Directions for the Tabernacle: Curtains, Planks, Bars, Veil & Screen
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 26 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እግዚአብሄር ለ40ቀንና ለ40ሌሊት በተራራው ላይ ሙሴን ተገናኘው እዚያውም ለሙሴ ቤተ አምልኮቱን(መቅደስና የመገናኛ ድንካን ተብሎም ይጠራል) እንዲሰራ አሰራሩን ገለጠለት ፡፡ ታቦቱ የያዛቸው አስሩን ትዕዛዝ፣ የመናውን የወርቅ ማድጋና የአሮንን በትር ነበር ፤ ከታቦቱ ከላይ የስርየት መቀመጫ ነበር ፡፡
በቤተ-አምልኮቱ(በቤተ-መቅደሱ) ውስጥ የህብስቱ ጠረንጴዛና የወርቅ መቅረዝ ነበሩ ፤ ዘጸ 26 የሚቀጥለው ሙሴ እንዲሰራቸው ተነግረውት የነበሩትን ነዉ ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት(26፡ 1-6); የመጀመሪያዎቹ 14 ቁጥሮች የሚሰጡን ዝርዝረ ስለ መጋረጃው ነው ፤ ቀለሞቹ ሰማያዊ፣ ወይነጠጅ እና ደማቅ ቀይ በዘጸዓት በዚህ በተለየ ቅደም ተከተል 20 ጊዜ ተጠቅሞባቸዋል ፡፡ የኪሩበል ድዛይን ተሰርቶ የነበረው መጋረጃዎቹ ውስጥ ነበር(ዘፍ3፡ 24; ኢሳ 37፡ 16) ፤ የትም ቢሄዱ ኪሩቤል የእግዚአብሄር መገኘት ወካዮች ናቸው ፤ እግዚአብሄር ይህን ከራሱ እይታ ገልፆት ነበር ፡፡ ለቤተ-መቅደሱ ለራሱ ሰማያዊ፣ ወይነጠጅና ደማቅ ቀይ የሆኑ አስር መጋረጃዎች ነበሩት ፡፡
ዘጸዓት(26፡ 7-14); “ከማደሪያው በላይ ለድንካኑ የሚሆኑ መጋረጃዎች ከፍየል ጠጉር አድርግ”(ቁጥር 7) 11 ነበሩ፡፡ መቼም ቢሆን ነቢያት እጆቻቸውን በፍየሉ ፀጉር ላይ ሲያስቀምጡ ሁልጊዜ ይህ የሚወክለው ከኃጢዓት መለየቱን ነው(ዘሌ 16) ፡፡እነዚህ መጋረጃዎች የተሰሩት በጣም ውድ ከነበረ የሚያምር ጥቁር ጨርቅ ነበር ፡፡ የበግ ቆዳ መሸፈኛና የአሳ(የባድገር የሚባላ ሰሜናዊ በረዳማ ቦታ የሚኖር እንስሳ) ቆዳ መሸፈኛ አሁንም ውሃ የማያሳልፍ ነበር ፡፡
ዘጸዓት(26፡ 15-25); እነዚህ ቁጥሮች ለማደሪያው የሚገልፁት የግራር እንጨት ስለሆኑት ሳናቃዎች ነው ፤ እነዚህ ሳንቃዎች ጠንካራ ጣውላዋች ወይም መቃኖች ነበሩ ? ሳንቃዎቹን አብረው የሚያገጣጥሙ ተሰካኪ እንጨትና መገጣተሚያ እንጨቶች ነበሩ ፡፡በባሉይ ኪዳን ይህ ለእግዚአብሄር ህዝቦች ያሳሰባቸው(ያስጨነቃቸው) ከሆነ እኛንም ሊያሳስበን(ሊያስጨንቀን) ይገባል ፡፡ ለረጅሙ የነበያቱን መፅሀፍትና የህግ መፅሀፍቱ ሀሳብ አለን ብዬ አስባለሁ፤ ይህ ለእግዚአብሄር አስፈላጊ ነው !
ዘጸዓት(26፡ 26-30); እግዚአብሄር ዝርዝር(የጠለቀ) ይወዳል ፤ የሆነ ነገር በሰራችሁ ጊዜ በጥሩ ስትሰሩ እርሱ ይወዳል ፡፡ እግዚአብሄር ለሙሴ ተናገረው “ እንደታደርግ የነገርኩህን በትክክል አድርግ ይህን እንድታስታውስ እፈልጋለሁ !” አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሄር የሆነ ነገር እንድናደርግ ይነግረናል ከዚያም የሚሰማን ጫፉን መቄረጥ እንደምንችል ነው ፤ ነገር ግን መዝ(119፡ 25) ናስብ ያለው “ እንደ ቃል ህያው አድርገኝ ፡፡” የሆነን ነገር በጥልቀት በሰራችሁ ጊዜ በአይምሮአችሁ ውስጥ የሚበልጥ ነገር ይኖረዋል ፡፡
ዘጸዓት(26፡ 31-35); እነዚህ ጥቅሶች ስለ መሸፈኛ ትዕዛዝ ይሰጣሉ ፤ የነበረው ሰማያው፣ ወይነጠጅና ደማቅ ቀይ” ብልህ ሰራተኛ እንደሚሰራ ኪሩቤል በእርሱ ላይ ይሁን”(ቁጥር 31) ፡፡ እስራኤላዊያን የምስክሩን ታቦት ከመሸፈኛው ጀርባ አስቀመጡት ፤ መሸፈኛው ይፈጥር የነበረው በቅዱስ ቦታና በቅደስተ ቅዱሳን መሀከል ልዩነት ማድረግ ነበር ፡፡ በጣም የተቀደሰው ቦታ(ቅድስተ ቅዱሳን) የኪዳኑን ታቦትና የስርየቱን መቀመጫ የያዘ ነበር ፤ ቅዱሱ ቦታ መቃረዙና የህብስቱ ጠረንጴዛ የተቀመጠበት ነበር ፡፡
እንደ አርቱር ፒንክ “ ሰማያዊ፣ ወይነጠጅና ደማቅ ቀይ ይህ ቅደም ተከተል በዘጸዓት ውስጥ 20 ጊዜ በፍፁም ሳይቀያየር ተደጋግማል….ሰማያው የሰማይ ቀለምና እንደ እግዚአብሄር ልጅ የክርስቶስ ንግግር ነው ፤ ደማቅ ቀይ የሁለቱም የመስዋዕትና የሰዉ ክብር ቀለም ነው ፤ ወይነጠጅ ሰማያዊውናን ደማቅ ቀዩን በማቀላቀል የሚገኝ ቀለም ነው ፡፡ ከወይነጠጅ ውጭ ከአይና አንፃር ሰማያዊውና ደማቅ ቀዩ በጣም ደምቆ ይታያል; ወይነጠጁ በመሀከላቸው በመምጣት አንዱ ከሌላዉ ያለውን በጣም የተራረቀውን ጥላ ያደርግበታል ፡፡ እነዚህ ቀለም አለመመሳሰል በቅድመ ክርስቶስ ውስጥ አለ ፤ እሱ ሰውም አምላክም ነበር ምንም እንካን እነዚህ ሁለት በጣም የተራረቁ የማይመሳሰሉ ተፈጥሮዎች በአንድ ፍፁም ሰው ውስጥ ተገለጡ ፡፡ ስለዚህ ወይነጠጁ በሰማያዊውና በደማቅ ቀዩ መሀከል መምጣቱ ፍፁም የሆነ መገጣጠም ወይም ሁለቱ የሱን ተፈጥሮን ውህደት ነው የሚናገረው፡፡”
ኢየሱስ በሞተ ጊዜ መሸፈኛው ተወገደ ! ስለዚህ አሁን ወደ አድሱ ኪዳን ደርሰናል ፤ አሁን ወደ እግዚአብሄርን መገኘት ደርሰናል(ማቴ27፡ 50-51) ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴን መሸፈኛውን በሰማያዊ፣ በወይነጠጅና በደማቅ ቀይ እንዲሰራው ተናገረው ነገር ግን በሁሉም ጊዜ ልጂ በሀሳቡ ነበር (ማር 15፡ 37-38) ፡፡ ለአይሁዳዊ ወደ አባታቸው መድረስ አሁን ተሰንጥቐልማ ተገፋልም ሀይማኖታቸውም ተፈፅማል(ሉቃ 23፡ 45-46) ፡፡
መሸፈኛው የሚያወራው ስለኢየሱስ ነው ! የሚወክለው የሱን ስጋ ነው ! (መዝ 27፡ 4) ፤ ይህ ነው አስራኤላዊያን የፈለጉት-በቤተ አምልኮቱ ውስጥ በእርሱ መገኘት እንዲሆኑ(መዝ 26፡ 8) ፤ ነግር ግን አሁን ኢየሱስ መንገድም፣ እውነትና ህይወት ነው ፡፡ ቀጥተኛ አማኝ አይሁዶች ለረጅም ጊዜ በእግዚአብሄር ግቢ ውስጥ ነበሩ ነገር ግን አልቀጠለም ! ኢየሱስ መሸፈኛውን አስወግዶታል ፡፡ በክርስቶስ በኩል ወደ እግዚአብሄር መገኘት መጥተናል ፡፡
ሁሉም የዚህ ሀሳብ ወደ መሲሁ ነው የሚያመለክቱት በተራራው ጫፍ ላይ እግዚአብሄር አሰራሩን ለሙሴ በመግለጥ ነበር መለማመድ የጀመረው ፤ በመጨረሻም እግዚአብሄር ልጁ እንደሚጮህ፣ መጋረጃው እንደሚወገድና እስራኤላዊያን ቀጥለው የእርሱን መገኘት በዚያ ቤት ውስጥ እንደማያዩት ያውቅ ነበር ፡፡ ይህ ያለው ክርስቶስ ውስጥ ነው ፡፡
ሁሉም መዝሙሮች የጮሁት በብዙ ለቤተ አምልኮቱ፣ በብዙ ለመገኘቱ ፤ ከዚያም ኢየሱስ ሲናገር “ እኔ ከሁሉም እበልጣለሁ” ይህ የሚያምር አስደናቂ መልክ ነው ቤተ አምልኮቱ ወደ ክርስቶስ ማመልከቱ፡፡
- አሁን ሁሉንም የእርሱን ሙሉነት በክርስቶስ አኖረ(ቆላ 1፡ 19) !
- እግዚአብሄር ነው ብለን የምናስበው ሁሉም ነገር አሁን በክርስቶስ ነው(ቆላ 2፡ 9) ፡፡
- በክርስቶስ ወደ ሁሉም ነገር ደርሰናል (ቆላ 2፡ 3) ፡፡
- እርሱን የምትሹ ከሆነ እያንዳንዳን(ሁላንም) መንፈሳው በረከት ትፈልጋላችሁ(ቆላ 3፡1) ፡፡
- ወደ ቤተ መቅደስ፣ ወደ ቤተ አምልኮ ወይም ድንካን መሄድ አያስፈልገንም ፤አሁን ሁሉም በረከቶች በክርስቶስ በኩል መጥተውልናል(ኤፌ1፡3) ፡፡
መዝጊያ
አንዳንድ ጊዜ በቤተ አምልኮቱ ውስጥ እግዚአብሄር በሁሉም ማመልከቱን ማሰብ ይከብዳል ፤ በቀስታ(ተረጋግቶ) ፡፡ በሚበቃው ጥልቀት የምንመለከት ከሆነ እዚያ መሲሁን እናየዋለን ምክንያቱም የእግዚአብሄር ቃል ስለሆነ ፡፡
Arthur W. Pink, Exposition of the Gospel of John (Grand Rapids: MI, Zondervan, 1975), p. 600.
Warren W. Wiersbe, The Bible Expository Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 239.
ጥያቄዎች
-
በዘጸ(26፡ 1) እግዚአብሄር ስለ አስሩ መጋረጃዎች ሙሴን አዘዘው ፤ እግዚአብሄር ሙሴ እንዲጠቀማቸው የነገረው ሰዎስቱ ቀለማት ምንድን ነበሩ ? የእነዚህ ሰዎስት ቀለማት አስፈላጊነት ምንድን እንደነበር ምን ታስባላችሁ ?
-
ከተወያየንባቸው ከአስሩ መጋረጃዎች በተጨማሪ ሙሴ 11 ተጨማሪ እንዲሰራ ታዘዘ ፤ ለእነዚህ ለተጨማሪዎቹ መጋረጃዎች ምክንያቱ ምን ነበር(ዘጸ26፡ 7) ?
-
ብር አንዳንድ ጊዜ በመፅሀፍ ውስጥ ይጠቀሳል እንደ ዘጸ(26፡ 19) እንዳለው ፤ በሚከተሉት መፅሀፍት ውስጥ የተጠቀመበትን ብር እንዴት ታዩታላችሁ(ዘጸ 21፡ 32; ዘሌ 5፡ 15; 27፡ 3; ዘኁ 18፡ 16; ማቴ 26፡ 15) ?
-
በምስክርነቱ ታቦት ላይ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ ምንድን ነበር(ዘጸ 26፡ 34) ? ይህ እንዴት ወደ ክርስቶስ ያመለክታል(ሮሜ 3፡ 23-26) ?
-
ሊቀ ካህናቱ ብቻ በአመት አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ይገባል(ዕብ9፡ 7) ፤ ይህን በማዎቅ በዕብ(9፡ 12) ላይ ያለው እውነት እንዴት እናንተና ያበረታታችኃል ? ሌሎችን ለማበረታታት ይህን እንዴት ልትጠቀሙበት ትችላላችሁ (10፡ 11-14) ?
-
በዘጸ 26 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 26:5-6
“Make 50 loops on the one curtain and make 50 loops on the edge of the curtain in the second set, so that the loops line up together. Also make 50 gold clasps and join the curtains together with the clasps, so that the tabernacle may be a single unit."
የማደርያዉ ድንኳን ትዕዛዝ፦ መጋረጃ፣ ሳንቃዎች፣ ዘንጎች፣ መሸፈኛ እና መታያዉ
ኦሪት ዘፀዓት 26 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እግዚዓብሔር የኪዳኑን ታቦት የሚይዝበትን፥ የማደሪያዉ ድንኳን እና መሸፈኛዉ እንዴት እንደሚሠራ ዝርዝር ትዕዛዛትን ለሙሴ ሰጠዉ። ለእስራኤላዉያን የተሰራዉ ማድርያዉ ድንኳን በምድረ በዳ ዉስጥ እንደ ቤተ-ክርስትያን አገልግሏል። በግንባታዉ ዝርዝር ዉስጥ አምሳ ቁጥር በጣም ብዙ ጊዜ ተጠቅሷል። እናም ሁለት ነገሮች አንድ ሲሆኑ እና ሲጋጠሙ ይታያል።
አምሳ ቁጥር የ "ጴንጤቆስጤ" ቃል ትርጉም ሲሆን ሙሉነትን ሊያመለክት ይችላል። አምሳ፦ ከ-የእግዚዓብሔር መንፈስ ቅዱስ መምጣት ጋራ የሚገናኝ ሲሆን የሚያሳየዉም ከሸክም ነፃ መዉጣትን እና ነፃነትን ነዉ። የማደርያዉን ድንኳን እና በህዝቡ መካከል ስለሆነዉ የእግዚዓብሔር ህልዉና ስታጠኑ፥ ከተሸካማችሁት ማንኛዉም ሸክም በማስወጣት መንፈስ ቅዱስ ነፃ እንዲያውጣችሁ ፀልዩ! በእግዚዓብሔር ህልዉና ሀሴት ማድረግ ይሁንላችሁ!
"ምሳ ቀለበቶችን በአንድ መጋረጃ አድርግ፥ አምሳውንም ቀለበቶች በሁለተኛው መጋረጃ ዘርፍ አድርግ፤ ቀለበቶቹ ሁሉ እርስ በርሳቸው ፊት ለፊት ይሆናሉ። አምሳ የወርቅ መያዣዎች ሥራ፤ ማደሪያውንም አንድ እንዲሆን መጋረጆችን እርስ በርሳቸው በመያዣዎች አጋጥማቸው።"
ኦሪት ዘፀዓት 26:5-6
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘፀዓት 26:10-11፦ "ከተጋጠሙት መጋረጆች በአንደኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ አምሳ ቀለበቶች አድርግ፤ ደግሞ ከተጋጠሙት ከሌሎቹ በአንድኛው መጋረጃ ዘርፍ ላይ እንዲሁ አምሳ ቀለበቶች አድርግ። አምሳም የናስ መያዣዎችን ሥራ፥ መያዣዎችንም ወደ ቀለበቶች አግባቸው፥ ድንኳኑም አንድ እንዲሆን አጋጥመው።"
- መዝሙረ ዳዊት 16:11፦ "የሕይወትን መንገድ አሳየኸኝ፤ ከፊትህ ጋር ደስታን አጠገብኸኝ፥ በቀኝህም የዘላለም ፍሥሐ አለ።"
- ወደ ቆላስይስ 1:19-20፦ "እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ እንዲኖር፥ በእርሱም በኩል በመስቀሉ ደም ሰላም አድርጎ በምድር ወይም በሰማያት ያሉትን ሁሉ ለራሱ እንዲያስታርቅ ፈቅዶአልና።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 42
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።