The Pentateuch Exodus

Israel at Mt. Sinai – God’s Treasure, Kingdom of Priests & Holy Nation

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 19-20 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 37 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ብዙዎች ዘጸዓት 19 የአምስቱ የህግ መፅሀፍት ዋና እንደሆነ ይናገራሉ ፡፡ ያለፍነው በአብርሃማዊ ኪዳን ውስጥና እንዴት በአብርሃም፣ በይስሐቅና በያዕቆብ ውስጥ ለህዝቡ እግዚአብሄር የነበረውን የተለየ እቅድ አይተናል (ዘፍ12፡1-3) ፡፡ አብርሃማዊ ኪዳን መሲሁ ተመልሶ እስኪመጣ አያቆምም ፤ ነገር ግን አብርሃማዊ ኪዳን እየቀጠለ እግዚአብሄር ሌላ ኪዳን ሙሴያዊ ኪዳን ለማድረግ ወሰነ ፤ ይህ ሙሴን ለህዝቡና ለዘሩ እንደ ነፃ አውጪ በመጠቀም ነው ፡፡ እስራኤላዊያን በመቅሰፍቶች ውስጥ እና ቀይ ባህርን በመክፈል ተሻገሩ ፤ በየቀኑ መናና ጅግራ ነበራቸው ከዚያም አሁን እግዚአብሄር “ አሁን እኔ ከአንተ ጋር መሆኔን ላሳይህ እፈልጋለሁ” ብሎ ተናገረው ፡፡ እዚህጋ ሙሴ በጣም ግልፅ በሆነ መልኩ የእግዚአብሄርን ድምፅ መስማት ጀመረ ፡፡

ትምህርት

ዘጸዓት(19፡ 1-3); ሙሴ እግዚአብሄርን ቃል ኪዳን በገባበት ተራራ በተመለከተ ጊዜ እስራኤላዊያን በሲና ምድረበዳ ነበሩ ! በዚህ ተራራ ስር የሰፈሩት 2 ሚሊዮን ሰዎች ምን ሊመስል እንደሚችል ማሰብ ትችላላችሁ ? የደቡብ ምስራቅ የሲና ስርጥ(በባህር የተከበበ) ክፍል ጀበል ሙሳ “የሙሴ ተራራ” ተብሎ ይጠራል ፤ ጆሴፍ በባህር ስርጥ(በባህር ከተከበበው) ቦታ የሚበልጥ ቦታ እንደ ነበር መዝግባል ፡፡ ቁጥር 3-6 የአምስቱ የመጀመሪያዎች የህግ መፅሀፍ ዋና ናቸው ፡፡ እግዚአብሄር ሙሴ ለእስራኤላዊያን የሚሰጣቸውን መልዕክት ሰጠው ፤ ይህ መናገር አልችልም ያለው ያው ሰው ነበር አሁን ከሁሉም ጋር እንዲነጋገር እግዚአብሄር ነገረው ፡፡

ዘጸዓት(19፡ 4-5); ሙሴ የራሱን ንግግር ፅሀፊ ነበረው-እግዚአብሄር ! ለምን የንስርን መልክ ተጠቀመ ?ዋይሰርቤ የፃፈው “ ወጣቱ ወፍ(ንስር) መጥናቱ እስኪቀርብ ይቆያል(ይቀመጣል) ከዚያም ከወደቁ ወጣቱ ንስር እንዴት ክንፎቹን መጠቀም እንዳለባቸው እስኪማሩ ድረስ በጠንካራ ክንፎቹ ይሸከማቸዋል ፣ በአየሩ ሁኔታ በራሉም እግዚአብሄር በሰጣቸው ችሎታም ይዝናናሉ(ደስ ይላቸዋል) “ ፤ በተጨማሪም ዋይሰርቤ ያለው “ ንስሮች ሰዎስት አይነት ነፃነት ያብራሩልናል; 1) ነፃነትከየት(ከጎጃቸው ዉጪ ሲሆኑ ይህ ለእኛ ቤዛነታችን ነው)፤ 2) ነፃነት በውስጥ(በአየር ላይ ቤት አላቸው ይህ ለእኛ ብስለታችን ነው) ፤ 3) ነፃነት ለምን( ለህይወታቸው አላማቸውን ማሳካት ይችላሉ ለእኛ አገልግሎታችን ነው) ፡፡” እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን በሰዎስት መንገድ አያቸው ፤ የመጀመሪያው የእግዚአብሄር የተለየ ሀብት(ርስት) ነበራቸው (ዘዳ 7፡6; 14፡2; መዝ 135፡ 4) ፤ ይህ እንዲገባቸው ምንም ያደረጉት አልነበረም; እግዚአብሄር መረጣቸው ፡፡ ይህ ሙሲያዊ ኪዳን ነበር እስራኤልን እግዚአብሄር የሚያስተዳድረው ሀብቱ አደረገው ፤ እግዚአብሄር እነርሱን እንደ ሚያስተዳድር ሀብቱ ማየት አላቆመም ፤ የእግዚአብሄር እጅ እዚህጋ በግልፅ በእነርሱ ላይ ነበር ፡፡

አብርሃማዊ ኪዳን ያማይለወጥ(ያለገደብ) ነው በእምነት ነው ፤ እግዚአብሄር በረከቱን ያፈስባቸዋል ዘሩንም ማብቂያ የለለው አደረገው ፡፡ ሙሴያዊ ኪዳን የሚለወጥ ነው ለተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ኪዳን ፤ በሙሴ ጀመረው ከዚያ በክርስቶስ አለቀ ፡፡ኢየሱስ በመጣ ጊዜ በአድስ ኪዳን ተለወጠ ፤ ሙሴያዊ ኪዳን ተመስርቶ የነበረው ለቅዱስ ስርአት(አምላኮ)፣ ለመኖር ህግ እና ሰዎችን ለመዋጀት(ገላ 3፡ 19) ፤ የሙሴ ህግ የተመሰረተው መሲሁ እስኪመጣ ነበር ፤ ለኃጢዓታችን እንደ መምሪያ የሚያገለግል ያስፈልገን ነበር ፡፡ ሙሴያዊው ኪዳን መንገድ ነበር ፤ አሁን እስራኤላዊያን ሀላፊነት ነበራቸው የእግዚአብሄርን በረከት ለመቀበል ይንን መፈፀም ይኖርባቸዋል ፡፡ የዚህ የሚቀየር ኪዳን ልዩነት እስካሁንም የእግዚአብሄር ሰዎች ሲሆኑ; ለእነሱ ያስቀመጠላቸውን ስተዋል ፡፡

ዘጸዓት(19፡ 6); ሁለተኛው የእግዚአብሄር መንግስት ካህናት ነበሩ ፤ የእግዚአብሄር አገዛዝ በሰው በምድር ላይ”የንጉስ ግዛት(መንግስት)” ይህን ለመጀመሪያ ጊዜ ሲጠቅስ ታዩታላችሁ ፡፡ እንደ ካህናት በእግዚአብሄር ባላቸው እምነት ይህ ሆነ ፤ የካህን ሚና በሰዎችና በእግዚአብሄር መሀከል መቆም ነው ፡፡ የሚሆኑት በእግዚአብሄርና በሌላ ህዝብ መሀከል መሀከለኛ ህዝብ ነበሩ ፤ የነበሩት የተለየ ህዝብ- የሚያገለግሉ እንጂ የሚመሩ አልነበሩም ፡፡

(ኢሳ 61፡6) “ እናንተ ግን የእግዚአብሄር ካህናት ትባላላችሁ ሰዎቹም የአምላካችን አገልጋዮች ብለው የጠሩአችኃል የአሕዛብን ሀብት ትበላላችሁ በክብራቸውም ትመካላችሁ ፡፡” አስተሳሰባቸውን “ ንጉሶች የምንሆን አይደለንም ግን ካህናት ነን” ወደ ሚል ይቀይራሉ ፡፡” አሮንና ልጆቹ ካህናት ሆኑ (ዘጸ 28-29) ፤ አሮን ሁልጊዜ በቁራጭ ድንጋይ ላይ 12ቱን ነገዶች በደረቱ ላይ እግዚአብሄር ፊት ይዞ ይሄዳል ፡፡

ሰዎስተኛው የእግዚአብሄር ቅዱስ ህዝብ ነበሩ ፤“ቅዱስ” የሚለው ቃል ተለይቶ የተቀመጠ ወይም የተለየ ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ነበሩ ምክንያቱም ለእግዚአብሄር ራሳቸውን የሰጡና ከኃጢዓት የራቁ ስለሆኑ ፤ በዘሌ ስድስት ጊዜ የሚለው “እኔ ቅዱስ ነኝና ለእኔ ተቀደሱ!” እግዚአብሄር በዘጸ(22፡ 31) “ ቅዱስ ወገን ትሆኑልኛላችሁ” በማለት ደግሞ ተናገረ ፡፡ እስራኤላዪያን የእግዚአብሄርን ቅዱስነት ያንፀባርቅ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎስት ሀረጎች የአምስቱ ህግ መፅሀፍት ዋና መሆናቸውን ማስታወስ ጠቃሚ ነው; የእግዚአብሄር የተለየ ሀብት፣ የእሱ መንግስት ካህናትና የእሱ ቅዱስ ህዝብ ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤልን እንደ ቅዱስ ህዝብ፣ እንደ ንጉስ ካህናትና እንደ ተለየ ሀብት(ርስት) አድርጎ ማየቱን አላቆመም ፤ ኮንስታብል የፃፈው “ እስራኤል ለመላዎ አለም እንዴት በእግዚአብሄር መንግስት ሰር እንደሚኖር ምስክር መሆን ትችላለች ፡፡” ነገር ግን ችግር ነበር በትምህርት ጊዜአቸው ከፊል በረከት ተለማምደዋል(አግኝተዋል) ምክንያቱም ከፊል ጊዜን መታዘዝ ብቻ ስላሳዩ ፡፡

ዘጸዓት(19፡ 7-12); ሙሴ ይህንን ንግግር በሰዎስት በማዉሪያ ነጥቦች አቀረበ; የተለየ ርስት(ሀብት)፣ የንጉስ ካህናትና ቅዱስ ህዝብ ፤” ኪዳኑን ለመጠበቅ ችሎታቸው ከብቁ በላይ እንደሆኑ ቢገምቱም ለእነሱ የእግዚአብሄር መለኪያ ከበቂ በታች እንደሆነ ገመቱ” ፤ እስራኤላዊያን በእነዚህ ነገሮች በመስማማታቸው ምክንያት ሂደቱን መጀመር አስፈለጋቸው ፡፡ በቁጥር 10 እግዚአብሄር ለሙሴ አለው “ ህዝቡን ዛሬና ነገ ቀድሳቸው” በእስራኤላዊያን መታጠብና ልብሳቸውን መቀየር አድስ ጅማሬን ያመለክታል ፡፡ በሰዎስተኛው ቀን እግዚአብሄር ወደ ታች ይመጣል ዋይሰርቤ ሙሴ ህዝቡን ከተራራው እንዲርቁ የሚጠብቅ አጥር አስቀምጣል እናም አጥሩን የሚያልፉትን የመግደል ስልጣንን ሰጥቶ ጠባቂዎችንም እንዳቆመ ይጠቅስልናል ፡፡

ዘጸዓት(19፡ 13-15); እግዚአብሄር እስራኤላዊያን ተራራውን እንዳይነኩት ለመጠበቅ ነገሮችን ማስቀመጥ ቀጠለ ፤ እዚህ ጋር እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን መንካት እንደማይቻል ያውቃሉ ፤ ነገር ግን መሲሁ በመጣ ጊዜ ሙሉ ለሙሉ ተቃራኒ ነው ! ዮሐ1፡ 14 የሚለው “ ቃልም ስጋ ሆነ ፡፡” በሙሴያዊ ኪዳን ከሁሉን ቻዩ ያሕዌ ርቀው የሚቀመጡበት ርቀት ያስፈልጋቸው ነበር ፤ ማቴ (1፡ 23) የሚያጎላው “ እግዚአብሄር ከእኛ ጋር ነው ፡፡”

6John J. Durham, Exodus, p. 263; quoted in Dr. Constable’s Expository Notes: Exodus, p. 174; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/exodus.pdf.

አንዳንድ ጊዜ ከባድ ጊዜ ሲሆንባቸው አይሁዶች ከመሲሁ ለምን ዞር እንደሚሉ ተረድቻለሁ ፤ ሁል ጊዜ አይምሮአቸው የሚያስበው እግዚአብሄር ቅዱስ እንደሆነና ሊቀርቡት እንደ ማይችሉ ነው ፡፡ በአድሱ ኪዳን ግን በድፍረት እግዚአብሄርን የምንቀርብበትን መንገድ ኢየሱስ ለኛ ሰጥቶናል (ዕብ 10፡ 19-25) ፤ የምንሰራው የለም ይህ ተራራ አለን ወይም ከእኛ ፊት ርቀት አለው ፡፡ አስታውሱ ይህንን ሂደት ለመጨረስ ሰዎስት ቀን መውሰዱን ፡፡እስራኤላዊያን በመንፃት ሂደት ውስጥ እየሄዱ እያለ እግዚአብሄር ወሲባዊ ግንኙነትን በጊዜያዊነት ከለከለ ፤ እግዚአብሄር ወሲብ መጥፎ ነው እያለ አልነበረም ነገር ግን አይናቸውን በእሱላይ እንዲያደርጉ ነበር ፡፡

ዘጸዓት(19፡ 16-25); እስራኤላዊያን ተቀደሱ ፤ ልብሳቸውን አጠቡ፣ ከወሲብ ግንኙነት ተቆጠቡ ከዚያም ተራራውን አልነኩም ነበር ፡፡ ደመናው ተራራውን ሸፈነው ሙሴም በፍርሀት ተንቀጠቀጠ (ዕብ 12፡ 21) ፤ ሙሴ ተናገረ እግዚአብሄርም ለእርሱ አደረሰው ፡፡ እንደገና ሙሴ ተመለሰ ከዚያም ከሕዝቡ በመነሳት ወደ እግዚአብሄር ተራራው ላይ ተመለሰ ፤ እዚህ ጋር እነማን ነበር ካህናቶቹ ? አሮንና ልጆቹ እስካሁን አልጀመሩም ፤ ምናልባት ወጣት ወንዶች በእግዚአብሄር ፊት መስዋዕት ያቀረበረብ ምናልባትም የበኩር ልጆች ይሆናሉ (ዘጸ 24፡ 5) ፡፡ ዘጸዓት 19 የሚያሳየን የኪዳን ጅማሮ መካሄዱን ነው ፡፡ በሙሴ ጊዜ ሁለት አይነት ኪዳኖች ነበሩ ፡ አቻ (በደንበ የተጠበቀ ሁለት እኩል በሆኑ መሀከል የሚደረግ ውል) እና የአንድን አገር የውጪ ግንኙነትን የሚቆጣተር ቅኝ ገዢ መንግስት( ከፍ ባለው አካልና በእሱ በሚገዙት መሀከል ያለ ኪዳን) ፤ የቅኝ ገዢነት ኪዳን የመግቢያ ንግግር ነበረው (ቁጥር 3)፣ ታሪካዊ ርዝማኔ (ቁጥር 4)፣ የጠቅላላ መርህ ንግግር(ቁጥር 5)፣ የመታዘዝ ውጤት (ቁጥር 6-7) እና ያለመታዘዝ ዉጤት ፤ እዚህ ጋር ያለው ኪዳን ለእስረራኤላዊያን ሙሉ ለሙሉ ያውቁት ነበር ፡፡

መዝጊያ

ዘጸዓት 20 አስሩን ትዕዛዝት ሀሳብ ያወጣልናል ፡፡ ጠቅላላ የነበሩት በጣም ብዙ ከአስር ይበልጣል ፤ ዋይሰርቤ ሲፅፍ “ 613 የህግ ትዕዛዞች የተፃፉ ነበራቸው ከዚህም ውስጥ 248 የሚጠቅሙና 365 የሚጎዱ ናቸው፡፡ “ ከጊዜ በኃላ እስራኤላዊያን ይህን እርምጃ መቀጠል እንደማይችሉ ማየት ጀመሩ ፤እነርሱን ከዚህ ኪዳን ለመሳብ በመጨረሻም እነሱን ነፃ ለማዉጣት ነፃ አዉጪው መምጣት ያስፈልገው ነበር ፡፡

  1. Warren W. Wiersbe, Be Delivered (Colorado Springs, CO: David C. Cook Publishing, 1998), p. 120.

  2. Wiersbe, p. 120.

  3. Thomas L. Constable, Dr. Constable’s Expository Notes: Exodus, p.173; available online at https://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/exodus.pdf.

  4. Constable, p. 173.

  5. Constable, pp. 173-174.

  6. Constable, p. 174.

  7. Constable, p. 174.

  8. Constable, p. 175.

  9. Wiersbe, p. 124.

  10. Constable, p. 176.

  11. Warren W. Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament (Colorado Springs, CO: David C. Cook Publishing, 2007), p. 66.

ጥያቄዎች

  1. ሙሴያዊው ኪዳን ምንድነው(በዘጸ 19 ያለው) ? ሙሴያዊው ኪዳን አልቃል ? አወ ከሆነ መቼ ?
  2. እንደ ዘጸ(19፡ 5-6) እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን በማየት እንዴት አደረገላቸው ? ዛሬ ለክርስቲያን በተመሳሳይ ታዩታላችሁ ?(1ጴጥ 2፡ 4-5; 9-10)
  3. በዘጸ(19፡ 7-8) እስራኤላዊያን እግዚአብሄር ላዘዘው ለሙሴ መልዕክት የመለሱለት በታማኝነት(በሀቀኝነት) ነበር ብላችሁ ታስባላችሁ ?
  4. አስሩን ትዕዛዝ ጥቀስ(ዘርዝር) ፤ እነዚህን እግዚአብሄር በቦታ ለማስቀመጥ ለምን እንደመረጠ ምን ታስባላችሁ ?
  5. ኢየሱስ በአገልግሎቱ አስርቱን ትዕዛዞች በዘጸ(20፡ 1-17) የተዘረዘሩትን ለምንድን ጠቀሰ ?(ማቴ5፡ 27; 15፡ 4; 19፡ 18-19)
  6. ለሆነ አካል ክርስቶስን ስታካፍሉ አስሩን ትዕዛዞች እንዴት ልትጠቀሙ ትችላላችሁ ?
  7. በዘጸ(19-20) ውስጥ በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Exodus 19:18-19

“Mount Sinai was completely enveloped in smoke because the Lord came down on it in fire. Its smoke went up like the smoke of a furnace, and the whole mountain shook violently. As the sound of the trumpet grew louder and louder, Moses spoke and God answered him in the thunder.”

ኦሪት ዘፀዓት 19-20 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

ከግብፅ ከወጡ ከሶስት ወር በኋላ፥ በሲና ተራራ የእስራኤል ልጆች ዳስ ሠሩ። እግዚዓብሔርም እንዴት ባለ የሚራራ ልብ፥ "በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንደተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።" በማለት ከግብፅ ምድር ወደ ዚህ ስፋራ እንዳመጣቸዉ አስታወሳቸዉ። ከዚያም በሶስተኛዉ ቀን፥ ራሳቸዉን የቀደሱ ሰዎች በተራራዉ ስራ በቆሙ ጊዜ፥ እግዚዓብሔር አምላክ በኃይል ራሱን ገለጠ። ተራራዉም ጭስ በጭስ ሆነ። እግዚዓብሔር በእሳት ወረደበት! ተራራዉ ሙሉ በመቆጣት ተንቀጠቀጠ! የመለከትም ድምፅ እየጨመረ፥ እየበረታ እና እየፀና ሄደ።

እስኪ አንዴ ቆም በልና ይህንን አስብ፥ የሰማያዊ አባት ርህራሄ የተሞላበት ፍቅር እና የእግዚዓብሔር ሁሉን ቻይነት ግርማዊ ኃይል አስብ! እርሱ ብቻዉን በሁሉ ላይ የከበረ ነዉ! ዛሬ፥ እርሱን በምትፈልግበት ጊዜ፥ በርሁሩህ ፍቅር እና ትልቅ ግርማ ራሱን ሲገልጥልህ ተመልከተዉ!

"እግዚአብሔርም በእሳት ስለ ወረደበት የሲና ተራራ ሁሉ ይጤስ ነበር፤ ከእርሱም እንደ እቶን ጢስ ያለ ጢስ ይወጣ ነበር፥ ተራራውም ሁሉ እጅግ ይናወጥ ነበር። የቀንደ መለከቱም ድምፅ እጅግ በበረታና በጸና ጊዜ ሙሴ ተናገረ እግዚአብሔርም በድምፅ መለሰለት።

ኦሪት ዘፀዓት 19:18-19

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ኦሪት ዘፀዓት 19:4፦ "በግብፃውያን ያደረግሁትን፥ በንስርም ክንፍ እንደተሸከምኋችሁ፥ ወደ እኔም እንዳመጣኋችሁ አይታችኋል።"
  • መጽሐፈ ዜና መዋዕል ቀዳማዊ 29:11፦ "አቤቱ፥ በሰማይና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነውና ታላቅነትና ኃይል፥ ክብርም፥ ድልና ግርማ ለአንተ ነው፤ አቤቱ፥ መንግሥት የአንተ ነው፥ አንተም በሁሉ ላይ ከፍ ከፍ ያልህ ራስ ነህ።"
  • ትንቢተ ኢሳይያስ 40:31፦ "እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 37