Ordinances Regarding Theft, Crops, & Personal Property
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 22 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
እግዚአብሄር እራሱን በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ እና በሴቲቱ ዘር ውስጥ ገለጠ ፡፡ ትናትና ስለ ጥዕዛዝት አውርተናል ፤ እግዚአብሄር እነዚህን ሁኔታዎች ጣልቃ በመግባት በተግባር ላይ አውላቸዋል በዚህም እስራኤላዊያን እንደ ተዋዋሉት እንዴት እንደሚያዙት(እንደ ሚፈፅሙት) ያውቃሉ ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት(22፡ 1); ቁጥር 1 የሚያወራው ስለ እንሰሳት ስርቆት ነው ፤ ለምን በጣም ጥብቅ ሆነ ? ምንድን ሆነ “ከብት ስለ ከብት” ወይም “በግ ስለ በግ” ? እንስሳቶች መተዳደሪያቸው ነበሩ-የመኖራቸው ትረጉም ፡፡ ለከብት አምስት እጥፍ ዋጋውንና ለበግ ደግሞ አራት እጥፍ ፡፡
2ሳሙ(12፡ 6) የሚለው” ይህን አድርጎአልና አላዘነምና ስለ አንዲቱ በግ አራት ይመልስ አለው ፡፡” ይህ የነበረው ዳዊት በራሱ ላይ ከቤርሳቤህ ጋር በመተኛቱ ፍርድን እያወጀ ነበር ፤ ዋይሰርቤ የፃፈው “ ነብዩ ናታን ንጉስ ዳዊትን እንደ በግ ሌባን ቤርሳቤህን ደግሞ እንደ በግ ነበር ያየቸው፣ ዝሙት ሌብነት ነው “ (1ተሰ 4፡ 1-7) በዚህ ኃጢዓት ምክንያት ዳዊት አራት እጥፍ ቅጣት አገኘው ፡፡
- 2ሳሙ(12፡ 18)-የዳዊት ልጅ ሞተ
- 2ሳሙ(13፡ 28-29)- አምኖን ተገደለ(የዳዊት ወንድ ልጅ ነበር)
- 2ሳሙ(18፡ 14)- አቢሴሎም ተገደለ(የዳዊት ወንድ ልጅ ነበር)
- 2ሳሙ(13፡ 14)- ትዕማር ተደፈረች(የዳዊት ሴት ልጅ ነበረች)
አዎ ይህ በተግባር ያወራ የነበረው ስለ በግ ነበር ነገር ግን በተጨማሪ የእግዚአብሄርን ተፈጥሮና መንፈሳዊ መርህን የገልጥ ነበር ፡፡
ዘጸዓት(22፡ 2-3); የሆነ ሰው በምሽት ሰብሮ ቢገባና እስራኤላዊዉ ቢገድለው ጥፋት አይሆንበትም ፤ ይሁን እንጂ በቀን ከሆነ ጥፋት ይሆንበታል(እዳ ይኖርበታል) ፡፡ ዋይሰርቤ የፃፈው “ ሌባን በቀን መግደል የማያስፈልግ በቀል እንዲሆን ይገልፅል “፤ ሌባው ሙሉ ካሳ የማድረግ ወይም እንደ ባሪያ ሆኖ ይሸጣል ፡፡
ዘጸዓት(22፡ 4-5); መልሶ ክፍያ እጥፍ ነበር ፡፡ ከቁጥር 1-4 የነበሩት ትዕዛዞች ስለ እንስሳት ስርቆት ነበር ፡፡ አንዱ የነበረው ከራሱ ምርጥ ማሳ ጋር መልሶ ይከፍል ነበር ፤ ከኃላቸው አጥር አልነበራቸውም ስለዚህ የድንበር ምልክት ብቻ ነበር(ዘዳ 19፡ 14) ፡፡ አጥር ባለመኖሩ ምክንያት እንስሳቶች በተፈጥሮ ድንበሩን አቃርጠው ይመጣሉ ፤ ምሳ(22፡ 28) የሚለው “ አባቶችህ የሰሩትን የቀድሞውን የድንበር ምልክት አታፍልስ ፡፡ “
ዘጸዓት(22፡ 6-8); እሳትን ያስጀመረው ስለጠፈው መልሶ ይክፈል ፤ “ሙሉ ካሳ” የሚለው ቃል ትርጉሙ በዘጻ 22 ውስጥ ስድስት ጊዜ አይተነዋል ፡፡ የዕብራዊ ቃል “ሻላን” ማለት “ ሙሉ ወይም ጠቅላላ ማድረግ” ሲሆን ፤ ”ሻሎም” ለሰሰላም ለሚለው ቃል በጣም የቀረበ ነው ፡፡ ሙሉ ካሳ ባመጣችሁ ጊዜ ሰላም ወደ ጫወታ መምጣት ይጀምራል ፤ እነዚህ ሁሉ ወደታች የመጡት ለልብ ሁኔታ ነው ፡፡
ዘጸዓት(22፡ 9); ከእንስሳት ስርቆት ወደ ዘር ስርቆት ሄደናል አሁን ደግሞ ስለ ሰው ንብርት እናወራለን ፡፡ ትክክለኛ መንገድ እኔ የማስበው ሰለሞንና የሱ ጥበብ በህፃኑ (1ነገ 3፡ 16-28) ፤ የእውነት ማን ነው ትክክል የልባቸው ሁኔታ የት ነው ?
ይህ በተጨማሪም ስለ ዮሴፍና ስለ ወንድሞቹ ዮሴፍን ለባርነት መሸጣቸውንና አባተቸውን መዋሸታቸውን እንዳስብ ያደርገኛል(ዘፍ 37፡ 25-36) ፤ ስለ ልባቸው ሁኔታ ተመልሼ መሄድ መቀጠልን እፈልጋለሁ ፤ ይህ ለእኔ መጥፎ ነው እንዴት ቅናትና ምሬት በዮሴፍ ላይና ባባታቸው ላይ ወንድሞቹ ይህን እንዲያደርጉ መራቸው ፡፡ መጥፎ ባህሪይ በምናይ ጊዜ (ያማለት ከጎረቤቶቻችሁ ስርቆት ስታዩ) የልባቸው ሁኔታ በዚህ ስር ነው ማለት ነው ፡፡
ዘጸዓት(22፡ 10-15); ካሳ የማያስፈልግ የነበረው የእውነት ስህተት ካልተፈፀመ ነበር ፡፡ የሆነ ሰው አደራ አስቀምጦ እና በጥንቃቄ ካልያዙለት እራሱኑ መልሰው ይከፍላሉ ፤ የጠፋው በኪራይ ዋጋ ሸፈን ነበር ፡፡ አስታዉሱ እስራኤላዊያን በበርሃ ሲንከራተቱ ነበር ስለዚህ ቅርፅና ህግ አስፈለጋቸው ፡፡
ዘጸዓት(22፡ 16-17); ሴት የአባታ ንብረት ነበረች ፤ ወጣት ጥንዶች ከጋብቻ የቀደመ ወሲብ ቢያደርጉ ከዚያም ሰዉየው ሴታን ቢያገባት በህግ ለአባታ ጥሎሽ ይስጥ ፤ አባታ ሴት ልጁን ለእሱ(ለወንዱ) ለመስጠት ባይፈቅድ ሰዉየው የሙሻራ ዋጋዋን ይከፍል ነበር ፡፡ የሙሽራ ዋጋው የነበረው 100 የብር ሰቅል(ዘዳ 22፡ 19)፡፡
በእኛ ትውልድ በአንዳንድ ምክንያቶች ከጋብቻ በፊት ወሲብና አብሮ መኖር ሰዎች ችግር የለውም ብለው ያስባል ፤ ይህ ኃጢዓት ነው ከዚያም ወደ መለየት ችግር ያመራል ፤ ዘፍ(2፡ 24) የሚለው ሁለት ሰዎች ወሲብ ባደረጉ ጊዜ አንድ ስጋ ሆነዋል ፡፡ እግዚአብሄር ይህን ያዘጋጀው ለአንደ ወንድና ለአንድ ሴት ነው ፡፡ ሰዶምንና ገሞራን ተመልከቱ; እግዚአብሄር ይህን አላዘጋጀም ወንድ ለወንድ ወይም ሴት ለሴት (ዘፍ 19) ፡፡ የክርስቶስ አካል እዉነት ማወጅ መጀመር ያስፈልጋታል ፡፡
ዘጸዓት(22፡ 18-24); ማርት(መተት) የእግዚአብሄርን ፈቃድ የመከልከል ሙከራና መሞት የሚያስቀጣ ነበር ፡፡ ከእንስሳት ጋር የሚገናኝ በሞት ይቀጣ ነበር ፤ በእነዚህ ሁሉ ታላቅ ፈተና የነበረው ጣኦት አምልኮ ነበር ለእስራኤል ፡፡
እግዚአብሄር ሲናገር “ የተጎዱትን ስደተኞችን፣ መበለቶችንና ቲሞችን ልከላከልላቸው እፈልጋለሁ” ፤ እግዚአብሄር ጩኸታቸውን ይሰማል እናም ቁጣው ያቃጥላችኃል ፤ ለመበለቲቱና ለየቲሞች ካልተጠነቀቃችሁ ትገደላላችሁ ከዚያም ሚስቶቻችሁና ልጆቻችሁ መበለትና የቲሞች ይሆናሉ ፡፡
ዘጸዓት(22፡ 25-27); ምሳ(28፡ 8) “ በአራጣ ብዛትና በቅሚያ ሀብቱን የሚያበዛ ለድሀ ለሚራራ ያከማችለታል ፡፡“ እስራኤላዊያን በራሳቸው ሳይሆን በእግዚአብሄር ላይ ቢያተኩር በተፈጥሮ ሌሎችን ይሃርካሉ ፡፡ ፈፅን ስለራሰችን እናስብ ግን ሌሎችንም እንደምናስበው ! ይህ ትክክለኛው የኢየሱስ መልዕክት ነው; እግዚአብሄርን መውደድና ሌሎችን መውደድ ፡፡
ዘጸዓት(22፡ 28-30); በሐዋ (23፡ 4-5) ውስጥ ጳውሎስ ሰለተናገረውን ሊቀ ካህን ይቅርታ አለ(ዘጸ 22 በመጥቀስ) ፤ የእግዚአብሄር ትዕዛዝ ; ለጋሽ ሁኑ፣ የታዘዛችሁትን አታዘግዩ፣ እስኪጠነክር ለእንስሳው ሰባት ቀን ፍቀዱለት እናም እኔ የጠየቃችሁን ወደ ኃላ አታስቀሩ ፡፡
ዘጸዓት(22፡ 31); በመጨረሻም እግዚአብሄር ሲናገር “ ቅዱስ ህዝብ ትሆኑኛላችሁ ”፤ አስታዉሱ ከአምስቱ የህግ መፅሀፍት ዉስጥ ዋና ነገሮችን(ዘጸ 19፡ 5-6) ፡፡
እናንተ የእኔ የተለየ ሀብት ናችሁ ፡፡
እናንተ የመንግስቴ ካህናት ናችሁ ፡፡
እናንተ ቅዱስ ህዝብ ናችሁ ፡፡
እግዚአብሄር አውሬ የቦጨቀዉ እንስሳት እንዳትበሉ ብሎ አዘዛቸው- እናንተ ቅዱስ ህዝብ ናችሁ ፡፡ ፃድቅ ምግብ አይለምንም (መዝ 37) ፤ እግዚአብሄር ለእነሱ ምግብ ይሰጣቸው ነበር ፡፡
መዝጊያ
አነዚህ ትዕዛዞች ያለማቐረጥ የሚያመለክቱት እስራኤላዊያንን ወደ እግዚአብሄር ለመመለስ ነበር ፤ እግዚአብሄር ይናገር የነበረው “ በንፁሁ በግ በኩል እንዴት ነጻ እንዳወጣኃችሁ ታስታውሳላችሁ ?በሂሶጵ እና በቐሚዎቹ ላይ በነበረው ደም በኩል ? ሁላችሁንም ከመቅሰፍቱ ነፃ ባደረገቻችሁ በትር በኩል ? ቀን በደመና አምድና ማታ በእሳት አምድ ውስጥ ?እንድታደርጉ የምፈልገው ልክ እኔ ነፃ እንደዳቸጣኃችሁ ነው ! እንድታደርጉ የምፈልገው ልክ ከበርሀቸው ውስጥ እንዳገኘኃችሁ ነው ፤ ለእናንተ እጠነቀቃለሁ ፡፡” እግዚአብሄር በሁሉም ነገር ውስጥ ነው ፤ እነዚህ ሁሉም ነገሮች ወደ መሲሁ ያመለክቱናል ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2007), p. 186.
Wiersbe, p. 186.
ጥያቄዎች
-
በዘጸ(22፡ 7-8) ሰው ለጎረቤቱ ገንዘብና እቃ(ሸቀጥ) ባላደራ ከሚሆንበት አንፃር ትዕዛዝ ተሰጥተዋል ፤ በአንተ ጋር ለተቀመጠው እንዴት ጥንቃቄ ታወስዳለህ ?
-
ጥቂት የሆኑ በሌባ ላይ የሚያወሩ ትዕዛዞችን በዘጸ 22 አውርተናል እናም አንዱ የአስሩ ትዕዝዝ “ በፍፁም አትስረቅ” ነው ፤ በሉቃ(6፡ 29) መልክ የሆነ ሰው ከእኛ የሆነ ነገር ቢሰርቀን እንዴት ነው ምላሽ መስጠት ያለብን ? ለእናንተ ይህን ማድርግ አስቸጋሪ ይሆናል ?
-
በዘጸ(22፡ 21-24) ውስጥእግዚአብሄር የእንግዶችን፣ የቲሞችንና መበለቶችን የተከላከለበት ደረጃ አላስደነቃችሁም ? ለምን ጠባቂያቸው እንደሆነ እንዳሰባችሁ አብራሩ (ዘዳ 10፡ 18; 24፡ 19; መዝ 68፡ 5; ኢሳ 1፡ 17; ያዕ 1፡ 27) ፤ ይህ እንዴት ያስቸግራችኃል(ቻለንጅ) ያደርጋችኃል ?
-
በዘጸ(22፡ 28) ውስጥ እስራኤላዊያን ፈራጅን ወይም ይህዝቡንአለቃን እንዳይሰድቡ አስጠነቀቃቸው ፤ አለቃው ሙሰኛ ቢሆንም እንካን ይህ ይሰራል ብላችሁ ታስባላችሁ ?(1ነገ21፡ 10; ሐዋ23፡ 5; ሮሜ13፡ 1-5)
-
በዘጸ(22፡ 31) እግዚአብሄር ለብቻቸው እንዲለዩ/የተለዩ እንዲሆኑ; በዱር በአውሬ የተቦጨቀውን ስጋ እንዳይበሉ ጠራቸው ፤” ለእኔ ቅዱስ ትሆንሉኛላችሁ” ይህንን ቃል ባነበባችሁት ጊዜ ወደ ኃሳባችሁ ምንድን መጣ ?(ዘሌ 11፡ 44-45; መዝ 96፡ 9; ዕብ 12፡ 14; 1ጴጥ1፡ 16)
-
በዘጸ 22 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 22:26-27
“If you ever take your neighbor’s cloak as collateral, return it to him before sunset. For it is his only covering; it is the clothing for his body. What will he sleep in? And if he cries out to Me, I will listen because I am compassionate.”
ኦሪት ዘፀዓት 22 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እግዚዓብሔር ለእስራኤል ህዝብ የሚሆን ሥርዓትና ድንጋጌዎችን ለሙሴ መስጠቱን ቀጥሏል። የህዝቡን ልቦና ጠንቅቆ ያዉቀዋል! ለእነሱ በማሰብ፥ እነዚህን ሥርዓቶች ተላልፈዉ ቢገኙ የሚያስከትለዉን መዘዝ ገልጦላቸዋል። ከዚያም፥ ሥራዓቱን እና ድንጋጌዎችን በሚያስረዳበት መሃከል፥ እግዚዓብሔር የልቡን ሃሳብ እና ባህሪዉን ይገልጥ ነበር።
ከየትኛዉም ምድራዊ አባት በላይ፥ እግዚዓብሔር ሰማያዊ አባትህ ነዉ! ደግሞም ይወድሃል! ወደ እርሱ ብትጮህ፥ ይሰማሃል። እርሱ ርህሩህ ነዉ! ስለአንተ ይጠነቀቃል፥ የሚያስፈልግህም ነገር ይረዳል። ወደ እርሱ እንድትጮህ እግዚዓብሔር ይናፍቃል! ደግሞም ሊያስመልጥህ ባለህበት እናዳለ ቃል ገብቷል!
"የባልንጀራህን ልብስ ለመያዣ ብትወስድ ፀሐይ ሳትገባ መልስለት፤ ሥጋውን የሚከድንበት እርሱ ብቻ ነውና፤ የሚተኛበትም ሌላ የለውምና፤ ወደ እኔም ቢጮኽ መሐሪ ነኝና እሰማዋለሁ።"
ኦሪት ዘፀዓት 22:26-27
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 91:15፦ "ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፤ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።"
- መዝሙረ ዳዊት 103:8፦ "እግዚአብሔር መሓሪና ይቅር ባይ ነው፥ ከቍጣ የራቀ ምሕረቱም የበዛ።"
- 2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 1:3፦ "የርኅራኄ አባት የመጽናናትም ሁሉ አምላክ የሆነ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክና አባት ይባረክ።"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 39
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።