The Pentateuch Exodus

The Priestly Garments

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 27-28 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 43 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

እግዚአብሄር ለሙሴ ቤተ መቅደሱኑ እንዲሰራ የሰጠውን ትዕዛዝ መመልከት እንቀጥላለን ፡፡ዘጸ 26 የገለፀው እንዴት 10 የውስጠኛውንና 11 የውጨኛውን መጋረጃ ድዛይን እንደተደረገና በበሮቹ ቐሚና ተሸጋሪ እንዲገባ ነበር ፤ እግዚአብሄር ለመግቢያው ስለመሸፈኛውና ስለጥልፉ መጋረጃ ዝርዝር ሰጥታል ፡፡ ዘጸ 27 የሚያወራው ስለሚቃጠል መስዋዕት መሰዊያውና ስለመሰዊያው እቃ፣ ግቢና በዘይት ሰለተሞላው መቅረዝ ፡፡ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ቅዱስ ነገር እንዲያገለግሉና እንዲጠብቁ እንደ ቅዱስ ክህናት እግዚአብሄር አሮንንና ልጆቹን እንዲሾማቸው ሙሴን አዘዘው፡፡

እንደ ፈጣን ክለሳ በዘጸ(19፡ 3-6) እግዚአብሄር ለእስራኤላዊያን በሰዎስት በተለያዩ መንገዶች ይጠቅሳቸዋል; 1) ለእግዚአብሄር የተለየ ርስት; 2) የንጉስ ካህናት(በብዙ አንፃር ሁሉም እስራኤላዊ ካህናት ነበሩ ነገር ግን እግዚአብሄር በተጨማሪ የተለዩ የቤቱ ካህናት በሌዋዊያን ውስጥ መሰረተ) እና 3) ቅዱስ ህዝብ ፡፡

ትምህርት

ዘጸዓት(28፡ 1); የእግዚአብሄርን ትዕዛዝ በመከተል ሙሴ ወንድሙን አሮንናን አራቱን ልጆቹን(የሙሴ ወንድም ወንድ ልጆችን) በእግዚአብሄር ፊት እንደ ካህን እንዲያገለግሉ ሾማቸው(መረጣቸው) ፡፡ ኮንስታብል አራት የተለዩ የካህን ሚናዎችን ሰጥቶናል; 1) የቤተ አምልኮቱን ቅዱስ ቦታ እጣን በማቀጣተል፣ መብራቱን በማስጌጥና ህብስቱን በመቀየር መንከባከብ; 2) የቤተ አምልኮቱን ግቢ የሚይዛቸው መስዋዕት የሚሰዋበትን፣ የሚነድደውን እሳት በመጠበቅና አመዱን በማስወገድ መንከባከብ; 3) ህዝቡንና መስዋዕታቸውን መፈተሸና መተመን እና 4) የሙሴን ህግ ማስተማር፣ ህዝቡን መምከርና አስቸጋሪ ነገሮች ውሳኔ መስጠት ፡፡

ናዳብና አብዩዱ በቤተ አምልኮቱ ያልተፈቀደ እሳት አቀረቡ በእግዚአብሄርም ፊት በእሳት ተቃጥለው ሞቱ(ዘሌ 10፡ 1-2) ፤ ይህን አጋጣሚ በመከተል አልአዛርና ኢታምር እግዚአብሄር እንደአዘዘው ትዓዛዝ መሰረት እንደ ካህን አገለገሉ፡፡ የካህናት ሚና የነበረው እግዚአብሄርን ማገልገል ነበር በዘጸዓትና በዘሌዋዊያን ከአምስት ጊዜ ያላነሰ ለዚህ አፅዓኖት ተሰጥታል ፡፡ ቀሪው የዚህ ምዕራፍ የገለፀው የካህናቱን ልብስለአገልግሎት ተመሳሳይ እንዲሆንላቸው ነበር፡፡

ዘጸዓት(28፡ 2); ስለዚህ እግዚአብሄር ለሙሴ ለካህናቶቹ ቅዱስ ልብስ እንዲሰራላቸው የተለየ ትዕዛዝ ሰጠው ፤ ዋይሰርቤ ሲናገር እነኚህ ቅዱስ ልብሶች “ ለካህናቶቹ ማዕረግና ክብር ይሰጣቸዋል….ከአገልግሎታቸው ጋር ለሚገናኘው የሚገናኘውን እውነቶች ይገላጣል…..እናም ክህናቶች የተለየ ልብሳቸውን የማይለብሱ ከሆነ ምናልባት ይሞቱ ነበር ፡፡“

እግዚአብሄርን ለማገልገል በሚናችሁ ላይ ትኩረት የማታደርጉ ከሆነ በሌላ መንገድ ሊሄድ ይችላል ፤ ሕዝቄል ሲናገር ካህናቶች ጣዖት እንዲያመልኩ ለህዝቡ ፈቀዱላቸው ስለዚህ ውጤቱ እስራኤላዊያን ወደ ባቢሎን ለግዞት ተላኩ ፤ በቸርች ውስጥ እንደ መሪ ይህት ትኩረት የሚፈልግ ኃላፊነት ነው ፡፡ በሌላ መንገድ የእግዚአብሄርን ሰዎች መምራት መፈለግ የለብንም ፤ ለዛ ነው መነቃቃት ያስፈለገን ፡፡

ዘጸዓት(28፡ 3-5); ሙሴ ለሚችሉ ሰራተኞች(ጥበበኞች) ትዕዛዙን አስተላለፈ የሚሰሩትም የክህነት ልብሶች;“ የደረት ኪስ ኤፉድም፣ ቀሚስም ዥንጉርጉር፣ ሸሚዝም፣ መጠምጠሚያም፣ መታጠቂያምና መታጠቂያም….(በመጠቀም) ወርቅንም፣ ሰማያዊና ሀምራዊ ቀይም ግምጃ ጥሩ በፍታም ይዉሰዱ ፡፡“ አስታውሱ ሰማያዊ-ሀምራዊና ደማቅ ቀይ የክርስቶስን ሰዋዊነትና መለኮታዊነት እንደሚወክል ፡፡

ዘጸዓት(28፡ 6-14); እነኝህ ልብሶች በጣም ጠቃሚ ነበሩ ካህናቶቹ እነዚህን ካለበሱ ሊገደሉ ይችል ስለነበር (ዘጸ28፡ 43) ፡፡ኤፉድ ተሰርቶ የነበረው ከጥሩ በፍታ ነበር “ በወርቅና በሰማያዊም በሀምራዊም በቀይም ግምጃ ከተፈተለ ከጥሩ በፍታም”(ቁጥር 6) ፤ በሁለቱም ትካሻ ላይ አብሮ የሚጋጠም ነበር በቦተውም ላይ በ” ጥበብ በተጠለፈ መታጠቂያ”(ቁጥር 8) ይቀመጣል ፡፡ የከበረ ድንጋዩን በመቅረፅና ከወርቅ ጌጥ ጋር በማድረግ በእያንዳንዱ ትካሻ ላይ የተያያዘ ነበር ፤ በቀኝ ትካሻው የተቀረፀው የከበረው ድንጋይ በ6ቱን ነገዶች ስም ሲሆን; ሮቤል፣ ስምዖን፣ ሌዊ፣ ይሁዳ፣ ዳንና ንፍታሌም(የያዕቆብ ስድስቱ የመጀመሪያ ወንድ ልጆቹ ነበሩ) ፤ በግራ ትካሻው የተቀረፀው የከበረ ድንጋይ በስም ጋድ፣ አሴር፣ ይሳኮር፣ ዛብሎን፣ ዮሴፍና ቢኒያም(የያዕቆብ ታናሽ ወንድ ልጆች) ነበሩ ፡፡ እንደ ሊቀ ካህን አሮን በትካሻው እነኝህን ድንጋዎች ለእስራኤላዊያን እንደ መታሰቢያ ይሸከም ነበር ፡፡ ረቂቅ ጌጥ ድቅቅ ባሉ ዶቃ ወይም ከተጠማዘዘ ክር የተሰራ ሰልክክ ያለ የብረት ስራ ነው ወይም በጥበበኛ የተደረደረን ንድፍንና አብሮ የተተኮሰን ወይም ነገሩ ውጨኛው አካል ላይ የተደረገውን ሁለቱንም በአንድ ላይ አጣምሮ የያዘ ነው ፤ ከዚህ አቀማመጥ በተጨማሪ በአቀማመጡ ላይ የወርቅ ጌጥን በመጠቀም ሁለት መጎንጎኒያ ገመድ በመፍጠር ይያያዥ ነበር ፡፡ የአሮን ልብስ የእርሱን ሚና ህዝቡን ወደ እግዚአብሄር እንዲያቀርብ ያሳስበው ነበር ፡፡

ዘጸዓት(28፡ 15-21); የተጠለፈው የደረት ኪስ የነበረው “ ርዝመቱ ስንዝር ስፋቱም ስንዝር ሆኖ ትክክልና ድርብ ይሆናል”(ቁጥር 16) እናም እንደ ኤፉድ በተመሳሳይ እቃ እና ሰራተኛ ነበር የተሰራው ፡፡ የደረት ኪስ ይጠቅም የነበረው ውሳኔ ለመስጠት ነው ፤ በወርቅ ጌጡ ውስጥ የተቀመጡ የሰዎስት ድንጋዮችን አራት ተርታዎች ይዛአል በእያንዳንዳቸው የተለያዩ ድንጋዮች የተቀረፀው አንድ የእስራኤል ነገድ ስም ነበር ፤ ስለዚህ ካህኑ ወደ ቅዱሱ ቦታ በገባ ጊዜ የነገዶቹን ስም በትካሻውና በልቡ ይሸከማል ፡፡ ሚል(3፡ 17) የሚለው “ እኔ በምሰራበት ቀን እነርሱ የእኔ ገንዘብ ይሆናሉ ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ሰውም የሚያገለግለውን ልጁን እንደሚምር እንዲሁ እምራቸዋለሁ “ ፤ “የተለየ ገንዘብ(ገንዘቤ ይሆኑኛል)” ሚለው ቃል የተለየ ጌጦች ማለት ይቻላል ፡፡

ዘጸዓት(28፡ 22-28); የደረት ኪሱ ከኤፉዱ ጋር በትካሻው ላይ የተያያዘ ነበር እናም መታጠቂያዉ በወርቅ የተጠለፈ ሰንሰለት እጫፉ ላይ በወርቅ ቀለበት ውስጥ ክር የገባበት ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ለሙሴ የሰጠውን ዝርዝር ትዕዛዝ ተመልከቱ ፤ እያንዳንዱ ነገር እግዚአብሄር እንዳቀደው በጥንቃቄ ተሰራ ፡፡

ዘጸዓት(28፡ 29-30); መቼም ቢሆን አሮን ወደ ቤተ መቅደሱ ሲገባ በልቡ ላይ የነገዶቹን ስም ይሸከማል፡፡ ኢየሱስና ጳዎሎስ ሰዎችን በልባቸው በተሸከሙ ጊዜ ይህ ምን በማድረግ ይመሳሰልል ? በእግዚአብሄር ፊት ሰዎችን በልባችን የምሸክመው መቼ ነው ?

በደረት ኪሱ ውስጥ ካህኑ ውሳኔ ለመስጠት የሚጠቅሙትን ኡሪምንና ቱሚምን ይሸከማል ፤ ኡሪም በዕብራዊያን ቅደም ተከተል የሚጀመረው በመጀመሪያው ፊደል ሲሆን ቱሚም ደግሞ የመጨረሻው ፡፡ ትንሽ ሀሳቦች እነዚህ ተራ ቁጥሮች(ወሮዎች) እድልን መወሰን ማለትም; “ኡሪም” ለአይሆንመ ሲሆን “ቱሚም” ደግሞ ለይሆናል የሚለውን ይወክላሉ፡፡በእርግጠኝነት ሁሉም የምናውቀው እንደምንም እግዚአብሄር ለእስራኤላዊያን መለኮታዊ አጋዥ ለመስጠት እነዚህን መሳሪያዎች ውስጥ ተናገራቸው(ዘሌ 8፡ 8; 1ሳሙ 28፡ 6)፡፡

ዘጸዓት(28፡ 31-35); ካባው ተሰርቶ የነበረው ከሰማያው ሱፍ ክር ነበር ፤ ይጠለቅ የነበረው ከኤፉድ፣ ከደረት ኪስና ከትካሻ ልብስ በታች ነበር ፡፡ የካበው ጠርዝ(ቅምቅማት) በወርቅ ቃጭል በአማራጭ ከሰማያዊ፣ ከሀምራዊና ከደማቅ ቀይ ከተሰራ ሮማን የተዋበ ነበር ፡፡ መቼም ቢሆን ሲያገለግሉ ክህናቶች ካባውን ይለብሳሉ ከዚያም ከእግዚአብሄር ቤተ መውደስ ሲገቡና ሲወጡ ቃጭሎቹ ድምፅ ይሰጣሉ ፤ ለምን ? ቃጭሉ ድምፅ የማይሰራ ከሆነ በቅደስተ ቅዱሱ ቦታ ክህኑ እንደሞተ ህዝቡ ያውቃል ፡፡ በካህኑ እግር ላይ ረጅም ገመድ ያስራሉ በቅድስተ ቅዱሳን ቦታ የሞተ እንደሆነ ወደ ውስጥ ሳይገቡ ወደ ውጭ መሳብ ይችላሉ ፡፡

ዘጸዓት(28፡ 36-38); ከጥሩ ወርቅ የተሰራ ሜዳሊያ ቅድስና ለእግዚአብሄር በሚል የተቀረፀ ከሰማያዊ ፈትል ጋር የታሰረና ከጥምጣም ጋር የተያያዘ ነበር ፤ ካህኑ ይህን ለእግዚአብሄር ተቀባይ ለመሆን ያጠልቅ ነበር እና እንዲችሉ “እስራኤላዊያን በሚያቀርቡትና በሚቀድሱት በቅዱስ ስጦታቸው ሁሉ ላይ ያለውን ኃጢዓት ይሸከም”(ቁጥር 8) ፡፡

ዘጸዓት(28፡ 39-43); ለካህናቱ ሸሚዝ፣ ጥምጣም፣ መታጠቂያና ቆቦችን ለካህኑ “ክብርና ውበት እንዲሰጡት”(ቁጥር 40) ከጥሩ በፍታና ከሚያምር ጥልፍ እንዲሰሩ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ አካቶታል ፡፡ እርቃኑን ለመሸፈን ከወገቡ እስከ ጭኑ የበፍታ ሱሪ ካህኑ ይለብስ ነበር ፡፡አሮንና ልጆቹ እግዚአብሄርን እንደ ካህን እንዲያገለግሉት ሙሴ “እንዲቀባቸው፣ እንዲሾማቸውና እንዲቀድሳቸው” ታዘዘ ፡፡ መቼም ቢሆን ካህናቱ ወደመገናኛው ድንካን ሲገቡ ወይም ወደ መሰዊያው ሲቀርቡ እነዚህን ልብሶች ይለብሱ ነበር ስለዚህ አይሞቱም ፡፡

መዝጊያ

ክህናቱ በንፁህ ልብ ወደ ጠረንጴዛው ይመጡ ነበር፣ ህዝቡንም ከተንኮል ውጭ ይወክላሉ እና ከትዓዛዙ ሳያፈነግጡ ያመልኩ ነበር ፡፡ ኢየሱስ የኛ ሊቀ ካህናችን ነው ፡፡ ወደ ቤተ አምልኮቱ(ቤተ መቅደሱ) ለህዝቡ የሚገባ ሊቀ ካህን አያስፈልገንም ምክንያቱም ለእኛ ለሁሌም ሊቀ ካህን ኢየሱስ አለን ፤ ዕባ(4፡ 14) ኢየሱስ የኛ ሊቀ ካህን እንደሆነ ያረጋግጥልናል ፡፡

ዕብ(2፡ 17) “ ስለዚህ የህዝብን ኃጢዓት ለማስተሰረይ ለእግዚአብሄር በሆነው ነገር ሁሉ የሚያምርና የታመነ ሊቀ ካህናት እንዲሆን በነገር ሁሉ ወንድሞቹን ሊመስል ተገባው ፡፡”

  1. Tom Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Exodus (available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/exodus.pdf), p. 251.

  2. Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 240.

ጥያቄዎች

  1. አሮን እንዴት ነበር የክርስቶስ አይነት የነበረው (ዕብ 5፡ 4-6; 9፡ 7-14) ?
  2. የክህነት ልብስ አላማው ምንድን ነበር (28፡ 3) ?
  3. በዘጸ(28፡ 4) ላይ ለመስራት ያስፈልጉአቸውን ልብሶች ዘርዝሩ ፤ በዚህ ጊዜ እግዚአብሄርን ለማገልገል የተለየ ልብስ/አለባበስ መልበስ ዋጋ አለው ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  4. አሮን ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በገባ ጊዜ በልቡ ላይ የእስራኤልን ልጆች ስም ይሸከማል(ዘጸ 28፡ 29-30) ፤ ስለ እስራኤላዊያን እንዲሰራ ብቻ አልነበረም የተጠራው እንዲወዳቸውም እንጂ ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር በምታወሩ ጊዜ “በልባችሁ የምትሸከማአቸው” ህዝቦች እነማን ናቸው ?
  5. እንደ ካህናት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲጠጉ ለአሮንና ለልጆቹ የነበሩት ጥቂት ትዕዛዝ ምንድን ነበሩ ? እንዴት ስለሚእንዲደረጉለትን ነገሮች የተለዩ እንዲሆኑ የፈለገው እግዚአብሄር ለምን ነበር ?
  6. በዘጸ(27-28) ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ(አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Exodus 28:4, 43

“These are the garments that they must make: a breast piece, an ephod, a robe, a specially woven tunic, a turban, and a sash. They are to make holy garments for your brother Aaron and his sons so that they may serve Me as priests...These must be worn by Aaron and his sons whenever they enter the tent of meeting or approach the altar to minister in the sanctuary area, so that they do not incur guilt and die. This is to be a permanent statute for Aaron and for his future descendants.”

የካህናት ልብሶች፥ ሊቀ-ካህናችን ኢየሱስ

ኦሪት ዘፀዓት 27-28 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

እግዚዓብሔር፥ የማደርያዉ ድንኳንን አደባባይ ለመሥራት ዝርዝር ትዕዛዛትን ለሙሴ ሰጠዉ። የማደርያዉ ድንኳል ህዝቡ ራሳቸዉን በእግዚዓብሔር ፊት የሚያቀርቡበት ስፍራ ነበረ። የመስዋዕቱን ስፋራ የሚቀርቡት ካህናት ብቻ ሲሆኑ የተለየ የካህን ልብስም መልበስ ይጠበቅባቸዋል።

በክርስቶስ እንደሚያምን፥ ከሌሎች የተለየን፥ ክርስቶስ በዉስጣችን የሚኖር ካህናት ነን! የደህንነትን ልብስ እና የፅድቅን ካባ የለበስክ ነህ! በራስህ ላይ የምታደርገዉ ወይንም በስራህ የምታገኘዉ ምንም ነገር አይደለም። ከእርሱ የተሰጠ ስጦታ ነዉ! ቀኑን በሙሉ የክርስቶስን ፅድቅ ለብሰህ እና በህልዉናዉ ዉስጥ በመሆን በነፃነት ተመላለስ! እርሱ ይወድሃል! ፍቅሩን ለሌሎች እንድታሳይ እና ክብር እንድትሰጠዉ ለእርሱ ካህን አድርጎ ጠርቶሃል።

"የሚሠሩአቸውም ልብሶች እነዚህ ናቸው፤ የደረት ኪስ ኤፉድም ቀሚስም ዝንጕርጕር ሸሚዝም መጠምጠሚያም መታጠቂያም፤ እነዚህም ካህናት ይሆኑልኝ ዘንድ ለወንድምህ ለአሮን ለልጆቹም የተቀደሰ ልብስ ያድርጉ።....ኃጢአትም እንዳይሆንባቸው እንዳይሞቱም፥ ወደ መገናኛው ድንኳን ሲገቡ በመቅደሱም ያገለግሉ ዘንድ ወደ መሠዊያው ሲቀርቡ በአሮንና በልጆቹ ላይ ይሆናል፤ ለእርሱ ከእርሱም በኋላ ለዘሩ ለዘላለም ሥርዓት ይሆናል።"

ኦሪት ዘፀዓት 28:4, 43

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ትንቢተ ኢሳይያስ 61:10፦ "አክሊልን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽልማትዋም እንዳጌጠች ሙሽራ፥ የማዳንን ልብስ አልብሶኛልና፥ የጽድቅንም መጐናጸፊያ ደርቦልኛልና በእግዚአብሔር እጅግ ደስ ይለኛል፥ ነፍሴም በአምላኬ ሐሤት ታደርጋለች።"
  • መዝሙረ ዳዊት 100:4፦ "እግዚአብሔር ቸር፥ ምሕረቱም ለዘላለም፥ እውነቱም ለልጅ ልጅ ነውና።"
  • ወደ ገላትያ ሰዎች 3:27፦ "ከክርስቶስ ጋር አንድ ትሆኑ ዘንድ የተጠመቃችሁ ሁሉ ክርስቶስን ለብሳችኋልና።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 43