Constructing the Tabernacle
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 37-38 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
ክለሳ
በዘጸዓት ውስጥ ሙሴ ለቤተ መቅደሱ ስራ የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ተከተለ ፤ ባስልኤል፣ ኤልያብና ጥበበኛ ሰራተኞች የቤተ መቅደሱን ስራ ጀመሩ ከዚያም በምዕራፍ 37 ቀጠለ ፡፡
ዘጸ 37 ለቤተ መቅደሱ የተሰሩትን እቃዎች ይገልፃል ፤ ታቦቱ ከግራር እንጨት ተሰራ (ቁጥር 1-5) ፡፡ የስርየቱ መቀመጫ ከንፁህ ወርቅ ተሰራ (ቁጥር 6-9) ፡፡ የህብስቱ ማስቀመጫ ጠረንጴዛ ከግራር እንጨት ተሰራ እናም እቃዎቹም የሚቀመጡበት ከንፁህ ወርቅ ተሰራ (ቁጥር 10-16) ፡፡ መቅረዙ በአንድ ቁራጭ ከተቀጠቀጠ ንፁህ ወርቅ ተሰራ (ቁጥር 17-24) ፡፡ የዕጣኑ መሰዊያ ከግራር እንጨት ከተደረበ ንፁህ የወርቅ ቀንድ ጋር ተሰራ (ቁጥር 25-28) ፡፡ ባስልኤል በተጨማሪ የተቀባውን ቅዱሱን ዘይት እና በችሎታ የተቀየጠውን ዕጣን ሰራ (ቁጥር 29) ፡፡ እነዚህን ሁሉ አካላት ሰሩ ስለዚህ እስራኤላዊያን የእግዚአብሄርን መገኘት መልመድ ይችላሉ ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት(38፡ 1); ባስልኤል ስሙ ትርጉም “በእግዚአብሄር ጥላ ስር” የሆነው እግዚአብሄር በገለፀው ትክክለኛ ልኬት ከግራር እንጨት የሚዋጠል መስዋዕት መሰዊያውን ገነባ ፤ በዘጸ(27፡ 1-8) እግዚአብሄር ለሙሴ የሰጠውን ትዕዛዝ ከእነዚህ ጥቅሶች ጋር ሲነፃፀር የባስልኤልን ስራ ስናይ ለእግዚአብሄር እቅድ በትክከል የታዘዘ ነበር ፤ ባስልኤል በተጨባጭ በጥሪው ነበር የሄደው ፤ ስራውን ስናይ የእግዚአብሄርን ንድፍ ወደ ፍሬ ያመጣ ነበር ይህ የሚያሸልም ነው ፡፡ የሙሴ መታዘዝ ወደ ባስልኤል መታዘዝ መራ ይህም ህዝቡን የእግዚአብሄርን መገኘት እንዲለምዱት መራ ፡፡ ሙሴ በፍፁም የእግዚአብሄርን አቅጣጫ በአጭር አልቀየረም ፡፡
ዘጸዓት(38፡ 2); ባስልኤል በመቀጠል ለአራቱ የመሰዊያው መዓዘን በንሀስ የተለበጠ ቀንድ ሰራ ፤ ባስልኤል ይህን መሰዊያ ሰራ ስለዚህ እስራኤላዊያን ለእግዚአብሄር መስዋዕታቸውን ማምጣት ይችላሉ ፤ ሁሉም መስዋዕታቸው ወደ መሲሁ ያመለክታሉ ፡፡ በዚህ በሚቃጠል መስዋዕት መሰዊያዉ ላይ ብዙ ነገር ይካሄዳል ፡፡
- ሁሉም የሚቃጠል መሥዋዕት; ሁል ጊዜ ጥዋትና ማታ ህዝቡ የንስሀ መስዋዕት ያደርጋሉ (ዘሌ 1)
- የአምልኮ መስዋዕት; ስብ አካሉ ለእግዚአብሄር ይቀርባል ከዚያም ሌላው የቀረው የእንሰሳው አካል ይበላል(ዘሌ 3)
- የኃጢዓት መስዋዕት; ለመንፃትና ለሆነ ኃጢዓት ንስሀ ለመግባት ይሰዋሉ (ዘሌ 4)
- የጥፋተኝነት መስዋዕት; ሳይታሰብ ለተደረገ ጥፋት ይሰዋል (ዘሌ 5)
- የንስሀ ቀን; ሊቀ ካህኑ ለኃጢዓቱ መስዋዕት ያቀርባል በመቀጠል ለህዝቡ ኃጢዓት ያቀርባል (ዘሌ 16)
ዘጸዓት(38፡ 3-7); ባስልኤል እሚቃጠል መስዋዕት መሰዊያው ጋር የሚጠቅሙ እቃዎች ለመስራት የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ተከተለ ፤ መሰዊያውን ለመሸከም የሚጠቅሙት ቐሚዎች ከግራር እንጨት በንሀስ በመለበጥ ሰራቸው ፡፡ አስታውሱ የግራር እንጨት በጣም ቀጥ ያለ፣ የማይጠቀለልና እርጥበትን የሚቐቐም ነው ፡፡
ዘጸዓት(38፡ 8); ባስልኤል የንሀስ ጎድጋአዳ ሳህን( የነሀስ መታጠቢያ ተብሎ ይጠራል) በመገናኛው ድንካን ከሚያገለግሉ ሴቶች ከተሰበሰበ ከንሀስ መስታወት ሰራው ፡፡ ባሪያ እያሉ በግብፅ የሚመሳሰል የነበረው የራሳቸው የእስራኤላዊያን መስታዎት ጥሩ አልነበረም ፤ ነገር ግን ግብፃዊያንን በዘረፉ ጊዜ ምናልባት ይህን የንሀስ መስታዎት ሰጡ ፤ ስለዚህ አሁን የእስራኤላዊያን ሴቶች ለቤተ መቅደሱ እንዲጠቅም እንደ ስጦታ እነኚህን መስታዎቶች ሰጡ ፡፡ ዘጸ(30፡ 17-20) ለሳህኑ አሰራሩና አጠቃቀም ትዕዛዝ ሰጥታአል ፤ ይህም በመገናኛው ድንካንና በመሰዊያው መሀከል ተቀመጠ ፡፡
ካህናቱ በዚህ ሳህን ላይ ዉሃ ውስጥ እጃቸውንና እግራቸውን ይታጠባሉ ስለዚህ ወደ እግዚአብሄር መገኘት በገቡ ጊዜ አይሞቱም ፤ የእግዚአብሄርን መገኘት ለመልመድ ይህ አስፈላጊ ነበር ! ይህ በሉቃ(21፡ 1-4) ያለውን የመበለቲቱን ሳንቲም ወደ ሀሳብ ያመጣል ፡፡ እግዚአብሄር መስታዎታቸዉን የሰጡትን ሴቶች ልብ አየ ስለዚህ ካህናቱ ስራቸውን የሚሰሩ ከሆነ አይሞቱም ፤ ሴቶቹ መስታዎታቸውን የሰጡት; ብልህ ጥበበኞች ሳህኑን ሰሩ(ገነቡ); ስለዚህ ካህናቱ ለህዝቡ ንስሀን ማድረግ ይችላሉ ፡፡ ሁሉም ድርሻውን አደረገ ፡፡
ካህናቱ በእግዚአብሄር ፊት ከመቅረባቸው በፊት መንፃት ያስፈልጋቸዋል ፤ ፍሊፕ ራይከን የዚህ ተመሳሳይ ሳለ(አስቀመጠ) ፡፡ ከመሰዊያዉ መስዋዕት ላይ ንስሀ በተቀበሉ ጊዜ ልክ እንደ ፋሲካ ነበር ፤ በሳህኑ ውስጥ በታጠቡ ጊዜ የሚመስለው ልክ እንደ ቀይ ባህር ክስተት ነበር ፡፡ አድስ ኪዳንም በእግዚአብሄር ፊት የመታጠብን ጠቀሜታ ያስቀምጣል ፤ በኤፌ(5፡ 25-26) ጳውሎስ ያስቀመጠው ኢየሱስ ቸርችን አነፃት(አጠባት) “ በውሃ መታጠብና ከቃሉ ጋር “ ፤ በቲቶ(3፡ 5) ጳዉሎስ ሲናገር እግዚአብሄር “ ለአድስ ልደት በሚሆን መታጠብና በመንፈስ ቅዱስ በታደስ” አዳነን ፤ በዮሐ(13፡ 8) ኢሱስ ጴጥሮስን ሲነግረው “ ካላጠበሁህ ከእኔ ጋር እድል የለህም “፡፡ እግዚአብሄር ህዝቡን ነፃ ለማውጣት በቤተ መቅደሱ በኩል መረጠ ይህ ሁሉም ወደ ኢየሱስ ያመለክታሉ ፡፡
ዘጸዓት(38፡ 9-17); ባስልኤል እንደ እያንዳናዱ ዝርዝር ለግቢው እቃዎችን ስራውን በመምራት የተለየውን የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ መከተል ቀጠለ ፡፡
ዘጸዓት(38፡ 18-20); እነዚህ ቁጥሮች የሚያወሩት የግቢውን በር ስለሚሸፍነውን መጋረጃ ነው ፤ የእግዚአብሄርን መገኘት ለመለማመድ(ለማግኘት) አንድ መግቢያ ብቻ ነበር የነበረው ፡፡ ሁል ጊዜ ወንጌልን ላካፍል እሄዳለሁ ጥቂቶች ሁል ጊዜ የሚሉኝ “ ወደ እግዚአብሄር ብዙ መንገድ አለ!” ነገር ግን ወደ እግዚአብሄር ያለው አንድ መንገድ ብቻ ነው ! ቤተ መቅደሱና በመጋረጃው ውስጥ ያለው አንድ መግቢያ የክርስቶስ አይነት እንደሆነ አምናለሁ ይህ ወደ እግዚአብሄር ያለው ብቸኛ መንገድ እሱ እንደሆነ ጥላ ነው ፤ የኃላ በር አልነበረም ፡፡ ኢየሱስ በአገልግሎቱ ወቅት ይህን እዉነት አብራርቶታል፡፡
በዮሐ(14፡ 6) ኢየሱስ ቶማስን አለው “ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም “ ፤ ማቴ (7፡ 13-14) የተመዘገበው በተራራው ስብከት ኢየሱስ ሲናገር “ በጠበበው ደጅ ግቡ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ መንገዱም ትልቅ ነውና ወደ እርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው ወደ ህይወት የሚወስደው ደጅ የጠበበ መንገዱም የቀጠነ ነውና የሚያገኙትም ጥቂቶች ናቸው ” ፤ በተጨማሪም በዮሐ(10፡ 9) ኢየሱስ ሲናገር “ በሩ እኔ ነኝ በእኔ የሚገባ ቢኖር ይድናል ይገባልም ይወጣልም መሰማሪያም ያገኛል ፡፡”
ዛሬ(በዚህ ጊዜ) ምንም የቤተ አምልኮት የለም ፤ ቤተ አምልኮቱ ወደ ቤተ መቅደስ መርቶ ነበር ከዚያም ከሁለት አንዳቸውም የቆየ መኖር የላቸውም ፤ ሰዎች መስዋዕታቸውን የሚያቀርቡበት መንገድ ከሌላቸው ሌላ መንገድ ይኖራቸዋል እናም ኢየሱስ ሲናገር “ አሁን በሩ እኔ ነኝ ፤ እኔ ጠባቡ በር ነኝ ፡፡”
ዘጸዓት(38፡ 21-23); በአሮን ልጅ በኢታማር መሪነት ሌዋዊያን ለቤተ አምልኮት መስሪያ የሚጠቅሙትን እቃና ሁሉንም የውስጥ እቃዎች ቆጥረው ተረከቡ ፡፡ ባስልኤልና ኤልያብ በግንባታው ብልህ ሰራተኞችን መሩ ፤ ስራው አለቀ(ተፈፀመ) ! የቤተ አምልኮቱ ተገነባ ! ብዙ ሰዎች ለእግዚአብሄር ታዘዙ የእግዚአብሄርን መገኘት እንድንለምደው(እንድንቀምሰው) ለእኛ በሩን ከፈቱልን ፡፡
ዘጸዓት(38፡ 24-28); ሙሴ የመዘገበው በትንሹ ከአንድ ቶን ወርቅ የሚበልጥና በባዙ ከሰዎስት ቶን የሚበልጥ ብር ለስራው እንደተጠቀመ ነበር ፡፡ እያንዳንዳቸው 603,550 ወንዶች ሁለት አምስተኛ የሚሆን ጥንሽ ብር ሰጥተዋል ፤ (የእስራኤል የህዝብ ቆጠራ በዘኁ 1 በተወሰደ ጊዜ ለቤተ አምልኮቱ ስራ ብር ያዋጡት ወንዶች ቁጥር በህዝብ ቆጠራው ከተመዘገበው ጋር ተመሳሳይ ነበር ፡፡) በግንባታው ውስጥ የተጠቀሙት ነሀስ ጠቃላላ 5,310 ታውንድ (ከ 2 ቶን ይበልጣል) ፡፡
መዝጊያ
የሚያስደንቅ የብርና ሀብት መጠን በየቀኑ ከህዝቡ ይመጣል ምክንያቱም እግዚአብሄር በዚህ ውስጥ እንደነበር ያምኑ ነበር ፤ ብልህ ሰራተኞቹ አንድ ጋር በመምጣት ህዝቡ ከእግዚአብሄር ጋር መገናኘት የሚጀምሩበትን መኖሪያ ቦታ ቤተ አምልኮቱን ሰሩ ፤ ከዚያም በሙሴ በተራራው ላይ ከእግዚአብሄር ይዞ በመጣው ሁሉም ተጀመረ ፡፡
Philip Graham Ryken, Exodus (ESV Edition): Saved for God’s Glory (Wheaton, IL: Crossway, 2015), p. 1067–68.
Ryken, p. 1070.
ጥያቄዎች
-
እግዚአብሄር መቅረዙ “ሁሉም አንድ ሆነው” እንዲሰራ አዘዘ (ዘጸ 37፡ 17; 22) ፤ በዚህ እግዚአብሄር አላማ እንደነበረው እናውቃለን ፤ አላማው ምን ሊሆን ይችል ነበር (ዮሐ14፡ 20; 17፡ 20-21; ራዕ 1፡ 20) ? ምን ታስባላችሁ በቅዱስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የብርሀን ምንጭ ነበር ?
-
መቅረዙ የተሰራው ከንፁኅ ወርቅ ነበር (ዘጸ 37፡ 17) ፤ ብቸኛው የብርሃን ምንጭ ነበር እናም በፍፁም ወደ ዉጭ አይወጣም (ዘጸ 27፡ 20) ፤ ይህ እንዴት በጥልቀት ወደክርስቶስ እንደሚያመለክት ማየት ትችላላችሁ? (ዮሐ1፡ 9; 8፡ 1; 1ጴጥ 2፡ 9; ራዕ 21፡ 23)
-
እያንዳንዱ የግቢው ዝርዝር እና በሩ ጥቅምና ምልክታዊ(ወካይ) ትርጉም ነበረው ፤ የመጋረጃው ቀለም( በመግቢያው ላይ የሚንጠለጠለው መጋረጃ) ሰማያዊ፣ ሀምራዊና ቀይ የሚወክሉት አምላክነት፣ የንጉሳዊያን ቤተሰብነትንና የተሰዋን ደምን በቅደም ተከተላቸው ፡፡ ነጩ መጋረጃ በግቢው ዙሪያ ያለው ቅዱስነትን ይወክላል ፡፡ እንዴት ታያቸዋላችሁ እነዚህ ሁሉ ዝርዝሮች ወደ መሲሁ ሲያመለክቱን ?
-
ወደ ግቢው ከአንዱ በር ውጪ በየትም መንገድ ማንም መግባት አይችልም ፤ ይህ እውነት እንዴት ወደ ክርስቶስ ያመለክታል ?
-
እግዚአብሄር ሙሴን እንዳዘዘው ለቤተ መቅደሱ(ድንካኑ ማደሪያ)ና ለግቢው ሁሉንም እቃዎችንና የውስጥ እቃዎችን በትክክለኛው ዝርዝር መስራት ለእነርሱ ቀላል ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ? ስለ እነዚህ ነገሮች የተለየ ዝርዝር በመስጠት እግዚአብሄር ለምን ብዙ ጊዜ እንደፈጀ ምን ታስባላችሁ ?(ዘጸ 25፡ 8-9; ዕብ 9፡11; 24)
-
ካለ የትኛው የቤተ መቅደሱ አካል በጥቂቱ መንገድ ወደ መሲሁ አያመለክትም ? (ዘጸ 25፡ 8-9)
-
በዘጸ (37-38) ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ አጉልቶ ምንድን አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin
“They shall construct an ark of acacia wood two and a half cubits long, and one and a half cubits wide, and one and a half cubits high.” Exodus 25:10 “Now Bezalel made the ark of acacia wood; its length was two and a half cubits, and its width one and a half cubits and its height one and a half cubits.” Exodus 37:1
የመሰዊያ ስፍራን ማዘጋጀት
ኦሪት ዘፀዓት 37-38 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
አሁንም እንደገና፦ በእግዚዓብሔር ምሪት፥ የዘፀዓት ደራሲ የሆነዉ ሙሴ የመገናኛዉ ድንኳን የሚገነባበትን ዝርዝር በትክክል ገለፀ። አንዴ ብቻ ሳይሆን ሁለቴም፥ ሙሴ እንደዚህ በዝርዝር የግንባታዉን ሂደት ለምን እንደዘገበዉ ገርሟችሁ ያዉቃል? ሁለቱም ዝርዝሮች ስትመለከትዋቸዉ ደግሞ ተመሳሳይ እና ትክክል ናቸዉ። በተማሳሳይ መንገድ፥ የአዲስ ኪዳን ፀሃፊዎች የጥንቷ ቤተ-ክርስትያን እንዲያስተዉሉት የሚፈልጉት እዉነት ካለ ይደጋግሙታል። ጳዉሎስ እዉነትን የሚደጋግመዉ እሱነን ለመጠብቅ እንደሆነ ይናገራል።
በህይወትህ ዉስጥ የሚደጋገሙ ወይንም ሁለቴ፣ ሶስቴ እና አራቴ የሚፈጠሩ ነገሮችን በአትኩሮት ተመልከታቸዉ። እግዚዓብሔር ወደ እርሱ እድትመለክት ፈልጎ፥ ከከፉ ሊጠብቅህ እና አንድን ሃሳብ ገንዘብ እንድታደርግ ፈልጎ ሊሆን ይችላል። እግዚዓብሔር ሁሉን ነገር የሚፈፅመዉ አቅዶ ነዉ። ግልፅ በሆነ መንገድ እግዚዓብሔር ሲናገር በቸልታ አትለፈዉ።
"ባስልኤልም ከግራር እንጨት ታቦቱን ሠራ፤ ርዝመቱም ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ነበረ።"
ኦሪት ዘፀዓት 37:1
"ከግራር እንጨትም ታቦትን ይሥሩ፤ ርዝመቱ ሁለት ክንድ ተኩል፥ ወርዱም አንድ ክንድ ተኩል፥ ቁመቱም አንድ ክንድ ተኩል ይሁን።"
ኦሪት ዘፀዓት 25:10
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ወደ ፊልጵስዩስ 3:1፦ "በቀረውስ፥ ወንድሞቼ ሆይ፥ በጌታ ደስ ይበላችሁ። ስለ አንድ ነገር መልሼ ልጽፍላችሁ እኔን አይታክተኝም ለእናንተ ግን ደኅና ነው።"
- 2ኛ የጴጥሮስ መለዕክት 1:12፦ "ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ምንም ብታውቁ በእናንተም ዘንድ ባለ እውነት ምንም ብትጸኑ፥ ስለ እነዚህ ዘወትር እንዳሳስባችሁ ቸል አልልም።"
- የይሁዳ መልዕክት 1:5፦ "ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈጽሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብፅ አገር ሕዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኋላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 49
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።