Festivals of Unleavened Bread, Harvest, & Ingathering
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 23-24 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በሲና ተራራ እግዚአብሄር ለሙሴ አስሩን ትዕዛዝ ብቻ ሳይሆን የሰጠው በተጨማሪም እንዴት ዝርዝር ሁኔታን እንዲያደርግ ዝርዝር ትዕዛዞችን ጭምር ሠጠው ፡፡ ትናትና ስለ እንስሳት ስርቆት፣ ዘርና ስለ ሰው ንብረት ስለሚያወሩ ትዕዛዞች አውርተናል ፤ በእነዚህ ሁሉ እግዚአብሄር የሚፈልገው ቅዱስ እንድንሆን ነው ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት(23፡ 1-9); እነኚህ ህጎች ስለ ታማኝነትና ስለ ፍትህ ናቸው ፤ እነኚህ ህጎች ከማንበብ በላይ ለመኖር ጠንካራ ናቸው ፤ ሀጢዓትን መቐቐም እንድንችል ይረዱናል ፡፡ ለዚህ ምሳሌ ኤልዛቤል ትሆነናለች ይህ ትዕዛዝ ያስጠነቀቀውን አድርጋለች፣ ወደ ሁኔታው ራሳን በማስገባት ንፁሀን ገድላለች እናም በ(1ነገ 20፡ 7-9) የሆነው ፤ አዚህ ጋር ያለው ሀሳብ ንፁሃን መገደሉየሆነው መሆኑ አይደለም ፤በዚያን ጊዜ እግዚአብሄር ጉቦ እንዳይቀበሉ ተናግራል ፡፡ ኑሮአቸው በኢፍትሀዊና በጉቦ የሆነ አለሞች አሉ እግዚአብሄር ያ እንዲሆን አይፈልግም ፡፡
ዘጸዓት(23፡ 10-13); ቁጥር 10-17 የሚያወራው ስለ ድግሶች ነው ፡፡ እግዚአብሄር አስራኤላዊያንን በሰባተኛው አመት መሬታቸው እንዲያርፍ እንዲተውት አዘዛቸው ፤ ለምን ? በዚህም በእነሱ መካከል ያሉት ድሀዎች ከመሬታቸው መብላት እንዲችሉ ፤ አስካሁን በምድረበዳ(በበርሃ) ናቸው ይህ የሚሆንበት ምድር አልደረሱም ፡፡ መርሁ አንተ እናንተ ብታርፉም እግዚአብሄር ሌሎችን የሚባርክበት ነው ፡፡
ዘጸዓት(23፡12-14); እግዚአብሄር ለሁሉም አካል የመተንፈሻ ጊዜ ሰጥታል ለእንስሳት እንካን፣ ለባሪያና ለስደተኛም ፤ እግዚአብሄር ህዝቡን በእነዚህ ትዕዛዞች ውስጥ ያሳሰበው-ጣዖት እንዳይሆኑባቸው ነው ! እግዚአብሄር ለእርሱ በአመት ሰዎስት ጊዜ ክብረ በዓል እስራኤላዊያንን እንዲያከብሩለት ፈለገ ፡፡
ዘጸዓት(23፡ 15); ያልቦካ ዳቦ በዓል የሚያከብረው ኃጢዓት የለም ነው ፤ እርሾ የኃጢዓት ምልክት ነው ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን እንከን የሌለበት በግ በአስረኛው ቀን እንዲፈልጉና በአስራራተኛው ቀን እንዲሰውት አዘዛቸው ፡፡ በዓሉ የሚጀምረው በፋሲካ ቀን14ኛው እና በሚቀጥሉት ከ15-21 ነበር ፤ የአቢብ ወር በግምት መጋቢት ውስጥ ወይም ሚያዚያ ውስጥ ነበር ፡፡ ዘጸዓት ተጀምሮ ነበር ! ለዛም ነበር 12ቱም የእስራኤል ነገድ በአመት ሰዎስት ጊዜ ያከብሩ የነበረው ፡፡እግዚአብሄር ነፃ አድርጋቸዋል ! (ዘጸ 12፡ 15-16; ዘሌ 23፡ 6; ዘኁ 28፡ 17)፡፡
ደግሞ ደግሞ ሙሴ ስለዚህ በዓል ፅፋል ፤ ከአይሁድ ሰዎች ጋር ለመገናኝት(ለመተሳሰር) ባዓሉን ልንረዳው ያስፈልገናል ! በዘጸዓትና በፋሲካው ምክንያት መሲ ኖረን ! የራሳጭንን ቅርስ ልንገነዘብ(ልንረዳ) ያስፈልገናል !
ዘጸዓት(23፡ 16ሀ); የመከር በዓል ያለው የጊዜ ርቀት ከፋሲካ በዓል በኃላ 50 ቀኖችን ነበር (ግንቦት/ሰኔ) ፡፡ የሳምንቱ ድግስ እና ጴንቴኮስታ በመባል ይታወቅ ነበር ፤ ሁሉም 12 ነገዶች አክብረውታል ! ይህ የሚሆነው የመኸር በኩራት በደረሰ ጊዜ ነው(ዘጸ 34፡ 22; ዘሌ 23፡ 15-21) ፡፡ እሰራኤላዊያን ሁለት የቦካ ዳቦ(በእርሾ)፣ ሰባት እንከን የሌለባቸው ጠቦቶች፣ አንድ ልጅ በሬ እና ሁለት የበግ ወጠጤ (እነዚህ ሁሉ ለእግዚአብሄር የሚቀርቡ በኩራት ናቸው) ፡፡ እግዚአብሄር ሲናገር “ ያደረኩላችሁን እንዳትረሱ” ፡፡ የጴንቴኮስታል ቀን መንፈስ ቅዱስ ወደ ቸርች የመጣበት ቀን ነበር(ሐዋ 2፡1) ፡፡ምርጥ ምርጡን ለእግዚአብሄር እያመጡ ይህንን በዓል ለ50 ቀን ያከብሩታል፣ ከፋሲካ እስከ ጴንቴኮስታል ሰባት ሳምንት ነው፡፡ ለእግዚአብሄር የምታቀርቡትን ወደ ኃላ አትመልሱ !
ዘጸዓት(23፡ 16ለ); የማከማቸት በዓል የዳስ ወይም የቤተ አምልኮት በዓል በመባል ይታወቃል ፤ የዚህ በዓል የጊዜ ቆይትው መስከረም /ጥቅምት ነው (ዘዳ 16፡ 13; ዘሌ 23፡ 34) ፡፡ እስራኤላዊያን በድንካን/በዳስ/በቤተ አምልኮ ሲኖሩ እንዴት እግዚአብሄር 40 አመት በበርሃ ውስጥ እንዳወጣቸው ያከብሩት ነበር ፡፡ በእስራኤል ዛሬ(በአሁኑ ጊዜ) ትንሽዬ ዳስ በሰገነታቸውና በእግር መሄጃ ላይ በመስራት ያከብሩታል ፡፡ እግዚአብሄር ከ40 አመት በርሃ ውስጥ ስላወጣቸው ይከብሩታል ፡፡
ዘጸዓት(23፡ 17-19); ሴቶችና ልጆች ከዚህ በዓል ተካተው ነበር ፡፡ ስብ የመስዋዕት ምርጡ አካል ነበር ፤ ልጅ ፍየሎች ለሰዎች ተመራጭ ምግብ ነበር ፤ ይህን በወተት መቀቀል ጣዕሙን የተሻለ አድርጎታል ነገር ግን ፍየሉን በእናቱ ወተት መቀቀል በልብ ውስጥ የኃጢዓት ባህርይ እንዳለ ይገልጣል ፤ እናም የሚያንፅባርቀው የከንዓናዊያን አከባበር ነበር ፡፡ ዋይሰርቤ ሲፅፍ “ ይህ(ወተቱን) ልምላሜ ለማስተዋወቅ እንዲረዳቸው በዚያን ጊዜ በዛፍ ላይ እና በማሳቸው ላይ ይረጩት ነበር ” ፤ እግዚአብሄር እነዚህን ነገሮች ለመግለፅ ነበረው ፡፡ አንድ ሀተታ ሰጪ የፃፈው “ ይህ እግዚአብሄር በወላጆቹና በልጅ መሀከል የሰጠውን ግንኙነት አለማክበር ነበር ፡፡”
ዘጸዓት(23፡ 20); ቀይ ባህር ላይ ከኃላ ይጋዓዝ የነበረው መልዓክ በእስራኤላዊያን ፊት ይሄድ ነበር ፡፡ አስራ አንድ ጊዜ በብሉይ ኪዳን መልዓኩ (ቅድመ ክርስቶስን) አሳይቶታል (ዘፍ 32: 1-2፣ 24-32; 48፡ 16; ዘጸ 3; 14፡ 19; 23፡ 20; ኢያ 5፡ 13-15; መሳ 6፡ 11፣ 22; 13፡ 3-4; 1ነገ 19፡ 7; ኢሳ 37፡ 6; ዳን 3፡ 25) ፡፡ እግዚአብሄር ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር ተገልጦ ነበር ከሙሴና ከህዝቡም ጋር ተመሳሳይ ነገር አደረገ ፡፡
ዘጸዓት(23፡ 21-29); ኢየሱስ ለእስራኤላዊን ታይቶላቸው ነበር (ይሁ 5) ! ብቸኛው ህዝቡን ከግብፅ ነፃ አውጥቶ የነበረው እግዚአብሄር ነበር(ኢሳ 7፡ 18; ዘዳ 7፡ 20) ፤ ከፊታቸው የሄደው እግዚአብሄር ነበር ፡፡ የእግዚአብሄር ጊዜ በጣም ጥሩ ነው ! ልናምነው ይገባናል !
ዘጸዓት(23፡ 30-33); ነገሮች በእግዚአብሄር ጊዜ እንዲሆኑ እንፍቀድ ቢዘገዩ እንካን ፡፡ በህይወት ውስጥ በትንሽ ትንሽ የሚፈልግ ማነው ? አሁን እያንዳንዱ ምድርን ይፈልጉታል ፡፡ ሜየርስ እንደ ፃፈው “ ትንሽ በትንሽ(ሁሉም ጎዞ) በግለሰብ ነፍስ የሚቀጥል እግዚአብሄር የሚያደርገው ስራ ነው ፤ ትንሽ በትንሽ(እያንዳንዱ ጎዞ) በአለም ላይ ተሻጋሪ ድል ማድረግ ነው ፤ ትንሽ በትንሽ(ሁሉም ጎዞ) አላመው ለሰውና ለመልዓክት እንዲገለጥ የተደረገውን ቤዛነት ማሳወቅ ነው ፡፡” ትንሽ በትንሽ(እያንዳንዱን) የመዋጀት ጥቅም በምድር ውስጥ በራሱ እንዲታወጅ መፍቀድ ነው ፡፡ ትንሽ በትንሽ(በእያንዳንዱ ውስጥ) እግዚአብሄር እቅድ አለው ፤ ሁሉንም አሁን እንፈልጋቸዋለን ነገር ግን እግዚአብሄር ይህ በተለያየ መንገድ አለው ፡፡
እግዚአብሄር ለምድሪቱም ድንበር አበጀላት፤ ለእነሱ ማሳሰቡን ቀጠለ; አይናችሁን በእኔ ላይ አድረጉ እንጂ በሌላ አምላክ ላይ አታድርጉ ዌም ወጥመድ ይሆኑባችኃል ፡፡ ደግም ደግሞ እንደገና እግዚአብሄር “ እኔ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ፣ አይናችሁን በእኔ ላይ አድርጉ በጊዜውም በእኔ ታመኑ፣ በበዓላችሁ ውስጥ እኔን አክብሩኝ እና አንድ ቀን በጊዜው ከእናናተ ጋር እሄዳለሁ ፡፡”
ዘጸዓት(24); ሙሴ ለሽማግሌዎቹ ሁሉንም ትዕዛዝ ነገራቸው ፤ እነርሱም “እናደርገዋለን ብለው” መለሱለት ከዚያም መሰዊያ በማቆም መስዋዕት አደረጉ ፡፡ ኪዳኑና አነበቡም ደሙንም በህዝቡ ላይ ረጩ ፡፡ሙሴና ኢያሱ ወደ ላይ ሄዱ ፡፡ ቁጥር 18 ላይ ሙሴ ወደ ደመናው ውስጥ ወጣ በዚያም እግዚአብሄር ጋር ለ40ቀንና 40ሌሊት ቆየ ፡፡
መዝጊያ
ዘጸዓትን በማናበብ ውስጥ ስትሄዱ እግዚአብሄር መስማት በሚያስፈልጋችሁ ይናገራችኃል ፤ መጫናችሁን ቀጥሉ ፤ በትዕዛዝ ውስጥ እንካን እግዚአብሄር ለእናንተ ሊናገራችሁ ይፈልጋል ፡፡ እኔ በጣም የተበረታታሁት እንዴት እግዚአብሄር ባለው “ እኔ በህይወታችሁ ውስጥ ያደረኩላችሁ ሁሉንም አክብራቸው ፤ እናም በምታደርጉት አስታውሱ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ በእያንዳንዱ ጉዞአችሁ፡፡”
Warren W. Wiersbe, Be Delivered (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 1998), p. 145.
F. B. Meyer, Devotional Commentary on Exodus (Grand Rapids, MI: Kregel Publications, 1978), p. 270.
ጥያቄዎች
-
በዘጸ(23፡ 1-9) እግዚአብሄር የሰጣቸው ጥቂት ህጎች ምንድን ናቸው ? የምናውቀው ኢየሱስ ትናትንም፣ ዛሬም፣ ለዘላለም ተመሳሳይ ነው(ዕብ 13፡ 8) እነዚህን ህጎች ዛሬ እንዴት ተደርገው ይተረጎማሉ ?
-
የሰባተኛው አመት ህግ እንዴት አድርጎ እስራኤላዊያንን ይለያቸዋል(ዘጸ 23፡ 10-11) ? እስራኤላዊያን ህጉን በመጠበቅ ስኬታማ ነበሩ ? ቅጣቱ ምንድን ነበር ?( ዘሌ 26፡ 32-35; 2ዘሌ36፡ 21)
-
እስራኤላዊያን እንዲጠብቐቸው የታዘዙት ሰዎስቱ በዓል ምንድን ነበሩ ? የእያንዳንዳቸው አስፈላጊነት ምንድን ነው (ዘጸ 23፡ 14-16) ?
-
በዘጸ(23፡ 16) እግዚአብሄር በምድር ላይ ከዘሩት የልፋታቸው ፍሬ በኩር እንዲያመጡ ተናገራቸው ፤ ይህ ምን እንደሚመስል ምንድን ታስባላችሁ ?
-
በዘጸ(23፡ 20) ውስጥ ባለው መልዓክ የእናንተ ሀሳብ ምንድን ነው ቅደመ ክርስቶስ ነው ? በዘጸ(23፡ 22-30) በመልዓኩ በኩል በእግዚአብሄር የተሰጡት በረከቶችና ቃል ኪዳኖች ምንድን ነበሩ ?
-
በዮሐ(1፡ 18) ውስጥ የሚለው በየተኛዉም ጊዜ እግዚአብሄርን ማንም አላየውም ፤ ያ እውነት ከሆነ በዘጸ(24፡ 10-11) ስላዩት ምንድን ታስባላችሁ ?
-
በዘጸ(23-24) ውስጥ በጥናት ወይም በንብብ መንፈስ ቅዱስ ምንድን እጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 24:17
“The appearance of the LORD’s glory to the Israelites was like a consuming fire on the mountaintop.”
የቂጣ፣ ሰብል የመሰብሰብ እና የምርት በዓላት
ኦሪት ዘፀዓት 23-24 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
ሙሴ ህጉን ሁሉ ለእስራኤላዉያን ከነገራቸዉ በኋላ እግዚዓብሔር የተናገረዉን ለመታዘዝ ተስማሙ። ከዚያም ሙሴ የእግዚዓብሔር ክብር ወዳረፈበት ወደ ሲና ተራራ ከፍታ ላይ ወጣ፥ ደመናም ሸፈነዉ! የእግዚዓብሔር ክብር መገለጥ፥ ይመለከቱት በነበሩት ህዝቦች እይታ የሚያቃጥል እሳት ነበረ።
እግዚዓብሔርን እንደሚያቃጥል እሳት፣ ሚባላ እና ፈፀሞ ማጥፋት እንደሚችል አስበህ ታዉቃለህ? መደነቅ እና ክብር የሚገባዉ የእግዝዚዓብሔር ተምሳሌት ነዉ! ጠላቶቻችንን ድል በመንሳት እኩይ የሆነን ነገር ሁሉ ጠርጎ ያጠፋዋል። እንዲህ ቢሆንም ግን በልጁ በኢየሱስ በነፃ ለሚቀበሉ ሁሉ ፀጋ አለ! በኃይሉ መደነቅ ዉስጥ ሆነህ የሚባላዉ እሳት ስለአንተ እንዲዋጋልህ ፍቀድለት።
"በተራራው ራስ ላይ በእስራኤል ልጆች ፊት የእግዚአብሔር ክብር መታየት እንደሚያቃጥል እሳት ነበረ።"
ኦሪት ዘፀዓት 24:17
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘዳግም 9:3፦ "አምላክህም እግዚአብሔር እንደሚበላ እሳት ሆኖ በፊትህ እንዲያልፍ ዛሬ እወቅ፤ እርሱ ያጠፋቸዋል፥ በፊትህም ያዋርዳቸዋል፤ እግዚአብሔርም እንደ ነገረህ አንተ ታሳድዳቸዋለህ፥ ፈጥነህም ታጠፋቸዋለህ።"
- መዝሙረ ዳዊት 50:3፦ "አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፤ እሳት በፊት ይቃጠላል፥ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ አለ።"
- ወደ ዕብራዉያን 12:28-29፦ "ስለዚህ የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ጸጋ እንያዝ፤ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 40
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።