Ordinances Regarding Slaves & Personal Injury
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 21 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
ለዘጸዓት በሙሉ የኛ ጭብጥ “ነፃ አውጪ” የሚል ነው ፡፡ ከግብፅ ህዝቡን ያወጣው አንዱ ኢየሱስ ነበር ፤ አዎ ሙሴን ተጠቅማል ፤ ነገር ግን ትልቅ ስዕሉ ከምርኮ ነፃ ያወጣቸው ኢየሱስ እንደነበር ነው (ሉቃ 4) ፡፡ ሙሴያዊ ኪዳን እግዚአብሄር ከእስራኤላዊያን ጋር ያደረገው የሚለወጥ ኪዳን ነበር ፡፡ ዘጸዓት 20 አስሩን ትዕዛዝ ይዘረዝራል ፤ እግዚአብሄር እነዚህን ቁልፍ መመሪያዎች ለእስራኤላዊያን ሰጣቸው ፤ ከዚያም ለመሄድ በመቀጠል ጠቅላላ 613 ትዕዛዞችን ሰጠ ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት(21 ፡1); አስሩ ትዕዛዝ ጥሩ ነበሩ ነገር ግን እነዚህ እንዳሉ እግዚአብሄር ሌላ ብዙ ትዕዛዝ ነበሩት ፡፡ አሁን የምናጠናው የተመረጡ ጉዳዮች ከአስሩ ትዕዛዞች በተሻለ በዝርዝር የተሰጡንን ነው ፡፡ እንዴት ስለ ትዕዛዝ ማጥናት ስለ ነፃ አዉጪው ኢየሱስ ለኛ ይገልጥልናል ?
- እግዚአብሄር የልባቸውን ጉዳይ ለማስተዳደር ይሞክር ነበር ፤ የልባቸውን ሁኔታ እንዲቀየር ለማድረግ አስተሳሰባቸውንና ሀሳባቸውን ለመቀየር ሞከረ ፡፡
- ማስታዎስ ያለብ; በበርሃ እየተንከራተቱ እንዳሉ እና እግዚአብሄርም ለእነርሱ ባህልን ለመፍጠር ፈለገ ፡፡
ዘጸዓት(21፡ 2); ከቁጥር(2-6) ስለ ባሪያ ነው የሚያወራው ፤ ባሪያ ያላቸው ዕብራዊያን ለምን ይህን አሰቡ ? ከብርነት ስለወጡ ፡፡ በእዉነቱ ከባሪያ አስተሳሰብ በይበልጥ ስለአገልጋይነት አስተሳሰብ ነው ፤ ከስድስት አመት በኃላ ይለቃቸው ነበር ፡፡ በተመሳሳይ የእብራዊያን ባሮች ባሪያ ይሆኑ ነበር ምክንያቱም የሆነ ሰው እዳ ሲኖርባቸው ፤ ለምሳሌ ያዕቆብ ልያንና ራሔልን ለማጋባት ለላባ ሰርታአል ፤ ጳዉሎስ ፊልሞንን ለእሱ የሚሰራውን አናሲሞስን እንደ ጋደኛና እንደ ወንድም እንዲከባከበው (እንዲያየው) አስገነዘበው (ፊል 15) ፡፡ ኮንስታብል እንደ ፃፈው “ ሌሎች የባሪያን ተፈጥሮዓዊ መብት ባላከበሩ ጊዜ ባርነት እንደ ማህበራዊ ተቃአም መጥፎ ይሆናል ፡፡” እግዚአብሄር ለተፈጥሮ መብት ዋጋ በመስጠት መከላከያ(የሚጠብቅ) ያዘጋጅ ነበር ፡፡
ዘጸዓት(21፡ 3-6); ባሪያ ከቤተሰቡ ጋር መቆየት የሚፈልግ ከሆነ ቅደም ተከተል ነበረው ፤ ባሪያ በወስፌ የተበሳ ጆሮ ከነበረው የሚያመለክተው በህይወቱ ለአዛዡ አባል እንደሆነ ነበር ፡፡ ወስፌ ረጅም ሹል መሳሪያ ለቆዳ ስራ ይጠቀሙታል ፡፡ ኔልሰን የፃፈው “ ባሪያ ከዳኛዎች ፊት የሚወሰዱ ይሆናል ይህም ሀሳባቸውን እንዲናገሩ የሰጣቸው እድል ይሆናል “ ፤ ከሚስት ጋር እና ከልጆች ጋር ለመቀመጥ ባሪያ አስቦበት ህይወቱን ሁሉ አስተዳዳሪውን ለማገልገል ይሰጥ ይሆናል ፡፡
ማክአርቱር የሚያስቀምጠው ሀሳብ እዚህ ጋር ባሪያው አገልጋይ ሆኖ የሚቀር ይሆናል ፤ በግብፅ ካለው የባርነት ባህል ከወጣን በኃላ (እስራኤላዊያን ያስተዳድራቸው በማስጨነቅ ባሪያ አድርገው አስቀምጠዋቸው ነበር) እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን የባሪያና አገልጋይ መኖር ጥቅም እንዳለው አስተማራቸው ፤ አገልጋይና ባሪያ መያዝ የነበረባቸው በዚህ መንገድ እንጂ እንደ ግብፅ አይደለም ፡፡
ዘጸዓት(21፡ 7-10); በሴቶች በኩል ያለውን ባርነት አሁን እንመለከታለን ፤ አባት ሴት ልጁን ከሸጣት ስልጣን አይኖራትም ፤ ይህ ከጋብቻ አንፃር ነበር ፡፡ የሕግ አባታ(ጌታዋ/አስተዳዳሪዋ) ለሌላ አገር ሰው እሳን መሸጥ አይችልም ፤ ሴታ የተሸጠች ከሆነ የህግ አባታ እንደ ባህላቸው እንደ ልጁ ሊያያት ግድ ነው ፤ ለወንድ ልጁ ካገባት በኃላ ልጁ ሁለተኛ ሚስት ለማግኝት መወሰን ይቸላል ፤ የመጀመሪያውን ሚስቱን ከሁለተኛው ሚስቱ በተለየ ማየት አይችልም፤ ልብሳን፣ ምግባንና የጋብቻ መብታን ይሰጣታል ፡፡
ዘጸዓት(21፡ 11); ለሴቲቱ ያልሰጣት ከሆነ ትውጣ (ትታው ትሂድ) ፤ ከስድስት አመት በኃላ ወንዱ ባሪያ ይወጣል ነገር ግን ይህ ብቸኛው ጊዜ ነበር ሴት ባሪያ መውጣት የምትችልበት ፡፡በዘፍጥረት ውስጥ ልያ ለያዕቆብ ሚስት እንድትሆነው ዘለፉን ሰጠችው (ዘፍ 30፡ 9) ፤ ስለዚህ ያዕቆብ በዚህ ህግ መሰረት ልያን ባየበት መንገድ በተመሳሳይ ዘለፉን ሊያያት ግድ ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ባህሪያቸውን የሚመራ ትዕዛዝ በቦታው አስቀምጦላቸው ነበር ፡፡
ዘጸዓት(21፡ 12-14); አሁን የይሙት በቃ ፍርድ አስፈላጊነት ምን እንደነበር እንመለከታለን ፤ ዘፍ(9፡ 6) የሚለው “የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ ደሙ ይፈስሳል ሰውን በእግዚአብሄር መልክ ፈጥሮታልና ፡፡” ኮንስታብል የፃፈው “ እግዚአብሄር ከቦታ መቀደስ ይልቅ ለሰው ህይወት መቀደስ ትኩረት ይሰጣል” ፤ በቀደሙት ምስራቅ ውስጥ የሆነን ሰው የገደሉ ይጠፉና ይደበቅ ነበር ፡፡ የእግዚአብሄር ህግ የሚጠይቀው አስቦበት የሆነን ሰው የገደለ ይገደል የሚል ነበር ፤ ሳያስበው ነፍስ የገደለ ውጤቱ ወደ ስደተኛ ከተማ መሰደድ ነበር ፤ ለስደተኛ ከተሞች ዘኁ 35 እና ዘዳ 19 እዩ፡፡ነፍስ ግድያን ቀድሞ ማሰብ በገዳዩ ላይ ዉጤቱ ለሞትማስቀመጥ ነበር ፡፡ ዮሐንስ ዳቪስ የፃፈው “ ህይወት ከመሰረቱ የእግዚአብሄር ንብረት ነው; የዚህ ባለቤት ለብዙ አመታት ለሰው ልጅ አከራይታት ነው….(ገዳዩ) አንዱን አስፈላጊ የእግዚአብሄርን ህግ ጣሰ በዚህም ለህይወት ባለቤቱ ተገቢውን መካስ አለበት ፡፡”
ዘጸዓት(21፡ 15-19); እንቱንና አባቱን የሚመታ በሞት ይቀጣ ፤ ለምን ነበር ይህ በጣም ጥብቅ የነበረው ? ይህ ከአስሩ ትዕዛዝ አንዱን የመጣስ ድርጊት ነበር ! እግዚአብሄር የማክበርን ባህል መስርቶ ነበር ፡፡ በባቢሎናዊያን ጊዜ አካባቢ የነበረ የሀሞራቢ ደንብ የጠቀሰው አባቱን የሚመታ ሰው እጁ እንደሚቆረጥ ነበር ፡፡ ዘራፊዎች(አጋቾች)ም በሞት ይቀጡ ነበር ፤ ከአስሩ ትዕዛዝ ውስጥ እገታ ተገቢ የሚሆነው ለየትኛው ነው ? አግታ ሌብነት(ስርቆት) ነው፡፡ አሁን ወደ ሰውነት ቅጣት እንገባለን ፤ አሰርታችሁ ከነበር ላሰራችሁት ሰው የምትከፍሉት ካሳ ነበራችሁ ፡፡ ማንም ሰው እነዚህ ህጎች በመጠብቅ መቀጠል አልቻለም ! ስለዚህ ጥፋተኞች ከነበራችሁ ትሞቱ ነበር ፤ እግዚአብሄር ይመስገን ስለመሲሁ ስለኛ ነፃ አውጪ !
ዘጸዓት (21፡ 20-21); ባለቤቱ ባሪያውን ቢገድለው ቅጣቱ ባሪያውን ማጣቱ ብቻ ነው ፤ ቁጥር 21 “ገንዘቡ ነውና አይቀጣ” ፤ ይህ አስቸጋሪ ነው ፤ እኔ ያሰብኩት ባሪያ እንደ ንብረት እንዲቆጠር ሳይሆን እንደ አገልጋይ እንዲቆጠር ተወያይተን ነበር ? ሙሴ ይህን ፃፈ ፤እሱ የሆነን ሰው አልገደለም ?
ዘጸዓት(21፡ 22-23); እዚህ ጋር ህይወት ስለህይወት አስተሳሰብ ያለበት ነው ፤ ሰዎች ይህንን ጥቅስ እንደ ቀድሞ ማጨናገፍ ይጠቀሙበታል ምክንያቱም ልጁ ቢሞትም ደህንነታ ብቻ ይፈለግ ስለነበረ ነገር ግን ሴቲቱ ከተጎዳች ስለ አይን አይን፣ ስለ ህይወት ህይወት ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ገና ከመጀመሪያው ህይወት በሁለቱም ከማሕፀን ዉስጥም ውጪም እንደሚኖር ያውቅ ነበር ፤ ፅንስ ሰው ነው ፡፡
መዝ(51፡ 5) “ እነሆ በአመፅ ተፀነስሁ እናቴም በኃጢዓት ወለደችኝ”
መዝ(58፡ 3) “ኀጥዓን ከማህፀን ጀምረው ተለዩ “
መዝ(139፡ 13-15) “ በእናቴም ሆድ ሰውረኸኛልን “
ዘጸዓት(21፡ 24-28); አይን ስለ አይን፣ ጥርስ ስለ ጥርስ እንዴት ሰራ ? ብዙ ሀተታ ሰጪዋች የሚሉት ይህ ምሳሌያዊ እንደነበር ማለትም የሚገባውን ለተመለከታችሁት ትከፍላላችሁ ማለት ነው ፡፡ ብዙና በብዙ ይህን ባህል የምታጠኑት ከሆነ ስለአጣችሁት የምትከፍሉትን ብዙ ታያላችሁ ፤ ከዚህ ለቀረው ደግሞ የሚያወራው ባለቤቱ ስለሰራነው ስህተት ነው ፡፡
ዘጸዓት(21፡ 33-36); በጠቅላላ የሚያወራው ስለተደረገው ስህተት ስለክፍያው እና ስለሚሰጠው ካሳ ነው ፤ ሁሉም ነገር እኩል ተደርጎ ተሰርቶ ነበር ፤ ሙሉ በሙሉ ልትክሱ ያገባችኃል ፤ የፍትህ ስምምነት ነበር ፡፡
መዝጊያ
በጣም ብዙ ትዕዛዞች ነበሩ ሰዎች በራሳቸው ሊጠብቃቸው ያልቻሉ-613 ትዕዛዞች ፡፡ግፊቱ የአይሁድ ሰዎች ዛሬም መሰረታዊ ክብደትን ዛሬም መሸከም አለባቸው ፤ ከባድ ክብደት ነው ምናልባት ማድረጋቸውን እንካን አያዉቁትም ፤ ምንም እንካን 613 መጥቀስ ብትችሉም መጠበቅ አትችሉም ፡፡
ነገሩ ግን ከዚሂ ክብደት ነፃ ወጥተናል ነው! ሁሉም እነዚህ የሚያመለክቱን ስለሚመጣው መሲህ እና ስለሱ የእኛን ፍላጎት ነው ! ምክንያቱም እሱ ስለመጣ እነዚህ ነገሮች በፍቃድ ለመሄድ ጊዜ አለ ስለዚህ በሙሉ ነፃነታ መሄድ እንችላለን !
Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Exodus’ available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/exodus.pdf, p. 204..
Earl D. Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville, TN: Thomas Nelson, Inc, 1999), p. 124.
John F. MacArthur, The MacArthur Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson Publishers, 2005), p. 116.
Constable, p. 206.
John Davis, Moses and the Gods of Egypt (Grand Rapids, MI: Baker Book House, 1971), p. 221.
ጥያቄዎች
-
ዘጸ(21፡ 17) በዘሌ(20፡ 9) ላይ ተደግሞአል በተጨማሪም በማቴ(15፡ 4) እና ማር(7፡ 10) ላይ ኢየሱስ ጠቅሶታል ፤ አባቱን ወይም እናቱን የሚሳደብ ማለት ምን ማለት ነው ?
-
ምን ታስባላችሁ “ አይን በአይን፣ ጥርስ በጥርስ፣ እጅ በእጅ፣ እግር በእግር” ማለት በዘጸ(21፡ 24) ? በማቴ(5፡ 38-42) በኢየሱስ ትምህርት ይህን ህግ ለመቀየር እንዴት አደረገ ?
-
በምን መንገድ ነው ገላ(6፡ 7) ከዘጸ(21፡ 23-25) የሚለየው ወይም የሚመሳሰለው ?(ሮሜ 12፡ 17-20)
-
በዘጸ(20፡ 1) ከሲና የእግዚአብሄር ቃል ያወጀው “እግዚአብሄር አምላክህ እኔ ነኝ” ከባርነት ያወጣኃችሁ ፤ አስሩን ትዕዛዝ ከተሰጡ ቦኃላ መብታቸው የተሰጣቸው(የተቀመጠላቸው) የመጀመሪያ ህዝቦች ማን(እነማን) ነበሩ ? ይህ አስፈላጊ ነው (ዘጸ 21፡ 2-11)
-
በህግ የሙሴ አባት ዮቶር ሁኔታዎችንና ህጎችን ለህዝቡ እንዲያስተምር ይመክረዋል እነዚህን በዘጸ(21-23) ተፅፈው እናያቸዋለን ፤ ማነው በእናንተ ህይወት ውስጥ ከየት እንዲመክራችሁ የምትፈልጉት ? እነሱ ወደ እግዚአብሄር ቃል ያመለክታችኃል ?
-
በዘጸ 21 ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 21:1
“These are the ordinances that you must set before them.”
ኦሪት ዘፀዓት 21 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እግዚዓብሔር ለሙሴ አስርቱን ትዕዛዛት በሲና ተራራ ከሰጠ በኋላ፥ ዘረዘር ያሉ፥ ለተለየ ነገር የሚሆኑ ድንጋጌዎችን ለህዝቡ እንዲናገር አዟል። እነዚህ ድንጋጌዎች፤ ፍርድ የሚበይኑ እና ማህበረሰባዊ አለመግባባቶችን የሚፈቱባቸዉ መዋቅር ነዉ። እስራኤላዉያን ገና ከባርነት ቀንበር የወጡ፥ ብዙ የማያዉቁ ናቸዉ። እግዚዓብሔርም አድስ በተገኘላቸዉ ነፃነት ዉስጥ ይህ መዋቅር እንደሚያስፈልጋቸዉ ያዉቃል።
በህይወትህ፥ ትክክለኛ እና የተሳሳተ ነገርን በተመለከተ ለመረዳት የምትሄደዉ ወዴት ነዉ? የምትሄደዉ ወደ ዓለም ጥበብ ወይስ እዉነቱን ለመገንዘብ ወደሚያስችለዉ ወደ እግዚዓብሔር ቃል ነዉ? የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው። ለመልሶች የእግዚዓብሔርን ቃል ፈልገዉ፥ መንገዱንም ያሳያሃል።
"በፊታቸው የምታደርገው ሥርዓት ይህ ነው።"
ኦሪት ዘፀዓት 21:1
ተጨማሪ ጥቅሶች
- መዝሙረ ዳዊት 103:7፦ "ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ፥ ለእስራኤል ልጆችም አደራረጉን።"
- መዝሙረ ዳዊት 119:105፦ "ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።"
- ወደ ዕብራዉያን 4:12፦ "የእግዚአብሔር ቃል ሕያው ነውና፥ የሚሠራም፥ ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፥ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፥ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፈት፡ ክፍል 38
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።