New Stone Tablets
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 34-35 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
ክለሳ
እስራኤላዊያን የወርቅ ጥጃውን በማምለክ ቆሽሸው ነበር ፤ ከእግዚአብሄር ጋር ከተገናኘበት ተራራ ሙሴበመውረድ መጣ ከዚያም በብስጭቱ አስሩን ትዕዛዝ ሰበራቸው ፤ በዚህም እግዚአብሄር መቅሰፍት አመጣ ሌዋዊያንም 3000 ወንዶችን ገደሉ ፡፡ በዚህም እግዚአብሄር “ ከዚህ በኃላ ከእናንተ ጋር አልሄድም” ሙሴንም እንዲሄድና ድንካኑን ከመኖራቸው ውጭ እንዲሆን ተናገረ ፡፡ በዚህ አነጋገር ውስጥ እግዚአብሄር ስለ ቀጣዩ ሂደት ሙሴን መናገር ጀምራአል ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት(34፡ 1-4); እግዚአብሄር ሙሴን እርሱ ሰብሮት ለነበረው መተኪያ ሁለት ድንጋዮች እንዲቆርጥ ነገረው እነዚህም ፅላቶች ላይ እግዚአብሄር ቃሉን ይፅፍባቸዋል ፡፡ በቀጣዩ ቀን በማለዳ እንደገና ከእግዚአብሄር ጋር ሊገናኝ ወደ ሲና ተራራ ተመልሶ ሄደ ፤ የዚህ ምዕራፍ ቁጥር 28 ሲናገር ሙሴ በእግዚአብሄር ፊት ሌላ 40ቀንና 40ሌሊት አሳለፈ በእነዚህ ጊዜያትም አልበላምም አልጠጣምም ፡፡ ነገ አድስ ቀን ይሆናል አስታዋሽ የእግዚአብሄር ምህረት ማለዳ ማለዳ አድስ ነው(ሰቆ ኤር 3፡ 22-23) ፡፡ ብዙ የሚታወቁ ክስተቶች በመፅኀፍ ውስጥ በማለዳ ሆነዋል ፤ በዘፍ(19፡ 27-28) አብርሃም በሰዶምና በጎሞራ ለውን ለመመልከት በጥዋት በማለዳ ነቃ ፤ በመሳ(6፡ 28) የከተማዋ ሰዎች የባኦልን መሰዊያ ተሰብሮ የወደቀውን ለመፈለግ ማልደው በጥዋት ተነሱ ፤ በኢዮ(1፡ 5) ኢዮብ ለልጆቹ መስዋዕቱን ሊያቀርብ በማለዳ ተነሳ ፤ በሉቃ(24፡ 1) ሴቶቹ ማልደው ወደ ኢየሱስ መቃብር ተመለሱ ፡፡ ኪዚያ ቦኃላ በቁጥር 2 ላይ የሆነው ምንድን ነው እግዚአብሄር ሙሴን ነገረው” ነገም የተዘጋጀህ ሁን በማለዳም ወደ ሲና ተራራ ወጥተህ በዚያ በተራራው ራስ ላይ በፊቴ ቁም “ ፡፡ በመቀጠል በቁጥር 3 ላይ እግዚአብሄር ማንም ወይም ኢያሱም አንስሳት እንካን ቢሆን ከሙሴ ጋር እንዲሄድ አልፈቀደም ነበር ወይም በተራራው ላይ የትም ቦታ መታየት እንደሌለባቸው ተናገረ ፤ ከዚያም ሙሴም የድንጋዮቹን ፅላት በመያዝ ከእግዚአብሄር ጋር ለመገናኘት ወደ ተራራው ወጣ ፡፡
ዘጸዓት(34፡ 5-7); እግዚአብሄር በደመና ውስጥ ሙሴን ለመገናኘት መጣ ፤ በተደጋጋሚ እግዚአብሄር በደመና ውስጥ ተገለጠ ፡፡ ነፃ አውጪው ህዝቡን ነፃ ወዳ ወጣው ወደ መሲሁ አመለከተ ፤ ዮሐ(1፡ 14) የሚለው “ ቃልም ስጋ ሆነ በእኛም አደረ”(ኢሰቪ) ፡፡ እግአብሄር ከሙሴ ጋር ተገናኘ ያህዌ የሆነውን ስሙንም አወጀ ፤ ይህ ጥምቀት ነበር- ሰዎችን ለማግኘት በታላቅ ዘር የእግዚአብሄር መልክ ነበር ፡፡
እግዚአብሄር በሙሴ ፊት ባለፈ ጊዜ ባህሪውን ገልጦለታል; መሀሪ፣ ደግ፣ ታጋሽም፣ ባለብዙ ቸርነትና ፍቅር፣ የሚታመን ፍቅርን የሚጠብቅ; ስህተትን፣ በደልንና ኃጢዓትን ይቅር የሚል; ጥፋተኛን ሳይቀጣ አይተውም ፡፡ ቆይቶ ሙሴ ይህን የእግዚአብሄርን መገለጫዎች ከእስራኤላዊያን ጋር በቃዴስ በፉራን ምድረበዳ አካፈላቸው(ዘኁ14፡17-19) ፤ አይሁዶች እግዚአብሄርን ለመግለፅ ይህንኑ ተመሳሳይ ንግግር(ቐናቐ) በነህ(9፡ 17-18) ተጠቅመውበታል ፡፡ እግዚአብሄር ነንዌን ይቅር ሊል በመረጠ ጊዜ ዮናስ ሲናገር “ አንተ ቸርና ይቅር ባይ ታጋሽም ምህረትህም የበዛ ከክፉው ነገርም የተነሳ የምትፀፀት አምላክም እንደ ሆንህ አውቄ ነበርና “(ዮና 4፡2) ፡፡ “እግዚአብሄር ረጅም ባልቦላ(ትዕግስት) አለው” ፤ እግዚአብሄር ምህረቱን ለማሳየት ፍቃደኛ ነው ነገር ግን ቁጣውም ይገለጣል ፡፡
ዘጸዓት(34፡ 8-9); ወዲያውኑ ሙሴ በመታዘዝ በመደፋት አመለከ(ሰገደ) ፡፡ ሙሴ የእግዚአብሄር መገኝት አብራአቸው እንዲሄድና ለኃጢዓታቸው ይቅርታ መፀለዩን ቀጠለ ፤ ስለ እግዚአብሄር ሰዎች እግዚአብሄር እንዲፀፀትና ሀሳቡን እንዲቀይር ማለደ ፡፡ ሙሴ ራሱን ከህዝቡ አለየም; ራሱን የህዝቡ አካል አድርጎአል ፤ ዕዝ(ምዕ 9)፣ ዳን(ምዕ9) እና ነህ(ምዕ 1) ሁሉም ጩኸቶች ስለ ህዝቡ ወደ እግዚአብሄር የተደረጎ ነበሩ ፡፡ ከህዝቡ የተለዩ ማንኛውንም መሪዎች ተጠንቀቁ ፤ ሙሴ ያንን አላደረገም ፤ ኢየሱስም ያንን አላደረገም ፡፡
ዘጸዓት(34፡ 10-14); እግዚአብሄር ለእስራኤል በፍፁም ያላደረገውን ድንቅ ሊያደርግ ኪደና አደረገላቸው “ በምድር ሁሉ በአህዛብም በአህዛብም ሁሉ ……..እኔም በአንተ ዘንድ የምሰራው ነገር የሚያስፈራ ነውና”(ቁጥር 10) ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤል እንደ ሚለምደ “ የሚያስደንቅ ነገር እርሱም የከንዓን አያያዝ” ቃል ገባ ፤ ነገር ግን በተጨማሪ እግዚአብሄር እስራኤል ከእርሱ ጋር በኪዳን እንዲኖር መምሪያ ሰጠ ፡፡ በዚያ ምድር ከሚኖሩት ጋር ስምምነት(ግንኙት) እንዳያደርጉ ተከለከሉ ምክንያቱም ለእስራኤል ወጥመድ እንዳይሆኑበት(ቁጥር 12) ፤ በዚያ ፋንታ እስራኤል የጣዖት መሰዊያዎቻቸውን እንዲሰብር፣ የእነርሱን ጣዖቶች እንዳይቀበልና እግዚአብሄርን ብቻ እንዲያመልክ ተጠየቀ ምክንያቱም እግዚአብሄር ቀናተኛ አምላክ ነው (ቁጥር 14) ፡፡ ዋይሰርቤ ያመለከተው “ እንደ በሰው አካል ላይ ያሉ የካንሰር እብጠቶች፣ የጣኦት አምላኪ ሰዎችን መቅደሶችና መሰዊያዎች አስወገደውና አጥፍተው ነበር ምድሪቱ ጤነኛ ከመሆና በፊት ፡፡“
ዘጸዓት(34፡ 15-16); የመጀመሪያው መመሪያ; እስራኤላዊያን ከምድሪቱ ነዋሪዎች ጋር ስምምነት እንዳያደርጉ ተከለከሉ ይህ በመጨረሻ የእነርሱን አምላክ እንዲያመልኩ ስለሚመራቸው ፤ ይህ ከወርቅ ጥጃው ጋር የተፈጠረውን ይመስላል ፤ በበርሃ እያሉ እስራኤላዊያን ወደ ድሮ የአናናር ዘይቤአቸው ተመለሱ ፡፡ ሀተታ ሰጪው ኔልሰን እንደ ተናገረው “ ጋብቻ ማድረግ ፈጣኑ መንገድ ለሀሰተኛ አምላክና መጥፎ ባህርይ አስታራቂ ሀሳብ ይሆናል፡፡”
ዘጸዓት(34፡ 17-20); ሁለተኛው መመሪያ; እስራኤላዊያን ለእግዚአብሄር ብቻ እንዲሰግዱ ታዘዙ ፤ “የተቀረፁ የአምላክ ምስሎች” እንዳይሰሩ ተከለከሉ እናም እግዚአብሄር ከግብፅ እንዴት እንዳወጣቸው እንዲያስታውሱ የቂጣን በዓል እንዲያከብሩ ታዘዙ ፡፡ እግዚአብሄር ያደረገላቸውን በማክበር እርሱ ላይ ትኩረት ያደርጋሉ ፡፡
ዘጸዓት(34፡ 21-26); በሰባተኛው ቀን ከስራቸው እንዲያርፉ ታዘዙ “የእርሻና የመኸር ጊዜ” ቢሆንም እንካን ፡፡ ምንም እንካን ብዙ የሚሰራ ስራ ቢኖራቸውም ሰንበት የበዓል አይነት ነበር ! የሳምንት በዓል የሚከበረው በበኩር ስንዴ በተሰበሰበውና ሁሉንም የመሰብሰብ በዓል የሚከበረው በግብርና አመቱ ይሆናል ፤ፋሲካ ከግብፅ ነፃ መውጣታቸውን ያስታውሳቸዋል ፡፡ ለእነዚህ በዓል በተሰበሰቡ ጊዜ እግዚአብሄር ምድራቸውን እንደሚጠብቅ ቃል ገባላቸው ፡፡ እስራኤላዊያን ወደ እግዚአብሄር እንዲመለከቱ የሚያስታውሱ አመልካቾች ያስፈልጋአቸው ነበር ፡፡
ዘጸዓት(34፡ 27-28); እግዚአብሄር ሙሴን ከእስራኤል ጋር ያደረጋቸውን የእርሱን ኪዳኖች “አነዚህን ቃሎች” እንዲፅፋቸው አዘዘው ፤ የሙሴያዊ ኪዳን ተመሰረተ ፡፡ ሙሴ ከእግዚአብሄር ጋር ሳይበላም ሳይጠጣም በተራራው ላይ 40ቀንና 40ሌሊት አሳለፈ በዚህ ጊዜ እግዚአብሄር አስሩን ትዕዛዝ በፅላቱ ላይ ፃፈ ፡፡
ዘጸዓት(34፡ 29-30); ሙሴ ከእግዛብሄር ጋር እንደ ነበር አላገናዘበም ነበር የእግዚአብሄር ክብር በፊቱ ላይ በህይወቱም ልይ አንፀባረቀ ፤ ነገር ግን እስራኤላዊያን ወደ እርሱ ቀርቦ ለመምጣት ፈሩ ምክንያቱም “ ተፊቱ ቁርበት አንፀባረቀ ”(ቁጥር 30) ፡፡ ይህ እኔን ኢየሱስ በተራራው ላይ ራሱን የቀየረበትን እንዳስብ ነው ያደረገኝ (ማቴ 17፡1-2) ፤ የኢየሱስ ፊት እንደ ፀሀይ አንፀባረቀ !
ዘጸዓት(34፡ 31-33); ነገር ግን ሙሴ ጠራቸው የፃፈውንም እያንዳንዱን ነገር ነገራቸው ፡፡ ቃለ ምልልሱ ምን ያህል ጊዜ ነበር ? 2ሚሊዮን ህዝብ ለመሰብሰብ ሙሴ እንዴት አደረገ እና እንዴትስ ሊሰሙት ቻሉ ? ስለዚህም ሙሴ በፊቱ ላይ መሸፈኛ አስቀመጠ ፡፡
ዘጸዓት(34፡ 34-35); ሙሴ ከእግዚአብሄር ጋር ሲገናኝ መሸፈኛውን ያስወግደው ነበር ፤ በሚያንፀባርቅ ፊቱ ወደ ህዝቡ ይመለሳል እግዚአብሄርም ያዘዘውን ለህዝቡ ይነግራቸዋል ፤ መልሶ መሸፈኛውን ያስቀምጠዋል እግዚአብሄር ጋር እንደ ገና ለመነጋገር እንደገና እስኪሄድ ድረስ ስለዚህ ህዝቡ የደበዘዘውን ክብር ማየት አልቻሉም ፡፡
በ 2ቆሮ(3፡ 7-18) ጳውሎስ ይህን ትክክለኛ መስተጋብር አድርሳአል ፤ “የሞት አገልግሎት”(ቁጥር 7) አስሩ ትዕዛዝ(የሙሴያዊ ኪዳን) ነበር ፡፡ ክብሩ ከሙሴ ፊት ላይ ደበዘዘ ምክንያቱም ከእግዚአብሄር መገኘት ስለሚሄድና ስለሚመጣ (ቁጥር 7) ፤ “ የኩነኔ አገልግሎት ክብር ከሆነ ይልቀ የፅድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና”(ቁጥር 9) ፡፡ እነዚህ በአድስ ኪዳን ወደ እምነት የመጡት የእግዚአብሄርን ክብር ይለማመዳሉ ፤ “ ወደ ጌታ ግን ዘወር ባለ ጊዜ ሁሉ መጋረጃው ይወሰዳል….እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስታዎት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን”(ቁጥር 16, 18) ፡፡ መጋረጃው በክርስቶስ ተወገደ ነው !
መዝጊያ
ወደ አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተመለስን ጊዜ መጋረጃው ተነስታአል ! ወደፊትና ወደኃ እና ወደፊትና ወደኃላ አንሄድም ፤ በኢየሱስ ክርስቶስ መገኝት ውስጥ ከሆንን ክብሩ በፍፁም አይተወንም ፡፡
Michael P. Knowles, The Unfolding Mystery of the Divine Name: The God of Sinai in Our Midst (Downers Grove, IL: InterVarsity Press, 2012), p. 98.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 144.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 248.
Radmacher, Allen, and House, eds., 145.
ጥያቄዎች
-
ዘጸ 34 መጀመሪያ ላይ እግዚአብሄር ሙሴን ልክ በዘጸ(32፡ 19) ሙሴ እንደ ሰበረው አይነት ሁለት የድንጋይ ፅላቶች እንዲቆርጥ(እንዲያዘጋጅ) አዘዘው ፤ እግዚአብሄር መጀመሪውን ራሱ እንዳዘጋጀ ይህን ለምን ራሱ እንዳላዘጋጀ ምን ታስባላችሁ (ዘጸ32፡ 16) ? በእነዚህ ድንጋዮች ላይ የተፃፉት ቃላቶች እንዴት ነበር የሚጠቃሙት (ዘጸ 25፡ 21; 31፡ 18; 34፡ 28) ?
-
በዘጸ(34፡ 6-7) ላይ እግዚአብሄር በሙሴ ፊት እንደሚያልፍ ራሱ ገለፀ ፤ በዚህ አገላለፅ ውስጥ ስለ እግዚአብሄር አሁን በህይወታችሁ ውስጥ እንዳታምኑ አስቸጋሪ የሆነባቹሁ ነገር አለ ?
-
በዘጸ(34፡ 40) መጨረሻው ላይ እግዚአብሄር የሚያስፈራ ነገር እንደሚያደርግ ሙሴን ነገረው (ናስብ) ፤ ሌላ ትርጉም የሚጠቅሙ ቃላቶች የሚያስገርም፣ አስፈሪ፣ የሚያስደንቅ እና የሚያስደነግጥ ፡፡ ይህ መልዕክት በእግዚአብሄር ለእናንተ ቢሆን ያስፈራችኃል ? አዎ ከሆነ ለምን ? አያስፈራኝም ከሆነ ለምን ?
-
በዘጸ(34፡ 29-35) ፅሁፉ የሚገልፀው የሙሴ ፊት አበራ ምክንያቱም በእግዚአብሄር መገኘት ውስጥ ስለነበር(ከእግዚአብሄር ጋር ስለተበጋገረ) ፤ ሙሴ እፊቱ ላይ ለምን መሸፈኛ አስቀመጠ ምን ታስባላችሁ (ዘጸ34፡ 30; 33; 2ቆሮ 3፡ 13-16)?
-
ዘጸ(35፡ 30-33) አንብቡ ፤ ባስልኤል በእግዚአብሄር መንፈስ ከፍተኛ የጥበብ ችሎታ ተሰጠው ፡፡ በህይዋታችሁ ውስጥ የምታውቁአቸው ችሎታዎች ምንድን ናቸው ? አነዚህ ችሎታዎች ከእግዚአብሄር እንደመጡ ግንዛቤው አላችሁ (ዘጸ31፡ 6; 36፡1) ?
-
በዘጸ(34-35) በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 34:29
"As Moses descended from Mount Sinai—with the two tablets of the testimony in his hands as he descended the mountain—he did not realize that the skin of his face shone as a result of his speaking with the LORD.”
አዲስ የድንጋይ ፅላቶች
ኦሪት ዘፀዓት 34-35
የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
ሙሴ፥ ሌሎች አርባ ቀኖች እና ሌሊቶች ከእግዚዓብሔር ጋራ በሲና ተራራ ላይ አሳልፏል። በዚህ ጊዜ፥ ምንም ሳይጠጣ እና ሳይበላ ፆሞ ነበር። ሙሴ እግዚዓብሔርን እያናገረ እና እየሰማ ከእርሱ ጋራ ጊዜ አሳለፈ። መሴ ከተራራዉ በወረደ ጊዜ፥ የእግዚዓብሔር ክብር እና ሃልዎት ጋራ ስለተገናኘው ፊቱ ያንፀባርቅ ነበር።
በእግዚዓብሔር ህልዉና፣ ቃሉን በማጥናት፣ በፀሎት እና እርሱን በመስማት ጊዜ የምታጠፋ ከሆነ ትለወጣለህ። ዋናዉ ቁልፍ ነገር ሃሳብን ከሚበታትኑ የዚህ ዓለም ነገሮች ዘወር ብሎ ከእግዚዓብሔር ጋራ ጊዜ ማሳለፍ ነዉ። እግዚዓብሔር የለዉጥ አምላክ ነዉ! የተወሰነ ጊዜ ሊወስድ ቢችልም፥ ከክርስቶስ ጋራ ብዙ በኖርክ ቁጥር፤ እርሱን እንድትመስል እየተሰራህ፥ ክብሩን እና ፍቅሩን የምታንፀባርቅ ትሆናለህ።
"እንዲህም ሆነ፤ ሙሴ ከሲና ተራራ በወረደ ጊዜ ሁለቱ የምስክር ጽላቶች በሙሴ እጅ ነበሩ፤ ሙሴም ከተራራው በወረደ ጊዜ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ስለ ተነጋገረ የፊቱ ቁርበት እንዳንጸባረቀ አላወቀም ነበር።"
ኦሪት ዘፀዓት 34:29
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የሐዋርያት ሥራ 4:13፦ "ጴጥሮስና ዮሐንስም በግልጥ እንደ ተናገሩ ባዩ ጊዜ፥ መጽሐፍን የማያውቁና ያልተማሩ ሰዎች እንደ ሆኑ አስተውለው አደነቁ፥ ከኢየሱስም ጋር እንደ ነበሩ አወቁአቸው፤"
- ወደ ሮሜ ሰዎች 12:2፦ "የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።"
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 3:18፦ "እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 47
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።