዕብ (8፡ 1-2) ፤ ኢየሱስ በእግዚአብሄር ቀኝ ነው በቤተ አምልኮቱ መሸፈኛ ውስጥ አይደለም ፤ የሚያገለግለው በእውነተኛው ቤተ አምልኮት ነው በሰማይ ፡፡
  • ኢየሱስ የሚያገለግለው በሚበልጥ ቅድስና ነው (ዕብ 7፡ 26-28) ፤ ቅዱስ፣ ንፁህና ኃጢዓት ያልነካው(ጉድለት ሌለበት) ነው ፤ በየቀኑ መስዋዕት ማቅረብ አያስፈልገውም ለሁሉም አንድ ጊዜ አድርጎታል ሁል ጊዜ ፍፅም ነው ፡፡
  • ኢየሱስ የሚያገለግለው በሚበልጥ ማፅናናት ነው (ዕብ 4፡ 15-16) ፤ ምክንያቱም ከእኛ ጋር መገናኘት ይችላል ከእርሱ ጋር መገናኘት እንችላለን ፤ በድፍረት እንቀርበዋለን ፡፡
  • ኢየሱስ የሚያገለግለው በሚበልጥ የጊዜ ርዝማኔ ነው (ዕብ 7፡ 23-24) ፤ እስከ ዘላለም የሚቀጥልና ካህናቱን በቐሚነት የያዘ ነው ፤ ስለዚህ ሁል ጊዜ ማዳን ይችላል ፡፡
  • ኢየሱስ የሚበልጥ መስዋዕት ነው (ዕብ 9፡ 12; 25-26) ፤ ያቀረበው ዘላለማዊ ቤዛነት አንዴ ለሁሉም !

በክህነት ልብሶቻቸው እንዴትም ወደ ኢየሱስ ቢያመለክቱም ሌዋዊያን ካህናቶች ሁል ጊዜ እጥረት ይሰማቸዋል ፤ ነገር ግን እስካሁን አኛን ወደ ክርስቶስ ያመለክተናል(1ጴጥ 2፡ 4-5; 9; ራዕ 1፡ 5-6) ፤ አነዚህ ሁሉም እኛን የእግዚአብሄርን መገኘት እንድንለማመደው ያመለክቱናል ፡፡ በቅዱሱ ቤተ አምልኮት በእግዚአብሄር ፊት የሚወክላቸው ያስፈልጋቸው ነበር ፡፡

ዘጸዓት(39፡ 32-33); ሁሉም ስራ አለቀ ! ልብሶቹም ተሰርተው አለቁ “ልክ እግዚአብሄር እንዳዘዘው”፤ አስታዉሉ ስራዉ በባስልኤል፣ በኤልያብ ወይም በሙሴ ብቻ አላለቀም ፤ የእግዚአብሄርን መገኘት ለመለማመድ ለሌሎች ቀላል የተደረገው የቡድን ጥረት ነበር ፡፡ ሁሉም ህዝብ አዚህ ተወክለዋል ፤ ለሙሴ ቤተ አምልኮት አምጥተዋል ፡፡

ዘጸዓት(39፡ 34-41); እስራኤላዊያን እግዚአብሄር እንዲሰሩአቸው ያዘዛቸውን እቃዎች መዘርዘር ጀመሩ ፤ ዮሐንስ ማክ አርቱር እንደ ፃፈው “ ሙሉ ለሙሉ የእሱ የህንፃ ጥበብና የእርሱ ፕላን በእንዳንዱ የስራ ደረጃ ነበር ” ፤ እነዚህ ነገሮች አብረው የመጡት ወደ ሚመጣው መሲህ ለማመልከት ፡፡

ዘጸዓት(39፡ 42-43); እስራኤላዊያን ሁሉንም ስራ ጨረሱ ፤ ምንም አቐራጭ አልወሰዱም ፤ ሙሴ ሁሉንም ተቆጣጠረ ፡፡ ሙሴ ህዝቡን ባረከ ይህ በዚህ መፅሀፍ ውስጥ የምናየው የመጀመሪያው ነው ፡፡

መዝጊያ

በዕብ(3፡ 1-6) ውስጥ በመፈለግና የሙሴን ስራ ከክርስቶስ ስራ በማነፃፀር ጥቂት ጊዜ አሳልፉ ፤ ሙሴ እንደ ነፃ አዉጪ በመጨረሻ እንደ ነፃ አዉጪ ወደ ኢየሱስ ያመለክታል ፡፡

  1. Philip Graham Ryken, Exodus (ESV Edition): Saved for God’s Glory (Wheaton, IL: Crossway, 2015), p. 1078.

  2. Ryken, p. 1076.

  3. David M. Levy, The Tabernacle: Shadows of the Messiah (Bellmawr, NJ: Friends of Israel Gospel Ministry, 1993), p. 160, quoted at Ryken, p. 1076.

  4. Ryken, p. 1080-1081.

  5. John F. McArthur, Exodus and Numbers: The Exodus from Egypt (Nashville, TN: Nelson Books, 2008), p. 77.

ጥያቄዎች

  1. የአሮን የክህነት ልብሶች ገለፃ በዘጸ 39 ከማቴሪያልና ከቀለም አንፃር ከመቅደሱ ገለፃ ጋር ብዙ እንደሚመሳሰል ይናገራል ፤ እግዚአብሄር ሙሴን ትዕዛዝ በሰጠው ጊዜ ይህ በሃሳቡ ውስጥ እንዳለ ታስባላችሁ ? ለምን ወይስ ለምን አላሰባችሁም ?
  2. በዘጸ 39 ሁሉም ነገር ሙሴን እግዚአብሄር እንዳዘዘው የሚለው ዘጠኝ ጊዜ ተፅፎአል (ቁጥር 1፣ 5፣ 7፣ 21፣ 26፣ 29፣ 32፣ 42ና 43) ፤ ይህን ለማድረግ ለምን አስፈላጊ ነበር አስባችሁታል(አገናዝባችሁታል) ?
  3. የክህነት ልብሶቹ ቅዱስ ልብሶች ተብለው ይጠሩ ነበር (ዘጸ 28፡ 2; 39፡ 4) ፤ በመዝ(139፡ 9) ካህናቶች በቅድስና ይልበሱ ፡፡ ቅድስናቸውን ልብሶቹ አንፀባርቀዉታል (መዝ 132፡ 9; ኢሳ 61፡ 10; ሮሜ 13፡ 14) ? በአድስ ኪዳን ካህናት ተብለን ከተጠራን ጀሞሮ ቅዱስ ልብሶችችን ምንድናቸው ? (ኢሳ 61፡ 10; ሮሜ 13፡ 14; ቆላ 3፡ 12-14)
  4. ለመቅደሱና ለሁሉም ውስጥ እቃዉ የተለየ ዝርዝርና አቅጣጫ እግዚአብሄር ሙሴን የሰጠበት ምክንያት ነበር ፤ የመፅሀፍ ቅዱስ ምሳሌ የሆነ ሰው እግዚአብሄር የጠየቀውን በትክክል ያልሰራ ማሰብ ትችላላችሁ ? እስካሁን የተለየ ነገር እንድትሰሩ እግዚአብሄር ጠርቶአችሁ ያውቃል ? አዎ ከሆነ እንደጠየቃችሁ አድርጋችሁ በመስራት ታግላችኃል ?
  5. በዘጸ 39 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንዱን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Exodus 39:42-43

"The Israelites had done all the work according to everything the Lord had commanded Moses. Moses inspected all the work they had accomplished. They had done just as the Lord commanded. Then Moses blessed them.”

ኦሪት ዘፀዓት 39 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

ኤፉድ፣ ጥሩር እና የክህነት ልብሶች እንዴት እንደሚሠሪ የሚያዝዘዉን ዝርዝር ትዕዛዛት ስትመለከቱ፥ "እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው" የሚለዉን ሃረግ አስር ጊዜ በተለያየ መንገድ ታገኙታላችሁ። አንድ ምዕራፍ ዉስጥ እንደዚህ አንድ ሃረግ ብዙ ጊዜ ተደጋግሞ ካያችሁ፥ በአትኩሮት አጢኑት። ብልሆቹ እስራኤላዉያን እግዚዓብሔር ያዘዛቸዉን ሁሉ ፈፅመዋል! ያልተደረገ አንድስ እንኳ አልነበረም!

በአዲስ ኪዳን ዉስጥ፥ ኢየሱስ ታላቁ ትዕዛዝ፥ እግዚዓብሔር አምላክህን በፍፁም ልብህ፣ በፍፁም ነፍስህ እና ሃሳብህ መዉደድ እና ባለንጀራህን እንደ ራስህ መዉደድ እንደሆነ ተናግሯል። ይህንን ትዕዛዝ ትፈፅማለህን? እግዚዓብሔርን መታዘዝ ፍቅር ነዉ! ከኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋን በምትቀበልበት ጊዜ፥ በእምነት ትዕዛዞቹን እየፈፀምክ መመላለስ ትችላለህ።

"እግዚአብሔር ሙሴን እንዳዘዘ ሁሉ እንዲሁ የእስራኤል ልጆች ሥራውን ሁሉ ሠሩ። ሙሴም ሥራውን ሁሉ አየ፥ እነሆም አድርገውት ነበር፤ እግዚአብሔር እንዳዘዘው እንዲሁ አድርገውት ነበር፤ ሙሴም ባረካቸው።"

ኦሪት ዘፀዓት 39:42-43

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • የማቴዎስ ወንጌል 22:35-39፦ "ከእነርሱም አንድ ሕግ አዋቂ ሊፈትነው፦ መምህር ሆይ፥ ከሕግ ማናቸይቱ ትእዛዝ ታላቅ ናት? ብሎ ጠየቀው። ኢየሱስም እንዲህ አለው፦ ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ። ታላቂቱና ፊተኛይቱ ትእዛዝ ይህች ናት። ሁለተኛይቱም ይህችን ትመስላለች፥ እርስዋም፦ ባልንጀራህን እንደ ነፍስህ ውደድ የምትለው ናት።"
  • ወደ ሮሜ ሰዎች 1:5፦ "በእርሱም ስለ ስሙ በአሕዛብ ሁሉ መካከል ከእምነት የሚነሣ መታዘዝ እንዲገኝ ጸጋንና ሐዋርያነትን ተቀበልን፤"
  • 2ኛ የዮሐንስ መልዕክት 1:6፦ "እንደ ትእዛዛቱም እንሄድ ዘንድ ይህ ፍቅር ነው፤ ከመጀመሪያ እንደ ሰማችሁ፥ በእርስዋ ትሄዱ ዘንድ ትእዛዙ ይህች ናት።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 50