Building the Tabernacle
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 36 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
ክለሳ
ካህናቱ ሁል ጊዜ እንዲያገለግሉ ተመረጡ(ተሾሙ) ፤ እንደ ሐዋ( 19፡ 8-10) ጳዉሎስ በየቀኑ ከ12 ተማሪዎች ጋር በጢራኖስ ትምህርት ቤት ይነጋገር ነበር ፤ በሪቫይብ(ህይወት ሰጪ) ትምህርት ቤት ውስጥ እያደረግን ያለነውን ፡፡
በዘጸ 34 ሙሴ አስሩ ትዕዝዝ ተሰጥተውት ነበር ፤ እግዚአብሄር ከእስራኤል ጋር ኪዳኑን መሰረተ; እስራኤላዊያን ከከነዓንዊያን ጋር ስምምነት እንዳያደርግ ተከለከለ በተጨማሪም በብዓላቸው ውስጥ እግዚአብሄርን ብቻ እንዲያመልኩ ታዘዙ ፡፡ ሙሴ እግዚአብሄር የተናገረውን ለህዝቡ በመናገር አደረሰ ፡፡ ከእግዚአብሄር መገኘት ሲወጣ ፊቱ ያንፀባርቃል ስለዚህ ለመሸፈን መሸፈኛ ያስቀምጥበታል በእዉነቱ ቢደበዝዝም ፡፡
በዘጸ 35 ሙሴ እስራኤላዊያንን ቤተ አምልኮቱን እንዲገነቡ ነገራቸው ፤ ባስልኤልና ኤልያብ ሸክሙን(ስራውን) መሩ ፤ እግዚአብሄር ለቤተ መቅደሱ ስጦታ እንዲሰበስቡ ነገራቸው ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት(36፡ 1); ባስልኤል፣ ኤልያብና ብልሀተኛ ሰዎች እግዚአብሄር እንዳዘዘው ቤተ መቅደሱን ሊሰሩ ሄዱ ፤ የኔልሰን ሀተታ የእነዚህን ብልሀተኛ ሰራተኞች ባህሪይ ገልፃአል ፤ ከሰራተኞቹ ውስጥ ሁለቱም ሴትም ወንድም ነበሩ(ዘጸ 35፡ 20-22; 25) ፤ “ ልባቸው ፍቃደኛ ወይም የተነቃቃ ነበር”(ዘጸ35፡ 5; 21-22; 26) ፤ ስራቸውን እንዲጨርሱ ችሎታና ስጦታ ነበራቸው (ዘጸ 35፡ 10; 25; 34-35; 36፡ 1-2) ፤ “ በችሎታቸው……እና በንብረታቸው ለጋስ ነበሩ” (ዘጸ 35፡ 5; 22; 29; 36፡ 3-7) ፤ የጨረሳአቸው ውጤቶች የሚያሳዩት የስራቸውን ምርጥነት ነበር ፡፡
ዘጸዓት(36፡ 2-3); ጥበበኛ ሰራተኞች ስራውን ለመጀመር ለሙሴ ጥሪ ወዲያወኑ ምላሽ ሰጡ ፤ ሰራተኞቹ እስራኤላዊያን ለቤተ አምልኮቱ ግንብታ በፍቃዳቸው ያዋጡትን ስጦታ ሰበሰቡ ፤ ስጦታቸውን “ ማለዳ ማለዳ” (ቁጥር 3) አመጡ ፤ ዘመቻ አልነበረም …..ህዝቡ ዝም ብሎ አዋጣ ፡፡
ህዝብ በጠራህ ጊዜ አታሳምናቸውም ፤ ልባቸው በተንቀሳቀሰ ጊዜ ስራውን ይሰሩታል ፡፡
ዘጸዓት(36፡ 4); ጥበበኛ ሰዎች አንድ በአንድ ይሰሩት ከነበረው ስራ መጡ ፤ እግዚአብሄር ለጠራቸው ስራ ሊሰሩ ሌላ ስራቸውን ተው ፡፡ እዚህ ስፍራ ላይ በመፅህፍ ቅዱስ ታሪክ ውስጥ ብቸኛው በእግዚአብሄር የተነደፈውን ህንጻ ይገነቡ ነበር ፡፡ የእነዚህ ብልህ ጥበበኛ ስራ እንደሚያምር አምናለሁ ፤ ሳሙኤል ማተር ሲናገር “ ሁሉም ጥበብ ምንም አይደል ነገር ግን የጥበብ ሀመልማሎዎችና ጨረሮች በፍጥረት፣ ማብራትና ማንፀባረቅ የመጀመሪያው በመሆን ከዚያም በሰው መነፅር ውስጥ መረዳታቸው; ከዚያም ከእሱ እንዳለ መጡ ስለዚህ ለእሱ ዝንባሌ አሳዩ ፡፡“
ምንድን እንስራ ምሳሌ እንዲሆን እግዚአብሄር እንዴት አገናኘን እና ክብር አገኝ ፡፡ በቤተ መቅደሱ ውስጥ እግዚአብሄር ውበቱን ለመግለጥ የሰውን ልጅ ተጠቀመ ፤ በመዝ( 27፡ 4) ዳዊት ሲናገር “ እግዚአብሄርን አንዲት ነገር ለመንሁት እርሱዋንም እሻለሁ ፤ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በእግዚአብሄር ቤት እኖር ዘንድ እግዚአብሄርንም ደስ የሚያሰኘውን አይ ዘንድ መቅደሱንም እመለከት ዘንድ ፡፡” መዝ(96፡ 6) የሚለው “ ምስጋናና ውበት በፊቱ ቅዱስነትና ግርማ በመቅደሱ ውስጥ ናቸው ፡፡” ጥበበኛ ሰራተኞች ትልቅ በሆነ ነገር ላይ ለመስራት አንድ በአንድ መጡ ፤ አነዚህ ብል ጥበበኞች የእርሱ ውበት ሊኖረበትና ሊታይበት የሚችለውን ቦታ ሰሩ(ፈጠሩ) ፡፡
ሰዎች በቸርች ውስጥ ፎታቸውን(ምስሎችን) ለጥፎ በመተው አብረው በመምጣት የእግዚአብሄርን ውበት ያሳያሉ ?
ዘጸዓት(36፡ 5); ጥበበኞች ለመስራት አብረው እንደመጡ ህዝቡ ቤተ መቅደሱን ለመገንባት ከሚያስፈልገው በላይ እንደሰጡ አወቅ(ተገነዘቡ) ፤ ህዝቡ በዚህ ጥሪ አምነዋል በዚህም ያላቸውን ሁሉ በፍቃደኝነት ሰጡ ፡፡ ድርጊታቸው ኢየሱስ በማቴ(6፡ 21) “ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናል” የተናገረውን ያስታውሰናል ፡፡ የእግዚአብሄር በሚሰራበት ጊዜ ማናናም አታሳምኑም ፤ ያውቃሉ ስለዚህ መስጠታቸውን ቀጠሉ ፡፡ ህዝቡ ወደፊት ተመሳሳይ ለጋሽነት ያሳያሉ ፤ ንጉስ ኢዮአስ “ የእግዚአብሄርን ቤት ለመጠገን”(2ዜና 24፡ 4) ገንዘብ ለመሰብሰብ ጥሪ ባደረገ ጊዜ ህዝቡ በለጋሽነት በስጠት መለሱለት በዚህም በእያንዳንዳ ቀን ደረቱን በገንዘብ ሞሉት (2ዜና 24፡ 8-11) ፡፡ ህዝቡ እግዚአብሄር በዛነገር ውስጥ እንዳለ ባዩና በተረዱ ጊዜ ገንዘብ በፍፁም አያጥራቸውም(እትረት ኤደለም) ፤ ንጉስ ሕዝቅያስ በለጋስነት እንዲሰጡ ህዝቡን በጠየቀ ጊዜ ካህናቱና ሌዋዊያን “ በእግዚአብሄር ቤት ለአገልግሎት እንዲፀኑ”(2ዜና 31፡ 4) ለእግዚአብሄር ቤት ስጦታቸውን አመጡ ከዚያም ተርፎ ተትረፍርፎ ነበር (2ዜና 31፡ 10) ፡፡ ህዝቡ ይሰጣሉ የእግዚአብሄር ጉዞ አስቸካይነትን በተገነዘቡ(በተረዱ) ጊዜ ፡፡
በማቴ(26፡ 6-13) ላይ አንዲት ሴት ኢየሱስን ለማክበር የነበራትን ሁሉን ነገር ሰጠች ፤ “ አንዲት ሴት ዋጋዉ እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰች ፡፡” በሐዋ(4፡ 34-35) ሉቃስ የመዘገበው “ በመካከላቸው አንድ ስንካን ችግረኛ አልነበረምና ፤ መሬት ወይም ቤት ያላቸው ሁሉ እየሸጡ የተሸጠውን ዋጋ ያመጡ ነበርና ፤ በሐዋሪያትም እግር አጠገብ ያኖሩ ነበር ማንኛውም እንደሚፈልግ መጠን ለእያንዳንዱ ያካፍሉት ነበር ፡፡” የመጀመሪያዎቹ ክፍለ ዘመን አማኞች ምንም የሚያስፈልጋቸው አልነበረም ምክንያቱም እርስ በእርሳቸው ይጠባበቁ(ይተሳሰቡ) ነበር ፡፡ በሉቃ(21፡ 1-4) አንዲት መበለት “ ሁለት ሳንቲም” ሰጠች ከዚያም ኢየሱስ ያመለከተው(የጠቀሰው) ሌሎች ከትርፋቸው ሰጡ እሳ ለመኖር ያላትን ሁሉን ሰጠች ፤ ይህ ሰዎች ስለሚያዩት አይደለም ! ስለልብ ነው ፡፡
በዘጸ 36 ላይ ህዝቡ ለእግዚአብሄር ወዲያውኑ ችሎታቸውን፣ ስጦታቸውንና ሀብታቸውን ሰጡ ፤ ወደ ስስት ማዕድ (ጠረንጴዛ) መምጣት አንችልም ! በማቴ(10፡ 39) ላይ ኢየሱስ ሲናገር “ነፍሱን የሚያገኝ ያጠፋታል ነፍሱንም ስለ እኔ የሚያጠፋ ያገኛትል ፡፡” እግዚአብሄር የሆነ ነገር እንድትሰሩ በጠየቃችሁ ጊዜ እየሰራችሁ ያላችሁትን በመተው እንደትሰሩ የጠየቃችሁን ለመስራት ሁሉንም ነገር መስጠት አለባችሁ ፤ በጥሪያችሁ ለመሄድ ዋጋ(መስዋዕትነት) መክፈል አለ ፡፡ እስራኤላዊያን በትዕዛዝ ለህዝቡ የእግዚአብሄርን መገኘት ለመለማመድ(ለመቅመስ) ሁሉንም ነገር ሰጥተዋል ፤ ይህ ለዚህ የሚገባ ነው ነገር ግን ቀላል ነው ማለት አይደለም ፡፡
ዘጸዓት(36፡ 6-7); ሙሴ ስጦታውን እንዲያዎሙ ትዕዛዝ ሰጠ ፤ ሁሉንም ስራ ለሚሰሩት ሰዎች ከበቂ በላይ እቃዎች ነበሩ ፡፡
ዘጸዓት(36፡ 8-38); ሰዎቹ ሰራውን ጀመሩ ! አስር የውስጠኛው መጋረጃዎች እግዚአብሄር እንደ ገለፀው ተሰሩ(ቁጥር 8-13) ፤ 11 የውጨኛው መጋረጃዎች ከፍየል ፀጉር ተሰሩ ከዚያም እግዚአብሄር እንዳዘዘው ከ” ቀይ አውራ በግ ቁርበት ከዚያም በላይ ሌላ መደረቢያ ከአስቆጣ ቁርበት”(ቁጥር 14-19) አያያዙት ፡፡ ሳንቃውን ከግራር እንጨት ጣውላ ሰሩ ከዚያም ከታች(እግሩ) ላይ የብር እግሮች ውስጥ አስገብተው ተከሉት (ቁጥር 20-30) ፤ መወረወሪያዎቹን ከግራር እንጨት ሰሩ በወርቅም ደረቡባቸው(ለበጡአቸው) (ቁጥር 31-34) ፡፡ በመቀጠልም የውስጠኛውን መሸፈኛና የውጨኛውን መሸፈኛ እንደ እግዚአብሄር ድዛይን ሰሩ(ቁጥር 35-36) ፡፡ የተጠለፈውን መጋረጃ በድንካኑ መግቢያ ላይ አስቀመጡት (ቁጥር 37-38) ፡፡
መዝጊያ
አ.ወ. ፒንክ በአዶለፍ ሳፊሪ የተለዩ ሰዎስት የቤተ መቅደስ ትርጎሞችን ገልፃአል; የመጀመሪያው ቤተ መቅደሱ እግዚአብሄር ስለሚኖርበት ቦታ የሚታይ ሰማያዊ ስዕል(ገለፃ) ይሰጣል፤ ሁለተኛው ቤተ መቅደሱ የክርስቶስ አይነት ነበር ወይም እንዴት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል እግዚአብሄርን ማግኘት እንደምንችል የሚያሳይ መልክ ነው ፤ ሰዎስተኛው ቤተ መቅደሱ በቸርች ውስጥ ያለው ክርስቶስ አይነት ነው ምክንያቱም አማዮች እግዚአብሄር መገኘት የመንፈስ ቅዱስ ቤተመቅደስ ናቸው ፡፡
ጥበበኛ ሰዎች እግዚአብሄር እንዲሰሩ ለጠየቃቸው በመታዘዝ ማድረጋቸው ይህ ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር ያመለክታል ፤ የእስራኤላዊያን መታዘዝ አኛን በመሲሁ በኩል ስላለን ነፃ መውጣት አመለከተን ፡፡
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 146.
Philip Graham Ryken, Exodus (ESV Edition): Saved for God’s Glory (Wheaton, IL: Crossway, 2015), p. 1038
Arthur. W. Pink, Gleanings in Exodus, paperback ed. (Chicago: Moody Publishers, 1981), p. 180.
ጥያቄዎች
-
በዘጸ(25፡ 8-28; 43) ላይ ቤተ መቅደሱን ወይም የመገናኛ ድንካኑን ለመስራት በዘጸ(36-39) በመድገም እግዚአብሄር በዝርዝር ለእስራኤላዊያን ለምን እንደሰጣቸው ምን ታስባላችሁ ? (ዘጸ 39፡ 42-43)
-
ለቤተ መቅደሱ(ለቤተ አምልኮቱ) ግንባታ ህዝቡ ያዋጣው ብዙው ከየት መጣ ? (ዘጸ 3፡ 22; 11፡ 2; 12፡ 35-36)
-
ለቤተ መቅደሱ መዋጮ የተጠየቀው እንደ ነፃ ስጦታ ነበር(ዘጸ 36፡ 3) ፤ ይህ ምን ማለት ነው ? (ዘጸ 35፡ 5-9; 21-22; 29)
-
መዋጮው እንዲቆም ሙሴ ለምን ትዕዛዝ ሰጠ (ዘጸ 36፡ 6-7) ? በአካባቢያችሁ እንደዚህ አይነት ለጋስነት አይታችኃል ?
-
ለሚያስፈልገው ስራ ጊዜ አቸውንና አገልግሎታቸውን የሚሰጡ ፈቃደኛ ሰዎችን ፍለጋ ሙሴን ችግር ሆኖበታል ? ይህ ስለልባቸው ምን ይላል ?
-
በዘጸ 36 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 36:2-3, 7
“So Moses summoned Bezalel, Oholiab, and every skilled person in whose heart the LORD had placed wisdom, everyone whose heart moved him, to come to the work and do it. They took from Moses’ presence all the contributions that the Israelites had brought for the task of making the sanctuary. Meanwhile, the people continued to bring freewill offerings morning after morning ....The materials were sufficient for them to do all the work. There was more than enough.”
መገናኛ ድንኳኑን መሥራት
ኦሪት ዘፀዓት 36
የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
ሙሴ፥ ቤተ-መቅደሱን ለመገንባት እግዚዓብሔር ማስተዋል እና ጥበብ የሰጣቸዉን ሁሉንም ብልህ ሰዎች ጠራቸዉ። ወዲያዉኑ እጃቸዉ ላይ ያለዉን ሥራ ለምሥራት ለባቸዉ ተነሳሳ። በማለዳ በማለድ የእስራኤል ልጆች ለግንባግታዉ የሚሆን መዋጮ እና ስጦታ ይዘዉ ያመጡ ነበር። ያመጡት ስጦታ ለግንባታዉ በቂ ብቻ ሳይሆን ከዚያም በላይ የሆነ ነበር። ከሚፈለገዉ በላይ ነዉ! እግዚዓብሔር እንደመራቸዉ ሁሉ፥ ልባቸዉን እያደመጡ፥ በመታዘዝ ምላሽ ሰጡ!
እግዚዓብሔር ለሆነ ነገር ዓላማ ወይም ግብ በሚያስቀምጥበት ጊዜና ብዝቡን ሲጠራ፥ መንገድን እርሱ ራሱ ያበጃል። በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬን እንድታፈራ የሚያድርግህን ጥበብ እና ማስተዋል በመስጠት ያስታጥቅሃል። የልብህን ድምፅ አድምጥ! ለእግዚዓብሔር ምላሽ ስጥ! እናም አስታዉስ፥ በክርስቶስ ከበቂ በላይ ይኖርሃል!
"ሙሴም ባስልኤልንና ኤልያብን፥ እግዚአብሔርም በልቡ ጥበብን ያደረገለትን በልብ ጥበበኛ ሰው ሁሉ፥ ሥራውንም ለመሥራት ይቀርብ ዘንድ ልቡ ያስነሣውን ሁሉ ጠራቸው። እነርሱም የእስራኤል ልጆች ለመቅደስ ማገልገያ ሥራ ያመጡትን ስጦታ ሁሉ ይሠሩ ዘንድ ከሙሴ ተቀበሉ። እነዚያም እንደ ፈቃዳቸው ማለዳ ማለዳ ስጦታውን ገና ወደ እርሱ ያመጡ ነበር።.... ያመጡትም ነገር ሥራን ሁሉ ለመፈጸም በቅቶ ገና ይተርፍ ስለ ነበረ ሙሴ አዘዘና፦ ወንድ ወይም ሴት ለመቅደስ ስጦታ ከዚህ የበለጠ የሚያመጣ አይኑር ብሎ በሰፈሩ ውስጥ አሳወጀ። ሕዝቡም እንዳያመጡ ተከለከሉ።"
ኦሪት ዘፀዓት 36:2-3, 6-7
ተጨማሪ ጥቅሶች
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 9:8-9፦ "ተነ፥ ለምስኪኖች ሰጠ፥ ጽድቁ ለዘላለም ይኖራል ተብሎ እንደ ተጻፈ፥ እግዚአብሔር፥ ሁልጊዜ በነገር ሁሉ ብቃትን ሁሉ አግኝታችሁ ለበጎ ሥራ ሁሉ ትበዙ ዘንድ፥ ጸጋን ሁሉ ሊያበዛላችሁ ይችላል።"
- ቆላስይስ 1:9-11፦ "ስለዚሁ እኛ ደግሞ ይህን ከሰማንበት ቀን ጀምረን የፈቃዱ እውቀት መንፈሳዊ ጥበብንና አእምሮን ሁሉ እንዲሞላባችሁ እየለመንን፥ ስለ እናንተ ጸሎትን አልተውንም፤ በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁ በእግዚአብሔርም እውቀት እያደጋችሁ፥"
- ወደ ዕብራዉያን 13:20-21፦ "በዘላለም ኪዳን ደም ለበጎች ትልቅ እረኛ የሆነውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ያወጣው የሰላም አምላክ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል በፊቱ ደስ የሚያሰኘውን በእናንተ እያደረገ፥ ፈቃዱን ታደርጉ ዘንድ በመልካም ሥራ ሁሉ ፍጹማን ያድርጋችሁ፤ ለእርሱ እስከ ዘላለም ድረስ ክብር ይሁን፤ አሜን።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 48
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።