Direction for the Tabernacle: Ark, Mercy Seat, Table & Lampstand
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 25 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በዘጸዓት ውስጥ ያየነው ነፃ አውጪውን ኢየሱስን ህዝቡን ከባርነት ነፃ ያወጣው ላይ ነው ፡፡ እስራኤላዊያን በበርሃ ዙሪያ ተንከራተቱ ከዚያም እግዚአብሄር አቅጣጫን ይሰጣቸው ጀመረ ፤ እንዴት እንደሚኖሩ አስሩን ህግና ትዕዛዝትን ሰጣቸው ፤ በተጨማሪም ልቡን ገለጠላቸው; የእርሱ በህት እንደሆኑ፣ የንጉስ ካህናት እንደሆኑና ቅዱስ ህዝብ እንደሆኑ ፡፡
በዘጸ 24፡ 18 ላይ ሙሴ ሁሉንም ህጎችና ትዕዛዝት ተቀበለ ከዚያም ወደ ተራራው በመውጣት ወደ ደመናው ገባ ፤ 40 ቀንና 40 ሌሊትም በዚያ ቆየ ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት(25፡ 1); እግዚአብሄር ለሙሴ በጣም አስደናቂ የሆነ ነገር ገለጠለት ፤ በህዝቡም መካከል እንዴት እንደሚኖር ገለጠ ፡፡አስታዉሱ እዚህ ጋር እስራኤላዊያን ተራራውን ለመንካት እንካን አልፈቀዱም ነበር ?
ዘጸዓት(25፡ 2); ሙሴ ከእያንዳንዳቸው በፍቃዳቸው የሰጡትን ስጦታ ተቀበለ ፤ ይህ አምልኮ ነበር ፤ አንዳንድ ጊዜ ከመታዘዝ መስጠት ይቀላል ፡፡ምንም እንካን እግዚአብሄር ይህን የጠራው “ ከመስዋዕት ይልቅ መታዘዝ እፈላጋለሁ“ ፤ እግዚአብሄር ስጦታ መቀበል የፈለገው እስራኤላዊያን የእግዚአብሄርን መገኘት መለማመድ ለሚችሉበት ቦታ መስሪያ ነበር ፡፡
ዘጸዓት(25፡ 3-7); ሙሴ የተወሰነ አቃ ለስጦታው ሰበሰበ ፡፡ እስራኤላዊያን ራሳቸውን የሰራቸው ቀለማት ነበራቸው; ሰማያዊ(ባለቅርፊት አሳ)፣ ሀምራዊ(ቀንድ አውጣ) እና ደማቅ ቀይ(የተፈጨ አንቁላልና ትል) ፤ ሙሴ በተጨማሪም ረቂቅ የአልጋ ልብስ መስሪያ ሰበሰበ; ግብፃዊያን ለረቂቅ አልጋልብስ ስራ ጥሩ የሆነ ስም ነበራቸው ፡፡ ይህ ሁሉ ስጦታ ከየት እንደመጣ ታስባላችሁ ? ግብፅ (ዘጸ 12፡ 35-36) !
የሆነው ሆኖ እስራኤላዊያን በፍፁም ገንዘብ አልነበራቸውም ፤ የኛ ገንዘብ የኛ አይደለም ፡፡እግዚአብሄር እንዴት በእናንተውስጥና በኩል ሊሰራ እንደፈለገ እናንተ ገንዘብ ማስተላለፊያ የሚወጣባችሁና የሚገባባችሁ ናችሁ ፡፡ የተቀደሰ ቦታውን ለመስራት እስራኤላዊያን ያመጡት እቃ ተትረፈረፈ አስደናቂ መልክ ነው ያ ህዝብ ለመስጠት ፍቃደኛ እንደነበር ፤ ከበቂ በላይ ነበር (ዘጸ 36፡ 3-7) ፤ ለኔ ሰዎች ከልባቸው ሲሰጡ እንደዚህ ነው የሚሆነው (1ቆሮ9፡ 7) ፤ ህዝቡ ለተለየ አላማ የተለየ ነገር አመጡ ፡፡
ዘጸዓት(25፡ 8-9); ህዝቡ ስለገነቡት መፅሀፍት የተጠቀመባቸው አራት ቃሎች ናቸው ፡፡
- መቅደስ ምልክት ነው ማለትም ለእርሱ መገለጥ ማለትም ክብሩ የሚገኝበት ስፍራ ነው ፤ ይህ እንደ ቅዱስ ከነበረው የሚነድደው ቁጥቐጦ ጋር ተመሳሳይ ሀሳብ ነው ፡፡ክብር ማለት “ክብደት” ነው ፤ የእርሱን መገኘት ክብተደት ተሰምታችኃል ፡፡
ቤተ-አምልኮ(ታቦት/ የሙሴ ፅላት) እንደ መቅደስ ተመሳሳይ ነገር ነው የቃል ብቻ ነው ልዩነታቸው ፡፡ ለእግዚአብሄር እንደ መገለጫ ቦታ ተመሳሳይ አሳብ ነው ያለው ፤ስንመለከተው ከሌሎች ዘላን ድንካኖች የሚለየው ነገር የለም፡፡
የመገናኛው ድንካን; ይህ ሌለኛው ቀል ነው ለመቅደሱ ወይም ቤተ-አምልኮው (ዘጸ 26፡ 36; 29፡ 42; 35፡ 21)፡፡
የምስክርነቱ ታቦት(ፅላት); እነዚህ አራቱም ሁሉ የተለያዩ ቃላት ለተመሳሳይ ቦታ (ዘጸ 38፡ 21; ዘኁ 9፡ 15) ፤ ሁሉም ቃል የሚሉት የእግዚአብሄር መገኘት በህዝቡ መሀከልነው ነው ፡፡ ስለቤተ አምልኮቱ (በታቦቱ) ውስጥ ምን መገኘት እንዳለበት እግዚአብሄር በደንብ በዝርዝር አደረሰ(ተናገረ) ፡፡
ዘጸዓት(25፡ 10-15); መጀመሪያ የተሰራው የኪዳኒ ታቦት ነበር “የግራር እንጨት ታቦት” ፡፡ የግራር እንጨት ቀጥያለ፣ ክፍተት የለለውና ለመስራት ወይም ለተባይ ያልተጋለጠ ነው ፤ ግራር ጠንካራ ዘርና በቀለም ብርቱካናማ-ቡናማ ነው ፡፡ የተሸፈነው በወርቅ ነበር፡፡ ኢያ(2፡ 1) የሚጠቅስው የግራር ጫካ (በአንዳንድ የመፅሀፍ ቅዱስ እትሞች ላይ ሰጢም ብለዉ ይጠሩታል) ፡፡ እስራኤላዊያን ታቦቱን እንዳይነኩ ታዘዙ ፤ አስታውሱ ዖዛ ታቦቱን በነካ ጊዜ ወድያውኑ ሞተ(2ሳሙ 6፡ 6-7)፡፡
ዘጸዓት(25፡ 16-22); በኪዳኑ ታቦት ውስጥ አስሩ ህጎች (የምስክርነቱ ጽላት)፣ የመናው የወርቅ ማድጋ(ዘጸ16፡ 32-34) እና የአሮን በትር (ዘኁ 17) ነበሩ ፡፡ ከዚያም እስራኤላዎያን በጥሩ ወርቅ የስርየት መቀመጫውን ሰሩ ፤ ማክአርተር ይህን የገለፀው “ ታቦቱ መክደኛ ወይም መሸፈኛ “የስርየት መቀመጫ” ወይም ስርየት የሚደረግበት ቦታ ነበር ፡፡ የመስዋዕቱ ደም (በስርየት መቀመጫው) የሚመለከተው በእግዚአብሄርና በተጣሰው የእግዚአብሄር ህግ መሀከል ነበር ፡፡” “ምህረት” ማለት መስዋዕት ወይም ይቅርታ አገኝ ማለት ነው ፤ ኢየሱስ የእኛ መስዋዕት ሆነ የስርየቱ መቀመጫ ለእስራኤላዊያን ያገለገላቸው ይቅርታ እንደማግኛ ነበር ነገር ግን ይህ አልቀጠለም(1ዮሐ 2፡ 2) ፡፡ ኢየሱስ ራስ ለእኛ ኃጢዓት ይቅርታ ሰጪ ነው ! ሰዎችን ወደ መሲሆ ለማምጣት ይህ የመጀመሪያው ደረጃ ነው ! ጠቦት ይሰዋ የነበረው በስርየት ቀን በአመት አንዴ ነበር (ዮም ኩፐር) ከዚያም በስርየት መክደኛው ላይ ደማቸው ይቀመጣል ፡፡
ዘጸዓት(25፡ 23-30); እስራኤላዊያን የገበታ ጠረንጴዛ ሰሩ(የግራር እንጨት ጠረንጴዛ) ፤ ወጭቶችን፣ ጭልፋዎችን፣ መቅጃዎቹንና ጽዋዎችን የተሰሩት ከንፁህ ወርቅ ነበር ከዚያም ሁል ጊዜ በእግዚአብሄር መገኘት ፊት ህብስቱን በጠረንጴዛው ላይ አደረጉ ፡፡ ካህኖች ባቻ የመገኘቱን(በፊቱ ያለዉን) ህብስት ይበላሉ (ዘሌ 24፡ 5-9) ፡፡ 12 ያልቦካ ህብስት በዚህ ቦታ ላይ ይቀመጣል 12ቱን ነገዶች ለመወከል ፤ ይህ ክርስቶስ በመጨረሻ የእኛ ህይወት ህብስት እንደሚሆን ገላጭ ነው ፡፡ ኢየሱስ ይህን ለአይሁድ በተናገረ ጊዜ እነርሱ ያዉቁት ስለነበረው (ዮሐ6፡ 32-36) ወደ መገኘቱ ህብስት እያመለከታቸው ነበር ፡፡ ሁሉም እነዚህ የምድር ላይ ቤተ አምልኮት አሰራር ወደ መሲሁ ይመለከቱ ነበር ፡፡
ዘጸዓት(25፡ 31-40); ሙሴ በእግዚአብሄር ለእሱ የተፃፈለትን ትዕዛዝ ተቀበለ ፡፡ እስራኤላዊያን ስድስት ቅርንጫፎች የነበሩት የወርቅ መቅረዝ ሰሩ ከመሀከለኛው በተጨማሪ በእያንዳንዱ ጎን ሰዎስት ሰዎስት ነበሩት ፤ ሻማ(ሳባት ሻማ የሚያዝ) ማስቀመጫ ተብሎ ይጠራል ፡፡ ወደ ቤተ አምልኮቱ ሲሄዱ የዚህን ብርሃን ያዩት ነበር ፡፡ ይህ የተሰራው 75 ፓውንድ ከሚመዝን ወርቅ ሲሆነ በተቀደሰ ቦታ ለሚያገለግሉ ካህናቶች ብርሃን ነበር ፤ መንደዱን እንዲቀጥል ዘይቱ እስፈላጊ ነበር ፡፡ የካህናቶቹ ሚና አክል የነበረው ሳያቐርጥ እንዲበራ መጠበቅ ነበር (ዘጸ 27፡ 20-21) ፡፡ ኢየሱስ ሲናገር “ እኔ የአለም ብርሃን ነኝ”(ዮሐ 8፡ 12) ፡፡ የወርቅ መቅረዙ በፍፁም ወደ ዉጪ አይወጣም ኢየሱስም እንደዚሁ ተመሳሳይ ነገር ተናግራል “ ደግማችሁ በጨለማ አትጋዓዙ” ፡፡
እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ሁሉንም ነገር እንዳሳያቸው ተጠንቅቀው እንዲሰሩ አስጠነቀቃቸው ፤ እግዚአብሄር አሰራሩን ለሙሴ በተራራው ላይ አሳየው ፡፡ ሙሴ የእግዚአብሄርን ህዝብ ነፃ ለማውጣትና የዚህ ሂደት አካል በመሆን እስራኤላዊያንን ወደ መገኘት እንዲገቡ የሚረዳ ባላደራ ነበር ፡፡
መዝጊያ
ዕብ(8፡ 5-6) “ እነርሱም ሙሴ ድንካኒቱን ሊሰራ ሳለ እንደ ተረዳ ለሰማያዊ ነገር ምሳሌና ጥላ የሚሆነውን ያገለግላሉ ፡፡በተራራው እንደ ተገለጠልህ ምሳሌ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ብሎት ነበርና ፡፡ አሁን ግን በሚሻል ተስፋ ቃል በተመሰረተ በሚሻል ኪዳን ደግሞ መካከለኛ እንደሚሆን በዚያ ልክ እጅግ የሚሻል አገልግሎት አግኝቶአል ፡፡”
ከእግዚአብሄር የተቀበለው የሙሴ ንድፍ የተሻለው ንድፍ ኢየሱስ ቅጂና ጥላ ነበር !
John MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishing, 2005), p. 121.
ጥያቄዎች
-
እግዚአብሄር በጣም የትልቀት(የዝርዝር) አምልክ ነው እናም ሙሴ ጡሩ ማስታወሻዎችን ወሰደ ፤ በተግባር ንግግር እንዴት ታስባላችሁ(ትገምታላችሁ) ሙሴ እግዚአብሄር ከሰጠው ዝርዝር ጋር በመቀጠሉ (ዕብ8፡5)? እግዚአብሄር የነገራችሁን ፅፋችሁታል ?
-
የኪዳኑ ታቦት ወደ ክርስቶስ የሚያመለክትበትን በጥቂት መንገድ የሚገልፅ አላችሁ ? አዎ ከሆነ ምንድን ናቸው (ዕባ 8፡ 5) ?
-
በዘጸ(25፡ 1-2) ውስጥ ስጦታ እንዲሰጡ ያዘዘው ማን ነበር ? ለእግዚአብሄር ስጦታ ለመስጠት ሲሰማችሁ እንዴት በማድረግ ነው የምትመልሱት (2ቆሮ 9፡ 6-7) ?
-
የቤተ መቅደሱ(የቤተ አምልኮቱ) የመጨረሻ አላማው ምንድን ነበር ?
-
እግዚአብሄር ህጉ ከመሰጠቱ በፊት የምስክርነቱን(ህጉን) በታቦቱ ውስጥ እንዲያስቀምጥ ሙሴን ነገረው ፤ እግዚአብሄር ይህን ለምን እንዳደረገ ምንድን ታስባላችሁ ? እምነት ይበቃንል በመታዘዝ ለመሄድ የእግዚአብሄርን አላማ ሙሉ በሙሉ ሳንረዳ ? ለምን ወይስ ለምን አይበቃም(2ቆሮ 5፡ 7) ?
-
በዘጸ 25 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 25:8-9
“They are to make a sanctuary for Me so that I may dwell among them. You must make it according to all that I show you—the pattern of the tabernacle as well as the pattern of all its furnishings.”
የማደርያዉ ድንኳን፥ ታቦት፣ የስርየት መክደኛ፣ ገበታ እና መቅረዝ
ኦሪት ዘፀዓት 25 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እዛዉ በሲና ተራራ ላይ እያሉ፥ እግዚዓብሔር የቃል ኪዳኑን ታብት የሚሰሩበትን እያንዳንዱ ዝርዝር ትዕዛዛት ለሙሴ ሰጠዉ። ታቦቱ ያገለገለዉ፥ የእግዚዓብሔር ህልዉና ሁልጊዜ ከእስራኤላዉያን ጋራ እንደሆነ በማሳየት ምትክ ነዉ። በሚያማርር እና በሚያጉረመርም ህዝብ አቅራቢያ ለመሆን በአንድ አጥር ዉስጥ መጋባቱ፤ በማደርያ ድንኳን እግዚዓብሔር መቀመጡ ያልተለመደ ነገር ነዉ። የኛ አምላክ ግን ትሁት እና መሃሪ ነዉ! ለሓጥያተኞች ቅርብ ነዉ!
ይመስገነዉና፥ ለአዲሱ የኪዳን አማኞችም ሁልጊዜ ከእኛ ጋራ እንደሚሆን እና እንደ መንፈስ ቅዱስ ኃይል ደግሞ በመካከላችን እንደሚኖር እግዚዓብሔር ቃል ገብቷል። ዛሬ፥ ሁልጊዜ ከእኛ ጋራ ስላለዉ የእግዚዓብሔር መገኘት አመስግን!
"በመካከላቸውም አድር ዘንድ መቅደስ ይሥሩልኝ። እኔ እንደማሳይህ ሁሉ፥ እንደ ማደሪያው ምሳሌ እንደ ዕቃውም ሁሉ ምሳሌ፥ እንዲሁ ሥሩት።"
ኦሪት ዘፀዓት 25:8-9
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘፀዓት 25:22፦ "በዚያም ከአንተ ጋር እገናኛለሁ፤ የእስራኤልንም ልጆች ታዝዝ ዘንድ የምሰጥህን ነገር ሁሉ፥ በምስክሩ ታቦት ላይ ባለው በሁለት ኪሩቤል መካከል፥ በስርየት መክደኛውም ላይ ሆኜ እነጋገርሃለሁ።"
- መዝሙረ ዳዊት 139:7-10፦ "ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? ወደ ሰማይ ብወጣ፥ አንተ በዚያ ነህ፤ ወደ ሲኦልም ብወርድ፥ በዚያ አለህ። እንደ ንስር የንጋትን ክንፍ ብወስድ፥ እስከ ባሕር መጨረሻም ብበርር፥ በዚያ እጅህ ትመራኛለች፥ ቀኝህም ትይዘኛለች።"
- የማቴዎስ ወንጌል 11:29፦ "ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ ከእኔም ተማሩ፥ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፥ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 41
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።