The Pentateuch Exodus

The Instructions of the Holy Priests

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 29 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 44 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እግዚአብሄር ቤተ መቅደሱን እንዲሰራና እንዲያዘጋጅ ለሙሴ ትዕዛዝ ሰጠው ፤በስተጎን አሮንንና ልጆቹን እንደ ካህናት እንዲያደርግና ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ለብሰው የሚያገለግሉበትን የክህነት ልብስ እንዲሰራላቸው ሙሴን አዘዘው ፡፡ አሁን እግዚአብሄር እንዲያገለግሉት ክህናቶቹን እንዴት እንደሚቀድሳቸው ገለፀ ፡፡

ትምህርት

ዘጸዓት(29፡ 1-4); አሮንና ልጆቹ በእግዚአብሄር ፊት እንደ ካህናት ከማገልገላቸው በፊት መቀደስ ነበረባቸው ፤ መቀደስ ማለት መለየት እግዚአብሄርን ለማገልገል ለተለየ አላማ ቅዱስ መደረግ ነበረባቸው ፡፡ መጀመሪያ ሙሴ አንድ ወይፈን፣ ሁለት አውራ በጎች፣ ያልቦካ ቂጣ፣ ኬኮችና ከጥሩ ስንዴ ዱቅት የተሰሩ ብስኮቶች መሰብሰብ ነበረበት ፤ ኪዚያም አሮንንና ልጆቹን ወደ መገናኛው ድንካኑ መግቢያ ጋር በማምጣት በውሃ አጠባቸው ፡፡ የኔልሰን ሀተታ የካህናት መታጠብ የሚያመለክተው “ ንፁህ መሆን በእግዚአብሄር ፊት አስፈላጊ እንደሆነ ምልክት ነበር ፤ በሲና በርሃ መታጠብ ብርቅ ድሎት ነበር ፡፡”

በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ኃጢዓት በብዙ መንገድ ተወክላል ፤ ኢሳ(1፡ 4-6) ሲናገር በሽታና ህመም ኃጢዓትን ወክለዋል ፤ በአድስ ኪዳን ጨለማና ሞት ኃጢዓትን ወክለዋል ፤ ኢሳ(1፡ 16) ቆሻሻን ከኃጢአት ጋር እኩል ያደርገዋል ከዚያም ሰዎቹን እንዲታጠቡናእራሳቸውን ከክፉ ድርጊታቸው እንዲያነፁ አነሳሳቸው(አሳሳባቸው) ፡፡ በወደፊት ትምህርታችን ላቨር(ለካህን መታጠቢያ የሚሆን ወንዝ) እንደ ሳህን ይገልጥልናል ይህም እግዚአብሄር ከማገልገላቸው በፊት ካህናቱ እጃቸውንና እግራቸውን የሚታጠቡበት ነበር ፡፡ ብዙ ቆይቶ ኢየሱስ ሲናገር እነዚያ ሙሉ አንዴ የታጠቡ ለተወሰነ አካላቸው መንፃት ያስፈልጋቸዋል (ዮሐ 13፡ 10) ፡፡

ዘጸዓት(29፡ 5-7); ክህኖቹ ታጠቡም ለበሱም ፡፡ ጥምቀት የሚወክለው መታጠብንና የቅድስና ካባ ላይ መቀመጥን ነው ፡፡ የኛ ኃጢዓት ይቅር በተባልን ጊዜ በአድስ ልብስ ተቀምጠናል ! ከኃጢዓታችን እኛን ነፃ ያወጣን ኢየሱስ ብቻ ነው ስለዚህ በእግዚአብሄር ፊት መምጣት እንችላለን ፡፡ በመቀጠል ካህናት ይቀቡ የነበረው የተቀባ ዘይት በራሳቸው ላይ በማፍሰስ ነበር(መዝ 133፡ 2-3) ፤ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ቅባት ለካህናት፣ ለነቢያትና ለናጉሶች መጥቶ ነበር ፡፡ ቅባት “ ለኃይልና ለአገልግት እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስን ስለሰጣቸው ምልክት” ነበር ፡፡

በሉቃ(4፡ 17-18) ኢየሱስ ከኢሳያስ ትንቢት እንዲያገለግልና የእግዚአብሄርን ስራ እንዲሰራ እንደ ሊቀ ካህን እንደ ተቀባ በመግለጥ ጠቀሰ ፡፡ ከብሉይ ኪዳን የተቀባ ካህን አያስፈልጋችሁም ! ቀደም ብሎ ተቀብታችኃል ! ዛሬ የካህናት ቤተሰቦች ነን ! መፅሀፍ የሚለው በኢየሱስ በሞቱ፣ በመቀበሩና በመነሳቱ ባመናችሁ ጊዜ ዘይቱ በራሳችሁ ላይ ፈሳል፡፡ በ1ዮሐ(2፡ 20፣ 27) አማኞች የነገሩን በቅዱሱ እንደተቀቡ ነው ፡፡ቅባቱ አይተወንም በዚህም ሁሉንም እውነት ሊያስተምረን መታመን ይችላል ፡፡

ይህ የካህናት ቤተሰብ(አካል) የሚያመለክተው ወደ መሲሁ እንደ ሊቀ ካህንና ወደ እኛ እንደ አድስ የካህናት ቤተሰብ መሆንን ነው ፡፡ በብሉይ ኪዳን ውስጥ ዘይት የመንፈስ ቅዱስ ምልክት ነበር ፡፡ በብሉይ ኪዳን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ይመጣም ይሄድም ነበር ፤ ዘኁ(11፡ 29) የሚገልጠው ህዝቡ በብሉይ ኪዳን ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ይጋአጉ እንደነበር ነው ፡፡ ግን መንፈሱ ወደ ህዝቡ(ሰዎች) በመሲሁ በኩል መጣ የክህናት ቤተሰብ ሆነው እንዲጋአዙ ስልጣን በመስጠት ፈቀደላቸው ፡፡

ዘጸዓት(29፡ 8-9); አሮንን ከቀባ በኃላ ሙሴ በሸሚዝ፣ መታጠቂያውንና ቆቡን አሮንንና ልጆቹን አለበሳቸው ፤ ከዚያ በኃላ በቐሚነት የካህናት ቤተሰብ ሆነው ተቀብተው ነበር ፡፡ “መሾም” የሚለው ቃል ትርጉሙ “ለስልጣን በእጁ ያለው አማላ(ይበቃል)” ማለት ነው ፡፡ የኔልሰን ሀተታ ያመለከተው ንጉሶች እጃቸውን በበትር በሞሉ ጊዜ ባለስልጣን ሆነዋል(ነግሰዋል) “እንደ ፖለቲካ ኃይል ምልክት” ፡፡

ዘጸዓት(29፡ 10-12); ካህናቱ ከታጠቡ፣ ከለበሱና ከተቀቡ ቦኃላ ምህረት ይደረግላቸው ነበር ፤ አሮንና ልጆቹ እጃቸውን በወይፈኑ ራስላይ በማድረግ የኃጢዓት መስዋዕት አደረጉ ይህም በመገናኛው ድንካን መግቢያላይ የታረደ ነበር ፡፡ ሙሴ የወይፈኑን ጥቂት ደም በመሰዊያው ቀንድ ላይ አደረገ ከዚያም የቀረውን ደም በመሰዊያው በታች አፈሰሰው ፡፡ የኔልሰን ሀተታ ያብራራው ሙሴ የቀረውን ደም ዝምብሎ አልነበረም የረጨው -ሁሉም ነገር ሙሴ ያደረገው አስቦበትና ጠቃሚ ነበር ፡፡

ዘጸዓት(29፡ 13-14); የወይፈኑ ስብ ክፍልና ኩላሊቶቹ በመሰዊያው ላይ ተቃጠሉ ነገር ግን ስጋው፣ ቆዳውና ፈርሱ ከድንካኑ(ከካንፑ) ውጪ ተቃጠለ ፡፡ ስለነዚህ ነገሮች መቃጠል ስታነቡ ሀሳባችሁ ውስጥ ማስቀመጥ ያለባችሁ የኛ የኃጢዓት ስጦታና መስዋዕት ኢየሱስ እንደሆነ ነው ፡፡ በኢሳ(53) ይቺን ምዕራፍ አይሁዶች እንካን አያነባትም የሚያስተምረን ኢየሱስ ህመማችንን ተሸከመ(ቁጥር 4) እና ስለመተላለፋችን ቆሰለ(ቁጥር 5) ፤ በእኛ ኃጢዓት ምክንያት ኢየሱስ ተቀጣ(ቁጥር 5-6); እሱ የኛ የኃጢዓት ስጦታ ነበር፡፡ ወደ እርሱ በተመለስን ጊዜ በእርሱ ቁስል ተፈውሰናል(ቁጥር 5) ፡፡

በማቴ(26፡ 28) ኢየሱስ ሲናገር “ ስለ ብዙዎች ለኃጢዓት ይቅርታ የሚፈስ…..ደሜ ይህ ነው “ ፡፡ የእርሱ ህይወት ካህናቶ ኃጢዓት ስጦታ በየቀኑ ለሚያቀርቡት ስጦታ ገላጭ ነበር ፤ እግዚአብሄር “ ኃጢዓት ያላወቀውን እርሱን ስለእኛ ኃጢዓት አደረገው “(2ቆሮ 5፡ 21) ፡፡ ይህ የኃጢዓት መስዋዕት ካህናቶች በየቀኑ ያቀረቡት አንዴና ለሁሉም ለኃጢአታችን መስዋዕት ለሆነው ወደ ኢየሱስ አመለከተ (1ጴጥ 2፡ 24) ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በራሱ ደም ከኃጢዓታችን ነፃ አድርጎናል(ራዕ 1፡ 5-6) ፡፡

ዘጸዓት(29፡ 15-18); በመቀጠል አሮንና ልጆቹ የሚቃጠል መስዋዕት ለእግዚአብሄር አደረጉ ፤ እጃቸውን በመጀመሪያው በግ ላይ አደረጉ አረዱት በሁሉም የመሰዊያው አቅጣጫ ላይ ደሙን ረጩ ከዚያም በጉን ወደ ቁርጥራጭ ቆራረጡ፣ ታጠቡ፣ ሁሉንም በጉን በመሰዊያው ላይ አቃጠሉት ለእግዚአብሄርም ደስ የሚል መዓዛ ፈጠረ ፡፡ ዋይሰርቤ እንደ ተናገረው ካህናቱ ታጠቡ፣ ለበሱ፣ ተቀቡ፣ ምህረት ተደረገላቸው ከዚያም አሁን በአላማው ተለዩ ፡፡

ዘጸዓት(29፡ 19-21); ከዚያ ቦኃላ አሮንና ልጆቹ እጆቻቸውን በሁለተኛው በግ ላይ አደረጉ በጉም ታረደ ከዚያም ደሙን በቀኝ ጆሮአቸው ጉትቻ ማንጠልጠያው ላይ፣ ቀኝ አውራ ጣታቸው ላይ እና ቀኝ እጅ አውራ ጣታቸው ላይ አደረጉት ፤ ዋይሰርቤ ሲናገር አሁን ካህናቶቹ በደም የሚታይ ምልክት አደረጉ የኔልስን ሀተታ ይህን እይታ ያቀረበው; ጆሮ መቀባቱ የእግዚአብሄርን ቃል መስማትን ይወክላል፣ አውራ ጣት መቀባቱ የእግዚአብሄርን ስራ መስራትን ይወክላል እና የእግር አውራ ጣት መቀባቱ እንደ እግዚአብሄር ፍቃድ መሄድን ይወክላል ፡፡ የቀረው ደም በመሰዊያው ላይ ረጩት ፡፡ ትንሽ ደም ከዘይት ጋር ቀላቅለው እነርሱን ቅዱስ ለማድርግ በአሮንና በልጆቹ ሰዉነትና ልብሳቸው ላይ ረጩት (ቁጥር 21) ፡፡ ኢየሱስ በደም ምልክት ተደርጎ ነበር ፤ እሱን በምንቀበለው ጊዜ በብዙ በደም ምልክት ተደርጎብናል ፡፡ ወደ እርሱ መገኘት እንድንገባ ተፈቅዶልናል ምክንያቱም በደሙ ምልክት ስለተደረገብን ፤ ሮሜ (12፡ 1) የሚነግረን ራሳችንን እንደ ህያው መስዋዕት፣ ቅዱስና ለእግዚአብሄር የሚመች፣ መንፈሳዊ አምልኮ ድርጊታችን እንድናቀርብ ነው ፡፡

ዘጸዓት(29፡ 22-25); ዋይሰርቤ ሲናገር ካህናቱ እንግዲህ ተካኑ ፡፡ አሮንና ልጆቹ የበጉን አካል በማዘጋጀት ከአንድ እንጀራ፣ ከአንድም ስስ ቂጣ፣ አንድም የዘይት ቂጣና በሌማት ውስጥ ካለው ቂጣ ጋር በማድረግ ለእግዚአብሄር እንደ ቁርባን ስጦታ ተወዘወዘ ይህም የሚያመለክተው “ እግዚአብሄር የኔ መጋቢ ነው” የሚለዉን ነበር በዮሐ(4፡ 34) ውስጥ ኢየሱስ ሲናገር “ የእኔስ መብል የላከኝን ፈቃድ አደርግ ዘንድ ነው” ፡፡ ዛሬ እንደ ካህናት በፍፁም ከእግዚአብሄር መመገብን፣ መቅመስንና መልካም እንደሆነ መመልከትን ማቆም የለብንም !

ዘጸዓት(29፡ 26-46); መቀደሳቸውን ለመጨረስ እያንዳንዳን ቀን ለሰባት ቀን ካህናቱ ከኃጢአታቸው ለመንፃትና መሰዊያውን ለማንፃት ለኃጢዓት ስጦታ ወይፈን ሰው (ቁጥር 35-37) ፡፡ ከዚያም እንደ ካህን ሁል ጊዜ በማለዳና ፅሀይ ስትገባ ጠቦት ያቀርቡ ነበር (ቁጥር 39-41) ፤ እያንዳንዳን ቀን በእግዚአብሄር ፊት በቀኑ መጀመሪያና መጨረሻ በመስዋዕት አገለገሉ ፡፡

መዝጊያ

ክርስቶስ በማለዳ በነቃን ጊዜ በሌሊት ለመተኛት በሄድን ጊዜ የሰራው(የከፈለው መስዋዕት) ላይ ትኩረት ስናደርግ የረጋ(የሚለይ) አልነበረም ? ኢየሱስ ነፃ ስላወጣኸኝ አመሰግንሀለሁ ፡፡ እንደ ቅዱስ ካህናት ቤተሰብ እንደታጠብን፣ አንደ ለበስን፣ እንደ ተቀባን፣ ይቅር እንደተባልን፣ እንደ ተለየን፣ በደሙ ምልክት እንደ ተደረገብንና እንደ ተካንን እናውቃለን ፡፡

  1. Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds. Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 136.

  2. Warren Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001) p. 243.

  3. Nelsons, p. 136.

  4. Wiersbe, p. 243.

  5. Nelsons, p. 136

  6. Wiersbe, p. 243.

  7. Wiersbe, p. 243-244.

  8. Nelsons, p. 137

ጥያቄዎች

  1. በዘጸ(29፡ 38-41) የየቀኑ መስዋዕት እንዴት አድርጎ የክርስቶስ ጥላ ሆነ (ዮሐ1፡ 29; 36) ?
  2. ምን ታስባላችሁ ለእግዚአብሄር በየቀኑ መስዋዕት እያቀረብን እንደ አሮን ካህን እንሆናለን (ዘጸ 29፡ 38) ? በዕብ(10፡ 11-14) ያለው እውነት እንዴት ያበረታታችኃል ?
  3. በዘጸ(29፡ 19-21) አሮንና ልጆቹ ራሳቸውን በበጉ ደም ምልክት ሊያደርጉ አስፈለጋቸው ፤ ይህንን ማድረግ ለምን አስፈለጋቸው ? የተለዩ የሰውነት አካላቸውን በደሙ ምልክት ስለ ማድረጋቸው አስፈላጊነቱ ምን እንደ ነበር ምን ታስባላችሁ ? በክርስቶስ ደም ምልክት እንደተደረገባችሁ ራሳችሁን ታስባላችሁ ?
  4. በዘጸ(29፡ 24; 26) “የመወዝወዝ መስዋዕት(ቁርባን)” ምን ነበር ? ካህናቱ ይህን እንዲያደርጉ ለምን እንደ ፈለገ ምን ታስባላችሁ ?
  5. የተሳለውን እንጀራ(ቂጣ) የሚበላው በካህናቱ ብቻ ነበር(ዘጸ 29፡ 32) ፤ ማቴ(12፡ 3-8) እና ማር(2፡ 23-27) አንብቡ ፡፡ ለዳዊት የስዕለቱን ዳቦ መብላት ለምን ተቀባይነት የነበረው ምን ታስባላችሁ (1ሳሙ 21፡ 1-9) ?
  6. በዘጸ 29 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Exodus 29:44-46

“I will consecrate the tent of meeting and the altar; I will also consecrate Aaron and his sons to serve Me as priests. I will dwell among the Israelites and be their God. And they will know that I am Yahweh their God, who brought them out of the land of Egypt, so that I might dwell among them. I am Yahweh their God.”

ኦሪት ዘፀዓት 29 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

እግዚዓብሔር፥ አሮን እና ልጆቹ እንዴት ካህናት መሆን እንዳለባቸዉ ትክክለኛዉን ስርዓት፦ ማለትም ራሳቸዉን በመቀደስ ሂደት ዉስጥ አልፈዉ እና ለህዝቡ መስዋዕት በማቅረብ መዘጋጀት እንዳለባቸዉ ለሙሴ አብራርቶለታል። ከነዚህ ዝርዝር ትዕዛዛት በኋላ፥ እግዚዓብሔር አምላካቸዉ እንደሆነ እንዲያዉቁ፥ በእነሱ መካከል እንደሚያድር ግልፅ አደረገላችሀዉ።

በአዲስ ኪዳን ዉስጥ መቀደስ፥ ራሳችንን ለእግዚዓብሔር በምናቀርብበት እና እንደ ህያዉ መስዋዕት፥ እኛነታችንን አሳልፈን በምንሰጥበት አኳሃን አማኝ ሁሉ የሚቃኝበት ነዉ። "አምላኬ ሆይ፥ የምኖረዉ ለአንተ ነዉ! ለራሴ፣ ለዓለም እና ለሌላ ነገር መኖር አቁሜአለሁ! ለክብርህ ተጠቀምብኝ!" የምንልበት ነዉ። የእርሱ የሆንክ የተመረጠክ ካህን እንደመሆንህ፥ ለእግዚዓብሔር መስዋዕት በምታቀርብበት ጊዜ፥ እግዚዓብሔር በአንተ ዉስጥ እንደሚያድር እና አምላክህ እግዚዓብሔር መሆኑን አስታስዉስ።

"የመገናኛውንም ድንኳን መሠዊያውንም እቀድሳለሁ፤ በክህነትም ያገለግሉኝ ዘንድ አሮንንና ልጆቹን እቀድሳለሁ። በእስራኤልም ልጆች መካከል እኖራለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ። በመካከላቸውም እኖር ዘንድ ከግብፅ ምድር ያወጣኋቸው አምላካቸው እግዚአብሔር እኔ እንደ ሆንሁ ያውቃሉ፤ እኔ አምላካቸው እግዚአብሔር ነኝ።"

ኦሪት ዘፀዓት 29:44-46

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ወደ ሮሜ ሰዎች 12:1፦ "እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።"
  • 2ኛ ወደ ጢሞቲዎስ 2:21፦ "እንግዲህ ማንም ራሱን ከእነዚህ ቢያነጻ፥ ለክብር የሚሆን የተቀደሰም ለጌታውም የሚጠቅም ለበጎም ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ዕቃ ይሆናል።"
  • 1ኛ የጴጥሮስ መልእክት 2:9፦ "እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 44