Skilled Workers & the Sabbath
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 30-31 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ሙሴ 40 ቀን ከእግዚአብሄር ጋር ከተገናኘ ቦኃላ ለቤተ መቅደሱ ሁሉንም የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ ተቀበለ ፡፡ እንደ ዘጸ(29፡ 45-46) ይህ ቤተ መቅደስ በጣም ጠቃሚ ነበር ምክንያቱም እግዚአብሄር ሲናገር “ በእስራኤልም ልጆች መካከል እኖራለሁ አምላክም እሆናቸዋለሁ ፤ በመካከላቸውም እኖር ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኃቸው አምላካቸው እግዚአብሄር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ እኔ አማላካቸው እግዚአብሄር ነኝ ፡፡” በዚህ መቅደስ ውስጥ ከእነርሱ ጋር የእግዚአብሄርን መኖር ያዩ ነበር እናም በእርሱ መገኘት ውስጥ ነበሩ ፡፡ በዘጸ 30 ለቤተ መቅደሱ ተጨማሪ ማስዋቢያ እንዲሰራ እግዚአብሄር ሙሴን ማዘዙን ቀጠለ; የዕጣን መሰዊያ(ቁጥር 1-10)፣ የማስተሰሪያ ገንዘብ ይህም ድሀና ሀብታም ይከፍሉበት የነበረው(ቁጥር 11-16)፣ የመታጠቢያ ሰን ወይም የንሀስ ጎድጋዳ ሳህን(ቁጥር 17-21)፣ የተለየው(የተቀባው) ዘይት(ቁጥር 22-23) እና የከበረ ዐጣን(ቁጥር 34-35) ፤ ስለዚህ ይህንን የሚሰራው ማን ነበር ?
ትምህርት
ዘጸዓት(31፡ 1-2); ስራውን እንዲመራ እግዚአብሄር ባስኤልን እንደ መረጠው ለሙሴ ነገረው ፤ ባስኤል ማለት “ በእግዚአብሄር ጥላ ስር” ማለት ነው ፡፡ ባስልኤል የሆር የልጅ ልጅ ነበር ብዙምች እንደሚያምኑት ሆር የማሪያም ባል ነበር ፤ ከሆነ ባስልኤል የማሪያም የልጅ ልጅ ነበር ማለት ነው ፤ ከይሁዳ ነገድ ነበር ! ቤተ መቅደሱን የገነባው ከመሲሁ የዘር መስመር ነበር ፡፡ የእኛ ቃል ለኢየሱስ በዘጸዓት ውስጥ ነፃ አውጪ ነው ፤ በሚያሰደነግጥ መልኩ ለኢየሱስ ባስልኤል እንደ ነፃ አውጪ አገለገለ ፡፡
የመገናኛው ድንካን የእግዚአብሄርን መገኘት እንዲለምዱት ለህዝቡ ይፈቅዳል በተጨማሪም ወደ መሲሁ ያመለክታል ፡፡ እግዚአብሄር በስትክክል ለባስልኤል ተናገረው “ በጠንካራ ባረሜጣህ ላይ እና አንዳንድ የስራ ጫማዎችህን ላይ ተቀመጥ ምክንያቱም እኔ ለአንተ ስራ አለኝ” ፤ ባስልኤል እንደ ግንባት ተቆጣጣሪ እግዚአብሄርን የሚያገለግል ተብሎ ይጠራ ነበር ፡፡ በህይወታችሁ ውስጥ ማንኛውንም ጥሪ በፍፁም እንዳታሳንሱ ፡፡
ዘጸዓት(31፡ 3); እግዚአብሄር ባስልኤልን ለእሱ “ጥበብን፣ ማስተዋልንና በስራ ሁሉ ብልሀትን” በሚሰጥ መንፈስ ሞላው ፤ ይህ የሚያስደንቅ መልክ ነበር እንዴት የግንባታ ሰራተኛ ወደ ሚመጣው ንጉስ እንዲሚያመለክት ፡፡ አዚህ ጋር በብሉይ ኪዳን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ከዚህ በፊት ሁለት ጊዜ ብቻ በግልፅ ተገልፃአል ፤ ዘፍ(1፡ 2) የተገለፀው የእግዚአብሄር መንፈስ በውሃው ላይ ሰፎ እንደነበር ፤ በዘፍ(41፡ 38) ፈርዖን ዮሴፍን የእግዚአብሄር መንፈስ እንዳለበት እውቅና ሰጠ ፡፡ ኢሳ(11፡ 2) መሲሀዊው ትንቢት የሚለው “ የእግዚአብሄር መንፈስ የጥበብና የማስተዋል መንፈስ ፣ የምክርና የኃይል መንፈስ፣ የእውቀትና እግዚአብሄርን የመፍራት መንፈስ ያርፍበታል ፡፡“ ሐዋ(2፡ 1-13) የገለፀው የጴንቴኮስታ ክስተትን አማኞች በመንፈስ ቅዱስ ሲሞሉ ፡፡ በመንፈስ ቅዱስ በተሞላችሁ ጊዜ የመንፈስ ስጦታዎች በህይወታችሁ ላይ ይንቀሳቀሳሉ ልክ ባስልኤል ህይወት ላይ እንደ እንደ ነበሩት ፡፡
በብሉይ ኪዳን ውስጥ እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስን የሰጠው ለተወሰኑ ጊዜና ለተወሰኑ አላማዎች ነበር ፤ በአድስ ኪዳን ውስጥ አማኞች የክርስቶስን ሞት፣ መቀበርና መነሳት ባመኑ ጊዜ መንፈስ ቅዱስን ተቀብለዋል( ሐዋ 4፡ 8; ኤፌ5፡ 18) ፡፡ በክርስቶስ በታመንን ጊዜ የመንፈሱ አብሮነት አለን በፍፁም አይተወንም ፤ ነገር ግን በይበልጥ ሳያቐርጥ እንዲሞላን እርሱን በመጠየቅ መነሳሳት አለብን ፡፡ እሱ በብዙ ካለን ለእግዚአብሄር ብዙ ክብር እንሰጣለን፡፡
ዘጸዓት(31፡ 4-5); እግዚአብሄር ለባስልኤል እግዚአብሄር ለእርሱ ያለውን ስራ እንዲሰራ የሚያስፈልገውን ስጦታ ሰጠው፡፡ ሁላችንም የተፈጥሮ ችሎታ አለን ከዚህ በተጨማሪ የእግዚአብሄር መንፈስ ወደ ህይወታችን በመጣ ጊዜ ለእራሱ እነዚያን የተፈጥሮ ችሎታዎች ያቀጣጥላቸዋል ፤ አንድ ምሳሌ በ 1ሳሙ 16፡ 13-23 የተገለፀው ፤ ሳሞኤል ዳዊትን ከቀባው ቦኃላ “ የእግዚአብሄር መንፈስ ከዚያ ቀን ጀምሮ በዳዊት ላይ በኃይል መጣ”(1ሳሙ 16፡ 13) ፡፡ ዳዊት በገና እንዴት እንደሚጫዎት ያውቅ ነበር በዚህም እግዚአብሄር የሳዖልን ክፉ መንፈስ ለማስወጣት በገነውን ተጠቀመ ፡፡ የእግዚአብሄርን መንፈስ በኑሮአችን ላይ በተቀበልን ጊዜ የተፈጥሮ ችሎታችን ለእግዚአብሄር ክብር ይንቀሳቀሳሉ(ይሰራሉ) ! እንዴት ከመንፈስ ቀዱስ እንሰማለን የሚለውን መማር ያስፈልገናል ፡፡ እራሳችንን በደንብ ለእርሱ በከፈትን ጊዜ በኑሮአችን ውስጥ የእግዚአብሄርን ስራ በአድስ መንገድ ማየት እንጀምራለን ፡፡
ዘጸዓት(31፡ 6); ከባስልኤል ጋር እንዲሰራ ከዳን ወገን ሆነውን ኤልያብን እግዚአብሄር መረጠው ፡፡ ኤልያብ ማለት “የአባቴ ድንካን ከእግዚአብሄር ጋር ተቀራርቦ የሚኖር” ማለት ነው ፡፡ ዳን ከያዕቆብ ቁባት ልጆች በኩር ነበር ፤ ሳምሶን ቆይቶ ከዳን ነገድ የተወለደ ነበር፡፡ ዳናዊያን ነገሮችን መገናባት የቻሉ ጥበበኛ በመባል ይታወቃሉ ነበር ፤ ብዙ አመታት ወደፊት ኪራም አቢ ብልሀተኛ ሰው ከዳን ነገድ ነበር የሰለሞንን ቤተ መቅደስ ለመገንባት የረዳው (2ዜና 2፡ 13) ፡፡ እግዚአብሄር “ በልባቸው ጥበበኞች በሆኑት ሁሉ ላይ ጥበብን አኖራለሁ”(ቁጥር 6) በባስልኤልና በኤላይብ ላይ ብቻ አይደለም ፤ እነዚህ ሰዎች በእግዚአብሄር ተቃኝተውም ሁሉንም የሚያስደንቅ እቃ እንዲሰሩ ታዘው ነበር ስለዚህ እስራኤላዊያን የእግዚአብሄርን መገኘት መለማመድ ይችላሉ ፡፡ እነዚህ ሰዎች የዘወትር ሰዎች ነበሩ እኔን 12ቱን የእስራኤል ወንድ ልጆች 12ቱን ነገዶች ማን ዝምብሎ ያለ ነገድ እንደሆነ እንዳስብ አድርጎኛል፤ ከዚያም ስርአታቸው ልክ እንደ ዘወትር ሰዎች አማካኝ ነበር ልክ እንደ ቀረጥ ሰብሳቢና አሳ አጥማጅ ፤ ነገር ግን የእግዚአብሄር መንፈስ በላያቸው ላይ በመጣ ጊዜ ኃይልን ሰጣቸው ! ራዕ(21፡ 12-15) የሚለው እነዚህን ሰዎች በአድሲቱ ኢየሩሳሌም እናስታውሳቸዋለን ፡፡ “ 12ቱም የእስራኤል ልጆች ነገዶች ስሞች ተፅፈውባቸው ነበር (በሮቹ ላይ)(ራዕ 21፡ 12) እና “የ12ቱ የበጉ ሐዋሪያት 12ቱ ስሞች” በከተማይቱ 12 መሰረት ቅጥር ላይ ይሆናሉ (ራዕ21፡14) ፡፡
ዘጸዓት(31፡ 7-11); እግዚአብሄር የመገናኛ ድንካኑን ለመትከልና የውስጥ እቃውን፣ እንዲሁም የካህናት ልብሱንና የተቀባ ዘይቱንና እጣኑን አቀማመጥ የተለየ ትዕዛዝ ሰጠ ፡፡ ብልህ ሰራተኞች እግዚአብሄር እንዳዘዘው አድርገው ሁሉንም ሰርተው ጨረሱ ፡፡
ዘጸዓት(31፡ 12-13); ለቤተ አምልኮቱ የእርሱን ትዕዛዝ መከተል ጥቅሙን ሲገልፀው እግዚአብሄር ሙሴ ለ”እስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው እኔ ይምቀድሳችሁ እግዚአብሄር እንደ ሆንሁ ታውቁ ዘንድ በእኔና በእናንተ ዘንድ ለልጅ ልጆቻችሁ ምልክት ነውና ሰንበቶቼን ፈፅሞ ጠብቁ ፡፡” እንዲሁም ለእግዚአብሄር በእነርሱ መሀከል መኖሪያ በቤቱ መሀከል ቦታ ላይ እግዚአብሄር በመገኘቱ ሊያሳርፋቸው ፈለገ ፡፡ እዚያ ጋር ያደረጉት ምንም አይነት ሌላ ልምድ አልነበረም ፡፡
ዘጸዓት(31፡ 14-15); እግዚአብሄር ሰንበትን መጠበቅ ጠቃሚ እንደሆነ ተመለከተ ማንኛውም ይህን የሚንቅ ወይም በዚያች ቀን ማንኛውንም ስራ የሚሰራ ከህዝቡ የሚወገድ ይሆናልም ይሞታልም ፡፡ እግዚአብሄር የሰንበት ቀንን በመጠበቅ በሙሉ አርፈው ለእግዚአብሄር እንዲያዉሉት አዘዘ ፡፡
ዘጸዓት(31፡ 16); ይህ ትዕዛዝ በጣም አድስ ነበር እስራኤላዊያን በእርግጠኝነት የትኛው ስራ የትኛው ደግሞ ስራ እንዳልሆነ አይለዩም ነበር ፤ ዘኁ(15፡ 32-35) የተፃፈው አንድ ሰው በሰንበት ቀን እንጨት ሊለቅም ሄደ ከዚያም ሰንበትን በመጣሱ በሙሴና በአሮን ፊት አመጡት ፤ ከዚያም እግዚአብሄር ከመኖሪያ ካንፕ ዉጭ በድንጋይ ተወግሮ እንዲሞት ሙሴን አዘዘው ፡፡ አስታውሱ መና ከሰንበት ቀን ዉጪ በየቀኑ እንደ ሚወርድ ፤ በስድስተኛው ቀን እስራኤላዊያን እጥፍ ይሰበሥቡ ነበር ስለዚህ በሰንበት ቀን አይሰሩም ፡፡ ሰንበት የሚያከብራት ቀን ነበረች !
ዘጸዓት(31፡ 17); ስንበት በእግዚአብሄርን በህዝቡ መሀከል የነበረ ምልክት ነበር እንጂ በህዝቡና በቸርች አይደለም ፤ በሰንበት ስራ እንዲያቆሙና ለእረፍት በእግዚአብሄር መገኘት ፊት እንዲመጡ ታዘዙ፡፡
የሰንበት ቀን አምልኮ አገልግሎትን ስለሚይዙ ነገሮች አይተናል ? አንዳንድ ጊዜ ከአገባበቸው ውጪ ነገሮችን ስንወስድ የእውነት ምን ማለት እንደ ፈለገ አንረዳውም ፡፡ በኢሳ (1፡ 13) እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን የነገራቸው “ ምናምንቴውን ቁርባን ጨምራችሁ አታምጡ ፤ ዕጣን በእኔ ዘንድ አሰጸያፊ ነው መባቻችሁንና ሰንበታችሁን አልወድድም ፤ በደልንም የተቀደሰውንም ጉባኤ አልታገስም ” ፤ በግልፅ አንዳንድ ስብሰባዎቻቸው እግዚአብሄርን አላስደሰቱትም ነበር ፡፡በሆሴ(2፡ 11) እግዚአብሄር ለእስራኤል ክብረ በዓል መጨረሻ እንዳስቀመጠ ተናገረ ፤ በዚህ አነጋገር(አገላለፅ) እግዚአብሄር ለአምልኮ አገልግሎት በጋራ ተቀመጡ አላለም -ያለው አበቃ፡፡
ዘጸዓት(31፡ 18); እግዚአብሄር “ በሲና ተራራ ከሙሴ ጋር የነበረውን ንግግር ጨረሰ” ከዚያም እስራኤላዊያን እንዲኖሩበት የፈለገውን ፅላቱን ከአስሩ ትዕዛዝ ጋር ሰጠው ፤ “ በእግዚአብሄር ጣት የተፃፈው ” ሀረግ አንትሮሞረፎዚም(የተለየ/የላቀ) ነበር; የእግዚአብሄርን ጥራት በሰው ባህሪይ ሲገለፅ ፤ ሲብራራ የእግዚአብሄር ቃል ለእግዚአብሄር ሰው ተሰጠው ከዚያም አሁን የእግዚአብሄር ሰው ይህን ለሁሉም እስራኤላዊያን እንዲያደርስ ተደረገ፡፡ እነዚህ አስር ትዕዛዞች ባስልኤልና ኤልያብ እየሰሩን በነበረው ቤተ መቅደስ ውስጥ ይቀመጣል፡፡
መዝጊያ
ሁሉም አካል የተለየ ድርሻቸውን ተጫውተዋል ! ሙሴ ቃሉን ተቀበለ፣ ብልሀተኞች ቤተ አምልኮቱን ሰሩ ከዚያም ካህናቱ በቤተ አምልኮቱ አገለገሉ ፡፡
Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Exodus (available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/exodus.pdf), p. 264.
Constable, p. 264..
Constable, p. 265
Constable, p. 266.
ጥያቄዎች
-
የዕጣኑ መሰዊያ የሚወመጠው የት ነበር ? ለሲህ መሰዊያ የእግዚአብሄር አላማ ምንድን ነበር (ዘሌ 16፡ 12-13)?
-
ለእግዚአብሄር ዕጣኑን እንዲያቃጥል(እንዲያነድ) አሮን የጠመረጠው ለምን ነበር (ዘጸ 28፡ 1; 1ሳሙ2፡28)?
-
በዘጸ(30፡ 7) የዕጣኑ መሰዊያ በምንድን ነበር የ(ራዕ 5፡ 8; 8፡ 3-4) መልክ የነበረው ? ለእኛ እግዚአብሄር ስለሚፈልገው ይህ ለእናንተ ምንድን ይገልጥላችኃል ?
-
በዘጸ(30፡ 9) እግዚአብሄር “ ሌላ” (የሚቃጠል መስዋዕት ወይም የእህልም መስዋዕት ወይም የሚፈሰስ መስዋዕት) በመሰዊያው ላይ አይደረግ ብሎ ተናገረ ፤ ይህ ምንድን ማለት ነበር(ዘሌ 10፡ 1-3) ? ዛሬ እግዚአብሄርን እንዴት ማገልገል ወይም ማምለክ እንዳለብን ይህ እንዴት ሊያገናኝ ይችላል ?
-
ዘጸ(31፡ 1-5) አንብቡ ፤ እግዚአብሄር ባስልኤልን በመንፈስ ቅዱስ የሞላው ለምን ነበር ? በእግዚአብሄር መንግስት ውስጥ እንድትሰሩ እግዚአብሄር የሰጣችሁ(ያስቀመጠባችሁ) ሚና(ሚናዎች) ምንድን ነው ?
-
በዘጸ(30-31) ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 31:2-6
“Look, I have appointed by name Bezalel son of Uri, son of Hur, of the tribe of Judah. I have filled him with God’s Spirit, with wisdom, understanding, and ability in every craft to design artistic works in gold, silver, and bronze, to cut gemstones for mounting, and to carve wood for work in every craft. I have also selected Oholiab son of Ahisamach, of the tribe of Dan, to be with him. I have placed wisdom within every skilled craftsman in order to make all that I have commanded you.”
ጥበበኛ ሠራተኞች እና ሰንበት
ኦሪት ዘፀዓት 30-31 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እግዚዓብሔር፥ ግንባታዉ የተሟላ እንዲሆን ለሙሴ ከሰጠዉ ትዕዛዛት አንዱ፥ እርሱ ጠራቢዎችን መምረጡ ነበር። እግዚዓብሔር በመንፈሱ በመሙላት፦ ከህይወት ጥሪያቸዉ አንፃር በጥበብ፣ በእዉቀት እና በብልኃት እንዲጎለብቱ አደረጋቸዉ።
እግዚዓብሔር ለህዝቡ ዓላማ ሲኖረዉ እና ለሆነ ጥሪ አንተን ሲያዘጋጅህ፥ ባለህ እምነት መፅናናት ይሁንልህ። የሚያስፈልግህን ነገር ሁሉ ያሟላልሃል። በመንፈስ ቅዱስም ጉልበት ይሰጠሃል። ለእግዚዓብሔር እንደሚትሠራ ስትተጋ፥ ኃይሉን በመሙላት ያስታጥቅሃል። እግዚዓብሔር ካዘዘህ ከምንኛዉም ነገር ቀድሞ ፊትለፊት እንደሄደ አስታዉስ!
"እይ ከይሁዳ ነገድ የሚሆን የሆር የልጅ ልጅ፥ የኡሪ ልጅ ባስልኤልን በስሙ ጠርቼዋለሁ። በሥራ ሁሉ ብልሃት በጥበብም በማስተዋልም በእውቀትም የእዚአብሔርን መንፈስ ሞላሁበት፤ የጥበብን ሥራ ያስተውል ዘንድ፥ በወርቅና በብር በናስም ይሰራ ዘንድ፥ ለፈርጥ የሚሆነውን የዕንቍ ድንጋይ ይቀርጽ ዘንድ፥ እንጨቱንም ይጠርብ ዘንድ፥ ሥራውንም ሁሉ ይሠራ ዘንድ። እኔም እነሆ ከእርሱ ጋር ከዳን ነገድ የሚሆን የአሂሳሚክን ልጅ ኤልያብን ሰጠሁ፤ ያዘዝሁህን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በልባቸው ጥበበኞች በሆኑት ሁሉ ጥበብን አኖርሁ።"
ኦሪት ዘፀዓት 31:2-6
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መጽሐፈ ኢያሱ ወልደ ነዌ 1:9፦ "ምትሄድበት ሁሉ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ነውና ጽና፥ አይዞህ አትፍራ፥ አትደንግጥ ብዬ አላዘዝሁህምን?"
- 1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 12:4-8፦ "የጸጋም ስጦታ ልዩ ልዩ ነው መንፈስ ግን አንድ ነው፤ አገልግሎትም ልዩ ልዩ ነው ጌታም አንድ ነው፤ አሠራርም ልዩ ልዩ ነው፥ ሁሉን በሁሉ የሚያደርግ እግዚአብሔር ግን አንድ ነው። ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን መግለጥ ለእያንዳንዱ ለጥቅም ይሰጠዋል። ለአንዱ ጥበብን መናገር በመንፈስ ይሰጠዋልና፥ ለአንዱም በዚያው መንፈስ እውቀትን መናገር ይሰጠዋል፥"
- ወደ ቆላስይስ ሰዎች 3:23፦ "ለሰው ሳይሆን ለጌታ እንደምታደርጉ፥ የምታደርጉትን ሁሉ በትጋት አድርጉት፥"
መሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 45
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።