The Pentateuch Exodus

Water from the Rock & Amalekite Defeat

ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 16-18 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)

ቀን 36 ከ730
ማውረዶች

ትምህርት

በYouTube ይመልከቱ

ድምፅ ብቻ

የማስተማሪያ ማስታወሻዎች

መግቢያ

ዘጸዓት ከብርነት “የወጡበት” የእስራኤላዊያን ታሪክ ነው ፡፡ እስካሁን በቀይ ባህር የእግዚአብሄርን ያደረገውንና ለዚህ ታአምራት የእስራኤላዊያንን ምስጋና ለእግዚአብሄር እና የእግዚአብሄርን ስጦታ ለህዝቡ አይተናል ፡፡

ትምህርት

ዘጸዓት(17፡ 1); የእስራኤላዊያን ቁጥር 2 ሚሊዮን ሰዎች ሲሆኑ 40 አመት በበርሃ ጉዞአቸው ቆዩ (ዘኁ 33) ፡፡ ኮንስታብል ሲናገር “ ቃል እንደገባው እንዲሰጣቸው እርሱን ከመጠበቅ ይልቅ እንደ ተመቻቸው(ፍላጎታቸው) ማድረግ ፈለጉ “ ፤ እግዚአብሄርን እነርሱን በመፈተን ፋንታ እስራኤላዊያን እግዚአብሄርን ፈተኑት ፡፡(1ቆሮ 10፡9-10)

ዘጸዓት( 17፡ 3); የእስራኤላዊያን ልብ አሁንም በግብፅ ነበር ፤ እግዚአብሄር ማን እንደሆነና ምን እንዳደረገ እረሱት፡፡ ዋይሰርቤ የሚለው ሁሉም ልምድ ሊሆን የሚችለው “ ፈተናው የተሻልን ሊያደርገን ወይም የፈተናው (ስሜትን የሚፈትን) መጥፎ ሊያደርገን ይችላል “ ፤ እያንዳንዱን ሁኔታ ለክብሩ መጠቀም ይችላል (ሮሜ 8፡ 28) !

ዘጸዓት(17፡ 4); ይህ ነበር የሆነው ሂደቱ; ሀይለኛ ሁኔታ፣ የህዝቡ ጥያቄ ከዚያም ሙሴ ያስቸገሩትን ለእግዚአብሄር አሳየ ፤ እንደ መሪ ሙሴ ፅኑ ነበር በጥያቁዎቻቸው መሀል; ስለ እነርሱ ወደ እግዚአብሄር ሄደ(ዘጸ 32፡ 30)፣ ከእግዚአብሄር ጋር ለመገናኘት ወደ ድንካኑ ሄደ (ዘጸ 33፡ 8) በተጨማሪም ነገሮች ጠንካራሲሆኑ ስለ ህዝቡ ይፀልይ ነበር (ዘኁ 11፡2) ፡፡ ሙሴ ነፃ አውጭ ነበር ፤ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን ከግብፅ በማዉጣት ህዝቡን ወደ እግዚአብሄር ፊት ለማምጣት ሙሴን ተጠቀመበት ፡፡ ከባድ ጊዜ በሚገጥመን ጊዜ ሰዎችን ወደ እግዚአብሄር ፊት ማምጣት አለብን (መዝ 46፡ 1) ፡፡

ዘጸዓት(17፡ 5-7); የሙሴ በትር ወደ እባብ ተቀየረች በግብፅም አባይ ወደ ደም ተቀየረ ፡፡ ሙሴ ከሽማግሌዎቹ ጋር በህዝቡ ፊት ቆመ እግዚአብሄርም በኮሬብ አለቱ ላይ ቆመ ፤ ማሳህ ማለት መፈትን ወይም ማረጋገጥ ; መሪባህ ማለት ማሩረምረም ወይም አለመርካት ማለት ነው ፡፡ ብዙ ፅሁፎች የእስራኤልን ማማረርና ቅሬታ መዝግበዋል ፤ (ዘጸ 15; 16; 17; ዘኁ 14; 16; 17) ይሁን እንጂ እግዚአብሄር ሁል ጊዜ ፍላጎታቸውን ሞልታል (መዝ 78፡ 15-16; 105፡ 41)፡፡ ለእስራኤላዊያን ከግብፅ ለመውጣት የፈጀው አንድ ምሽት ነበር ነገር ግን ከእስራኤላዊያን ወጥቶ ግብፅን ለማግኝት 40 አመታት ፈጀ ፡፡

ዘጸዓት(17፡ 8-9); አማሌቅ በመምጣት ከእስራኤል ጋር ተዋጋ ፤ እግዚአብሄር ምድራቸውን እንደሚሰጣቸው ቃል ገብቶላቸዋል ነገር ግን ከእነረሱ እንዲወስዱ ቃል አልገባም ፤ ይህን ለመውሰድ ሊዋጉ ሄዱ ፡፡ አሜሌቃዊያን ሽፍታ አይነት ሰዎች ነበር(ቁጥር 8) ፤ ይህለኢያሱ የመጀመሪያዉ መጠቀስ ነው ፤ 200 ጊዜ ይጠቀሳል ፡፡ ሙሴ ለኢያሱ የነፃ አውጭነትን አስተሳሰብ አደራ(ማስቀመጥ) መስጠት ጀመረ(ቁጥር 9) ፤ ሁል ጊዜ እውነተኛ መሪ ለሌሎች ስልጣን ይሰጣል ፡፡

ዘጸዓት(17፡ 10); ኢያሱ ቅሬታ አላቀረበም ፤ ሙሴ እንዲያደርግ የነገረውን አደረገ ፤ ሙሴ፣ አሮንና ሆርም ወደ ተራራው ወጡ ፡፡

4 Josephus.

ሙሴና አሮን የእንበረምምና ዮካብድ ልጆች ነበር ፤ ሆር የካሌብና ኤፍራታ ልጅ ነበር (1ዜና 2፡ 19) ፤ የቤተ መቀደስ ስራ ቅርፅ ሰሪ የሆነው የባስልኤል አያት ሆናል(ዘጸ 31፡ 2) ፡፡ አሮንና ሙሴ ሌዋዊያን ነበሩ ፤ ሆር ከይሁዳ ዘር ነበር ፤ ሌዋዊያንና አይሁዳዊያን አብረው ነበር የሰሩት ፡፡

ጆሴፍ ያቀረበው ሆር የማሪያም ባል ሊሆን ይችላል ፡፡

ዘጸዓት(17፡ 11-12); የሙሴ እጆች ውጤቱን ወሰኑ ፤ ሙሴ ባወረደ ጊዜ አሮንና ሆር ወደ ላይ እጆቹን ያነሳቸዋል ፡፡ ጆሴፍ አማልቃዊያንን ሲጠራቸው በጣም ጦር ወዳድ ጎረቤት ህዝብ ይላቸዋል ፤ ምናልባት የእስራኤላዊያን የመጀመሪያ ውጊያቸው የነበረው ሀይለኛ ከሆኑት ተጋጣሚዎቻቸው ጋር ነበር ፡፡

ከእርሱ ተለይተን ምንም ልናደርግ አንችልም (ዮሐ 15፡ 5) ፤ አሸናፊነት የሚወሰነው በእኛ ሳይሆን በእግዚአብሄር ነው ፡፡ ሙሴ የፀለየውን መልክ ወድጀዋለሁ ፤ ለእግዚአብሄር መፀለይ አሸናፊዎች ለመሆን ያስፈልገናል ፡፡ ራሱን እንዲተው ለሙሴ ጥንካሬ ይህ ተስፋ አስቆራጭ ሂደት ሆነበት ምክንያቱም ባረጀ ጊዜ እንካን በጥንካሬው ታዋቂ ነበር(ዘዳ 34፡ 7)፡፡ ዘዉመር ፀሎትን “ ለነፍስ ማጠንከሪያ ነው” ብሎ ይጠራዋል ፤ አኛ በብዙ ወደ እግዚአብሄር እጆቻችንን እንድናነሳ ይነግረናል (መዝ 28፡ 2; 44፡20; 63፡4) ፡፡

ዘጸዓት(17፡ 13); ኢያሱ በሙሴ፣ በአሮንና ሆር በአማላጅነት(ፀሎት) ምክንያት አማሌቃዊያንን አሸነፋቸው ፤ የቡድን ዉጤት ነበር ፡፡ ጆሴፍ የፃፈው ዕብራዊያን አልሞቱም ነገር ግን ለመቁጠር የሚያስቸግር አማሌቃዊያን ሞተዋል ፤ እስራኤላዊያን የወቅቱ ተዋጊዎች አልነበሩም ፤ ይህ ተአምራት ነበር ! ጸሎት አስፈላጊ ነበር ! ሙሴ ለእኛ ለሚማልደው እንደ ክርስቶስ መልክ የኢየሱስ አይነት ነው(ዕብ 7፡ 25) ፡፡ መንፈስ ቅዱስ ስለ እኛ ይማልዳል (ሮሜ8፡26-27) ፡፡

ዘጸዓት(17፡ 14); እግዚአብሄር ይህን ቅፅበት ኢያሱ እንዲያስታውሰው ፈለገ ፤ ሙሴ ወደታች የመጣውን ነገር በዘጸዓት ሶስት ጊዜና በዘኁልቁ ሁለት ጊዜ እንዲፅፍ ታዘዘ ፤ እስራኤላዊያን የመርሳት ዝንባሌ ነበራቸው ፡፡ እግዚአብሄር ለሙሴ እንዲፅፈው የነገረው ሙሉ በሙሉ ወደ ፍሬ የመጣ አልነበረም ፤ ትንቢት ነበር ፡፡ እግዚአብሄር ከቆይታ በኃላ ማስታወሳቸውን ያጠፋ ስለነበር ፡፡

ዘጸዓት(17፡ 15-16); ሙሴ መሰዊያ ሰራ ስሙንም “ ያህዌህ ንሲ” ብሎ ጠራው ፤ እግዚአብሄር ከአማሌቅ ጋር ከትውልድ ወደ ትውልድ ሰልፍ ይሆናል ፤ መፅሀፍ ሌላ አምስት ጊዜ እስራኤል ከአማሌቃዊያን ጋር የገጠሙበትን መዝግባቸዋል (ዘኁ 14; መሳ 6; 1ሳሙ 15; 16; እና 2ሳዘሙ 8) ፡፡ ትንቢቱ የተፈፅመ መሰለ (1ቆሮ 4፡ 42-43) ፤ ዘጸ17 ነፃ አውጪ በመሆን የሙሴ መልክ ነው ፡፡

ዘጸዓት(18); ዮቶርና የቀሩት የሙሴ ቤተሰቦች ወደ ሙሴ መጡ ፤ እግዚአብሄር ለህዝቡ ባደረገው ሁሉ ደስታ አገኛቸው ፤ አሮንና ሽማግሌዎቹ ከሙሴ ቤተሰብጋር ምግብ በሉ ፡፡ ዮቶር መሴ ይደክም እንደነበር በዚህ ሙሴ በሌላ በራሱ መሪዎች እንዲከበብ ነገረው ፤ ማንኛውም ትሁት መሪ የሚያደርገው በህግ አባቱ የሆነው የነገረውን ሙሴ አደረገው ፡፡

መዝጊያ

እግዚአብሄር ሰዎችን ነፃ ማውጣት ስራ ላይ ነው ይህን ለማድረግ እናንተንም እኔንም ሊጠቀምብን ይወዳል፡፡

  1. Thomas Constable, Dr. Constable’s Expository (Study) Notes: Exodus, p. 152; available online athttps://planobiblechapel.org/tcon/notes/pdf/exodus.pdf

  2. Warren Wiersbe, Be Delivered (Exodus): Finding Freedom by Following God. (Colorado Springs, CO: David C. Cook) p. 104

  3. Josephus, Antiquities of the Jews. (via BibleStudyTools.com). Book 3, Chapter 2.

  4. Samuel M. Zwemer, quoted in Warren Wiersbe, The Wiersbe Bible Commentary: Old Testament. (Colorado Springs, CO: David C. Cook), p.176.

  5. Josephus, Antiquities of the Jews, Book 3, Chapter 2; available via BibleStudyTools.com

ጥያቄዎች

  1. በዘጸ 16 እግዚአብሄር ምንድን ሰጣቸው(አቀረበላቸው) ? የእነርሱ ምላሽ ምን ነበር ? (ዘጸ 16፡20፣ 27; ዘኁ11፡ 4-6) ለእግአብሄር ስጦታ ልክ እንደ እስራኤላዊያን የመለሳችሁበትን ጊዜ ማሰብ ትችላላችሁ ?
  2. በዘጸ 16 መና እንዴት የኢየሱስ ጥላ ሆነ ? እንደ ዮሐ(6፡ 48-51) ኢየሱስ እንዴት ከሰማይ ከወረደው መና በለጠ ?
  3. በዘጸ (17፡ 6) የኮሬብ አለት የክርስቶስ ጥላ ነበር ?(መዝ 105፡ 41; 1ቆሮ 10፡ 1-4)
  4. በዘጸ(17፡ 10-16) ሙሴ እጆቹን ስለ እስራኤል ወደ ላይ ማንሳቱን የፀሎት መልክ እንደሆኑ ታዩታልችሁ ? እጅን ወደ እግዚአብሄር ማንሳት የሚወክልው ምንድን ነው ?(መዝ 28፡ 2; 63፡ 4; 141፡ 2) እስካሁን ለፀሎት እጃችሁን አስታችሁ ታውቃላችሁ ? ለምን አነሳችሁ ወይም ለምን አላነሳችሁም ?
  5. በዘጸ(16-18) ሙሴን ለእስራኤላዊያን እንደ ነፃ አውጪ እንዴት ታዩታላችሁ ? እንደ ነፃ አውጪ ከክርስቶስ ጋር የሚያመሳስላቸው ማሰብ ትችላላችሁ ?
  6. በዘጸ(16-18) ውስጥ በትምንርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አሳያችሁ(አስረዳችሁ) ?

ቀጣይ፦ የዕለቱ ቃል →

የዕለቱ ቃል

Laura Martin Exodus 18:18-19a

“You will certainly wear out both yourself and these people who are with you, because the task is too heavy for you. You can’t do it alone. Now listen to me; I will give you some advice, and God be with you.”

ድል መንሣት የእግዚዓብሔር ነው!

ኦሪት ዘፀዓት 16-18 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን

የሙሴ እጆች ዝለዉ ነበር፥ የደከመዉም በቀጥታ እጆቹን ደግሞም በምልክትም ነዉ። ብቻዉን ሆኖ ህዝቡን መምራት አልቻለም! መናገር እንዲችል አሮን እጁን ሰጥቶታል። ሖር እና አሮንም ከአማሌቅ ጋራ በነበርዉ ፍልምያ እጆቹን ደግፈዉ ይዘዉለታል። ከዚያም እግዚዓብሔር፥ ሙሴን በምርጫ እና አመራር እንዲመክረዉ አማቹን ዮቶርን ወደ እሱ ላከዉ። ዮቶር የመጣዉ ከሌላ ስፍራ ሲሆን ሁኔታዉንም የገመገመዉ ከራሱ ምልከታ አንፃር ነዉ።

ሙሴ እርዳታን የተቀበልዉ በትህትና ነዉ። በጣም ከባድ ከሆነ ኃላፊነት ጋራ ፊት ለፊት ተጋጥመሃል? ከአቅምህ በላይ ሆኖብሃል? ብቻህን አይደለህም! እግዚዓብሔርን ፈልገዉ! ኃላፊነቱን የማትወጣዉ በሚመስልህ ጊዜ፥ የሚያስፈልግህን እርዳታ እና ምልከታ ይልክልሃል። ተቀበለዉ፥ እግዚዓብሔርም ከአንተ ጋራ ይሆናል።

"ይህ ነገር ይከብድብሃልና አንተ ከአንተም ጋር ያለው ሕዝብ ትደክማላችሁ፤ አንተ ብቻህን ልታደርገው አትችልም። አሁንም እመክርሃለሁና ቃሌን ስማ፥ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋር ይሆናል፤ አንተ በእግዚአብሔር ፊት ለሕዝቡ ሁን፥ ነገራቸውንም ወደ እግዚአብሔር አድርስ፤

ኦሪት ዘፀዓት 18:18-19

ተጨማሪ ጥቅሶች

  • ኦሪት ዘፀዓት 18:24፦ "ሙሴም የአማቱን ቃል ሰማ፥ ያለውንም ሁሉ አደረገ።"
  • መዝሙረ ዳዊት 34:17፦ "ጻድቃን ጮኹ፥ እግዚአብሔርም ሰማቸው ከመከራቸውም ሁሉ አዳናቸው።"
  • የማቴዎስ ወንጌል 11:28፦ "እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ።"

የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 36