Moses Intercedes for the People
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 32-33 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሁሉም ዘጸዓት ውስጥ መሲሁ ለመግለፅ የተጠቀምነው ቃል ነፃ አውጪ ነው ፤ለምን ? ምክንያቱም ኢየሱስ ብቻውን ህዝቡን ከግብፅ ባርነት ነፃ እንዳወጣቸው ስለምናምን ፡፡ ይሁ 5 የሚለው “ ዳሩ ግን ሁሉን አንድ ጊዜ ፈፅሞ ምንም የተማራችሁ ብትሆኑ ጌታ ከግብፅ አገር ህዝቡን አድኖ የማያምኑትን በኃላ እንዳጠፋቸው ላሳስባችሁ እወዳለሁ ፡፡” ሙሴ ከአምላክ የተቀበለውን ከሁሉም ትዕዛዝጋር በእግዚአብሄር ጣት በፅላቱ ላይ የተፃፈውን ይዞ ከተራራው ወረደ፡፡ ነገር ግን በዚህ ጊዜ እስራኤላዊያን ትዕጋስት አጥተው ስለነበረ የወርቅ ጥጃ ሰሩ ፡፡
ትምህርት
ለፈጣን ማጠቃለያ ዘጸዓት 32; አሮን እስራኤላዊያንን ከግብፃዊያን ወስደውት ከነበረው ጌጥ የወርቅ ጥጃውን በመቅረፅ(በመንደፍ) እንዲሰሩ መራቸው ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያን የወርቅ ጥጃ እያመለኩ ባየ ጊዜ በጣም ተበሳጨ እስራኤላዊያንንም ሊያጠፋና ከሙሴ ጋር ሌላ ሊጀምር ፈለገ (ቁጥር 10) ፤ ሙሴ ልክ እንደ ክርስቶስ አይነት ሚና ተጫወተ ለህዝቡ ከእግዚአብሄር ምህረት ጠየቀ(ማለደ) (ቁጥር 11) ፡፡ ሙሴ ከተራራው በወረደና ጥጃውን እና እስራኤላዊያን በጥጃዉ ፊት ሲደንሱ ባዬ ጊዜ በእግዚአብሄር ጣት የተፃፈውን ፅላት ሰበረው (ቁጥር 19) ፡፡ ሙሴም “ለእግዚአብሄር የሆነ” ከእርሱ ጋር እንዲቆሙ ተጣራ ከዚያም ሌዋዊያን በዙሪያው ተሰበሰቡ ፤ ሙሴም ሌዋዊያንን ወንድሞቻቸውን፣ ጋደኞቻቸውንና ጎረቦቶቻቸውን እንዲገድሉ አዘዛቸው ; 3000 ወንዶች በሞት ተመቱ (ቁጥር 27-28) ፤ ከዚያም እግዚአብሄር “ አሮን የሰራውን ጥጃ ስለ ሰሩ እግዚአብሄር ህዝቡን ቀሰፈ”(ቁጥር 35) ፡፡ ኃጢዓት ሁል ጊዜ የሚወስደው ወደ ሞት ነው (ሮሜ 3፡ 23; 1ዮሐ 5፡ 16-17) ! ሁለተኛው ፍርድ ዘጸዓት 33 ላይ ነው; እግዚአብሄር በጉዞአቸው ከእስራኤላዊያን ጋር ወደ ተስፋይቱ ምድር መሄድ አልፈለገም ፡፡
ዘጸዓት(33፡ 1-2); እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን “ አንተ(ሙሴን) ከግብፅ ያወጣኸው ህዝብ” ብሎ በመጥቀስ አስታወቀው ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን ለአብርሃም፣ ለይስሐቅና ለያዕቆብ የገባውን የሱን ቃል በእስራኤላዊያን አመፅ መሀከል እንካን አስታወሰው ፡፡ እግዚአብሄር ከእነርሱ ፊት ህዝቡን ምድሪቱ ውስጥ የሚያስገባ “መልዓክት” እንደ ሚልክ ቃል ገባላቸው ፤ ነገር ግን ይህ መልዓክ የእግዚአብሄር መልዓክ አልነበረም ፡፡
ዘጸዓት(33፡ 3-6); እግዚአብሄር ስለተናደደ ከእስራኤል ጋር አልሄደም ምክንያቱም እሱ “ በመንገድ ላይ እንዳላጠፋህ”(ቁጥር 3) ፤ ኃጢዓት በእግዚአብሄር እና በእስራአል መሀከል አጥር(አጋጅን) ፈጠረ ፤ እስራኤላዊያን ይህን በሰሙ ጊዜ አዘኑ ጌጣቸውንም አላደረጉም ፤ ምናልባት ከግብፅ ከወሰዱት ጌጥ ጥጃ ለመስራት ያልተጠቀሙበትን ቀሪው ነበር(ይሆናል) ፡፡ መጨረሻ ላይ የወርቅ ጥጃውን በድፍረት ስላመለኩ እግዚአብሄር ለህዝቡ የሚገባውን አደረገ ! ከእነርሱ ጋር ምን እንደሚሰራ እስኪወስን ድረስ እግዚአብሄር ከእነርሱ ተለይቶ ቆየ ፡፡
ኢሳ(59፡ 2) የሚለው “ ነገር ግን በደላችሁ በእናንተና በአምላካችሁ መካከል ለይታለች እንዳይሰማም ኃጢዓታችሁ ፊቱን ከእናንተ ሰውሮታል “(2ተሰ 1፡ 9) ፡፡ በዚህ በብሉይ ኪዳን አስተሳሰብ በኃጢዓት ምክንያት ከእግዚአብሄር መገኘትና ታለቅ ጥንካሬ የማያቆም መለየት ቅጣት ነበር ፤ ነገር ግን በአድስ ኪዳን ዘመን እግዚአብሄር በኢየሱስ ካለው ፍቅር ማንም ሊለየን አይችልም (ሮሜ 8፡ 38-39) !
ዘጸዓት(33፡ 7-11); የእግዚአብሄር በእስራኤል ላይ ሰዎስተኛው ፍርድ የመገናኛ ድንካኑን ከእስራኤላዊያን መኖሪያ ካንፕ ዉጪ እንዲሰራ ለሙሰ ተናገረው ፤ (ይህ ያልተገነባው ቤተ አምልኮቱ አልነበረም) እግዚአብሄር ከእስራኤላዊያን ርቆ በራሱ በውጪ ተጋአዘ ፡፡ በድንካኑ ውስጥ እግዚአብሄርን ኢንዲያገኘው ሙሴ ተፈቀደለት ነገር ግን እስራኤላዊያን የሚችሉት ሙሴ ወደ ድንካኑ ሲገባ ማየት ብቻ ሲሆን ከዚያም የዳመና አምድ ወደ ታች በመምጣት የድንካኑን መግቢያ ይሸፍነዋል ፡፡ ሀሚልተን ሲናገር “ ሙሴ በተነሳ ጊዜ እግዚአብሄር(በአምድ) ወደ ታች ይመጣል”፤ ምናልባት የደመና አምዱን ባዩ ጊዜ እግዚአብሄር ለእነርሱ ያደረገላቸውን እያንዳንዱን ነገር ያስታውሳሉ ፡፡ መቼም ቢሆን የደመናውን አምድ ሲያዩ እግዚአብሄር “ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነጋገር ነበር”(ቁጥር 11) በዚህ ጊዜ በራሳቸው ድንካን በር ላይ በአምልኮ ይደፉ ነበር ፡፡ ሌሎች ምንባቦች የሚገልፁት በእግዚአብሄርና በሙሴ መሀከል ያለውን ይህን ጋአደኝነት ነው ፡፡ ዘዳ(34፡ 10) የሚለው “ እግዚአብሄር ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነብይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሳም ፡፡“ ሙሴ እግዚአብሄርን በሚያገኝበት ጊዜ ኢያሱ በመገናኛ ድንካኑ ውስጥ ይቆይ ነበር ፤ እየተማረ ነበር፣ በእግዚአብሄርም መገኘት ይረሰርስ ነበር ፡፡
ዘጸዓት(33፡ 12-13); ሙሴ ለእስራኤል መማለዱን ቀጠለ ይህ በሉቃ(18፡ 1-8) ያለችውን መበለት ያስታውሰኛል በዳኛው ፊት ያደረገችውን የፀና ጥያቄዋን ፤ አባታችን ሊባርከን ይፈልጋል; ጥያቄው “ እንጠይቃልን ወይ ?” ሙሴ “ይህ ሕዝብ የአንተ ህዝብ “ መሆኑን ለማስታወስ ሙሴ ለእግዚአብሄር መለመለ ፡፡ ሙሴ የሚያስደንቅ ምሳሌ ነበር በፀሎት እንዴት ከእግዚአብሄር ጋር እንደሚስማማ ፤ እግዚአብሄርን ሙሴ “ እባክህን መንገድህን አሳየን” ብሎ ጠየቀው ፤ መዝ 103 ፡7 የሚለው እግዚአብሄር የሙሴ ፀሎት የመለሰለት “ ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ ለእስራኤል ልጆችም አደራረጉን ፡፡”
ዘጸዓት(33፡ 14-17); እግዚአብሄር ሲናገር “ እኔ ከአንተ ጋር እሄዳለሁ አሳርፍህማለሁ “ ፤ “መገኘት” የሚለው ቃል “ፊት “እና “እረፍት” ማለትም ተስፋይቱ ምድር በሚለው ቃል ሊተካ የሚችል ነው ፡፡ ሙሴ ከእግዚአብሄር ጋር ያለውን ቃለ ምልልስ በመገኘትህ ምክንያት እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ካልወጣህ በስተቀር ሌሎች ህዝቦች እስራኤል የእግዚአብሄር ህዝብ እንደሆነ አያውቁም በማለት ቀጠለ “የታወቀ” እስራኤል ከ” በምድርም ፊት ካለው ህዝብ ሁሉ”(ቁጥር 16) ፡፡ እግዚአብሄር ከእስራኤል ጋር እንደሚሄድ ቃል ገባላቸው ምክንያቱም ሙሴ በእግዚአብሄር እይታ ሞገስ አገኘ እግዚአብሄርም በስሙ አወቀው ፡፡ እግዚአብሄር እያንዳንዳችንን በስማችን ያውቀናል ፤ ስለእኛ እያንዳንዱን ነገር ያውቃል ፡፡
ዘጸዓት(33፡ 18); ሙሴ የእግዚአብሄርን ክብር ለማየት ጠየቀ ፤ “ክብር” ማለት “ቅዱስነት” ማለት ነው ፡፡ ሙሴ እግዚአብሄርን በፍፁም ከዚህ በፊት እግዚአብሄርን እንደተለማመደው ሳይሆን በተለየ ለመልመድ ፈለገ ፡፡ ሙሴ በመጀመሪ እግዚአብሄርን በሚነድደው ቁጥቐጦ ውስጥ ባገኘው ጊዜ ጫማውን በማውለቅ የእግዚአብሄርን ክብር ተለማመደ ነገር ግን ፊቱን ሸፈነ “ምክንያቱም ወደ እግዚአብሄር ያይ ዘንድ ፈርታአልና” (ዘጸ 3፡ 1-6) ፡፡ አሁን በይበልጥ ፈለገ !
ዘጸዓት(33፡ 19-23); እግዚአብሄር በሙሴ ፊት እንደሚያልፍና በእርሱ ፊት ያህዌ የሚለውን ስም እንደሚያውጅ ተናገረው ነገር ግን ለሙሴ በተጨማሪ “ ሰው አይቶኝ አይድንምና ፊቴን ፊቴን ማየት አትችልም” አለው ፤ መሳ(13፡ 22) የተፃፈው የሳምሶን አባት እሱና ሚሰቱ የእግዚአብሄርን ፊት አይተው ነበርና እናዳይ ሞቱ ፈራ ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን አለቱ ላይ እንዲ ቆም ነገረው ፤ እግዚአብሄር በዚያ እስኪያልፍ ድረስ ሙሴን በአለቱ ስጥቅ ውስጥ እንደ ሚያስቀምጠው ሙሴን ተናገረው ከዚያም እጁን ሲያነሳለት ሙሴ የእርሱን ጅርባውን ማየት ይችላል ፡፡ እግዚአብሄር ፊቱ እንዲታይ አልፈቀደም ፡፡ እግዚአብሄር ለሙሴ ክብሩን እንዲቀምሰው(እንዲለምደው) ፈቀደለት ግን ሁሉንም አይደለም ፡፡
ሙሴ ያሳየን የእግዚአብሄርን ፊት ስንፈልግ ይመልስልናል ፤ የእግዚአብሄርን ፊት የምንፈልገው የት ነው ? እንዴትስ የእግዚአብሄርን መገኘት እንፈልጋለን ? የእግዚአብሄርን ፊት እንድንፈልግ የሚጋብዙን መፅሀፍት
1ዜና 16፡ 11; “እግዚአብሄርን ፈልጉት ትፀናላችሁም ፤ ሁል ጊዜ ፊቱን ፈልጉ”
2ዜና 7፡ 14; “በስሜ የተጠሩት ህዝቤ ሰውነታቸውን አዋርደው ቢፀልዩ ፊቴንም ቢፈልጉ ከክፉ መንገዳቸውም ቢመለሱ በሰማይ ሆኜ እሰማለሁ ኃጢዓታቸውንም ይቅር እላለሁ ምድራቸውንም እፈውሳለሁ ፡፡”
መዝ 27፡ 8; “አቤቱ ፊትህን እሻለሁ”
መዝ 105፡ 4; “ እግዚአብሄርን ፈልጉት ትፀናላችሁም ሁል ጊዜ ፊቱን ፈልጉት፡፡”
መዝጊያ
እግዚአብሄር ለሙሴ በአለት ውስጥ በማስገባት በመጠበቅ ሁሉን ቻይ በሆነው ኃይሉ እራሱን ገለጠለት፡፡ ሙሴ በጥሩ ደከመ ፤ በህዝቡ ሰለቸም በህዝቡ ጥያቄና ባደረጉት ስህተት ነገር ደከመ ፤ ይሁን እንጂ እስካሁን ስለ እነርሱ ፀለየ(ማለደ) ፡፡ ዋይሰርቤ ሲናገር “ የእግዚአብሄር አገልጋዮች በህዝባቸው ኃጢዓት ምክንያት ተስፋ በሚቆርጡና በሚበሳጩ ጊዜ ተመራጩ መሰራት ለተሰበረው ልብ ለእግዚአብሄር ክብር አድስ ራዕይ ነው ” ፤ ብስጥትን(ቅሬታን) ለማሸነፍ የእግዚአብሄር ክብር መውሰድ ያስፈልገናል ፡፡
ሙሴ እስኪ ማልድና የእግዚአብሄርን ክብር ለመልመድ በአለቱ ላይ እስኪ ቆም ድረስ ነገሮች ቆሽሸው ነበር ፡፡ በአድስ ኪዳን ለዛሬ(በዚህ ጊዜ) ፈጣን መልስ ፡፡ የመነሳሳት መድኃኒት የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ ወደ እግዚአብሄር ፊት በመሄድ ክብሩን እስክትቀምሱት(እስክትለምዱት) ድረስ መፈለግ ያስፈልጋችኃል ፤ ነገር ግን ሁል ጊዜ ልክ ለሙሴ እንደሆነው አይሆንም ፤ በ1ነገ (19፡ 11-12) ኤልያስ በአለት ዋሻ ውስጥ በሚጠብቅበት ጊዜ እግዚአብሄር በንፋሱ ውስጥ ወይም በመሬት መንቀጥቀጡ ውስጥ ወይም በእሳቱ ውስጥ አልነበረም ; በሹክሽክታ ድምፅ ውስጥ ነበር ፡፡
Victor P. Hamilton, Exodus: An Exegetical Commentary (Grand Rapids: Baker Publishing Group, 2011), p.
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 247.
ጥያቄዎች
-
አሮን የወርቅ ጥጃ የመስራቱን መንገድ ለምን መራ ? የእግዚአብሄር ምላሽ ምንድን ነበር(ዘጸ 32፡ 7-10) ?
-
ሙሴ በኃጢዓታቸው ምክንያት ለህዝቡ ሁለት ጊዜ ማለደ(ዘጸ 32፡ 11-13; 31-32) ፤ የእግዚአብሄር መልስ ምን ነበር ? ለሌሎች የመማለድ(የመፀለይ) ልምድ አላችሁ ? የለንም ከሆነ እንዴት አስቸገራችሁ ?
-
በዘጸ(32፡ 32) ሙሴ እግዚአብሄርን የህዝቡን ኃጢዓት ይቅር የማይል ከሆነ ከህይወት መፅሀፉ ላይ ስሙን እንዲያጠፋ ነገረው ፤ የሙሴን መንፈሳዊ ባህሪይ ይህ እንዴት ይናገራል ? በሮሜ(9፡ 3) ጳውሎስ ተመሳሳይ ልብ ነበረው ፤ ለጠፈው የጠለቀ ርህራሄ እንዲኖራችሁ የሙሴና የጳውሎስ ድርጊት እንዴት ሊያስገድዳችሁ ይቻለዋል ? የሙሴ ወይም የጳውሎስ እምነት አላችሁ በእናንተ ተፅዕኖ ዙሪያ ላሉት በእግዚአብሄር ተመሳሳይ መልስ(ክስ) ለመስረት ?
-
በዘጸ(33፡ 3) እግዚአብሄር ሙሴን ለእነርሱ ቃል ወደ ተገባችው ምድር እሱና ህዝቡ መሄድ እንደ ሚችሉ ነገረው ነገር ግን እግዚአብሄር ከእነርሱ ጋር አይሆንም ፤ ይህንን ባነበባችሁ ጊዜ የመጀመሪያ ምላሻችሁ ምን ነበር ? የሙሴን መልስ በዘጸ(33፡ 15) አንብቡ ፤ አዚህ በምድር ላይ እስካሁን ትፈልጉት ወይም ትመኙት የነበረው ሁሉም ነገር የእናንተ መሆን ቢችል ግን እግዚአብሄር ባይኖር ልትረኩ ትችላላችሁ ? አዎ ከሆነ ለምን ? አልከካም ከሆነ ለምን ?
-
በዘጸ(33፡ 7) ላይ ህዝቡ እግዚአብሄርን ማግኘት ከፈለጉ እንዲያደርጋአቸው የታዘዙት ምንድን ነበሩ ? ሙሴ የመገናኛ ድንካኑን ከሰፈሩ ለምን እንዳራቀው ምን ታስባላችሁ ?
-
በዘጸ(33፡ 21-22) ላይ እንደተጠቀሰው አለት ክርስቶስን እንዴት ማየት እንችላለን ?(መዝ 118፡ 22; 1ጰጥ2፡ 4)
-
በዘጸ(32-33) ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 33:11a
“The LORD spoke with Moses face to face, just as a man speaks with his friend.”
ሙሴ፥ ስለህዝቡ ማለደ
ኦሪት ዘፀዓት 32-33 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
የወርቅ ጥጃን መሥራት መርጠዉ እና ስላመለኩ፥ የእግዚዓብሔር ቁጣ በእስራኤላዉን ላይ በተነሳ ጊዜ፥ እግዚዓብሔር እና መሴ እንደ ጓደኛ ፊት ለፊት ተጋናኝተዉ ግልጽ የሆነ ንግግር አድርገዋል። የእርሱ ሃዘን እንዳለ ሆኖ፥ ሙሴን እና ህዝቡን በቀጣይነት በመምራት እና ነፃ በማዉጣት፥ እንደዉም ከቀድሞ የተሻለ ቅርብ ፍቅር አሳይቷል።
ብዙ ጉድለት ቢኖርብህም እንኳን እግዚዓብሔር በጥልቅ ፍቅር ይወድሃል! እግዚዓብሔር ከአንተ እየራቀ በሚመስልበት ጊዜ እንኳ ወደ እርሱ በምትቀርብበት ጊዜ እርሱም ወደ አንተ ይቀርባል። እግዚዓብሔር፥ ግላዊ፣ ግልፅ፣ ፊት ለፊት በሆነ መንገድ እንድታዉቀዉ ይናፍቃል። እግዚዓብሔርን ልክ ጓደኛህ እንደሆነ ታናግረዋለህ? እግዚዓብሔርን በመከተል እና ከእርሱ ጋራ በማዉራት ጊዜ የምታጠፋ ከሆነ ወደ እርሱ እየተቀራረብክ እንደ ጓደኛ ትሆናለህ።
"እግዚአብሔርም ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር ፊት ለፊት ከሙሴ ጋር ይነጋገር ነበር። ሙሴም ወደ ሰፈሩ ይመለስ ነበር፤ ነገር ግን ሎሌው ብላቴና የነዌ ልጅ ኢያሱ ከድንኳኑ አይለይም ነበር።"
ኦሪት ዘፀዓት 33:11
ተጨማሪ ጥቅሶች
- የዮሐንስ ወንገል 15:12-15፦ "እኔ እንደ ወደድኋችሁ እርስ በርሳችሁ ትዋደዱ ዘንድ ትእዛዜ ይህች ናት። ነፍሱን ስለ ወዳጆቹ ከመስጠት ይልቅ ከዚህ የሚበልጥ ፍቅር ለማንም የለውም። እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ። ከእንግዲህ ወዲህ ባሮች አልላችሁም፤ ባርያ ጌታው የሚያደርገውን አያውቅምና፤ ወዳጆች ግን ብያችኋለሁ፥ ከአባቴ የሰማሁትን ሁሉ ለእናንተ አስታውቄአችኋለሁና።"
- የያዕቆም መልዕክት 2:23፦ "መጽሐፍም፦ አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት ያለው ተፈጸመ፤ የእግዚአብሔርም ወዳጅ ተባለ።"
- የያዕቆብ መልዕክት 4:8፦ "ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 46
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።