Crossing the Red Sea
ኢየሱስን እንዲህ ብለው ያግኙት፦ Deliverer Exodus 14-15 በBible Gateway ያንብቡ (NASV)
ትምህርት
ድምፅ ብቻ
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች
መግቢያ
በፋሲካ እንከን ወደ ሌለበት የመጨረሻ ፋሲካ ክርስቶስ የሚያመለክት አስደናቂ የሆነ እንከን የሌለበትን በግ መልክ አይተናል ፡፡ በብዙ ነፃ ወጥተናል ምክንያቱም “ ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዳልና ”(1ቆሮ 5፡ 7) ፡፡ ጥናታችንን ስንቀጥል እስራኤላዊያን ነፃ ሆነዋል ስለዚህ አሁን እግዚአብሄር ከግብፅ አውጥቶ ይመራቸው ነበር ፤ በመንገድ አልበራቸውም ነገር ግን በበርሀ ውስጥ ወደ ቀይ ባህር መራቸው (ዘጸ 13፡ 17-18) ፡፡
ትምህርት
ዘጸዓት(14፡ 1-4); አስባችሁታል 2 ሚሊዮን ህዝብ በበርሃ መምራት የስንቅ ችግሩን ?መዝ(105፡ 7) የሚለው እግዚአብሄር “ ለሙሴ መንገዱን አስታወቀ” ፡፡ በመንገድ ፋንታ እስራኤልን በበርሃ ከመራቸው በኃላ እግዚአብሄር በብሀሩ ፊት እንዲሰፍሩ ነገራቸው ፤ ዋይሰርቤ ያመለከተን “ የአይሁድ ህዝብ ለእግዚአብሄር ምን እንዲያደርጉለት እንደሚፈልግ ተናገሩ ነገር ግን እግዚአብሄር ለምን ይህን ያደርግ እንደነበር ለሙሴ ገልጦለታል ፡፡ “እስራኤላዊያን በቅርቡ በቀይ ባህርና በግብፃዊያን ጦር መሀከል ወጥመድ ውስጥ ይገባሉ ፤ እግዚአብሄር ወጥመዱን አዘጋጀ ስለዚህ በበርሃ ክብር ያገኛልም ግብፃዊያንም ያህዌ እንደነበር ያውቃሉ (ቁጥር 2) ፡፡ ምን ያክል ጊዜ ሰምታችኃል “ ይህ የቀይ ባህር ክስተት ነው !” ? በእነዚህ ጊዜያት እራሳችንን በሁኔታ ውስጥ ስንፈልግ እንዲገለጥና በሁኔታችን ውስጥ ክብሩን እንዲገልጥ እግዚአብሄር ያስፈልገናል ፡፡
ዘጸዓት(14፡ 5-10); አንዴ እስራኤላዊያን ከግብፅ ከወጡ ፈርዖንና አገልጋዮቹ ወዲያውኑ ነፃ የሰራተኛ ኃይላቸውን እንደለቀቁ አወቁ ! ስለዚህ ፈርዖን አምላካቸውን ሊያመልኩና ሊያመሰግኑ ግብፅን ትተው የወጡትን እስራኤላዊያንን ወታደሮቹንና ሰረገላዎቹን ሰብስቦ ተከተላቸው ፡፡ ጆሴፍስ ምናልባት 50000 ሰረገላ፣ 200000 እግረኛ ጦር እንደነበሩ ተናግራል ፤ የቅርስ አጥኒዎች ይህን ቦታ ቢያጠኑም ትክክለኛ ቦታዉን አላገኙም ፡፡ እስራኤላዊያን ፈርዖን አያሳደዳቸው እንደሆነ ባወቁ ጊዜ ፈሩም እግዚአብሄር እንዲረዳቸው ወደሱ ጮሁ ፡፡
ዘጸዓት(14፡ 11-12); እንዴት እስራኤላዊያን በፍጥነት መቅሰፍቶቹንና እግዚአብሄር እነርሱን ከግብፅ ለማውጣት ያደረገውን ሁሉ ረሱ ! እግዚአብሄርን መታመን በመቀጠል ፋንታ ወደ ሙሴ በመመለስ ከግብፅ አውጥተህ የመራሀን በበርሃ እንድንሞት ነውን ብለው ጠየቁት ፡፡ በባህር ከመሞት ግብፅን ማገልገል እንደሚሻል ጠየቁት ፤ መፅሀፍ የእስራኤላዊያንን ያላቃረጠ በሙሴ ላይ ያላቸውን ቅሬታ መዝግባል ፡፡ በዘጸ 5 ከመጀመሪያው ከሙሴና ከአሮን እንዲለቃቸው ከጠየቁ በኃላ ፈርዖን በቀጣቸው ጊዜ ቅሬታ አቅርበዋል ፤ በዘጸ 16 ምግብ ሲያጡ ቅሬታ አቅርበዋል እና ዘጸ 17 ለራሳቸውና ለመንጎቻቸው ውሃ በማጣታቸው ቅሬታ አቅርበዋል ፡፡ ጆሴፍስ የፃፈው መጥፎ ነበያገኘው ያም እስራኤላዊያን ሙሴን በድንጋይ ሊወግሩት ፈለጉ ፡፡ ሙሴ ወይም ኢየሱስ ማንም ሆንክ ችግር የለውም አንተ ነፃ አዉጪ ከሆንክ ከአንተ በኃላ ይመጣሉ ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የቸርች ቃል ልክ በበጉ ደም ከሞት ወደ ህይወት እንደተሸገርንና ነፃ እንደወጣን እንደረሳነው ነው ፡፡ እሰኪ ቅር መሰኘታችንንና ማማረራችንን አቁመን በእንነት እንጋአዝ ! በእምነት በሰራን ጊዜ እናሸንፋለን ፤ ግን በፍርሀት፣ በማማረርና በመነጫነጭ ቦታ ባደረግን ጊዜ እንሸነፋለን ፡፡
ዘጸዓት(14፡ 13-14); ከእስካሁን በጠንካራ የጀርባ አጥንት ሙሴ ወደ ህዝቡ ተመለከተና ነገራቸው “ አትፍሩ ፤ ቁሙ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋት የእግዚአብሄርን ማዳን እዩ……እግዚአብሄር ስለእናንተ ያዋጋልና እናንተም ዝም ትላላችሁ፡፡ “ እንደ ዋይሰርቤ ንግግር ፍርሀት ወይ ጠንካራ ወይ ደግሞ ሽባ(ደካማ) ማድረግ ይችላል ፡፡ በዚህ አገላለፅ “ደህንነት”(የሹዋ) የሚለው ቃል “ቦታ” ወይም “ክፍል” ማለት ነው ፡፡ ኔልሰን ሀተታ የሚለው “ ሰዎቹ ከፊታቸው ባለው ዉሃና ከኃላቸው ባሉት የፈርዖን ጦር መሀከል ተጣብቀው ታላቅ ጭንቀት ውስጥ ነበሩ ፤ በሚያስገርም መንገድ ድነት ጭንቀታቸውን ያስታግስላቸዋል ፡፡” ሁሉም እስራኤል አድርገውት የነበረው በመቆምና እግዚአብሄር ስለ እነረሱ የሚሰራውን መመልከት ነበር ፤ መፅሀፍ ሌላ ጊዜ በእስራኤል እግዚአብሄር በታአምራት የሰራቸውን መዝግባል (1ሳሙ 17፡ 47; 2ቆሮ 20፡ 15-17; ትቢ ዘካ 14፡ 3) ፡፡ ልክ እንደ እስራኤላዊያን አናዳንድ ጊዜ የእግዚአብሄርን ስራ ለማየት በእምነታችን ፀንተን መቆም አለብን ፡፡ ይመስለኛል በአሜሪካ ያለ ቸርች የራሳችንን ድነት ለመፍጠር ሞክረናል፡፡ የራሳችንን ትግል ለመታገል ሞክረናል ከዚያም በመጨረሻ እግዚአብሄር ያዋህደናል (ያግዘናል) ፡፡ እንዴት ነው ለእግዚአብሄር የምንቆመውና የምንጠብቀው ለመጋጠም (ግጥሚያ ለማድረግ) ?
ዘጸዓት(14፡ 15-18); እግዚአብሄር ለሙሴ ወደ እርሱ መጮሁን እንዲያቆምና ከሰፈሩበትእንዲነሱና መጋአዝ እንዲቀጥሉ ተናገረው ! በፍርሀት ሽባ ሆኖ ከመቀመጥ ይልቅ ወደ ፊት እግዚአብሄር እንደሚገለጥና ተአማራት እንደሚያደርግ ተስፍ በማድረግ መጋአዝ ያስፈልጋቸዋል ፡፡ ከዚያም እግዚአብሄር ሙሴን ምን እንደሚያደርግና ምን እንደሚሆን ነገረው “ አንተም በትርህን አንሳ እጅህንም በባህሩ ላይ ዘርጋ ክፈለውም የእስራኤልም ልጆች በባህሩ ውስጥ በየብስ ያልፋሉ “(ቁጥር 16) ፡፡ እግዚአብሄር እስራኤላዊያንን በባህር ውስጥ ለመውሰድ አቀደ ! ከዚያም በፈርዖን ጦር መጥፋት እግዚአብሄር ይከብራል በዚህም ግብፃዊያን ያህዌ እንደነበር ያውቃሉ ፡፡ ማርና ወተት የምታፈሰውን ምድር ለማግኘት በባህር ውስጥ ማለፍ አለብን ይህ ማለት በእምነት ተጉዘን እናገኘዋለን ማለት ነው፡፡
ዘጸዓት(14፡ 19-20); አስታዉስ አጥፊው በፋሲካ ኢየሱስ ሊሆን እንደሚችል ፤ አሁን ዒየሱስን እንደገና በዚህ ሚና እናየዋለን ፡፡ የእግዚአብሄር መልዓክ በደመና አምድ እስራኤልን የመራው በመሄድ በእስራኤልና በፈርዖን ጦር መሀከል ቆመ ፤ይህን ከኢሳ(63፡ 8-9) “ እርሱም በእዉነት ህዝቤ ሀሰትን የማያደርጉ ልጆች ናቸው አለ መድሀኒትም ሆነላቸው ፡፡ በጭንቃቸውም ሁሉ እርሱ ተጨነቀ የፊቱም መልዓክ አዳናቸው በፍቅሩና በርህራሄውም ተቤዣቸው በቀደመውም ዘመን ሁሉ አንስቶ ተሸከማቸው ፡፡” ዘጸ 13፡21; 14፡19; 23፡ 20-23; 32፡34 እና 33፡2 ሁሉም የሚገልፁት ነፃ ሊያወጣቸው፣ ሊጠብቃቸው፣ ሊመራቸውና ጠላቶቻቸውን ሊያሳድድ ከእስራኤል ፊት ስለወጣው የእግዚአብሄር መልዓክ ነው ፤ ዘዳ(8፡ 2) የሚለው እግዚአብሄር ሁሉንም 40 አመታት እስራኤል በበርሃ እንዲከራተቱ አደረገ ፡፡ የእግዚአብሄር መገኝት የእግዚአብሄር መልዓክ በደመናና በእሳት አምድ ነበር ፤ የእግዚአብሄር መልዓክ ኢየሱስ ነው ፡፡
ዘጸዓት(14፡ 21-25); ሙሴ በባህሩ ላይ እጁን አነሳ እግዚአብሄርም ውሀውን ከፈለው ስለዚህ እስራኤላዊያን በደረቅ ምድር ተሸገሩ “ ውሃውም በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ሆነላቸው”(ቁጥር 22) ፡፡ ባህር የግድግዳን ቅርፅ ሲቆምና በደረቅ ምድር ሲሻገሩ ማየትን ማሳብ ትችልላችሁ ? ግብፃዊያን በተከተላቸው ጊዜ በጦራቸው ታላቅ ግራ መጋባት እግዚአብሄር ፈጠረባቸው ከዚያም ከእስራኤል ለመራቅ ሞከሩ “ ምክንያቱም እግዚአብሄር ለእነረሱ ይዋጋላቸዋልና”(ቁጥር 25) ፡፡ ግብፃዊያን እግዚአብሄር በስራ ላይ እንደነበር ተገነዘቡ ፤ እግዚአብሄርን እንደ ሆነ ባወቅን ጊዜ የሚሆነው ይህ ነው ፤ ለሰዎች መናገር አይጠበቅባችሁም ይህን ስለሚያውቁት ፡፡
ዘጸዓት(14፡ 26-28); እግዚአብሄር ሙሴን አለው “ እጅህን በባህሩ ላይ ዘርጋ ውሃውም በግብፃዊያን በሰረገሎቻቸውም በፈረሰኞቻቸውም ላይ ይመለስ አለው “፤ ስለዚህ ሙሴ እጁን ዘረጋ ከዚያም በእግዚአብሄር ምክንያት ውሃው ሙሉ ለሙሉ ሸፈናቸውም ፈርዖንንና የእርሱን ጦር አጠፋቸው ፡፡ ሀሚልተን ይህን ድርጊት በማር(5፡ 1-20) ካለው ኢየሱስ ሲያስተላልፋቸው “ እርኩሳን መናፍስቱም ወጥተው ወደ እሪያዎቹ ገቡ 2000 የሚያህል መንጋ ከአፋፉ ወደ ባህሩ ተጣደፉና በባህር ሰጠሙ” ታሪክ ጋር ያነፃፅረዋል ፤ በሁለቱም ላይ እግዚአብሄር ኃይሉን ገልጣል ፡፡
ዘጸዓት(14፡ 29-31); እስራኤል በባህሩ ውስጥ በደረቅ ምድር ሄደ በዚህም በግብፃዊያን ላይ ያሳየውን የእግዚአብሄርን ታላቅ ኃይል አዩ ፡፡ ህዝቡም እግዚአብሄርን ፈሩ በእርሱና በአገልጋዩ በሙሴም አመኑ ፤ ይህ የቀይ ባህር ቅፅበታዊ ድርጊት የእስራኤላዊያንን ባህል በፍጥነት ቀየረው ፡፡ ለምን ? ምክንያቱም በእምነት በእግዚአብሄር ስለተደገፉ እግዚአብሄርም እነርሱን ከባርነት ነፃ ለማውጣት ሙሴን ተጠቀመ ፤ እግዚአብሄር እንደገና ከግብፅ የሚያወጣ ነፃ አውጪ ሆኖ አወጣ ፡፡ ማቴ(2፡ 13) የሚለው የእግዚአብሄር መልዓክ ዮሴፍን ማሪያምንና ኢየሱስን ይዘህ ከሄርዶስ በእስራኤል ወንድ ህፃናትን ከመግደል ለማምለጥ ወደ ግብፅ ይዘህ ውረድ ብሎ ተናገረው ፡፡ ማቴ(2፡15) የሚለው “ ..ከጌታ ዘንድ በነቢይ ልጄን ከግብፅ ጠራሁት የተባለው እንዲፈፅም ወደ ግብፅ ሄደ ሄርዶስም እስኪሞት ድረስ በዚያ ኖረ ፡፡“
እግዚአብሄር ሙሴንና እምነቱን እስራኤላዊያንን ነፃ ለማዉጣት ከዚያም ወደ ክርስቶስ ዘር እንዲመራው እንደተጠቀመበት አምናለሁ ፤ እዚህ ጋር የነበረው አስተሳሰብ እኔ እንደማስበው “ ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት” ፡፡ ሆሴ(11፡1) የሚለው “ እስራኤል ህጻን በነበረ ጊዜ ወደደሁት ልጄንም ከግብፅ ጠራሁት” ይህ ለኢየሱስ በእስራኤል በሚዜያዊነት የሚቀመጥ ጥላ ሆነ የሄሮዶስን ግድያ ለማምለጥና ሄርዶስ ከሞተ በኃላ ወደ እስራኤል እንደሚመለስ፡፡
መዝጊያ
የእግዚአብሄርን የጠብቅ ግንኙነት በመፅሀፍ ውስጥ ማየት እወዳለሁ ፤ የሙሴ እምነት ወደ መጨረሻ ነፃ አውጪው ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከግብፅ ነፃ ለማድረግ ወደጠራን መራን ፡፡ ሁላችንም የሆነ ሰዓት ላይ “የቀይ ባህር ቅፅበት” እንደሚገጥመን ቃል እገባላችኃለሁ ፡፡ ስታደርጉ ዝም ብላችሁ ቁሙ ከዚያም እግዚአብሄር ለእናንተ ሲዋጋ ተመልከቱ፡፡ ዘጸ 15 የተመዘገበው የእስራኤላዊያን የምስጋና መዝሙር ለእግዚአብሄር እንዴት በዘጸዓት 14 ስላዳናቸው ፡፡
Warren W. Wiersbe, The Bible Exposition Commentary: Genesis–Deuteronomy (Colorado Springs, CO: David C. Cook, 2001), p. 204.
Wiersbe, p. 204.
Earl Radmacher, Ronald B. Allen, and H. Wayne House, eds., Nelson’s New Illustrated Bible Commentary (Nashville: Thomas Nelson, 1999), p. 112.
Victor P. Hamilton, Exodus: An Exegetical Commentary (Grand Rapids: Baker Publishing Group, 2011), p. 220.
ጥያቄዎች
-
ዘጸ(14፡ 13) አንብቡ ፤ ግብፃዊያን የባርነት ኃጢአት ምልክት መሆናቸውንና ከዚህ ባርነት የእኛን የመጨረሻ ነፃ መውጣት እንዴት ታዩታላችሁ ?(ሮሜ 6፡ 6-7)
-
በዘጸ(14፡ 15; 25) እግዚአብሄር ለእስራኤላዊያን ሲዋጋና ግብፃዊያን ለመሸሽ ሲሞክሩ አይተናል ፤ መቼ ነበር እግዚአብሄረ እንዲዋጋላችሁ የተራችሁት በሁኔታ ውስጥ ተስፋ መቁረጥ የታያችሁና እርሱ ነፃ ያወጣችሁ ?
-
በዘጸ (14፡ 11) የእስራኤል ልጆች ለሙሴ ቅሬታ(ጥያቄ) አቀረቡ ምክንያቱም በዘጸ(14፡10) ጠላቶቻቸው ሲቀርባቸው አዩ በዚህም በፍርሀት ሆኑ ሁሉም በዚህ ሆነው እግዚአብሄር የፈፀመውን አዩ ፤ በጠላቶቻችሁ መጠቃት ስር በሆናችሁ(በወደቃችሁ) ጊዜ አይናችሁን ከእግዚአብሄር ላይ ወስዳችሁ በፍርሀት ሆናችሁ ታውቃላችሁ ?
-
በዘጸ(15፡ 13) የሙሴ መዝሙር ያወጀው በቸርነት የዋጀሀቸውን ህዝብ መራሀቸው ፤ በቸርነትህ የሚለው ቃል ምን ማለቱ ነው ? ማነው በመጨረሻ እኛን የዋጀን እንዴትስ መራን ?(መዝ 23፡ 1-3; ዮሐ 10፡ 3-4; 14፡6)
-
በዘጸ(14-15) በትምህርት ወይም በጥናት መንፈስ ቅዱስ ምንድን አጉልቶ አስረዳችሁ(አሳያችሁ) ?
የዕለቱ ቃል
Laura Martin Exodus 14:13-14
“But Moses said to the people, ‘Don’t be afraid. Stand firm and see the LORD’s salvation He will provide for you today; for the Egyptians you see today, you will never see again. The LORD will fight for you; you must be quiet.’”
ዉስጥ የእግዚዓብሔር መልዓክ
ኦሪት ዘፀዓት 14-15 የዕለቱ ቃል፥ ከላዉራ ማርቲን
እስራኤላዉያም ግብፅን ለቀዉ ከወጡ ከጥቂት ጊዜ በኋላ የፈርዖን ልብ እንደገና ደነደነ። ከቀይ ባህር ጋር ፊት ለፊት ተጋጥመዉ እስከ ሞት አፋፍ ላይ ተከተላቸዉ። እስራኤላዉያንም በጣም ፈርተዉ ስለነበረ፥ ወደ እግዚዓብሔር ጮሁ። በእነሱ አስተሳሰብ ከዚህ ምንም የሚያመልጡበት መንገድ የለም። ይህም ታላቁ እኔ ለሆነዉ እግዚዓብሐር፥ እርሱ አምላክ መሆኑን የሚያሳይበት ሌላ እድል ፈጠረ። በኃይሉም ቀይ ባህርን ከፈለዉ! እስራኤላዉያንን አድኖ፥ ግብፃዉያንን አጠፋቸዉ።
በህይወትህ ዉስጥ እንደ ቀይ ባህር ዓይነት ጊዜ እያሳለፍክ ነው? ምንም የምታመልጥበት ቦታ የሌለ ይመስልሃል? አስታዉስ፥ እግዚዓብሔር ከአንተ ጋራ ነዉ! እግዚዓብሔር ይዋጋልሃል። እርሱ ዓላማ አለዉ! ልክ ለእስራኤላዉያን እግዚዓብሔር እንደተናገራቸዉ "እረፉ" እንዳላቸዉ ባልጠበከዉ መንገዱ በምታልፍበት ሁናቴ፥ ድል ማድረገን እንደሚያመጣ እርሱን እመነዉ!
"ሙሴም ለሕዝቡ፦ አትፍሩ፥ ዛሬ የምታዩአቸውን ግብፃውያንን ለዘላለም አታዩአቸውምና ቁሙ፥ ዛሬ ለእናንተ የሚያደርጋትን የእግዚአብሔርን ማዳን እዩ። እግዚአብሔር ስለ እናንተ ይዋጋል፥ እናንተም ዝም ትላላችሁ አላቸው።"
ኦሪት ዘፀዓት 14:13-14
ተጨማሪ ጥቅሶች
- ኦሪት ዘፀዓት 14:31፦ "እስራኤልም እግዚአብሔር በግብፃውያን ላይ ያደረጋትን ታላቂቱን እጅ አዩ፥ ሕዝቡም እግዚአብሔርን ፈሩ፥ በእግዚአብሔርም በባሪያውም በሙሴ አመኑ።"
- ኦሪት ዘዳግም 20:4፦ "ከእናንተ ጋር የሚሄድ፥ ያድናችሁም ዘንድ ጠላቶቻችሁን ስለ እናንተ የሚወጋ አምላካችሁ እግዚአብሔር ነውና።"
- ወደ ሮሜ ሰዎች 8:31፦ "እንግዲህ ስለዚህ ነገር ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?"
የመሲሁ ሙሉ ስዕል በመጀመሪያዎቹ አምስት የህግ መፅሀፍት፡ ክፍል 35
ትምህርት እና የዕለቱ ቃል
እያንዳንዱ ቀን ሁለት ክፍሎች አሉት፦ ትምህርቱ እና የዕለቱ ቃል። ከአንዱ ወደ ሌላው ለመሄድ እነዚህን አዝራሮች ይጠቀሙ።
የማስተማሪያ ማስታወሻዎች እና ጥያቄዎች
ከቪዲዮው አጠገብ እነዚህ ትሮች የማስተማሪያ ማስታወሻዎችን እና ጥያቄዎችን ያሳያሉ። ለጥያቄ የሰጡት መልስ ከመልስ ሳጥኑ ሲወጡ ይቀመጣል።
የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል
ይህ አገናኝ ክፍሉን በBible Gateway ይከፍታል፣ ክፍሉም ምልክት ያገኛል። በራስዎ መጽሐፍ ቅዱስ ካነበቡት፣ በ«እድገት» ውስጥ በእጅዎ ምልክት ያድርጉበት።
በዚህ ትምህርት ላይ ያለዎት እድገት
ቪዲዮውን ወይም ድምፁን እስከ መጨረሻ ሲያጫውቱ፣ ማስታወሻዎቹን ወይም የዕለቱን ቃል እስከ መጨረሻ ሲያነቡ፣ ወይም እያንዳንዱን ጥያቄ ሲመልሱ አንድ ክፍል በራሱ ምልክት ያገኛል። እዚህም አንድን ክፍል በእጅዎ ምልክት ማድረግ ይችላሉ።
ማውረዶች
እዚህ ቪዲዮውን፣ ድምፁን እና ትምህርቱን እንደ PDF ፋይሎች ማስቀመጥ ይችላሉ። ማውረዶች በእድገትዎ ውስጥ አይቆጠሩም።
እርዳታ ይፈልጋሉ?
ጥያቄ ለመላክ ወይም ስለ ችግር ለመንገር ይህን አዝራር ይጠቀሙ። ከዚያም ይህን ጉብኝት እንደገና ማድረግ ይችላሉ።